Family of Imran · Aal 'Imran · سورة آل عمران · 200 ayahs

القرآن الكريمAfrica Academy

بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።

الم

አሊፍ፤ ላም፤ ሚም፤

اللَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ

አላህ ከእርሱ ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም። አላህ ህያው፤ በራሱ የተብቃቃና የሁሉ ነገር አስተናባሪ (የፍጡራን ተንከባካቢ) ነው።

نَزَّلَ عَلَيْكَ الْكِتَابَ بِالْحَقِّ مُصَدِّقًا لِمَا بَيْنَ يَدَيْهِ وَأَنْزَلَ التَّوْرَاةَ وَالْإِنْجِيلَ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ መጽሃፍን (ቁርኣንን) ከእርሱ በፊት ያሉትን መጽሐፍት የሚያረጋግጥ ሲሆን ባንተ ላይ (ከፋፍሎ) በእውነት አወረደው። ተውራትንና ኢንጅልን አወረደ።

مِنْ قَبْلُ هُدًى لِلنَّاسِ وَأَنْزَلَ الْفُرْقَانَ ۗ إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا بِآيَاتِ اللَّهِ لَهُمْ عَذَابٌ شَدِيدٌ ۗ وَاللَّهُ عَزِيزٌ ذُو انْتِقَامٍ

(ከቁርኣን) በፊትም ለሰዎች መሪ አድርጎ (ተውራትንና ኢንጅልን አውርዷል)። (በእውነትና በውሸት መካከል መለያ የሆነውን) ፉርቃንንም አወረደ። እነዚያ በአላህ አናቅጽ የካዱ ሁሉ ብርቱ ቅጣት አለባቸው። አላህ ሁሉን አሸናፊ፤ አስተባባዮችን ተበቃይም ነውና።

إِنَّ اللَّهَ لَا يَخْفَىٰ عَلَيْهِ شَيْءٌ فِي الْأَرْضِ وَلَا فِي السَّمَاءِ

አላህ በምድርም ሆነ በሰማይ ምንም ነገር አይሸሸግበትም።

هُوَ الَّذِي يُصَوِّرُكُمْ فِي الْأَرْحَامِ كَيْفَ يَشَاءُ ۚ لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ

በማህጸኖች ውስጥ እንደፈለገው አድርጎ የሚቀርፃችሁ እርሱው ነው። ከእርሱ ከአሸናፊዉና ከጥበበኛው ጌታ በስተቀር ሌላ ትክክለኛ አምላክ በፍጹም የለም።

هُوَ الَّذِي أَنْزَلَ عَلَيْكَ الْكِتَابَ مِنْهُ آيَاتٌ مُحْكَمَاتٌ هُنَّ أُمُّ الْكِتَابِ وَأُخَرُ مُتَشَابِهَاتٌ ۖ فَأَمَّا الَّذِينَ فِي قُلُوبِهِمْ زَيْغٌ فَيَتَّبِعُونَ مَا تَشَابَهَ مِنْهُ ابْتِغَاءَ الْفِتْنَةِ وَابْتِغَاءَ تَأْوِيلِهِ ۗ وَمَا يَعْلَمُ تَأْوِيلَهُ إِلَّا اللَّهُ ۗ وَالرَّاسِخُونَ فِي الْعِلْمِ يَقُولُونَ آمَنَّا بِهِ كُلٌّ مِنْ عِنْدِ رَبِّنَا ۗ وَمَا يَذَّكَّرُ إِلَّا أُولُو الْأَلْبَابِ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ያ ባንተ ላይ መጽሐፍን-(ቁርኣንን) ያወረደ ነው። ከመጽሐፉም ውስጥ ግልጽ የሆኑ አናቅጽ አሉ። እነርሱም የመጽሐፉ መሰረቶች ናቸው። ሌሎች ደግሞ አሻሚ ትርጉም ያላቸው አሉ። እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ ጥመት ያለባቸው ሌሎችን ለማሳሳት በማሰብና ትርጉሙን በሻቸው ለመለወጥ ሲሉ አሻሚ ትርጉም (ተመሳሳይነት) ያሏቸውን አናቅጽ ብቻ ይከታተላሉ። ትክክለኛ ትርጉማቸውን አላህ ብቻ እንጂ ሌላ ማንም አያውቀዉም። እነዚያ በእውቀት የጠለቁት ግን «በእርሱ አምነናል። ሁሉም ከጌታችን ዘንድ ነው።» ይላሉ። ከአእምሮ ባለቤቶች በስተቀር ማንም አይገሰጽም።

رَبَّنَا لَا تُزِغْ قُلُوبَنَا بَعْدَ إِذْ هَدَيْتَنَا وَهَبْ لَنَا مِنْ لَدُنْكَ رَحْمَةً ۚ إِنَّكَ أَنْتَ الْوَهَّابُ

(እነርሱም የሚሉ ናቸው:) «ጌታችን ሆይ! ቅኑን መንገድ ከመራኸን በኋላ ልቦቻችንን ወደ መጥፎ አታዘንብልብን። ካንተ ዘንድ የሆነን እዝነት ስጠን። አንተ ብቻ በጣም ለጋሽ ነህና።

رَبَّنَا إِنَّكَ جَامِعُ النَّاسِ لِيَوْمٍ لَا رَيْبَ فِيهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ لَا يُخْلِفُ الْمِيعَادَ

«ጌታችን ሆይ! አንተ በዚያ ለመምጣቱ ጥርጥር በሌለበት ቀን ሰውን ሁሉ ሰብሳቢ ነህ። ምን ጊዜም አላህ ቀጠሮን አያፈርስምና»።

إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا لَنْ تُغْنِيَ عَنْهُمْ أَمْوَالُهُمْ وَلَا أَوْلَادُهُمْ مِنَ اللَّهِ شَيْئًا ۖ وَأُولَٰئِكَ هُمْ وَقُودُ النَّارِ

እነዚያ የካዱትን ገንዘቦቻቸውና ልጆቻቸው ከአላህ (ቅጣት) ምንም አያስጥሏቸዉም። እነዚያም እነርሱ የእሳት ማገዶዎች ናቸው።

كَدَأْبِ آلِ فِرْعَوْنَ وَالَّذِينَ مِنْ قَبْلِهِمْ ۚ كَذَّبُوا بِآيَاتِنَا فَأَخَذَهُمُ اللَّهُ بِذُنُوبِهِمْ ۗ وَاللَّهُ شَدِيدُ الْعِقَابِ

ምሳሌያቸው ልክ እንደ ፈርዖን ቤተሰቦችና እንደነዚያ ከበፊታቸዉም እንደነበሩት ሕዝቦች ልማድ ነው። በአናቅጻችን አስተባበሉ። እናም አላህ በኃጢአቶቻቸው ቀጣቸው። አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና።

قُلْ لِلَّذِينَ كَفَرُوا سَتُغْلَبُونَ وَتُحْشَرُونَ إِلَىٰ جَهَنَّمَ ۚ وَبِئْسَ الْمِهَادُ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእነዚያ በአላህ ለካዱ ሰዎች «በቅርብ ጊዜ ትሸነፋላችሁ። ከዚያም ወደ ገሀነም ትሰበሰባላችሁ። ምንጣፊቱም (ገሀነም) ምን ትከፋ!» በላቸው።

قَدْ كَانَ لَكُمْ آيَةٌ فِي فِئَتَيْنِ الْتَقَتَا ۖ فِئَةٌ تُقَاتِلُ فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَأُخْرَىٰ كَافِرَةٌ يَرَوْنَهُمْ مِثْلَيْهِمْ رَأْيَ الْعَيْنِ ۚ وَاللَّهُ يُؤَيِّدُ بِنَصْرِهِ مَنْ يَشَاءُ ۗ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَعِبْرَةً لِأُولِي الْأَبْصَارِ

በእነዚያ (የበድር) ቀን በተጋጠሙት ሁለት ቡድኖች ለእናንተ (ታላቅ) ተዓምር አለላችሁ። አንደኛዋ ቡድን በአላህ መንገድ ትጋደላለች። ሌላይቱ ቡድን ደግሞ ከሓዲ ናት። በዓይን አስተያየት እጥፋቸው ሆነው ያዩዋቸዋል (በቁጥር የነርሱ እጥፍ ሁነው በአይናቸው ተመለከቷቸው)። አላህ በእርዳታው የሚሻውን ሁሉ ያበረታልና። በዚህ ውስጥ ለማስተዋል ባለቤቶች ሁሉ በእርግጥ መገሰጫ አለበት።

زُيِّنَ لِلنَّاسِ حُبُّ الشَّهَوَاتِ مِنَ النِّسَاءِ وَالْبَنِينَ وَالْقَنَاطِيرِ الْمُقَنْطَرَةِ مِنَ الذَّهَبِ وَالْفِضَّةِ وَالْخَيْلِ الْمُسَوَّمَةِ وَالْأَنْعَامِ وَالْحَرْثِ ۗ ذَٰلِكَ مَتَاعُ الْحَيَاةِ الدُّنْيَا ۖ وَاللَّهُ عِنْدَهُ حُسْنُ الْمَآبِ

ከሴቶች፣ ከወንዶች ልጆች፣ ከወርቅ፣ ከብር፣ ከተከማቹ የወርቅና የብር ገንዘቦች፣ ከተሰማሩ ፈረሶች፣ ከግመል ከከብትና ከፍየል፣ ከአዝመራም የሆኑ ፍላጎቶችን መውደድ ለሰዎች ተሸለመላቸው (ሰዎች ዘንድ የተወደዱ ተደረገላቸው)። ይህ ሁሉ የቅርቢቱ ሕይወት መጠቃቀሚያ ብቻ ነው። አላህ ግን እርሱ ዘንድ መልካም የሆነ መመለሻ (ገነት) አለው።

قُلْ أَؤُنَبِّئُكُمْ بِخَيْرٍ مِنْ ذَٰلِكُمْ ۚ لِلَّذِينَ اتَّقَوْا عِنْدَ رَبِّهِمْ جَنَّاتٌ تَجْرِي مِنْ تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا وَأَزْوَاجٌ مُطَهَّرَةٌ وَرِضْوَانٌ مِنَ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ بَصِيرٌ بِالْعِبَادِ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከዚህ ከተዋበላችሁ ጉዳይ የሚበልጥን ልንገራችሁን? እርሱም ለእነዚያ አላህን ለሚፈሩ ሁሉ በጌታቸው ዘንድ በስራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች በውስጧ ሁልጊዜ ነዋሪዎች ሲሆኑ ንጹህ ሚስቶችና ከአላህ የሆነ ውዴታም አለላቸው። አላህም ባርያዎቹን ተመልካች ነው።» በላቸው።

الَّذِينَ يَقُولُونَ رَبَّنَا إِنَّنَا آمَنَّا فَاغْفِرْ لَنَا ذُنُوبَنَا وَقِنَا عَذَابَ النَّارِ

(እነርሱም) እነዚያ «ጌታችን ሆይ! እኛ ባንተ አመንን። ኃጢአቶቻችንን ማርልን። የእሳትን ቅጣት ጠብቀን።» የሚሉ ናቸው።

الصَّابِرِينَ وَالصَّادِقِينَ وَالْقَانِتِينَ وَالْمُنْفِقِينَ وَالْمُسْتَغْفِرِينَ بِالْأَسْحَارِ

እነርሱም ታጋሾች፤ እውነተኞች፤ ታዛዦች፤ ለጋሾችና በሌሊት መጨረሻዎች ሰዓታት ላይ አላህን ምህረት የሚለምኑ ናቸው።

شَهِدَ اللَّهُ أَنَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ وَالْمَلَائِكَةُ وَأُولُو الْعِلْمِ قَائِمًا بِالْقِسْطِ ۚ لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ

አላህ በፍትሕ ቋሚ (አስተናባሪ) ሲሆን ከእርሱ በስተቀር ሌላ ትክክለኛ አምላክ የሌለ መሆኑን መሰከረ። መላዕክትና የእውቀት ባለቤቶችም መሰከሩ። ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም። እርሱ ሁሉን አሸናፊውና ጥበበኛው ነው።

إِنَّ الدِّينَ عِنْدَ اللَّهِ الْإِسْلَامُ ۗ وَمَا اخْتَلَفَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ إِلَّا مِنْ بَعْدِ مَا جَاءَهُمُ الْعِلْمُ بَغْيًا بَيْنَهُمْ ۗ وَمَنْ يَكْفُرْ بِآيَاتِ اللَّهِ فَإِنَّ اللَّهَ سَرِيعُ الْحِسَابِ

አላህ ዘንድ (ተቀባይነት ያለው) ሀይማኖት ኢስላም ብቻ ነው። እነዚያ መጽሐፉን የተሰጡ ሰዎች በመካከላቸው ባለው ምቀኝነት እውቀቱ ከመጣላቸው በኋላ እንጂ አልተለያዩም። በአላህ አናቅጽ ለሚክድ ሁሉ አላህ ምርመራው ፈጣን ነው።

فَإِنْ حَاجُّوكَ فَقُلْ أَسْلَمْتُ وَجْهِيَ لِلَّهِ وَمَنِ اتَّبَعَنِ ۗ وَقُلْ لِلَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ وَالْأُمِّيِّينَ أَأَسْلَمْتُمْ ۚ فَإِنْ أَسْلَمُوا فَقَدِ اهْتَدَوْا ۖ وَإِنْ تَوَلَّوْا فَإِنَّمَا عَلَيْكَ الْبَلَاغُ ۗ وَاللَّهُ بَصِيرٌ بِالْعِبَادِ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢከራከሩህ «ፊቴን ለአላህ ብቻ ሰጠሁ። የተከተሉኝም እንደዚሁ ለአላህ ብቻ ሰጡ።» በላቸው። ለእነዚያም መጽሐፉን ለተሰጡ ሰዎችና ለመሃይማኑ (ዐረቦች)፡- «ሰለማችሁን?» በላቸው። ቢሰልሙ በእርግጥ ወደቀናው መንገድ ተመሩ። እምቢ ቢሉ ግን ባንተ ላይ ያለብህ መልዕክትን ማድረስ ብቻ ነው። አላህ ባሮቹን ተመልካች ነውና።

إِنَّ الَّذِينَ يَكْفُرُونَ بِآيَاتِ اللَّهِ وَيَقْتُلُونَ النَّبِيِّينَ بِغَيْرِ حَقٍّ وَيَقْتُلُونَ الَّذِينَ يَأْمُرُونَ بِالْقِسْطِ مِنَ النَّاسِ فَبَشِّرْهُمْ بِعَذَابٍ أَلِيمٍ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ በአላህ አናቅጽ የሚክዱ፤ ነብያትንም ያለ አግባብ የሚገድሉ፤ ከሰዎችም ውስጥ እነዚያን በትክክለኛነት የሚያዙትን የሚገድሉ በአሳማሚ ቅጣት አብስራቸው።

أُولَٰئِكَ الَّذِينَ حَبِطَتْ أَعْمَالُهُمْ فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ وَمَا لَهُمْ مِنْ نَاصِرِينَ

እነዚያ በቅርቢቱም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም ስራዎቻቸው የተበላሹ ናቸው። ለእነርሱም ምንም ረዳቶች የሏቸዉም።

أَلَمْ تَرَ إِلَى الَّذِينَ أُوتُوا نَصِيبًا مِنَ الْكِتَابِ يُدْعَوْنَ إِلَىٰ كِتَابِ اللَّهِ لِيَحْكُمَ بَيْنَهُمْ ثُمَّ يَتَوَلَّىٰ فَرِيقٌ مِنْهُمْ وَهُمْ مُعْرِضُونَ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እነዚያ ከመጽሐፍ (ትምህርት) ድርሻን ወደ ተሰጡት ሰዎች አላየህምን? ወደ አላህ መጽሐፍ በመካከላቸው ይፈርድ ዘንድ ይጠራሉ። ከዚያ ከእነርሱ ገሚሶቹ (ከፊሎቹ) እውነቱን ወደ ጎን የተው ሆነው ይሸሻሉ።

ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ قَالُوا لَنْ تَمَسَّنَا النَّارُ إِلَّا أَيَّامًا مَعْدُودَاتٍ ۖ وَغَرَّهُمْ فِي دِينِهِمْ مَا كَانُوا يَفْتَرُونَ

