The Quran

القرآن الكريمAfrica Academy

The Opening · al-Fatihah · سورة الفاتحة · 7 ayahs

بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።

الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ

ምስጋና ሁሉ ለዓለማቱ ጌታ፣ ለአሏህ ይገባው።

الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ ለሆነው።

مَالِكِ يَوْمِ الدِّينِ

የፍርዱ ቀን ባለቤት ለሆነው (ለአላህ ብቻ ይገባው)።

إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ

(ሙስሊሞች ሆይ! ጌታችሁን) አንተን ብቻ እንገዛለን። ካንተም ብቻ እርዳታን እንለምናለን (በሉት)።

اهْدِنَا الصِّرَاطَ الْمُسْتَقِيمَ

ቀጥተኛውን መንገድ ምራን።

صِرَاطَ الَّذِينَ أَنْعَمْتَ عَلَيْهِمْ غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلَا الضَّالِّينَ

የእነዚያን ለእነርሱ በጎ የዋልክላቸውን፤ በእነርሱ ላይ ያልተቆጣባቸውንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ (ምራን በሉ)።