አላህም ከሁለቱ ጭፍሮች አንደኛዋን እርሷ ለናንተ ናት ሲል ተስፋ በሰጣችሁ ጊዜ፣ የሀይል ባለቤት ያልኾነችውም (ነጋዴይቱ) ለናንተ ልትኾን በወደዳችሁ ጊዜ፣ አላህም በተስፋ ቃላቱ እውነትን ማረጋገጡን ሊገልጽና የከሓዲዎችንም መጨረሻ ሊቆርጥ በሻ ጊዜ (የኾነውን አስታውስ)፡፡
Al-Anfal 8:7
Compare 2 Amharic translations
وَإِذْ يَعِدُكُمُ اللَّهُ إِحْدَى الطَّائِفَتَيْنِ أَنَّهَا لَكُمْ وَتَوَدُّونَ أَنَّ غَيْرَ ذَاتِ الشَّوْكَةِ تَكُونُ لَكُمْ وَيُرِيدُ اللَّهُ أَنْ يُحِقَّ الْحَقَّ بِكَلِمَاتِهِ وَيَقْطَعَ دَابِرَ الْكَافِرِينَ
DragHold to move · × to hide
(እናንተ ተከራካሪዎች ሆይ!)፤ አላህ ከሁለቱ ቡድኖች አንደኛዋን ለእናንተ ናት ሲል ተስፋ በሰጣችሁና የኃይል ባለቤት ያልሆነችውን የነጋዴይቱን ቡድን ለእናንተ ልትሆን በወደዳችሁ ጊዜ አላህም በተስፋ ቃላቱ እውነቱን ማረጋገጡን ሊገልጽና የካሓዲያንንም መጨረሻ ሊቆርጥ በፈለገ ጊዜ (የሆነውን አስታውሱ)።