ይህም እነርሱ «የገሀነም እሳት የተቆጠሩ ቀናትን ብቻ እንጂ አትነካንም።» በማለታቸው ነው። በሀይማኖታቸዉም ይቀጣጥፉት የነበሩት ነገር አታለላቸው።

فَكَيْفَ إِذَا جَمَعْنَاهُمْ لِيَوْمٍ لَا رَيْبَ فِيهِ وَوُفِّيَتْ كُلُّ نَفْسٍ مَا كَسَبَتْ وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ

በእርሱ መምጣት ጥርጥር የሌለበት በሆነው ቀን በሰበሰብናቸውና ነፍስ ሁሉ የሰራችውን ስራ በተሞላች ጊዜ እንዴት ይሆናሉ? እነርሱም ቅንጣትንም አይበደሉም።

قُلِ اللَّهُمَّ مَالِكَ الْمُلْكِ تُؤْتِي الْمُلْكَ مَنْ تَشَاءُ وَتَنْزِعُ الْمُلْكَ مِمَّنْ تَشَاءُ وَتُعِزُّ مَنْ تَشَاءُ وَتُذِلُّ مَنْ تَشَاءُ ۖ بِيَدِكَ الْخَيْرُ ۖ إِنَّكَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! እንዲህ) በል: «የንግስና ባለቤት የሆንከው አላህ ሆይ! ለምትሻው ሰው ንግስናን ትሰጣለህ። ከምትሻዉም ሰው ንግስናን ትነጥቃለህ። የምትሻውንም ሰው ታከብራለህ። የምትሻውንም ሰው ደግሞ ታዋርዳለህ። መልካም ነገር ሁሉ በእጅህ ብቻ ነው። አንተ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነህና።

تُولِجُ اللَّيْلَ فِي النَّهَارِ وَتُولِجُ النَّهَارَ فِي اللَّيْلِ ۖ وَتُخْرِجُ الْحَيَّ مِنَ الْمَيِّتِ وَتُخْرِجُ الْمَيِّتَ مِنَ الْحَيِّ ۖ وَتَرْزُقُ مَنْ تَشَاءُ بِغَيْرِ حِسَابٍ

«ሌሊቱን በቀን ውስጥ ታስገባለህ። ቀኑንም በሌሊት ውስጥ ታስገባለህ። ሕያውንም ከሙት ታወጣለህ። ሙታንንም ከሕያው ታወጣለህ፤ ለምትሻውም ሁሉ መጠን የለሽ ሲሳይ ትሰጣለህ።» በል።

لَا يَتَّخِذِ الْمُؤْمِنُونَ الْكَافِرِينَ أَوْلِيَاءَ مِنْ دُونِ الْمُؤْمِنِينَ ۖ وَمَنْ يَفْعَلْ ذَٰلِكَ فَلَيْسَ مِنَ اللَّهِ فِي شَيْءٍ إِلَّا أَنْ تَتَّقُوا مِنْهُمْ تُقَاةً ۗ وَيُحَذِّرُكُمُ اللَّهُ نَفْسَهُ ۗ وَإِلَى اللَّهِ الْمَصِيرُ

አማኞች ከሓዲያንን ከአማኞች ሌላ ረዳቶች አድርገው አይያዙ። ይህንን የሚሰራ ከአላህ ሀይማኖት በምንም ውስጥ አይደለም። ከእነርሱ መጠበቅን ብትጠበቁ እንጂ። አላህ ከእርሱው ያስጠነቅቃችኋል። መመለሻም ወደ አላህ ብቻ ነውና።

قُلْ إِنْ تُخْفُوا مَا فِي صُدُورِكُمْ أَوْ تُبْدُوهُ يَعْلَمْهُ اللَّهُ ۗ وَيَعْلَمُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۗ وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በልቦቻችሁ ውስጥ ያለውን ሁሉ ብትደብቁት ወይም ብትገልጹት አላህ ያውቀዋል። በሰማያት ውስጥ ያለውንና በምድር ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል። አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው።» በል።

يَوْمَ تَجِدُ كُلُّ نَفْسٍ مَا عَمِلَتْ مِنْ خَيْرٍ مُحْضَرًا وَمَا عَمِلَتْ مِنْ سُوءٍ تَوَدُّ لَوْ أَنَّ بَيْنَهَا وَبَيْنَهُ أَمَدًا بَعِيدًا ۗ وَيُحَذِّرُكُمُ اللَّهُ نَفْسَهُ ۗ وَاللَّهُ رَءُوفٌ بِالْعِبَادِ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያን ነፍስ ሁሉ ከመልካም ነገር የሰራችውን የቀረበ ሆኖ የምታገኝበትን ቀን (አስታውስ)። ከመጥፎም የሰራችው በእርሷና በኃጢአቱ መካከል በጣም የሰፋ ርቀት ቢኖር ትመኛለች። አላህ ከእርሱው ያስጠነቅቃችኋል። አላህ ለባሮቹ ሩህሩህ ነውና።

قُلْ إِنْ كُنْتُمْ تُحِبُّونَ اللَّهَ فَاتَّبِعُونِي يُحْبِبْكُمُ اللَّهُ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْ ۗ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَحِيمٌ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!)፡- «አላህን የምትወዱ እንደሆናችሁ እኔን ተከተሉኝ። አላህም ይወዳችኋል፤ ኃጢአቶቻችሁንም ለእናንተ ይምራልና። አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና።» በላቸው።

قُلْ أَطِيعُوا اللَّهَ وَالرَّسُولَ ۖ فَإِنْ تَوَلَّوْا فَإِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ الْكَافِرِينَ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!)፡- «አላህንና መልዕክተኛውን ታዘዙ። ቢሸሹም አላህ ከሓዲያንን አይወድም» በላቸው።

إِنَّ اللَّهَ اصْطَفَىٰ آدَمَ وَنُوحًا وَآلَ إِبْرَاهِيمَ وَآلَ عِمْرَانَ عَلَى الْعَالَمِينَ

አላህ (ነብዩ) አደምን፣(ነብዩ) ኑህን፣(የነብዩ) ኢብራሂምን ቤተሰብ እና የዒምራንን ቤተሰብ ከአለማት አበለጣቸው (መረጣቸው)።

ذُرِّيَّةً بَعْضُهَا مِنْ بَعْضٍ ۗ وَاللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ

እኒህን ቤተሰቦች ከፊሉ ከከፊሉ የሆነ ዝርያ አድርጎ መረጣቸው። አላህ ሁሉን ሰሚና ሁሉንም አዋቂ ነው።

إِذْ قَالَتِ امْرَأَتُ عِمْرَانَ رَبِّ إِنِّي نَذَرْتُ لَكَ مَا فِي بَطْنِي مُحَرَّرًا فَتَقَبَّلْ مِنِّي ۖ إِنَّكَ أَنْتَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የዒምራን ባለቤት (ሀና) «ጌታዬ ሆይ! በሆዴ ውስጥ ያለውን ጽንስ ከሥራ ነፃ የተደረገ ሲሆን ላንተ አገልግሎት ይውል ዘንድ ተሳልኩ። እናም ከእኔ ተቀበል። አንተ ሰሚና አዋቂ ነህና።» ባለች ጊዜ የሆነውን አስታውሱ በላቸው።

فَلَمَّا وَضَعَتْهَا قَالَتْ رَبِّ إِنِّي وَضَعْتُهَا أُنْثَىٰ وَاللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا وَضَعَتْ وَلَيْسَ الذَّكَرُ كَالْأُنْثَىٰ ۖ وَإِنِّي سَمَّيْتُهَا مَرْيَمَ وَإِنِّي أُعِيذُهَا بِكَ وَذُرِّيَّتَهَا مِنَ الشَّيْطَانِ الرَّجِيمِ

በወለደቻትም ጊዜ፡- «ጌታዬ ሆይ! ሴት ሆና ወለድኳት።» አለች። አላህ የወለደችውን ምንነት አዋቂ ነው። የተመኘችው ወንድ እንደ ወለደቻት ሴት የሚሆን አልነበረም። «መርየምም ብዬ ስም አወጣሁላት። እኔም እርሷንና ዝርያዋን ከተረገመው ሰይጣን ተንኮል ባንተ እጠብቃቸዋለሁ።» አለች።

فَتَقَبَّلَهَا رَبُّهَا بِقَبُولٍ حَسَنٍ وَأَنْبَتَهَا نَبَاتًا حَسَنًا وَكَفَّلَهَا زَكَرِيَّا ۖ كُلَّمَا دَخَلَ عَلَيْهَا زَكَرِيَّا الْمِحْرَابَ وَجَدَ عِنْدَهَا رِزْقًا ۖ قَالَ يَا مَرْيَمُ أَنَّىٰ لَكِ هَٰذَا ۖ قَالَتْ هُوَ مِنْ عِنْدِ اللَّهِ ۖ إِنَّ اللَّهَ يَرْزُقُ مَنْ يَشَاءُ بِغَيْرِ حِسَابٍ

ጌታዋም በመልካም አቀባበል ተቀበላት። በመልካም አስተዳደግም አፋፋት። ከዚያም ዘከርያ አሳደጋት። ዘከርያም ወደ ምኩራቧ በሷ ላይ በገባ ቁጥርም እርሷ ዘንድ ሲሳይን አገኘ። «መርየም ሆይ! ይህ ለአንቺ ከየት ነው የሚመጣልሽ?» አላት። «እርሱ የሚመጣልኝ ከአላህ ዘንድ ነው። አላህ እኮ ለሚሻው ሁሉ ሲሳዩን ያለ ሂሳብ ይሰጣል።» አለችው።

هُنَالِكَ دَعَا زَكَرِيَّا رَبَّهُ ۖ قَالَ رَبِّ هَبْ لِي مِنْ لَدُنْكَ ذُرِّيَّةً طَيِّبَةً ۖ إِنَّكَ سَمِيعُ الدُّعَاءِ

እዚያ ዘንድም ዘከርያ ጌታውን እንደዚህ በማለት ለመነ: «ጌታዬ ሆይ! ካንተ ዘንድ መልካም ዘርን ለእኔ ስጠኝ። አንተ ጸሎትን ሰሚ ነህና» አለ።

فَنَادَتْهُ الْمَلَائِكَةُ وَهُوَ قَائِمٌ يُصَلِّي فِي الْمِحْرَابِ أَنَّ اللَّهَ يُبَشِّرُكَ بِيَحْيَىٰ مُصَدِّقًا بِكَلِمَةٍ مِنَ اللَّهِ وَسَيِّدًا وَحَصُورًا وَنَبِيًّا مِنَ الصَّالِحِينَ

እርሱም በምኩራቡ ውስጥ ቆሞ ሶላት ሲሰግድ መላዕክት:- «አላህ በየህያ: ከአላህ በሆነ ቃል የሚያረጋግጥ፣ በላጭ፣ ከሴት ጋር የማይገናኝ ድንግልና ከደጋጎቹም የሆነ ነቢይ ሲሆን ያበስርሃል።» በማለት ጠሩት።

قَالَ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي غُلَامٌ وَقَدْ بَلَغَنِيَ الْكِبَرُ وَامْرَأَتِي عَاقِرٌ ۖ قَالَ كَذَٰلِكَ اللَّهُ يَفْعَلُ مَا يَشَاءُ

ዘከርያም «ጌታዬ ሆይ! እኔ እርጅና የደረሰብኝ ሚስቴም መካን ስትሆን እንዴት ልጅ ይኖረኛል?» አለ። መልአኩም: «ልክ እንደዚሁ ነው። አላህ የሚሻውን ነገር ሁሉ ይሰራልና።» አለው።

قَالَ رَبِّ اجْعَلْ لِي آيَةً ۖ قَالَ آيَتُكَ أَلَّا تُكَلِّمَ النَّاسَ ثَلَاثَةَ أَيَّامٍ إِلَّا رَمْزًا ۗ وَاذْكُرْ رَبَّكَ كَثِيرًا وَسَبِّحْ بِالْعَشِيِّ وَالْإِبْكَارِ

ዘከርያም «ጌታዬ ሆይ! ለእዚህ ነገር ምልክትን አድርግልኝ።» አለ። «ምልክትህ ሶስት ቀን በጥቅሻ እንጂ ሰዎችን አለማናገርህ ነው። በዚያ ጊዜ ጌታህን በብዙ አውሳ። በማታና በጠዋትም አወድሰው።» አለው።

وَإِذْ قَالَتِ الْمَلَائِكَةُ يَا مَرْيَمُ إِنَّ اللَّهَ اصْطَفَاكِ وَطَهَّرَكِ وَاصْطَفَاكِ عَلَىٰ نِسَاءِ الْعَالَمِينَ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መላእክትም ባሉ ጊዜ: «መርየም ሆይ! አላህ በእርግጥ መረጠሸ። ከነውሮች ሁሉ አጸዳሸ። ከዓለማት ሴቶችም መካከል መረጠሸ።

يَا مَرْيَمُ اقْنُتِي لِرَبِّكِ وَاسْجُدِي وَارْكَعِي مَعَ الرَّاكِعِينَ

«መርየም ሆይ! ለጌታሽ ታዘዢ። ስገጂም። ከአጎንባሾች ጋርም ሁነሽ አጎንብሺ።» (ያለበትን ታሪክ ለህዝቦችህ አውሳ።)

ذَٰلِكَ مِنْ أَنْبَاءِ الْغَيْبِ نُوحِيهِ إِلَيْكَ ۚ وَمَا كُنْتَ لَدَيْهِمْ إِذْ يُلْقُونَ أَقْلَامَهُمْ أَيُّهُمْ يَكْفُلُ مَرْيَمَ وَمَا كُنْتَ لَدَيْهِمْ إِذْ يَخْتَصِمُونَ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ታሪክ ወደ አንተ ከምናወርደው ከሩቅ ወሬ ነው። መርየምን ማን እንደሚያሳድግ ብዕሮቻቸውን ለዕጣ በጣሉ ጊዜ አንተ እነርሱ ዘንድ አልነበርክም። በሚከራከሩም ጊዜ እነርሱ ዘንድ አልነበርክም።

إِذْ قَالَتِ الْمَلَائِكَةُ يَا مَرْيَمُ إِنَّ اللَّهَ يُبَشِّرُكِ بِكَلِمَةٍ مِنْهُ اسْمُهُ الْمَسِيحُ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ وَجِيهًا فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ وَمِنَ الْمُقَرَّبِينَ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መላዕክትም «መርየም ሆይ! አላህ ከእርሱ በሆነው ቃል የሚፈጠር ስሙ አል መሲህ ዒሳ የመርየም ልጅ በሚባል፤ በዚህ ዓለምም ሆነ በመጨረሻው ዓለም የተከበረና ከባለሟሎቹ አንዱ በሆነ ልጅ ያበስርሻል። (ባላት ጊዜ እዚያ ቦታ አልነበርክም) ።

وَيُكَلِّمُ النَّاسَ فِي الْمَهْدِ وَكَهْلًا وَمِنَ الصَّالِحِينَ

«እርሱም ገና በህፃንነቱ ካደገም በኋላ ሰዎችን ያነጋግራል። ከመልካሞቹም አንዱ ነው።» (አላት)።

قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ ۖ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُنْ فَيَكُونُ

እርሷም «ጌታዬ ሆይ! ማንም ሰው በትዳርም ሆነ በዝሙት ሳይነካኝ እንዴት ልጅ ይኖረኛል?» አለች። መልአኩ ጅብሪልም አላት: «እንደዚሁ ነው። አላህ የሚሻውን ሁሉ ይፈጥራል። የአንድን ነገር መሆን በፈለገ ጊዜ የሚለው ‹ሁን› ብቻ ነው። ወዲያውኑም ያ ነገር ይሆናል።

وَيُعَلِّمُهُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَالتَّوْرَاةَ وَالْإِنْجِيلَ

