The Shocker · al-Qari'ah · سورة القارعة · 11 ayahs

القرآن الكريمAfrica Academy

بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።

الْقَارِعَةُ

ቆርቋሪይቱ (ጩኸት)፤

مَا الْقَارِعَةُ

ቆርቋሪይቱ (ጩኸት) ምንድን ናት!

وَمَا أَدْرَاكَ مَا الْقَارِعَةُ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቆርቋሪይቱ ምን እንደሆነች ምን አሳወቀህ?

يَوْمَ يَكُونُ النَّاسُ كَالْفَرَاشِ الْمَبْثُوثِ

ሰዎች እንደተበታተነ ቢራቢሮ (ኩብኩባ) የሚሆኑበት ቀን፤

وَتَكُونُ الْجِبَالُ كَالْعِهْنِ الْمَنْفُوشِ

ጋራዎችም እንደ ተነደፈ ሱፍ የሚሆኑበት (አስደንጋጭ ቀን) ናት።

فَأَمَّا مَنْ ثَقُلَتْ مَوَازِينُهُ

(በዚያ ዕለት) ያ ሚዛኖቹ የከበዱለት ሰውማ

فَهُوَ فِي عِيشَةٍ رَاضِيَةٍ

እርሱ በአስደሳች ኑሮ (በገነት) ውስጥ ይሆናል።

وَأَمَّا مَنْ خَفَّتْ مَوَازِينُهُ

ያ ሚዛኖቹ የቀለሉበት ሰው ደግሞ

فَأُمُّهُ هَاوِيَةٌ

መኖሪያው ሃዊያህ (የምትባል የገሀነም እሳት) ናት።

وَمَا أَدْرَاكَ مَا هِيَهْ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እርሷ ምን እንደሆነች ምን አሳወቀህ?

نَارٌ حَامِيَةٌ

(እርሷ) በጣም ተኳሳ እሳት ናት።