The Racers · al-'Adiyat · سورة العاديات · 11 ayahs

القرآن الكريمAfrica Academy

بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።

وَالْعَادِيَاتِ ضَبْحًا

እያለከለኩ ሩዋጮች በሆኑ (ፈረሶች)፤

فَالْمُورِيَاتِ قَدْحًا

ምድርን በሸሆናቸው እያጋጩ የእሳት ብልጭታን አውጪዎች በሆኑትም (ፈረሶች)፤

فَالْمُغِيرَاتِ صُبْحًا

በማለዳ (በጧት) ወራሪዎች በሆኑትም ፈረሶች፤

فَأَثَرْنَ بِهِ نَقْعًا

በእርሱም አቧራን በቀሰቀሱት፤

فَوَسَطْنَ بِهِ جَمْعًا

በፈረሰኞቻቸው በኩል (የጠላት) ስብስብ መሀልን በተጋፈጡትም (ፈረሶች) እምላለሁ።

إِنَّ الْإِنْسَانَ لِرَبِّهِ لَكَنُودٌ

የሰው ልጅ ለጌታው (ጸጋ) በጣም ውለታ ቢስ ነው።

وَإِنَّهُ عَلَىٰ ذَٰلِكَ لَشَهِيدٌ

እርሱም በዚያ (ክህደቱ) ላይ መስካሪ ነው።

وَإِنَّهُ لِحُبِّ الْخَيْرِ لَشَدِيدٌ

እርሱም ገንዘብን በመውደድ ላይ በጣም ብርቱ ነው።

أَفَلَا يَعْلَمُ إِذَا بُعْثِرَ مَا فِي الْقُبُورِ

የሰው ልጅ በመቃብሮች ዉስጥ ያሉት ሙታን ሁሉ በተቀሰቀሱ ጊዜ ምን እንደሚከሰት አያውቅምን?

وَحُصِّلَ مَا فِي الصُّدُورِ

በልቦች ውስጥ ያለዉም ሁሉ በተገለጸ ጊዜ እንዴት እንደሚሆን አያውቅምን?

إِنَّ رَبَّهُمْ بِهِمْ يَوْمَئِذٍ لَخَبِيرٌ

ጌታቸው በዚያ ቀን በእነርሱ ነገር በእርግጥ ውስጠ አዋቂ ነው።