«ጽሕፈትንና ጥበብን፤ ተውራትንና ኢንጂልንም ያስተምረዋል።

وَرَسُولًا إِلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ أَنِّي قَدْ جِئْتُكُمْ بِآيَةٍ مِنْ رَبِّكُمْ ۖ أَنِّي أَخْلُقُ لَكُمْ مِنَ الطِّينِ كَهَيْئَةِ الطَّيْرِ فَأَنْفُخُ فِيهِ فَيَكُونُ طَيْرًا بِإِذْنِ اللَّهِ ۖ وَأُبْرِئُ الْأَكْمَهَ وَالْأَبْرَصَ وَأُحْيِي الْمَوْتَىٰ بِإِذْنِ اللَّهِ ۖ وَأُنَبِّئُكُمْ بِمَا تَأْكُلُونَ وَمَا تَدَّخِرُونَ فِي بُيُوتِكُمْ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لَكُمْ إِنْ كُنْتُمْ مُؤْمِنِينَ

«ወደ ኢስራኢል ልጆችም መልዕክተኛ ያደርገዋል። ይላልም: ‹እኔ ከጌታዬ ዘንድ በተዐምር መጣሁላችሁ። እኔ ለእናንተ ከጭቃ የወፍ ቅርጽ አይነት እፈጥራለሁ። በእርሱም እተነፍስበታለሁ። ከዚያም በአላህ ፈቃድ ወፍ ይሆናል። እውር ሆኖ የተወለደንም ለምጸኛንም በአላህ ፈቃድ አድናለሁ። ሙታንንም በአላህ ፍቃድ አስነሳለሁ። የምትበሉትንና በየቤቶቻችሁ የምታደልቡትን ሁሉ እነግራችኋለሁ። (መረጃዎችን አገናዝባችሁ) የምታምኑ እንደሆናችሁ ለእናንተ በዚህ ውስጥ ግልጽ ተዐምር አለበት።

وَمُصَدِّقًا لِمَا بَيْنَ يَدَيَّ مِنَ التَّوْرَاةِ وَلِأُحِلَّ لَكُمْ بَعْضَ الَّذِي حُرِّمَ عَلَيْكُمْ ۚ وَجِئْتُكُمْ بِآيَةٍ مِنْ رَبِّكُمْ فَاتَّقُوا اللَّهَ وَأَطِيعُونِ

«‹ከእኔ በፊት የነበረውን ተውራትን ያረጋገጥኩ ስሆን ያንም በእናንተ ላይ እርም የተደረገውን ነገር ከፊሉን ለእናንተ እፈቅድ ዘንድ መጣሁላችሁ። ከጌታችሁም በሆነ ተዐምር መጣሁላችሁ። አላህን ፍሩ። እኔንም ታዘዙኝ።

إِنَّ اللَّهَ رَبِّي وَرَبُّكُمْ فَاعْبُدُوهُ ۗ هَٰذَا صِرَاطٌ مُسْتَقِيمٌ

«‹አላህ ጌታዬ የእናንተም ጌታችሁ ነው። ስለዚህ በብቸኝነት ተገዙት። ይህ ቀጥተኛው መንገድ ነው።› ይላቸዋል»

فَلَمَّا أَحَسَّ عِيسَىٰ مِنْهُمُ الْكُفْرَ قَالَ مَنْ أَنْصَارِي إِلَى اللَّهِ ۖ قَالَ الْحَوَارِيُّونَ نَحْنُ أَنْصَارُ اللَّهِ آمَنَّا بِاللَّهِ وَاشْهَدْ بِأَنَّا مُسْلِمُونَ

ዒሳ ከእነርሱ ክህደት በተሰማው ጊዜ፡- «ወደ አላህ የእኔ ረዳቶች የሚሆኑ እነማን ናቸው?» አለ። ሀዋርያትም አሉ፡- «ዒሳ ሆይ! እኛ የአላህ ረዳቶች ነን። በአላህ አምነናል። ሙስሊሞች (ታዛዦች) መሆናችንን መስክር።

رَبَّنَا آمَنَّا بِمَا أَنْزَلْتَ وَاتَّبَعْنَا الرَّسُولَ فَاكْتُبْنَا مَعَ الشَّاهِدِينَ

«ጌታችን ሆይ! ባወረድከው አምነን መልዕክተኛውን ተከትለናል።እኛንም (ባንተ ብቸኛ አምላክነት በነብያት መልዕክተኛነት) ከመስካሪዎች ጋራ መዝግበን።» (አሉ)።

وَمَكَرُوا وَمَكَرَ اللَّهُ ۖ وَاللَّهُ خَيْرُ الْمَاكِرِينَ

(አይሁድም በዒሳ ላይ) አደሙ። አላህም (በእነርሱ ላይ) አሴረባቸው (ዘዴ አደረገባቸው)። አላህ ከአሴሪዎቹ ሁሉ በላጭ ነውና።

إِذْ قَالَ اللَّهُ يَا عِيسَىٰ إِنِّي مُتَوَفِّيكَ وَرَافِعُكَ إِلَيَّ وَمُطَهِّرُكَ مِنَ الَّذِينَ كَفَرُوا وَجَاعِلُ الَّذِينَ اتَّبَعُوكَ فَوْقَ الَّذِينَ كَفَرُوا إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ ۖ ثُمَّ إِلَيَّ مَرْجِعُكُمْ فَأَحْكُمُ بَيْنَكُمْ فِيمَا كُنْتُمْ فِيهِ تَخْتَلِفُونَ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ባለ ጊዜ (አስታውስ)፡- «ዒሳ ሆይ! እኔ ወሳጅህና ከምድር ወደ እኔ አንሽህ ነኝ። ከነዚያም በእኔ ከካዱ ሰዎች (ተንኮል) አጥሪህ ነኝ። እነዚያ የተከተሉህንም እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ከነዚያ ከካዱት በላይ አድራጊ ነኝ። ከዚያ የሁላችሁም መመለሻችሁ ወደ እኔ ነው። ያን ትለያዩበት በነበራችሁበት ነገርም በመካከላችሁ እፈርዳለሁ።

فَأَمَّا الَّذِينَ كَفَرُوا فَأُعَذِّبُهُمْ عَذَابًا شَدِيدًا فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ وَمَا لَهُمْ مِنْ نَاصِرِينَ

«እነዚያማ የካዱትን በቅርቢቱ ዓለምም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም ብርቱ ቅጣትን እቀጣቸዋለሁ። ለእነርሱም ምንም ረዳቶች የሏቸዉም»

وَأَمَّا الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ فَيُوَفِّيهِمْ أُجُورَهُمْ ۗ وَاللَّهُ لَا يُحِبُّ الظَّالِمِينَ

እነዚያማ አምነው መልካም ስራዎችን የሰሩትን አላህ ምንዳቸውን ይሞላላቸዋል። አላህም በዳዮችን አይወድምና።

ذَٰلِكَ نَتْلُوهُ عَلَيْكَ مِنَ الْآيَاتِ وَالذِّكْرِ الْحَكِيمِ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ተዓምራትና ጥበብን ከያዘው ተግሳጽ በአንተ ላይ የምናነበው ነው።

إِنَّ مَثَلَ عِيسَىٰ عِنْدَ اللَّهِ كَمَثَلِ آدَمَ ۖ خَلَقَهُ مِنْ تُرَابٍ ثُمَّ قَالَ لَهُ كُنْ فَيَكُونُ

አላህ ዘንድ የዒሳ (ያለ አባት መፈጠሩ) ምሳሌው ልክ እንደ (ያለ አባትና ያለ እናት እንደተፈጠሩት አባታችን) አደም ቢጤ ነው። አላህ ከአፈር ፈጠረውና ከዚያም «ሁን» አለው። ከዚያ ሰው ሆነ።

الْحَقُّ مِنْ رَبِّكَ فَلَا تَكُنْ مِنَ الْمُمْتَرِينَ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እውነታው ከጌታህ ዘንድ የመጣልህ እውነት ነው። እናም ከተጠራጣሪዎች አትሁን።

فَمَنْ حَاجَّكَ فِيهِ مِنْ بَعْدِ مَا جَاءَكَ مِنَ الْعِلْمِ فَقُلْ تَعَالَوْا نَدْعُ أَبْنَاءَنَا وَأَبْنَاءَكُمْ وَنِسَاءَنَا وَنِسَاءَكُمْ وَأَنْفُسَنَا وَأَنْفُسَكُمْ ثُمَّ نَبْتَهِلْ فَنَجْعَلْ لَعْنَتَ اللَّهِ عَلَى الْكَاذِبِينَ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እውቀት ከመጣልህ በኋላ በእርሱ (በዒሳ) የተከራከሩህን «ኑ ልጆቻችንንና ልጆቻችሁን፣ ሴቶቻችንንና (ሚስቶቻችንና) ሴቶቻችሁን (ሚስቶቻችሁን)፣ ነፍሶቻችንንና ነፍሶቻችሁን እንጥራና ከዚያ አላህን እንለምን። የአላህንም እርግማን በውሸታሞች ላይ እናድርግ።» በላቸው።

إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ الْقَصَصُ الْحَقُّ ۚ وَمَا مِنْ إِلَٰهٍ إِلَّا اللَّهُ ۚ وَإِنَّ اللَّهَ لَهُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ እውነተኛው ታሪክ ነው። ትክክለኛ አምላክም ከአላህ በስተቀር የለም። አላህም አሸናፊውና ጥበበኛው አምላክ ነው።

فَإِنْ تَوَلَّوْا فَإِنَّ اللَّهَ عَلِيمٌ بِالْمُفْسِدِينَ

(ከማመን) እምቢ ቢሉም (አጥፊዎቹ እነርሱ ናቸው።) አላህ አጥፊዎቹን (ከደህናዎቹ) ለይቶ አዋቂ ነው።

قُلْ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ تَعَالَوْا إِلَىٰ كَلِمَةٍ سَوَاءٍ بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمْ أَلَّا نَعْبُدَ إِلَّا اللَّهَ وَلَا نُشْرِكَ بِهِ شَيْئًا وَلَا يَتَّخِذَ بَعْضُنَا بَعْضًا أَرْبَابًا مِنْ دُونِ اللَّهِ ۚ فَإِنْ تَوَلَّوْا فَقُولُوا اشْهَدُوا بِأَنَّا مُسْلِمُونَ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ሆነችው ቃል ኑ። (እርሷም) ‹አላህን ብቻ እንጂ ሌላን ላንገዛ፤ በእርሱም ምንንም ላናጋራ፤ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይዝ› ነው።» በላቸው። (ሙስሊሞች ሆይ!) እምቢ ካሉም «እኛ ሙስሊሞች መሆናችንን መስክሩ።» በሏቸው።

يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لِمَ تُحَاجُّونَ فِي إِبْرَاهِيمَ وَمَا أُنْزِلَتِ التَّوْرَاةُ وَالْإِنْجِيلُ إِلَّا مِنْ بَعْدِهِ ۚ أَفَلَا تَعْقِلُونَ

እናንተ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በኢብራሂም (ዙሪያ) ለምን ትከራከራላችሁ? ተውራትና ኢንጂል ከእርሱ በኋላ እንጂ አልተወረዱም። ልብ አትሉምን?

هَا أَنْتُمْ هَٰؤُلَاءِ حَاجَجْتُمْ فِيمَا لَكُمْ بِهِ عِلْمٌ فَلِمَ تُحَاجُّونَ فِيمَا لَيْسَ لَكُمْ بِهِ عِلْمٌ ۚ وَاللَّهُ يَعْلَمُ وَأَنْتُمْ لَا تَعْلَمُونَ

እናንተ እነዚያ እውቀት ባላችሁ ነገር የተከራከራችሁ ናችሁ። ታዲያ እውቀት በሌላችሁ ነገር ላይ ለምን ትከራከራላችሁ? አላህ ሁሉን ነገር ያውቃል። እናንተ ግን አታውቁም።

مَا كَانَ إِبْرَاهِيمُ يَهُودِيًّا وَلَا نَصْرَانِيًّا وَلَٰكِنْ كَانَ حَنِيفًا مُسْلِمًا وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِينَ

ኢብራሂም አይሁድም ሆነ ክርስቲያን አልነበረም። ግን በቀጥተኛው ሃይማኖት ቀጥ ያለ ሙስሊም ነበር። ከአጋሪዎችም አልነበረም።

إِنَّ أَوْلَى النَّاسِ بِإِبْرَاهِيمَ لَلَّذِينَ اتَّبَعُوهُ وَهَٰذَا النَّبِيُّ وَالَّذِينَ آمَنُوا ۗ وَاللَّهُ وَلِيُّ الْمُؤْمِنِينَ

በኢብራሂም ይበልጥ ተገቢዎቹ እነዚያ የተከተሉት፤ ይህ ነብይ (ነብዩ ሙሐመድ) እና እነዚያ ያመኑት ብቻ ናቸው። አላህ የአማኞች ወዳጅ ነው።

وَدَّتْ طَائِفَةٌ مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ لَوْ يُضِلُّونَكُمْ وَمَا يُضِلُّونَ إِلَّا أَنْفُسَهُمْ وَمَا يَشْعُرُونَ

(ሙስሊሞች ሆይ!) ከመጽሐፉ ባለቤቶች የተወሰኑት እናንተን ሊያሳስቷችሁ ተመኙ። እራሳቸውን እንጂ ማንንም አያሳስቱም። እነርሱ ግን ይህንን እውነታ አያውቁም።

يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لِمَ تَكْفُرُونَ بِآيَاتِ اللَّهِ وَأَنْتُمْ تَشْهَدُونَ

እናንተ የመጽሐፍ ባለቤቶች ሆይ! እናንተ የምታውቁ ስትሆኑ በአላህ አናቅጽ ለምን ትክዳላችሁ?

يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لِمَ تَلْبِسُونَ الْحَقَّ بِالْبَاطِلِ وَتَكْتُمُونَ الْحَقَّ وَأَنْتُمْ تَعْلَمُونَ

እናንተ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! እውነትን ከውሸት ጋር ለምን ትቀላቅላላችሁ? እውነቱንም የምታውቁ ስትሆኑ ለምን ትደብቃላችሁ?

وَقَالَتْ طَائِفَةٌ مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ آمِنُوا بِالَّذِي أُنْزِلَ عَلَى الَّذِينَ آمَنُوا وَجْهَ النَّهَارِ وَاكْفُرُوا آخِرَهُ لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ

ከመጽሐፉ ባለቤቶች የሆነ ቡድንም በዚያ ባመኑት ላይ በተወረደው ቁርኣን «በቀኑ መጀመሪያ ላይ እመኑበትና በቀኑ መጨረሻ ላይ ካዱ። እነርሱ ሊመለሱ ይከጀላልና።» አሉ።

وَلَا تُؤْمِنُوا إِلَّا لِمَنْ تَبِعَ دِينَكُمْ قُلْ إِنَّ الْهُدَىٰ هُدَى اللَّهِ أَنْ يُؤْتَىٰ أَحَدٌ مِثْلَ مَا أُوتِيتُمْ أَوْ يُحَاجُّوكُمْ عِنْدَ رَبِّكُمْ ۗ قُلْ إِنَّ الْفَضْلَ بِيَدِ اللَّهِ يُؤْتِيهِ مَنْ يَشَاءُ ۗ وَاللَّهُ وَاسِعٌ عَلِيمٌ

(አሉም) «ሃይማኖታችሁን ለተከተለ እንጂ አትመኑም።» (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ትክክለኛው መመሪያ የአላህ መመሪያ ብቻ ነው። እናንተ ያገኛችሁትን እድል እንዳያገኙ ወይም በእርሱ ከጌታችሁ ፊት እንዳይሞግቷችሁ በመፍራት ነውን?» በላቸው። (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ችሮታ በአላህ እጅ ብቻ ነው። ለሚፈልገውም ይሰጠዋል። አላህም ችሮታው ሰፊና ሁሉን አዋቂ ነው።» በላቸው።

يَخْتَصُّ بِرَحْمَتِهِ مَنْ يَشَاءُ ۗ وَاللَّهُ ذُو الْفَضْلِ الْعَظِيمِ

በእዝነቱ የሚሻውን ይመርጣል። አላህ የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነውና።

وَمِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ مَنْ إِنْ تَأْمَنْهُ بِقِنْطَارٍ يُؤَدِّهِ إِلَيْكَ وَمِنْهُمْ مَنْ إِنْ تَأْمَنْهُ بِدِينَارٍ لَا يُؤَدِّهِ إِلَيْكَ إِلَّا مَا دُمْتَ عَلَيْهِ قَائِمًا ۗ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ قَالُوا لَيْسَ عَلَيْنَا فِي الْأُمِّيِّينَ سَبِيلٌ وَيَقُولُونَ عَلَى اللَّهِ الْكَذِبَ وَهُمْ يَعْلَمُونَ

