Victory · an-Nasr · سورة النصر · 3 ayahs

القرآن الكريمAfrica Academy

بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።

إِذَا جَاءَ نَصْرُ اللَّهِ وَالْفَتْحُ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የአላህ እርዳታና (የመካ) መከፈት በመጣ ጊዜ፤

وَرَأَيْتَ النَّاسَ يَدْخُلُونَ فِي دِينِ اللَّهِ أَفْوَاجًا

ሰዎችም ቡድን ቡድን እየሆኑ ወደ አላህ ሃይማኖት ሲገቡ ባየህ ጊዜ፤

فَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ وَاسْتَغْفِرْهُ ۚ إِنَّهُ كَانَ تَوَّابًا

ጌታህን ከማመስገን ጋር አጥራው። ምህረትንም ለምነው፤ እርሱ ጸጸትን በጣም ተቀባይ ነውና።