ከመጽሐፉ ባለቤቶች መካከል በብዙ ገንዘብ ላይ ብታምነው ቅንጣት ሳያጎድል የሚመልስልህ አለ። ከእነርሱም መካከል በአንድ ዲናር እንኳን ብታምነው ሁል ጊዜም እሱ ላይ የምትጠባበቅ ካልሆንክ በስተቀር የማይመልስልህም አለ። ይህ «በመሀይማን ህዝቦች ላይ በምናደርገው በደል በእኛ ላይ የምንጠየቅበት መንገድ የለብንም።» ስለሚሉና እነርሱም እያወቁ በአላህ ላይ ውሸትን ስለሚናገሩ ነው።

بَلَىٰ مَنْ أَوْفَىٰ بِعَهْدِهِ وَاتَّقَىٰ فَإِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُتَّقِينَ

ጉዳዩ እነርሱ እንዳሉት አይደለም (ተጠያቂነት አለባቸው)። ያ በቃል ኪዳኑ የሞላና የተጠነቀቀን ሁሉ (አላህ ይወደዋል)፤ አላህ ጥንቁቆችን ይወዳል።

إِنَّ الَّذِينَ يَشْتَرُونَ بِعَهْدِ اللَّهِ وَأَيْمَانِهِمْ ثَمَنًا قَلِيلًا أُولَٰئِكَ لَا خَلَاقَ لَهُمْ فِي الْآخِرَةِ وَلَا يُكَلِّمُهُمُ اللَّهُ وَلَا يَنْظُرُ إِلَيْهِمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ وَلَا يُزَكِّيهِمْ وَلَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ

እነዚያ በአላህ ቃል ኪዳንና በመሀላዎቻቸው ጥቂትን ዋጋን የሚለውጡ ሁሉ በመጨረሻይቱ ዓለም ምንም እድል የላቸዉም። በትንሳኤም ቀን አላህ አያነጋግራቸዉም። ወደ እነርሱም አይመለከትም። አያጸዳቸዉምም። ከቶውንም ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣት አለባቸው።

وَإِنَّ مِنْهُمْ لَفَرِيقًا يَلْوُونَ أَلْسِنَتَهُمْ بِالْكِتَابِ لِتَحْسَبُوهُ مِنَ الْكِتَابِ وَمَا هُوَ مِنَ الْكِتَابِ وَيَقُولُونَ هُوَ مِنْ عِنْدِ اللَّهِ وَمَا هُوَ مِنْ عِنْدِ اللَّهِ وَيَقُولُونَ عَلَى اللَّهِ الْكَذِبَ وَهُمْ يَعْلَمُونَ

ከእነርሱም መካከል ከመጽሐፉ ያልሆነን ነገር ከመጽሐፉ አካል መሆኑን እንድታስቡ በመጽሐፉ ምላሶቻቸውን የሚያጣምሙም አሉ። እርሱ ከአላህ ዘንድ ያልመጣ (ያልወረደ) ሲሆን «ከአላህ ዘንድ የመጣ (የወረደ) ነው።» ይላሉ። የሚያውቁ ሲሆኑ በአላህ ላይ ውሸትን ይናገራሉ።

مَا كَانَ لِبَشَرٍ أَنْ يُؤْتِيَهُ اللَّهُ الْكِتَابَ وَالْحُكْمَ وَالنُّبُوَّةَ ثُمَّ يَقُولَ لِلنَّاسِ كُونُوا عِبَادًا لِي مِنْ دُونِ اللَّهِ وَلَٰكِنْ كُونُوا رَبَّانِيِّينَ بِمَا كُنْتُمْ تُعَلِّمُونَ الْكِتَابَ وَبِمَا كُنْتُمْ تَدْرُسُونَ

ለማንም ሰው አላህ መጽሐፍን፣ ጥበብንና ነብይነትን ሰጥቶት ከዚያ ለሰዎች «ከአላህ ሌላ ለእኔ ባሮች ሁኑ።» ሊል አይገባዉም። ይልቁንም «መጽሐፉን የምታስተምሩና የምታጠኑ በነበራችሁበት በእውቀታችሁ (ጌታችሁን የምትገዙ) ሊቃውንት ሁኑ።» ይላቸዋል።

وَلَا يَأْمُرَكُمْ أَنْ تَتَّخِذُوا الْمَلَائِكَةَ وَالنَّبِيِّينَ أَرْبَابًا ۗ أَيَأْمُرُكُمْ بِالْكُفْرِ بَعْدَ إِذْ أَنْتُمْ مُسْلِمُونَ

መላዕክትንና ነብያትንም አማልክት አድርጋችሁ እንድትይዙ ሊያዛችሁ አይገባም። (እናንተ) ሙስሊሞች ከሆናችሁ በኋላ በክህደት ያዛችኋልን?

وَإِذْ أَخَذَ اللَّهُ مِيثَاقَ النَّبِيِّينَ لَمَا آتَيْتُكُمْ مِنْ كِتَابٍ وَحِكْمَةٍ ثُمَّ جَاءَكُمْ رَسُولٌ مُصَدِّقٌ لِمَا مَعَكُمْ لَتُؤْمِنُنَّ بِهِ وَلَتَنْصُرُنَّهُ ۚ قَالَ أَأَقْرَرْتُمْ وَأَخَذْتُمْ عَلَىٰ ذَٰلِكُمْ إِصْرِي ۖ قَالُوا أَقْرَرْنَا ۚ قَالَ فَاشْهَدُوا وَأَنَا مَعَكُمْ مِنَ الشَّاهِدِينَ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «መጽሐፍንና ጥበብን ሰጥቻችሁ ከዚያ ከናንተ ጋር ላለው መጽሀፍ የሚያረጋግጥ መልዕክተኛ ቢመጣላችሁ በእርሱ እንድታምኑበት እንድትረዱትም።» ሲል አላህ የነቢያትን ቃል ኪዳን በያዘ ጊዜ (የነበረውን ክስተት ለህዝቦችህ አስታውስ)። «አረጋገጣችሁን? በዚህስ ላይ ቃል ኪዳኔን ያዛችሁን?» አላቸው። እነርሱም «አዎ አረጋገጥን» አሉ። «እንግዲያውስ መስክሩ። እኔም ከናንተ ጋር ከመስካሪዎቹ ነኝ።» አላቸው።

فَمَنْ تَوَلَّىٰ بَعْدَ ذَٰلِكَ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الْفَاسِقُونَ

እናም ከዚህ በኋላ የሸሹ አመጸኞቹ እነርሱ ብቻ ናቸው።

أَفَغَيْرَ دِينِ اللَّهِ يَبْغُونَ وَلَهُ أَسْلَمَ مَنْ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ طَوْعًا وَكَرْهًا وَإِلَيْهِ يُرْجَعُونَ

በሰማያትና በምድር ያሉ ሁሉ በውድም ሆነ በግድ ለእርሱ የታዘዙና ወደ እርሱ የሚመለሱ ሲሆኑ (ከሓዲያን) ከአላህ ሃይማኖት ሌላን ይፈልጋሉን?

قُلْ آمَنَّا بِاللَّهِ وَمَا أُنْزِلَ عَلَيْنَا وَمَا أُنْزِلَ عَلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَمَا أُوتِيَ مُوسَىٰ وَعِيسَىٰ وَالنَّبِيُّونَ مِنْ رَبِّهِمْ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِنْهُمْ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በአላህ አምነናል በእኛም ላይ በተወረደው በቁርኣን (በነብዩ) ኢብራሂም፣ (በነብዩ) ኢስማኢል፣ (በነብዩ) ኢስሀቅ፣ (በነብዩ) የዕቆብና በነገዶች ላይ በተወረደው፣ ለነብዩ ሙሳ ለነብዩ ዒሳና ለነብያትም ሁሉ ከጌታቸው በተሰጠው ሁሉ አምነናል። በእነርሱ መካከል አንድንም አንለይም። እኛ ለእርሱ ብቻ ታዛዦች ነን።» በል።

وَمَنْ يَبْتَغِ غَيْرَ الْإِسْلَامِ دِينًا فَلَنْ يُقْبَلَ مِنْهُ وَهُوَ فِي الْآخِرَةِ مِنَ الْخَاسِرِينَ

ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሁሉ ፈጽሞ ከእርሱ ተቀባይነት የለዉም። እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ አንዱ ነው።

كَيْفَ يَهْدِي اللَّهُ قَوْمًا كَفَرُوا بَعْدَ إِيمَانِهِمْ وَشَهِدُوا أَنَّ الرَّسُولَ حَقٌّ وَجَاءَهُمُ الْبَيِّنَاتُ ۚ وَاللَّهُ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الظَّالِمِينَ

ከእምነታቸውና መልዕክተኛዉም እውነት መሆኑን ከመሰከሩ፤ የተብራሩ አናቅጽም ከመጡላቸው በኋላ የካዱ ሕዝቦችን አላህ እንዴት ያቀናል? አላህ በዳዮችን ሕዝቦች አያቀናምና።

أُولَٰئِكَ جَزَاؤُهُمْ أَنَّ عَلَيْهِمْ لَعْنَةَ اللَّهِ وَالْمَلَائِكَةِ وَالنَّاسِ أَجْمَعِينَ

እነዚያ መሰሎች ቅጣታቸው የአላህ፣ የመላዕክትና የሰዎች ሁሉ እርግማን በእነርሱ ላይ መውረዱ ነው።

خَالِدِينَ فِيهَا لَا يُخَفَّفُ عَنْهُمُ الْعَذَابُ وَلَا هُمْ يُنْظَرُونَ

በውስጧ ዘወታሪዎች ሲሆኑ ቅጣቱም ከእነርሱ ላይ አይቃለልላቸዉም። ጊዜም አይሰጡም።

إِلَّا الَّذِينَ تَابُوا مِنْ بَعْدِ ذَٰلِكَ وَأَصْلَحُوا فَإِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَحِيمٌ

እነዚያ ከዚያ በኋላ ንስሀ የገቡና ስራቸውን ያሳመሩ ሁሉ ሲቀሩ፤ (አላህ እነዚህንማ ይምራቸዋል።) አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና።

إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا بَعْدَ إِيمَانِهِمْ ثُمَّ ازْدَادُوا كُفْرًا لَنْ تُقْبَلَ تَوْبَتُهُمْ وَأُولَٰئِكَ هُمُ الضَّالُّونَ

እነዚያ ከእምነታቸው በኋላ የካዱና ከዚያ ክህደትን በክህደት ላይ የጨመሩ ንሰሃቸው ፈጽሞ ተቀባይነት የለዉም። የተሳሳቱ ማለት እነርሱው ናቸው።

إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا وَمَاتُوا وَهُمْ كُفَّارٌ فَلَنْ يُقْبَلَ مِنْ أَحَدِهِمْ مِلْءُ الْأَرْضِ ذَهَبًا وَلَوِ افْتَدَىٰ بِهِ ۗ أُولَٰئِكَ لَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ وَمَا لَهُمْ مِنْ نَاصِرِينَ

እነዚያ የካዱና በክህደታቸው ላይ እንዳሉ የሞቱ፤ ከእነርሱ አንዳቸው ምድርን የሞላ ወርቅ ቤዛ ቢያቀርብም እንኳ ፈጽሞ ተቀባይነት አያገኝም። እነዚያ ለእነርሱ የሚያሰቃይ ቅጣት አለባቸው። ለእነርሱም (ከዚህ ቅጣት) የሚያድኗቸው ምንም ረዳቶች የሏቸዉም።

لَنْ تَنَالُوا الْبِرَّ حَتَّىٰ تُنْفِقُوا مِمَّا تُحِبُّونَ ۚ وَمَا تُنْفِقُوا مِنْ شَيْءٍ فَإِنَّ اللَّهَ بِهِ عَلِيمٌ

(ሙስሊሞች ሆይ!) ከምትወዱት ነገር እስከምትለግሱ ድረስ የበጎ ስራን ዋጋ (ገነትን) አታገኙም። ከምንም ነገር ብትለግሱም አላህ ያውቀዋል።

كُلُّ الطَّعَامِ كَانَ حِلًّا لِبَنِي إِسْرَائِيلَ إِلَّا مَا حَرَّمَ إِسْرَائِيلُ عَلَىٰ نَفْسِهِ مِنْ قَبْلِ أَنْ تُنَزَّلَ التَّوْرَاةُ ۗ قُلْ فَأْتُوا بِالتَّوْرَاةِ فَاتْلُوهَا إِنْ كُنْتُمْ صَادِقِينَ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ተውራት ከመውረዱ በፊት ኢስራኢል በራሱ ላይ እርም ካደረገው ነገር በስተቀር ምግብ ሁሉ ለኢስራኢል ልጆች የተፈቀደ ነበር። «እውነተኞች ከሆናችሁ እስኪ ተውራትን አምጡና አንብቡት።» በላቸው።

فَمَنِ افْتَرَىٰ عَلَى اللَّهِ الْكَذِبَ مِنْ بَعْدِ ذَٰلِكَ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الظَّالِمُونَ

ከዚህ በኋላ በአላህ ላይ ውሸትን የቀጣጠፉ ሰዎች እነዚያ እነርሱ ብቻ በዳዮች (በደለኞች) ናቸው።

قُلْ صَدَقَ اللَّهُ ۗ فَاتَّبِعُوا مِلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِينَ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ እውነትን ተናገረ። (ትክክለኛ የኢብራሂም ወዳጆች ከሆናችሁ) የኢብራሂምንም መንገድ ቀጥተኛ ሲሆን ተከተሉ። ከአጋሪዎችም አልነበረም።» በላቸው።

إِنَّ أَوَّلَ بَيْتٍ وُضِعَ لِلنَّاسِ لَلَّذِي بِبَكَّةَ مُبَارَكًا وَهُدًى لِلْعَالَمِينَ

ለሰዎች (ማምለኪያ ይሆን ዘንድ በመሬት ላይ) በመጀመሪያ የተሰራው ቤት ብሩክና ለዓለማት ሁሉ መመሪያ ሲሆን ያ በበካህ (በመካ) ያለው ቤት (ካዕባ) ነው።

فِيهِ آيَاتٌ بَيِّنَاتٌ مَقَامُ إِبْرَاهِيمَ ۖ وَمَنْ دَخَلَهُ كَانَ آمِنًا ۗ وَلِلَّهِ عَلَى النَّاسِ حِجُّ الْبَيْتِ مَنِ اسْتَطَاعَ إِلَيْهِ سَبِيلًا ۚ وَمَنْ كَفَرَ فَإِنَّ اللَّهَ غَنِيٌّ عَنِ الْعَالَمِينَ

በውስጡ ግልጽ የሆኑ ተዐምራት አሉበት። የኢብራሂምም መቆሚያ (የነበረው በዉስጡ አለ።) ወደ እርሱ የገባም ሁሉ ሰላም ይሆናል። ወደ እርሱ መሄድን ከሰዎች የቻለ ሁሉ ቤቱን መጎብኘት (ሐጅ ማድረግ) ለአላህ በሰዎች ላይ ግዴታ ነው። በአላህ የካደ (ግን እራሱን እንጂ ማንንም አይጎዳም።) አላህ ከዓለማት ሁሉ የተብቃቃ ነውና።

قُلْ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لِمَ تَكْفُرُونَ بِآيَاتِ اللَّهِ وَاللَّهُ شَهِيدٌ عَلَىٰ مَا تَعْمَلُونَ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! አላህ በምትሰሩት ሁሉ ላይ አዋቂ ሲሆን በአላህ ተዐምራት ለምን ትክዳላችሁ?» በላቸው።

قُلْ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لِمَ تَصُدُّونَ عَنْ سَبِيلِ اللَّهِ مَنْ آمَنَ تَبْغُونَهَا عِوَجًا وَأَنْتُمْ شُهَدَاءُ ۗ وَمَا اللَّهُ بِغَافِلٍ عَمَّا تَعْمَلُونَ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! እናንተ መስካሪዎች ሆናችሁ ከአላህ መንገድ መጥመሟን የምትፈልጉ ስትሆኑ ያመነን ሰው ለምን ትከለክላላችሁ? አላህም ከምትሰሩት ነገር ላይ ሁሉ ዘንጊ አይደለም።» በላቸው።

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِنْ تُطِيعُوا فَرِيقًا مِنَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ يَرُدُّوكُمْ بَعْدَ إِيمَانِكُمْ كَافِرِينَ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእነዚያ መጽሐፍትን ከተሰጡ መካከል ከፊሎቹን ብትታዘዙ ከእምነታችሁ በኋላ ወደ ክህደት ይመልሷችኋል።

وَكَيْفَ تَكْفُرُونَ وَأَنْتُمْ تُتْلَىٰ عَلَيْكُمْ آيَاتُ اللَّهِ وَفِيكُمْ رَسُولُهُ ۗ وَمَنْ يَعْتَصِمْ بِاللَّهِ فَقَدْ هُدِيَ إِلَىٰ صِرَاطٍ مُسْتَقِيمٍ

የአላህ አናቅጽ በእናንተ ላይ እየተነበቡና መልዕክተኛዉም በመካከላችሁ እያለ እንዴት ትክዳላችሁ? በአላህ የሚጠበቅ ሰው ሁሉ ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ተመራ።

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ حَقَّ تُقَاتِهِ وَلَا تَمُوتُنَّ إِلَّا وَأَنْتُمْ مُسْلِمُونَ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ትክክለኛውን ፍራቻ ፍሩት። እናንተም ሙስሊሞች ሆናችሁ እንጂ አትሙቱ።

وَاعْتَصِمُوا بِحَبْلِ اللَّهِ جَمِيعًا وَلَا تَفَرَّقُوا ۚ وَاذْكُرُوا نِعْمَتَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ إِذْ كُنْتُمْ أَعْدَاءً فَأَلَّفَ بَيْنَ قُلُوبِكُمْ فَأَصْبَحْتُمْ بِنِعْمَتِهِ إِخْوَانًا وَكُنْتُمْ عَلَىٰ شَفَا حُفْرَةٍ مِنَ النَّارِ فَأَنْقَذَكُمْ مِنْهَا ۗ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمْ آيَاتِهِ لَعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ

(እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) የአላህን ጠንካራ የእምነት ገመድም ሁላችሁም ያዙ። አትለያዩም። ጠበኞች በነበራችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ የዋለውን የአላህን ጸጋም አስታውሱ። ይሀውም በልቦቻችሁ መካከል አስማማ በጸጋዉም ወንድማማቾች ሆናችሁ። በእሳት ጉድጓድ አፋፍ ላይ የነበራችሁ ስትሆኑ ከእርሷም አዳናችሁ። ወደ ቀጥተኛው መንገድ ትመሩ ዘንድ አላህ ለእናንተ አናቅጽን እንደዚሁ ያብራራል።

وَلْتَكُنْ مِنْكُمْ أُمَّةٌ يَدْعُونَ إِلَى الْخَيْرِ وَيَأْمُرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَيَنْهَوْنَ عَنِ الْمُنْكَرِ ۚ وَأُولَٰئِكَ هُمُ الْمُفْلِحُونَ

(እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ከናንተ መካከል ወደ በጎ ነገር የሚጠሩና በመልካም ስራ የሚያዙ፤ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ቡድኖች ይኑሩ። እነዚያ ከእሳት የሚድኑ እነርሱው ናቸው።

وَلَا تَكُونُوا كَالَّذِينَ تَفَرَّقُوا وَاخْتَلَفُوا مِنْ بَعْدِ مَا جَاءَهُمُ الْبَيِّنَاتُ ۚ وَأُولَٰئِكَ لَهُمْ عَذَابٌ عَظِيمٌ

(እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) እንደነዚያ ግልጽ ተዐምራት ከመጣላቸው በኋላ እንደተለያዩትና እንደተጨቃጨቁት (የመጽሐፉ ባለቤት) ሰዎች አትሁኑ። እነዚያም ለነርሱ ታላቅ ቅጣት አለባቸው።

يَوْمَ تَبْيَضُّ وُجُوهٌ وَتَسْوَدُّ وُجُوهٌ ۚ فَأَمَّا الَّذِينَ اسْوَدَّتْ وُجُوهُهُمْ أَكَفَرْتُمْ بَعْدَ إِيمَانِكُمْ فَذُوقُوا الْعَذَابَ بِمَا كُنْتُمْ تَكْفُرُونَ

ያን ፊቶች የሚያበሩበትና ፊቶች የሚጠቁሩበትን የትንሳኤን ቀን አስታውሱ። እነዚያ ፊቶቻቸው የጠቆሩት ወገኖች «ከእምነታችሁ በኋላ ካዳችሁን? እንግዲያዉስ ትክዱ የነበራችሁትን ነገር ቅጣቱን ቅመሱ።» ይባላሉ።

وَأَمَّا الَّذِينَ ابْيَضَّتْ وُجُوهُهُمْ فَفِي رَحْمَةِ اللَّهِ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ

እነዚያ ፊቶቻቸው ያበሩት ወገኖች ደግሞ በአላህ እዝነት (ገነት) ውስጥ ናቸው። እነርሱ በውስጧ ዘወታሪዎች ናቸው።

تِلْكَ آيَاتُ اللَّهِ نَتْلُوهَا عَلَيْكَ بِالْحَقِّ ۗ وَمَا اللَّهُ يُرِيدُ ظُلْمًا لِلْعَالَمِينَ

እነኚህ ባንተ ላይ በእውነት የምናነባቸው የአላህ አናቅጽ ናቸው። አላህም ለዓለማት በደልን የሚሻ አይደለም።

وَلِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۚ وَإِلَى اللَّهِ تُرْجَعُ الْأُمُورُ

በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለ ሁሉ የአላህ ነው። ነገሮች ሁሉ ወደ አላህ ይመለሳሉ።

كُنْتُمْ خَيْرَ أُمَّةٍ أُخْرِجَتْ لِلنَّاسِ تَأْمُرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَتَنْهَوْنَ عَنِ الْمُنْكَرِ وَتُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ ۗ وَلَوْ آمَنَ أَهْلُ الْكِتَابِ لَكَانَ خَيْرًا لَهُمْ ۚ مِنْهُمُ الْمُؤْمِنُونَ وَأَكْثَرُهُمُ الْفَاسِقُونَ

(ሙስሊሞች ሆይ!) ለሰው ልጆች ከተገለፁት ሕዝቦች ሁሉ በላጭ ሆናችሁ። ይኸዉም በመልካም ነገር ታዛላችሁ። ከመጥፎም ነገር ትከለክላላችሁ። በአላህም አንድነት ታምናላችሁና ነው። የመጽሐፉ ሰዎችም ልክ እንደናንተው ባመኑ ኑሮ ለእነርሱ የተሻለ በሆነ ነበር። ከእነርሱ መካከል ትክክለኛ አማኞችም አሉ። አብዛሀኞቻቸው ግን አመጸኞች ናቸው።

لَنْ يَضُرُّوكُمْ إِلَّا أَذًى ۖ وَإِنْ يُقَاتِلُوكُمْ يُوَلُّوكُمُ الْأَدْبَارَ ثُمَّ لَا يُنْصَرُونَ

(ሙስሊሞች ሆይ!) ማስከፋትን እንጂ ፈጽሞ አይጎዷችሁም። ቢዋጓችሁም ጀርባዎችን ያዞሩላችኋል (ይሸሻሉ)። ከዚያም በምንም ረዳት አያገኙም።

ضُرِبَتْ عَلَيْهِمُ الذِّلَّةُ أَيْنَ مَا ثُقِفُوا إِلَّا بِحَبْلٍ مِنَ اللَّهِ وَحَبْلٍ مِنَ النَّاسِ وَبَاءُوا بِغَضَبٍ مِنَ اللَّهِ وَضُرِبَتْ عَلَيْهِمُ الْمَسْكَنَةُ ۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ كَانُوا يَكْفُرُونَ بِآيَاتِ اللَّهِ وَيَقْتُلُونَ الْأَنْبِيَاءَ بِغَيْرِ حَقٍّ ۚ ذَٰلِكَ بِمَا عَصَوْا وَكَانُوا يَعْتَدُونَ

በየተገኙበት ስፍራ ከአላህ በሆነ ቃልኪዳን ወይም ከሰዎች በሆነ ቃል ኪዳን የተጠበቁ ካልሆኑ በስተቀር በእነርሱ ላይ ውርደት ተጽፎባቸዋል። ከአላህ በሆነ ቁጣ ተመለሱ። ድህነትም በእነርሱ ላይ ተፅፎባቸዋል። ይህ የሆነውም በአላህ ተዐምራት (አናቅጽ) ይክዱ፤ ነቢያትንም ያላ አግባብ ይገድሉ ስለነበሩ ነው። ይህም የሆነው በማመፃቸውና ወሰንን ይተላለፉ ስለነበሩ ነው።

لَيْسُوا سَوَاءً ۗ مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ أُمَّةٌ قَائِمَةٌ يَتْلُونَ آيَاتِ اللَّهِ آنَاءَ اللَّيْلِ وَهُمْ يَسْجُدُونَ

የመጽሐፉ ባለቤቶች ሁሉ እኩል አይደሉም። ከመጽሐፉ ባለቤቶች መካከል ቀጥ ያሉና በሌሊት ሰዓቶች እየሰገዱ የአላህን አናቅጽ የሚያነቡ ሕዝቦችም አሉ።

يُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ وَيَأْمُرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَيَنْهَوْنَ عَنِ الْمُنْكَرِ وَيُسَارِعُونَ فِي الْخَيْرَاتِ وَأُولَٰئِكَ مِنَ الصَّالِحِينَ

በአላህና በመጨረሻዉም ቀን ያምናሉ። በጽድቅም ነገር ያዛሉ። ከመጥፎ ነገርም ይከለክላሉ። ለበጎ ስራዎችም ይጣደፋሉ። እነርሱ ከደጋግ ሰዎች ናቸው።

وَمَا يَفْعَلُوا مِنْ خَيْرٍ فَلَنْ يُكْفَرُوهُ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ بِالْمُتَّقِينَ

ከበጎ የሚሰሩትን አይካዱም። (ውድቅ አይደረግባቸዉም።) አላህ ጥንቁቆቹን ሁሉ አዋቂ ነውና።

إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا لَنْ تُغْنِيَ عَنْهُمْ أَمْوَالُهُمْ وَلَا أَوْلَادُهُمْ مِنَ اللَّهِ شَيْئًا ۖ وَأُولَٰئِكَ أَصْحَابُ النَّارِ ۚ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ

እነዚያ በአላህ የካዱት ገንዘቦቻቸውና ልጆቻቸው ከአላህ ቅጣት ምንንም አያድኗቸዉም። እነዚያም የእሳት ጓዶች ናቸው። እነርሱም በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው።

مَثَلُ مَا يُنْفِقُونَ فِي هَٰذِهِ الْحَيَاةِ الدُّنْيَا كَمَثَلِ رِيحٍ فِيهَا صِرٌّ أَصَابَتْ حَرْثَ قَوْمٍ ظَلَمُوا أَنْفُسَهُمْ فَأَهْلَكَتْهُ ۚ وَمَا ظَلَمَهُمُ اللَّهُ وَلَٰكِنْ أَنْفُسَهُمْ يَظْلِمُونَ

በዚህች በቅርቢቱ ሕይወት የሚለግሱት ነገር ምሳሌው በውስጧ ውርጭ ያለባት ነፋስ ነፍሶቻቸውን የበደሉን ሕዝቦች አዝመራ እንደነካችና እንዳጠፋች ብጤ ነው። አላህም አልበደላቸዉም። ግን እነርሱ ነፍሶቻቸውን በእራሳቸው የሚበድሉ ናቸው እንጂ።

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا بِطَانَةً مِنْ دُونِكُمْ لَا يَأْلُونَكُمْ خَبَالًا وَدُّوا مَا عَنِتُّمْ قَدْ بَدَتِ الْبَغْضَاءُ مِنْ أَفْوَاهِهِمْ وَمَا تُخْفِي صُدُورُهُمْ أَكْبَرُ ۚ قَدْ بَيَّنَّا لَكُمُ الْآيَاتِ ۖ إِنْ كُنْتُمْ تَعْقِلُونَ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሚስጥረኛን (የልብ ወዳጅ) ከእናንተ ሌላ ከሆኑት አታድርጉ። የእናንተን ጉዳይ ከማበላሸት አይቦዝኑላችሁምና። ጉዳታችሁን ይወዳሉና (ይመኛሉ)። ለእናንተ ያላቸው ጥላቻ ከአፎቻቸው ላይ እንኳ ተገለጸ። በልቦቻቸው የሚደብቁት ደግሞ ከዚህ ይበልጥ የከፋ ነው። ልብ የምታደርጉ እንደሆናችሁ ለእናንተ ማብራሪያዎችን በእርግጥ ገለጽን።

هَا أَنْتُمْ أُولَاءِ تُحِبُّونَهُمْ وَلَا يُحِبُّونَكُمْ وَتُؤْمِنُونَ بِالْكِتَابِ كُلِّهِ وَإِذَا لَقُوكُمْ قَالُوا آمَنَّا وَإِذَا خَلَوْا عَضُّوا عَلَيْكُمُ الْأَنَامِلَ مِنَ الْغَيْظِ ۚ قُلْ مُوتُوا بِغَيْظِكُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ عَلِيمٌ بِذَاتِ الصُّدُورِ

እናንተ ትወዷቸዋላችሁ። እነርሱ ግን በፍጹም አይወዷችሁም። እናንተ በሁሉም መጽሐፍት ታምናላችሁ። እነርሱ ግን ባገኟችሁ ጊዜ «አምነናል» ይላሉ። ከናንተ ባገለሉ ጊዜ ግን ከቁጭታቸው የተነሳ በእናንተ ላይ ዐጥቆቻቸውን (ጣቶቻቸውን) ይነክሳሉ። (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በቁጭታችሁ ሙቱ። አላህ ልቦች የቋጠሩትን ሁሉ አዋቂ ነውና።» በላቸው።

إِنْ تَمْسَسْكُمْ حَسَنَةٌ تَسُؤْهُمْ وَإِنْ تُصِبْكُمْ سَيِّئَةٌ يَفْرَحُوا بِهَا ۖ وَإِنْ تَصْبِرُوا وَتَتَّقُوا لَا يَضُرُّكُمْ كَيْدُهُمْ شَيْئًا ۗ إِنَّ اللَّهَ بِمَا يَعْمَلُونَ مُحِيطٌ

ደግ ነገር ብታገኙ ይከፋቸዋል። መጥፎ ነገር ቢደርስባችሁ ግን በሷ ይደሰታሉ። ከታገሳችሁና አላህን ከፈራችሁ ተንኮላቸው ምንም አይጎዳችሁም። አላህ ለሚሰሩት ሁሉ በዕውቀቱ ከባቢ ነውና።

وَإِذْ غَدَوْتَ مِنْ أَهْلِكَ تُبَوِّئُ الْمُؤْمِنِينَ مَقَاعِدَ لِلْقِتَالِ ۗ وَاللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አማኞችን ለውጊያ ስፍራዎች የምታዘጋጅ ሆነህ ከቤተሰብህ በጧት በወጣህ ጊዜ የሆነውን አስታውስ። አላህ ሁሉን ሰሚ ሁሉንም አዋቂ ነውና።

إِذْ هَمَّتْ طَائِفَتَانِ مِنْكُمْ أَنْ تَفْشَلَا وَاللَّهُ وَلِيُّهُمَا ۗ وَعَلَى اللَّهِ فَلْيَتَوَكَّلِ الْمُؤْمِنُونَ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ረዳታቸው ሲሆን ከእናንተ መካከል ሁለት ቡድኖች (ወገኖች) ለመፍራት ባሰቡ ጊዜ የሆነውን አስታውስ። በአላህ ላይ ብቻ አማኞች ይመኩ።

وَلَقَدْ نَصَرَكُمُ اللَّهُ بِبَدْرٍ وَأَنْتُمْ أَذِلَّةٌ ۖ فَاتَّقُوا اللَّهَ لَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ

(እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) በበድር ዘመቻ ዕለት እናንተ ጥቂቶች ሆናችሁ ሳለ አላህ በእርግጥ ረዳችሁ። አላህን ታመሰግኑ ዘንድ ፍሩት።

إِذْ تَقُولُ لِلْمُؤْمِنِينَ أَلَنْ يَكْفِيَكُمْ أَنْ يُمِدَّكُمْ رَبُّكُمْ بِثَلَاثَةِ آلَافٍ مِنَ الْمَلَائِكَةِ مُنْزَلِينَ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለአማኞች (እንዲህ) በምትል ጊዜ የሆነውን አስታውስ: «ጌታችሁ በሶስት ሺ መላዕክት የተወረዱ ሲሆኑ ቢረዳችሁ አይበቃችሁምን?»

بَلَىٰ ۚ إِنْ تَصْبِرُوا وَتَتَّقُوا وَيَأْتُوكُمْ مِنْ فَوْرِهِمْ هَٰذَا يُمْدِدْكُمْ رَبُّكُمْ بِخَمْسَةِ آلَافٍ مِنَ الْمَلَائِكَةِ مُسَوِّمِينَ

«አዎን! ብትታገሱና ብትጠነቀቁ አሁኑኑ በፍጥነት ጠላቶቻችሁ ቢመጡባችሁም ጌታችሁ ምልክት ባላቸው አምስት ሺህ መላዕክት ይረዳችኋል።»

وَمَا جَعَلَهُ اللَّهُ إِلَّا بُشْرَىٰ لَكُمْ وَلِتَطْمَئِنَّ قُلُوبُكُمْ بِهِ ۗ وَمَا النَّصْرُ إِلَّا مِنْ عِنْدِ اللَّهِ الْعَزِيزِ الْحَكِيمِ

አላህ ለእናንተ ብስራትና ልቦቻችሁ በእርሱ እንዲረኩ እንጂ እርዳታውን ለምንም አላደረገዉም። ድልም አሸናፊና ጥበበኛ ከሆነው ከአላህ ዘንድ ብቻ እንጂ ከሌላ ከማንም የሚገኝ አይደለም።

لِيَقْطَعَ طَرَفًا مِنَ الَّذِينَ كَفَرُوا أَوْ يَكْبِتَهُمْ فَيَنْقَلِبُوا خَائِبِينَ

(ድልን ያጎናፀፋችሁ) ከእነዚያ ከካዱት ከፊልን ሊቆርጥ (ሊያጠፋ) ወይም ሊያዋርዳቸውና ያፈሩ ሁነው እንዲመለሱ ነው።

لَيْسَ لَكَ مِنَ الْأَمْرِ شَيْءٌ أَوْ يَتُوبَ عَلَيْهِمْ أَوْ يُعَذِّبَهُمْ فَإِنَّهُمْ ظَالِمُونَ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱ ራሳቸውን በዳዮች ናቸውና አላህ በእነርሱ ላይ ከፈለገም ይቅርታ ቢያደርግ ወይም በጥፋታቸው ቢቀጣቸውም ላንተ በነገሩ ላይ ምንም የለህም።

وَلِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۚ يَغْفِرُ لِمَنْ يَشَاءُ وَيُعَذِّبُ مَنْ يَشَاءُ ۚ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَحِيمٌ

በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለውም ሁሉ የአላህ ብቻ ነው። ለሚፈልገው ሰው ይምራል። የሚፈልገውን ሰው ይቀጣል። አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና።

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَأْكُلُوا الرِّبَا أَضْعَافًا مُضَاعَفَةً ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አራጣን የተነባበሩ እጥፎች ሲሆኑ አትብሉ። ከገሀነም እሳት ትድኑም ዘንድ (አራጣን በመተው) አላህን ፍሩ።

وَاتَّقُوا النَّارَ الَّتِي أُعِدَّتْ لِلْكَافِرِينَ

ያችን ለከሓዲያን የተዘጋጀችውን የገሀነም እሳት ተጠንቀቁ።

وَأَطِيعُوا اللَّهَ وَالرَّسُولَ لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ

(እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ይታዘንላችሁም ዘንድ አላህንና መልዕክተኛውን ታዘዙ።

وَسَارِعُوا إِلَىٰ مَغْفِرَةٍ مِنْ رَبِّكُمْ وَجَنَّةٍ عَرْضُهَا السَّمَاوَاتُ وَالْأَرْضُ أُعِدَّتْ لِلْمُتَّقِينَ

ወደ ጌታችሁ ምህረትና ስፋቷ (ሰባቱ) ሰማያትንና ምድርን ያክል ወደ ሆነችው ገነት አላህን ለሚፈሩ የተዘጋጀች ስትሆን ተቻኮሉ።

الَّذِينَ يُنْفِقُونَ فِي السَّرَّاءِ وَالضَّرَّاءِ وَالْكَاظِمِينَ الْغَيْظَ وَالْعَافِينَ عَنِ النَّاسِ ۗ وَاللَّهُ يُحِبُّ الْمُحْسِنِينَ

ለእነዚያ በድሎትም ሆነ በችግር ጊዜ ለሚለግሱት፤ ቁጭትንም ገቺዎች፤ ለሰዎችም ይቅርታ አድራጊዎች ለሆኑት፤ አላህ በጎ ሰሪዎችን ሁሉ ይወዳልና።

وَالَّذِينَ إِذَا فَعَلُوا فَاحِشَةً أَوْ ظَلَمُوا أَنْفُسَهُمْ ذَكَرُوا اللَّهَ فَاسْتَغْفَرُوا لِذُنُوبِهِمْ وَمَنْ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ إِلَّا اللَّهُ وَلَمْ يُصِرُّوا عَلَىٰ مَا فَعَلُوا وَهُمْ يَعْلَمُونَ

ለእነዚያም መጥፎ ስራን በሰሩ ወይም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ አላህን የሚያስታውሱና ለኃጢአቶቻቸው ምህረትን የሚለምኑ ለሆኑት ተደግሳለች። ከአላህ ሌላ ኃጢአቶችን የሚምር ማን ነው? (አንድም የለም።) በሰሩት ላይ እነርሱ የሚያውቁ ሲሆኑ የማይዘወትሩ ለሆኑት ሁሉ ተደግሳለች።

أُولَٰئِكَ جَزَاؤُهُمْ مَغْفِرَةٌ مِنْ رَبِّهِمْ وَجَنَّاتٌ تَجْرِي مِنْ تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا ۚ وَنِعْمَ أَجْرُ الْعَامِلِينَ

እነዚያ ምንዳቸው ከጌታቸው ምህረትና በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ በስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶችም ናቸው። የመልካም ሰሪዎች ሁሉ ምንዳ የሆነችው ገነት ምንኛ አማረች!

قَدْ خَلَتْ مِنْ قَبْلِكُمْ سُنَنٌ فَسِيرُوا فِي الْأَرْضِ فَانْظُرُوا كَيْفَ كَانَ عَاقِبَةُ الْمُكَذِّبِينَ

(እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ከእናንተ በፊት በእርግጥ ብዙ የአላህ ድንጋጌዎች (በቀደሙት ሕዝቦች ላይ) አልፈዋል። በምድር ላይ ሂዱና ያስተባባዮች ፍፃሜ እንዴት እንደነበረ ተመልከቱ።

هَٰذَا بَيَانٌ لِلنَّاسِ وَهُدًى وَمَوْعِظَةٌ لِلْمُتَّقِينَ

ይህ ቁርኣን ለሰዎች ሁሉ ማብራርያ፤ ለጥንቁቆችም መመሪያና ገሳጭ ነው።

وَلَا تَهِنُوا وَلَا تَحْزَنُوا وَأَنْتُمُ الْأَعْلَوْنَ إِنْ كُنْتُمْ مُؤْمِنِينَ

(እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) እናንተ የበላዮች ናችሁና ትክክለኛ አማኞች እንደሆናችሁ አትድከሙ (አትስነፉ)። አትዘኑም።

إِنْ يَمْسَسْكُمْ قَرْحٌ فَقَدْ مَسَّ الْقَوْمَ قَرْحٌ مِثْلُهُ ۚ وَتِلْكَ الْأَيَّامُ نُدَاوِلُهَا بَيْنَ النَّاسِ وَلِيَعْلَمَ اللَّهُ الَّذِينَ آمَنُوا وَيَتَّخِذَ مِنْكُمْ شُهَدَاءَ ۗ وَاللَّهُ لَا يُحِبُّ الظَّالِمِينَ

አማኞች ሆይ! የመቁሰል ጉዳት ቢያገኛችሁ ሌሎች ህዝቦችም መሰሉ የመቁሰል ጉዳት አግኝቷቸዋል። እንዲሁ ቀናትን በሰዎች መካከል እናፈራርቃቸዋለን። አላህ እነዚያን በትክክል በሱ ያመኑትን ሊለይና ከእናንተም መካከል ሰማዕታትን ሊመርጥ እንዲህ አይነት ቀናት እንዲፈራረቁ ያደርጋል። አላህም በዳዮችን ሁሉ አይወድምና።

وَلِيُمَحِّصَ اللَّهُ الَّذِينَ آمَنُوا وَيَمْحَقَ الْكَافِرِينَ

አላህ እነዚያን በትክክል በእርሱ ያመኑትን ከኃጢአት ሊያጸዳና ከሓዲያንንም ሊያጠፋ ይህንን አደረገ።

أَمْ حَسِبْتُمْ أَنْ تَدْخُلُوا الْجَنَّةَ وَلَمَّا يَعْلَمِ اللَّهُ الَّذِينَ جَاهَدُوا مِنْكُمْ وَيَعْلَمَ الصَّابِرِينَ

(እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) አላህ ከናንተ መካከል እነዚያን የታገሉትንና ታጋሾችን ሳይለይ ገነትን የምትገቡ መሰላችሁን?

وَلَقَدْ كُنْتُمْ تَمَنَّوْنَ الْمَوْتَ مِنْ قَبْلِ أَنْ تَلْقَوْهُ فَقَدْ رَأَيْتُمُوهُ وَأَنْتُمْ تَنْظُرُونَ

በጦርነት ላይ መሞትን ሳታገኙት በፊት የምትመኙት ነበራችሁ። እናንተም በአይናችሁ የምትመለከቱ ስትሆኑ በእርግጥ አያችሁት። (ታዲያ ለምን ሸሻችሁት?)

وَمَا مُحَمَّدٌ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِنْ قَبْلِهِ الرُّسُلُ ۚ أَفَإِنْ مَاتَ أَوْ قُتِلَ انْقَلَبْتُمْ عَلَىٰ أَعْقَابِكُمْ ۚ وَمَنْ يَنْقَلِبْ عَلَىٰ عَقِبَيْهِ فَلَنْ يَضُرَّ اللَّهَ شَيْئًا ۗ وَسَيَجْزِي اللَّهُ الشَّاكِرِينَ

(መልዕክተኛችን) ሙሐመድ ከበፊቱ ብዙ መልዕክተኞች እንዳለፉት የሆነ መልዕክተኛ እንጂ አይደለም። ታዲያ እሱ ቢሞት ወይ ቢገደል ወደ ኋላችሁ ትገለበጣላችሁን? ወደ ኋላው የሚቀለበስም አላህን ምንም አይጎዳም። አላህ አመስጋኞቹን ተገቢዉን ይመነዳልና።

وَمَا كَانَ لِنَفْسٍ أَنْ تَمُوتَ إِلَّا بِإِذْنِ اللَّهِ كِتَابًا مُؤَجَّلًا ۗ وَمَنْ يُرِدْ ثَوَابَ الدُّنْيَا نُؤْتِهِ مِنْهَا وَمَنْ يُرِدْ ثَوَابَ الْآخِرَةِ نُؤْتِهِ مِنْهَا ۚ وَسَنَجْزِي الشَّاكِرِينَ

ማንኛዋም ነፍስ በተወሰነላት ጊዜ በአላህ ፈቃድ ቢሆን እንጂ አትሞትም። የቅርቢቱን ዓለም ምንዳ የሚፈልግን ሁሉ ከእርሷ እንሰጠዋለን። የመጨረሻይቱን ዓለም ምንዳ የሚፈልግንም ከእርሷ እንሰጠዋለን። አመስጋኞችንም በእርግጥ ተገቢውን እንመነዳለን።

وَكَأَيِّنْ مِنْ نَبِيٍّ قَاتَلَ مَعَهُ رِبِّيُّونَ كَثِيرٌ فَمَا وَهَنُوا لِمَا أَصَابَهُمْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَمَا ضَعُفُوا وَمَا اسْتَكَانُوا ۗ وَاللَّهُ يُحِبُّ الصَّابِرِينَ

ከነብያት መካከል ብዙ ሊቃውንት አብረውት የተዋጉ ብዙዎች አሉ። እናም በአላህ መንገድ ለሚደርስባቸው ነገር ምንም አልፈሩም። አልደከሙም። ለጠላት አልተዋረዱም። አላህም ትዕግስተኞቹን ይወዳል።

وَمَا كَانَ قَوْلَهُمْ إِلَّا أَنْ قَالُوا رَبَّنَا اغْفِرْ لَنَا ذُنُوبَنَا وَإِسْرَافَنَا فِي أَمْرِنَا وَثَبِّتْ أَقْدَامَنَا وَانْصُرْنَا عَلَى الْقَوْمِ الْكَافِرِينَ

ንግግራቸዉም «ጌታችን ሆይ! ኃጢአቶቻችንንና በነገራችን ሁሉ ወሰን ማለፋችንን ማርልን። እግሮቻችንንም አጽናልን። በከሓዲያን ሕዝቦች ላይም እርዳን።» ማለታቸው እንጂ ሌላ አልነበረም።

فَآتَاهُمُ اللَّهُ ثَوَابَ الدُّنْيَا وَحُسْنَ ثَوَابِ الْآخِرَةِ ۗ وَاللَّهُ يُحِبُّ الْمُحْسِنِينَ

አላህ የቅርቢቱን ዓለም ምንዳና የመጨረሻይቱን መልካም ምንዳ ሰጣቸው። አላህ በጎ አድራጊዎችን ሁሉ ይወዳልና።

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِنْ تُطِيعُوا الَّذِينَ كَفَرُوا يَرُدُّوكُمْ عَلَىٰ أَعْقَابِكُمْ فَتَنْقَلِبُوا خَاسِرِينَ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እነዚያን በአላህ የካዱትን ብትታዘዙ ወደ ኋላችሁ ይመልሷችኋል። ከከሳሪዎቹም ትሆናላችሁ።

بَلِ اللَّهُ مَوْلَاكُمْ ۖ وَهُوَ خَيْرُ النَّاصِرِينَ

ይልቁን አላህ ብቻ ረዳታችሁ ነው። እርሱ ከረዳቶች ሁሉ በላጭ ነውና።

سَنُلْقِي فِي قُلُوبِ الَّذِينَ كَفَرُوا الرُّعْبَ بِمَا أَشْرَكُوا بِاللَّهِ مَا لَمْ يُنَزِّلْ بِهِ سُلْطَانًا ۖ وَمَأْوَاهُمُ النَّارُ ۚ وَبِئْسَ مَثْوَى الظَّالِمِينَ

በእነዚያ በካዱት ልቦች ውስጥ አላህ በእሱ አስረጂ ያላወረደበትን ነገር በአላህ በማጋራታቸው ምክንያት ፍርሃትን እንጥላለን። መኖሪያቸዉም የገሀነም እሳት ናት። የበዳዮች መኖሪያ የሆነችው ገሀነምም መኖሪያነቷ ምን ትከፋ!

وَلَقَدْ صَدَقَكُمُ اللَّهُ وَعْدَهُ إِذْ تَحُسُّونَهُمْ بِإِذْنِهِ ۖ حَتَّىٰ إِذَا فَشِلْتُمْ وَتَنَازَعْتُمْ فِي الْأَمْرِ وَعَصَيْتُمْ مِنْ بَعْدِ مَا أَرَاكُمْ مَا تُحِبُّونَ ۚ مِنْكُمْ مَنْ يُرِيدُ الدُّنْيَا وَمِنْكُمْ مَنْ يُرِيدُ الْآخِرَةَ ۚ ثُمَّ صَرَفَكُمْ عَنْهُمْ لِيَبْتَلِيَكُمْ ۖ وَلَقَدْ عَفَا عَنْكُمْ ۗ وَاللَّهُ ذُو فَضْلٍ عَلَى الْمُؤْمِنِينَ

በእርግጥ አላህ በፈቃዱ ጠላቶቻችሁን በምትጨፈጭፏቸው ጊዜ ቃልኪዳንን በእርግጥ አረጋገጠላችሁ። የምትወዱትንም ነገር ካሳያችሁ በኋላ በፈራችሁ፣ በትዕዛዙም በተጨቃጨቃችሁና ባመፃችሁም ጊዜ (ግን እርዳታውን ከለከላችሁ)። ከናንተ ውስጥ ቅርቢቱን ዓለም የሚሻ አለ። ከናንተም ውስጥ የመጨረሻይቱን ዓለም የሚሻ አለ። ከዚያም ሊሞክራችሁ ከእነርሱ አዞራችሁ። በእርግጥም ለእናንተ ይቅርታ አደረገላችሁ። አላህ ሁልጊዜም በአማኞች ላይ የችሮታ ባለቤት ነውና።

إِذْ تُصْعِدُونَ وَلَا تَلْوُونَ عَلَىٰ أَحَدٍ وَالرَّسُولُ يَدْعُوكُمْ فِي أُخْرَاكُمْ فَأَثَابَكُمْ غَمًّا بِغَمٍّ لِكَيْلَا تَحْزَنُوا عَلَىٰ مَا فَاتَكُمْ وَلَا مَا أَصَابَكُمْ ۗ وَاللَّهُ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ

(የመልዕክተኛችን ሙሐመድ ባልደረቦች ሆይ!) መልዕክተኛው ከኋላችሁ ሁኖ እየጠራችሁ የማትዞሩ ሆናችሁ በርቀት በምትሸሹ ጊዜ የሆነውን አስታውሱ። ባመለጣችሁ እድልና በደረሰባችሁም ነገር አለማዘንን ሊያስተምራችሁ በሀሳብ ላይ ሀሳብን አደረሰባችሁ። አላህ በምትሰሩት ነገር ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው።

ثُمَّ أَنْزَلَ عَلَيْكُمْ مِنْ بَعْدِ الْغَمِّ أَمَنَةً نُعَاسًا يَغْشَىٰ طَائِفَةً مِنْكُمْ ۖ وَطَائِفَةٌ قَدْ أَهَمَّتْهُمْ أَنْفُسُهُمْ يَظُنُّونَ بِاللَّهِ غَيْرَ الْحَقِّ ظَنَّ الْجَاهِلِيَّةِ ۖ يَقُولُونَ هَلْ لَنَا مِنَ الْأَمْرِ مِنْ شَيْءٍ ۗ قُلْ إِنَّ الْأَمْرَ كُلَّهُ لِلَّهِ ۗ يُخْفُونَ فِي أَنْفُسِهِمْ مَا لَا يُبْدُونَ لَكَ ۖ يَقُولُونَ لَوْ كَانَ لَنَا مِنَ الْأَمْرِ شَيْءٌ مَا قُتِلْنَا هَاهُنَا ۗ قُلْ لَوْ كُنْتُمْ فِي بُيُوتِكُمْ لَبَرَزَ الَّذِينَ كُتِبَ عَلَيْهِمُ الْقَتْلُ إِلَىٰ مَضَاجِعِهِمْ ۖ وَلِيَبْتَلِيَ اللَّهُ مَا فِي صُدُورِكُمْ وَلِيُمَحِّصَ مَا فِي قُلُوبِكُمْ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ بِذَاتِ الصُّدُورِ

ከዚያም ከጭንቅ በኋላ ጸጥታን ከናንተ ከፊሎችን የሚሸፍንን እንቅልፍ በእናንተ ላይ አወረደ። ከፊሎችንም ነፍሶቻቸው በእርግጥ አሳሰቧቸው። እውነት ያልሆነውን የመሀይምነትን መጠራጠር በአላህ ላይ ይጠራጠራሉ። «በነገሩ ላይ ምንም የመወሰን መብት አለን? (የለንም።)» ይላሉ። (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የመወሰን መብት ሁሉ የአላህ ብቻ ነው።» በላቸው። ላንተ ግልጽ የማያደርጉትን በልቦቻቸው ውስጥ ይደብቃሉ። «የመወሰን መብት ቢኖረን ኖሮ በዚህ ቦታ ላይ ባልተገደልን ነበር» ይላሉ። (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በቤታችሁ ውስጥ በሆናችሁም ኖሮ እነዚያ በእነርሱ ላይ መገደል የተጸፈባቸው ወደየመውደቂያቸው በወጡ ነበር።» በላቸው። አላህ (ፍርዱን ሊፈጽምና) በደረቶቻችሁም ውስጥ ያለውን ሊፈትን በልቦቻችሁም ውስጥ ያለውን ነገር ሊገልጽ ይህንን ሰራ። አላህ በደረቶች ውስጥ ያለውን ሁሉ ነገር ሳይቀር አዋቂ ነውና።

إِنَّ الَّذِينَ تَوَلَّوْا مِنْكُمْ يَوْمَ الْتَقَى الْجَمْعَانِ إِنَّمَا اسْتَزَلَّهُمُ الشَّيْطَانُ بِبَعْضِ مَا كَسَبُوا ۖ وَلَقَدْ عَفَا اللَّهُ عَنْهُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ حَلِيمٌ

(የመልዕክተኛችን ባልደረቦች ሆይ!) እነዚያ ሁለቱ ቡድኖች በተገናኙ ቀን ከናንተ የሸሹትን ሰዎች በዚያ በሰሩት ከፊል ምክንያት ያሳሳታቸው ሰይጣን ነው። አላህ ከእነርሱ በእርግጥ ይቅር ብሏል። አላህ መሀሪና ለቅጣት የማይቸኩል ታጋሽ ነውና።

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَكُونُوا كَالَّذِينَ كَفَرُوا وَقَالُوا لِإِخْوَانِهِمْ إِذَا ضَرَبُوا فِي الْأَرْضِ أَوْ كَانُوا غُزًّى لَوْ كَانُوا عِنْدَنَا مَا مَاتُوا وَمَا قُتِلُوا لِيَجْعَلَ اللَّهُ ذَٰلِكَ حَسْرَةً فِي قُلُوبِهِمْ ۗ وَاللَّهُ يُحْيِي وَيُمِيتُ ۗ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ

(እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) እንደነዚያ በአላህ እንደካዱትና ስለ ወንድሞቻቸው በምድር ላይ በተጓዙና ወይም ዘማቾች በሆኑ ጊዜ እኛ ዘንድ በነበሩ ኖሮ ባልሞቱ ባልተገደሉም ነበር እንደሚሉት ሰዎች አትሁኑ። አላህ በልቦቻቸው ውስጥ ጸጸት ያደርግባቸው ዘንድ ይህንን አሉ። አላህ የፈለገውን ሕያው ያደርጋል። የፈለገውን ይገድላልም። አላህ የምትሰሩትን ነገር ሁሉ ተመልካች ነው።

وَلَئِنْ قُتِلْتُمْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ أَوْ مُتُّمْ لَمَغْفِرَةٌ مِنَ اللَّهِ وَرَحْمَةٌ خَيْرٌ مِمَّا يَجْمَعُونَ

(እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) በአላህ መንገድ ላይ ስትዋጉ ብትገደሉ ወይም ብትሞቱ ከአላህ የሆነው ምህረትና እዝነት እነርሱ ከሚሰበስቡት ሀብት ሁሉ በእርግጥ በላጭ ነው።

وَلَئِنْ مُتُّمْ أَوْ قُتِلْتُمْ لَإِلَى اللَّهِ تُحْشَرُونَ

ብትሞቱ ወይም ብትገደሉ ወደ አላህ ብቻ ትሰበሰባላችሁ።

فَبِمَا رَحْمَةٍ مِنَ اللَّهِ لِنْتَ لَهُمْ ۖ وَلَوْ كُنْتَ فَظًّا غَلِيظَ الْقَلْبِ لَانْفَضُّوا مِنْ حَوْلِكَ ۖ فَاعْفُ عَنْهُمْ وَاسْتَغْفِرْ لَهُمْ وَشَاوِرْهُمْ فِي الْأَمْرِ ۖ فَإِذَا عَزَمْتَ فَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُتَوَكِّلِينَ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከአላህ በሆነ እዝነት ለዘብክላቸው። አመለ መጥፎና ልበ ደረቅ በሆንክ ኖሮ ከአጠገብህ በተበተኑ ነበር። ከእነርሱም ጥፋት ይቅር በል። ለእነርሱም ከአላህ ምህረትን ለምንላቸው። በነገሩ ላይ አማክራቸው። ከዚያ ቁርጥ ሀሳብ ባደረግክ ጊዜ በአላህ ላይ ብቻ ተመካ። አላህ በእርሱ ላይ ብቻ ተመኪዎችን ይወዳልና።

إِنْ يَنْصُرْكُمُ اللَّهُ فَلَا غَالِبَ لَكُمْ ۖ وَإِنْ يَخْذُلْكُمْ فَمَنْ ذَا الَّذِي يَنْصُرُكُمْ مِنْ بَعْدِهِ ۗ وَعَلَى اللَّهِ فَلْيَتَوَكَّلِ الْمُؤْمِنُونَ

(ሙስሊሞች ሆይ!) አላህ ከረዳችሁ እናንተን የሚያሸንፍ የለም። እርሱ ካዋረዳችሁ ደግሞ ከእርሱ ማዋረድ በኋላ የሚረዳችሁ ያ ማን ነው? አማኞች በአላህ ላይ ብቻ ይመኩ።

وَمَا كَانَ لِنَبِيٍّ أَنْ يَغُلَّ ۚ وَمَنْ يَغْلُلْ يَأْتِ بِمَا غَلَّ يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۚ ثُمَّ تُوَفَّىٰ كُلُّ نَفْسٍ مَا كَسَبَتْ وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ

የምርኮን ገንዘብ መደበቅ ከነብይ የሚሆን አይደለም። የምርኮን ገንዘብ የሚደብቅም በትንሳኤ ቀን የደበቀውን ነገር ተሸክሞ ይመጣል። ከዚያ ነፍስ ሁሉ የስራዋን ዋጋ ትመነዳለች። እነርሱም አይበደሉም።

أَفَمَنِ اتَّبَعَ رِضْوَانَ اللَّهِ كَمَنْ بَاءَ بِسَخَطٍ مِنَ اللَّهِ وَمَأْوَاهُ جَهَنَّمُ ۚ وَبِئْسَ الْمَصِيرُ

የአላህን ውዴታ የተከተለ ሁሉ የአላህን ቁጣ እንዳተረፈና መኖሪያውም ገሀነም እንደሆነው ነውን? (ገሀነም ) ማረፊያነቷ እጅግ ከፋ!

هُمْ دَرَجَاتٌ عِنْدَ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ بَصِيرٌ بِمَا يَعْمَلُونَ

ሁሉም በአላህ ዘንድ ባለ ልዩ ልዩ ደረጃዎች ናቸው። አላህ የሚሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና።

لَقَدْ مَنَّ اللَّهُ عَلَى الْمُؤْمِنِينَ إِذْ بَعَثَ فِيهِمْ رَسُولًا مِنْ أَنْفُسِهِمْ يَتْلُو عَلَيْهِمْ آيَاتِهِ وَيُزَكِّيهِمْ وَيُعَلِّمُهُمُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَإِنْ كَانُوا مِنْ قَبْلُ لَفِي ضَلَالٍ مُبِينٍ

አላህ በአማኞች ላይ ከመካከላቸው የሆነን፤ በእነርሱም ላይ አናቅጽን የሚያነብ፤ ከርክሰት የሚያጠራቸው፤ መጽሐፍንና ጥበብንም የሚያስተምራቸውን መልዕክተኛ በላከላቸው ጊዜ በእርግጥ ለገሰላቸው። እነርሱም ከዚያ በፊት ግልጽ ስህተት ውስጥ ነበሩ።

أَوَلَمَّا أَصَابَتْكُمْ مُصِيبَةٌ قَدْ أَصَبْتُمْ مِثْلَيْهَا قُلْتُمْ أَنَّىٰ هَٰذَا ۖ قُلْ هُوَ مِنْ عِنْدِ أَنْفُسِكُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

(ሙስሊሞች ሆይ!) እናንተ ያደረሳችሁትን ጥቃት ግማሽ በአገኛችሁ (በደረሰባችሁ) ጊዜ «ይህ ከየት ነው የመጣብን?» አላችሁን? (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እርሱ ከነፍሶቻችሁ ዘንድ ነው።» በላቸው።አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው።

وَمَا أَصَابَكُمْ يَوْمَ الْتَقَى الْجَمْعَانِ فَبِإِذْنِ اللَّهِ وَلِيَعْلَمَ الْمُؤْمِنِينَ

(የመልዕክተኛችን ባልደረቦች ሆይ!) ያ ሁለት ቡድኖች በተጋጠሙ ቀን የደረሰባችሁ በአላህ ፈቃድ ብቻ ነው። የአማኞችን አቋም ሊፈትንና ማንነታቸውን ሊገልጽ ነው።

وَلِيَعْلَمَ الَّذِينَ نَافَقُوا ۚ وَقِيلَ لَهُمْ تَعَالَوْا قَاتِلُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ أَوِ ادْفَعُوا ۖ قَالُوا لَوْ نَعْلَمُ قِتَالًا لَاتَّبَعْنَاكُمْ ۗ هُمْ لِلْكُفْرِ يَوْمَئِذٍ أَقْرَبُ مِنْهُمْ لِلْإِيمَانِ ۚ يَقُولُونَ بِأَفْوَاهِهِمْ مَا لَيْسَ فِي قُلُوبِهِمْ ۗ وَاللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا يَكْتُمُونَ

እነዚያንም የነፈቁትንና «ኑ በአላህ መንገድ ተጋደሉ ወይም ተከላከሉ።» የተባሉትን ሊገልጽ ነው ይህን ያደረገው። አስመሳዮቹም «ውጊያን ብናውቅ ኖሮ በተከተልናችሁ ነበር።» አሉ። እነርሱም ያን ጊዜ ከእምነት ይልቅ ወደ ክህደት የቀረቡ ናቸው። በልቦቻቸው የሌለውን በአፎቻቸው ይናገራሉ። አላህም የሚደብቁትን ሁሉ አዋቂ ነው።

الَّذِينَ قَالُوا لِإِخْوَانِهِمْ وَقَعَدُوا لَوْ أَطَاعُونَا مَا قُتِلُوا ۗ قُلْ فَادْرَءُوا عَنْ أَنْفُسِكُمُ الْمَوْتَ إِنْ كُنْتُمْ صَادِقِينَ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚህ ከትግል ወደ ኋላ የቀሩ ሲሆኑ ለወንድሞቻቸው «እኛን በታዘዙን ኖሮ ባልተገደሉ ነበር።» ያሉ ናቸው። «እውነተኞችም ከሆናችሁ እስቲ ከነፍሶቻችሁ ላይ ሞትን ገፍትሩ።» በላቸው።

وَلَا تَحْسَبَنَّ الَّذِينَ قُتِلُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ أَمْوَاتًا ۚ بَلْ أَحْيَاءٌ عِنْدَ رَبِّهِمْ يُرْزَقُونَ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያንም በአላህ መንገድ የተገደሉትን ሰማዕታት ሙታን አድርገህ አትገምታቸው። በእርግጥ እነርሱ ጌታቸው ዘንድ ሕያው ናቸውና። ከጌታቸው ዘንድም ሲሳይ ይለገሳሉ።

فَرِحِينَ بِمَا آتَاهُمُ اللَّهُ مِنْ فَضْلِهِ وَيَسْتَبْشِرُونَ بِالَّذِينَ لَمْ يَلْحَقُوا بِهِمْ مِنْ خَلْفِهِمْ أَلَّا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ

አላህ ከችሮታው በሰጣቸው ነገር ተደሳቾች (ሲሆኑ ይመገባሉ)። በእነዚያም ከኋላቸው ገና ባልተከተሏቸውም (ባልሞቱትም እንደነርሱው ከተሰው) በእነርሱ ላይ ስጋትም ትካዜም የሌለባቸው ለመሆናቸው ይደሰታሉ።

يَسْتَبْشِرُونَ بِنِعْمَةٍ مِنَ اللَّهِ وَفَضْلٍ وَأَنَّ اللَّهَ لَا يُضِيعُ أَجْرَ الْمُؤْمِنِينَ

በአላህ ጸጋ፤ ችሮታና አላህም የአማኞችን ምንዳ የማያጠፋ በመሆኑም ይደሰታሉ።

الَّذِينَ اسْتَجَابُوا لِلَّهِ وَالرَّسُولِ مِنْ بَعْدِ مَا أَصَابَهُمُ الْقَرْحُ ۚ لِلَّذِينَ أَحْسَنُوا مِنْهُمْ وَاتَّقَوْا أَجْرٌ عَظِيمٌ

እነዚያን የመቁሰል አደጋ ከደረሰባቸው በኋላ ለአላህና ለመልዕክተኛው የታዘዙት ከእነርሱ መካከል በጎ ተግባርን ለሰሩና አላህንም ለፈሩት ሁሉ ታላቅ ምንዳ አለላቸው።

الَّذِينَ قَالَ لَهُمُ النَّاسُ إِنَّ النَّاسَ قَدْ جَمَعُوا لَكُمْ فَاخْشَوْهُمْ فَزَادَهُمْ إِيمَانًا وَقَالُوا حَسْبُنَا اللَّهُ وَنِعْمَ الْوَكِيلُ

እነዚያም ሰዎች ለእነርሱ «ጠላቶች ለእናንተ ጦርን እንደገና አከማችተዋልና ፍሯቸው።» ያሏቸውና ይህም በእምነት ላይ እምነትን የጨመረላቸው ቃላቸዉም «በቂያችን አላህ ነው፤ እርሱም ምን ያምር መጠጊያ ነው!» ያሉ ናቸው።

فَانْقَلَبُوا بِنِعْمَةٍ مِنَ اللَّهِ وَفَضْلٍ لَمْ يَمْسَسْهُمْ سُوءٌ وَاتَّبَعُوا رِضْوَانَ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ ذُو فَضْلٍ عَظِيمٍ

ከዚያም የአላህን ጸጋና ችሮታ ይዘው ምንም ክፉ ነገር ሳይነካቸው በሰላም ተመለሱ። የአላህን ውዴታም ተከተሉ። አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነውና።

إِنَّمَا ذَٰلِكُمُ الشَّيْطَانُ يُخَوِّفُ أَوْلِيَاءَهُ فَلَا تَخَافُوهُمْ وَخَافُونِ إِنْ كُنْتُمْ مُؤْمِنِينَ

ይህ (የሚያስፈራራችሁ) ሰይጣን ብቻ ነው። በወዳጆቹ ያስፈራራችኋል። (አማኞች ሆይ!) የሰይጣንን ወዳጆችን አትፍሯቸው። ትክክለኛ አማኞች ከሆናችሁም እኔን ብቻ ፍሩኝ።

وَلَا يَحْزُنْكَ الَّذِينَ يُسَارِعُونَ فِي الْكُفْرِ ۚ إِنَّهُمْ لَنْ يَضُرُّوا اللَّهَ شَيْئًا ۗ يُرِيدُ اللَّهُ أَلَّا يَجْعَلَ لَهُمْ حَظًّا فِي الْآخِرَةِ ۖ وَلَهُمْ عَذَابٌ عَظِيمٌ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የእነዚያ ወደ ክህደት የሚቻኮሉ ሰዎች አድራጎት (ተግባር) አያሳዝንህ። እነርሱ ፈጽሞ አላህን በምንም አይጎዱትምና። አላህ በመጨረሻይቱ ዓለም ለእነርሱ እድልን ላያደርግ ይሻልና። ለእነርሱም ታላቅ ቅጣት አለባቸው።

إِنَّ الَّذِينَ اشْتَرَوُا الْكُفْرَ بِالْإِيمَانِ لَنْ يَضُرُّوا اللَّهَ شَيْئًا وَلَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ

እነዚያ እምነትን በክህደትን የለወጡ ክፍሎች ሁሉ አላህን በምንም ነገር ፈጽሞ አይጎዱትም። ለእነርሱም አሳማሚ ቅጣት አለባቸው።

وَلَا يَحْسَبَنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا أَنَّمَا نُمْلِي لَهُمْ خَيْرٌ لِأَنْفُسِهِمْ ۚ إِنَّمَا نُمْلِي لَهُمْ لِيَزْدَادُوا إِثْمًا ۚ وَلَهُمْ عَذَابٌ مُهِينٌ

እነዚያ በአላህ የካዱ ሰዎች ሁሉ እነርሱን ማዘግየታችንን ለነፍሶቻቸው ደግ ነገር ነው ብለው አያስቡ። እነርሱን የምናዘገያቸው ኃጢአትን እንዲጨምሩ ብቻ ነውና። ለእነርሱም አዋራጅ ቅጣት አለባቸው።

مَا كَانَ اللَّهُ لِيَذَرَ الْمُؤْمِنِينَ عَلَىٰ مَا أَنْتُمْ عَلَيْهِ حَتَّىٰ يَمِيزَ الْخَبِيثَ مِنَ الطَّيِّبِ ۗ وَمَا كَانَ اللَّهُ لِيُطْلِعَكُمْ عَلَى الْغَيْبِ وَلَٰكِنَّ اللَّهَ يَجْتَبِي مِنْ رُسُلِهِ مَنْ يَشَاءُ ۖ فَآمِنُوا بِاللَّهِ وَرُسُلِهِ ۚ وَإِنْ تُؤْمِنُوا وَتَتَّقُوا فَلَكُمْ أَجْرٌ عَظِيمٌ

(እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) አላህ መጥፎውን ከመልካሙ እስከሚለይ ድረስ አማኞችን እናንተ ባላችሁበት ሁኔታ ላይ የሚተዋቸው አይደለም። አላህም ሩቁን ነገር የሚያሳውቃችሁ አይደለም። ግን አላህ ከመልዕክተኞቹ የሚሻውን ይመርጣል። እናም በአላህና በመልዕክተኞቹም እመኑ። ብታምኑና ብትጠነቀቁ ለእናንተ ታላቅ ምንዳ አለላችሁ።

وَلَا يَحْسَبَنَّ الَّذِينَ يَبْخَلُونَ بِمَا آتَاهُمُ اللَّهُ مِنْ فَضْلِهِ هُوَ خَيْرًا لَهُمْ ۖ بَلْ هُوَ شَرٌّ لَهُمْ ۖ سَيُطَوَّقُونَ مَا بَخِلُوا بِهِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۗ وَلِلَّهِ مِيرَاثُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۗ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرٌ

እነዚያ አላህ ከችሮታው ከሰጣቸው ገንዘብ የሚነፍጉ ሰዎች ንፉግነት ደግ ተግባር አይምሰላቸው። ይልቁንም እርሱ ለእነርሱ መጥፎ ባህሪ ነው። ያንን በእርሱ የነፈጉበት ገንዘብ በትንሳኤ ቀን (እባብ ሆኖ) በአንገታቸው ይጠለቃሉ። የሰማያትና የምድር ውርስ ለአላህ ብቻ ነው። አላህ በምትሰሩት ነገር ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነውና።

لَقَدْ سَمِعَ اللَّهُ قَوْلَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ فَقِيرٌ وَنَحْنُ أَغْنِيَاءُ ۘ سَنَكْتُبُ مَا قَالُوا وَقَتْلَهُمُ الْأَنْبِيَاءَ بِغَيْرِ حَقٍّ وَنَقُولُ ذُوقُوا عَذَابَ الْحَرِيقِ

አላህ የእነዚያን «አላህ ድሃ ነው እኛ ግን ከበርቴዎች ነን።» ያሉትን ሰዎች ቃል በእርግጥ ሰማ። ያንን ያሉትንና ነብያትን ያለ ህግ መግደላቸውንም በእርግጥ እንጽፋለን። «የማቃጠልንም ስቃይ ቅመሱ።» እንላቸዋለን።

ذَٰلِكَ بِمَا قَدَّمَتْ أَيْدِيكُمْ وَأَنَّ اللَّهَ لَيْسَ بِظَلَّامٍ لِلْعَبِيدِ

ያ (ስቃይ) እጆቻችሁ ባሳለፉት ስራና አላህም ለባሮቹ በዳይ ባለመሆኑ ነው።

الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ عَهِدَ إِلَيْنَا أَلَّا نُؤْمِنَ لِرَسُولٍ حَتَّىٰ يَأْتِيَنَا بِقُرْبَانٍ تَأْكُلُهُ النَّارُ ۗ قُلْ قَدْ جَاءَكُمْ رُسُلٌ مِنْ قَبْلِي بِالْبَيِّنَاتِ وَبِالَّذِي قُلْتُمْ فَلِمَ قَتَلْتُمُوهُمْ إِنْ كُنْتُمْ صَادِقِينَ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ ይህን ቃል የተናገሩት: «ለማንኛዉም መልዕክተኛ እሳት የምትበላው ቁርባን እስከሚያመጣልን ድረስ በሱ እንዳናምን አላህ ወደ እኛ አዝዟል።» ያሉ ናቸው። «ብዙ መልዕክተኞች ከእኔ በፊት በግልጽ ተዓምራትና በዚያ ባላችሁት ቁርባን በእርግጥ መጥተውላችኋል። እውነተኞች ከሆናችሁ ታዲያ ለምን ገደላቹኋቸው?» በላቸው።

فَإِنْ كَذَّبُوكَ فَقَدْ كُذِّبَ رُسُلٌ مِنْ قَبْلِكَ جَاءُوا بِالْبَيِّنَاتِ وَالزُّبُرِ وَالْكِتَابِ الْمُنِيرِ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢያስተባብሉህም ካንተ በፊትም በግልጽ ተዐምራት፣ በጽሁፎች፣ በብሩህ መጽሐፍም የመጡ መልዕክተኞችም በእርግጥ (በእነርሱ መሰሎች) ተስተባብለዋል።

كُلُّ نَفْسٍ ذَائِقَةُ الْمَوْتِ ۗ وَإِنَّمَا تُوَفَّوْنَ أُجُورَكُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۖ فَمَنْ زُحْزِحَ عَنِ النَّارِ وَأُدْخِلَ الْجَنَّةَ فَقَدْ فَازَ ۗ وَمَا الْحَيَاةُ الدُّنْيَا إِلَّا مَتَاعُ الْغُرُورِ

ነፍስ ሁሉ ሞትን በእርግጥ ቀማሽ ናት። ምንዳዎቻችሁንም የምትሞሉት በትንሳኤ ቀን ብቻ ነው። ከእሳት እንዲርቅ ተደርጎ ገነት እንዲገባ የተደረገም በእርግጥ ምኞቱን አገኘ። የቅርቢቱ ሕይወት የማታለያ ጥቅም እንጂ ሌላ አይደለችም።

لَتُبْلَوُنَّ فِي أَمْوَالِكُمْ وَأَنْفُسِكُمْ وَلَتَسْمَعُنَّ مِنَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ مِنْ قَبْلِكُمْ وَمِنَ الَّذِينَ أَشْرَكُوا أَذًى كَثِيرًا ۚ وَإِنْ تَصْبِرُوا وَتَتَّقُوا فَإِنَّ ذَٰلِكَ مِنْ عَزْمِ الْأُمُورِ

(እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) በገንዘቦቻችሁና በነፍሶቻችሁ ትፈተናላችሁ። ከእነዚያ ከናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡትም ከእነዚያ በአላህ ካጋሩትም ቡድኖች ብዙ መጥፎ ነገሮችን ትሰማላችሁ። ብትታገሱና ብትጠነቀቁ (በጣም ጥሩ ነው።) ይህ ተግባር ከታላላቅ ነገሮች አንዱ ነው።

وَإِذْ أَخَذَ اللَّهُ مِيثَاقَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ لَتُبَيِّنُنَّهُ لِلنَّاسِ وَلَا تَكْتُمُونَهُ فَنَبَذُوهُ وَرَاءَ ظُهُورِهِمْ وَاشْتَرَوْا بِهِ ثَمَنًا قَلِيلًا ۖ فَبِئْسَ مَا يَشْتَرُونَ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ የእነዚያ መጽሐፍን የተሰጡትን ለሰዎች በእርግጥ «ልታብራሩት እንጂ ላትደብቁት» በማለት የያዘባቸውን ቃል ኪዳን አስታውስ። እናም በጀርባዎቻቸው በኋላ ወረወሩት። በእርሱም ጥቂትን ዋጋ ገዙበት። የሚገዙትም ነገር ከፋ!

لَا تَحْسَبَنَّ الَّذِينَ يَفْرَحُونَ بِمَا أَتَوْا وَيُحِبُّونَ أَنْ يُحْمَدُوا بِمَا لَمْ يَفْعَلُوا فَلَا تَحْسَبَنَّهُمْ بِمَفَازَةٍ مِنَ الْعَذَابِ ۖ وَلَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ

እነዚያን በሰሩት ነገር የሚደሰቱና ባልሰሩትም መመስገንን የሚወዱ ሰዎችን ከቅጣት በመዳን ላይ ናቸው ብለህ አታስባቸው። ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣት አለባቸውና።

وَلِلَّهِ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۗ وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

የሰማያትና የምድር ንግስና ለአላህ ብቻ ነው። አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና።

إِنَّ فِي خَلْقِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَاخْتِلَافِ اللَّيْلِ وَالنَّهَارِ لَآيَاتٍ لِأُولِي الْأَلْبَابِ

በሰማያትና በምድር መፈጠር፤ በሌሊትና በቀንም መተካካት ለባለ አእምሮዎች ሁሉ ታላላቅ ምልክቶች አሉበት።

الَّذِينَ يَذْكُرُونَ اللَّهَ قِيَامًا وَقُعُودًا وَعَلَىٰ جُنُوبِهِمْ وَيَتَفَكَّرُونَ فِي خَلْقِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ رَبَّنَا مَا خَلَقْتَ هَٰذَا بَاطِلًا سُبْحَانَكَ فَقِنَا عَذَابَ النَّارِ

እነርሱም እነዚያ ቆመው ተቀምጠዉም በጎኖቻቸው ተጋድመዉም አላህን የሚያወሱ በሰማያትና በምድር አፈጣጠርም የሚያስተነትኑና (እንዲህም) የሚሉ ናቸው: «ጌታችን ሆይ! ይህን በከንቱ አልፈጠርከዉም ጥራት ይገባህ። ከእሳትም ቅጣት ጠብቀን።

رَبَّنَا إِنَّكَ مَنْ تُدْخِلِ النَّارَ فَقَدْ أَخْزَيْتَهُ ۖ وَمَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ أَنْصَارٍ

«ጌታችን ሆይ! አንተ እሳት የምታስገባው ሰው ሁሉ በእርግጥ አዋረድከው። ለበደለኞች ምንም ረዳቶች የሏቸዉም።

رَبَّنَا إِنَّنَا سَمِعْنَا مُنَادِيًا يُنَادِي لِلْإِيمَانِ أَنْ آمِنُوا بِرَبِّكُمْ فَآمَنَّا ۚ رَبَّنَا فَاغْفِرْ لَنَا ذُنُوبَنَا وَكَفِّرْ عَنَّا سَيِّئَاتِنَا وَتَوَفَّنَا مَعَ الْأَبْرَارِ

«ጌታችን ሆይ! እኛ በጌታችሁ እመኑ በማለት ወደ እምነት የሚጠራን ጠሪ ሰማንና ወዲያዉኑ አመንም። ጌታችን ሆይ! ኃጢአቶቻችንንም ማርልን ክፉ ስራዎቻችንንም አብስልን። ከንጹሆች ሰዎች ጋርም ግደለን።

رَبَّنَا وَآتِنَا مَا وَعَدْتَنَا عَلَىٰ رُسُلِكَ وَلَا تُخْزِنَا يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۗ إِنَّكَ لَا تُخْلِفُ الْمِيعَادَ

«ጌታችን ሆይ! በመልዕክተኞችህ አማካኝነት የሰጠኸንን፤ የገባህልንን የተስፋ ቃል ስጠን። በትንሳኤ ቀንም አታዋርደን። (አታሳፍረን።) አንተ ቀጠሮን አታፈርስምና።»

فَاسْتَجَابَ لَهُمْ رَبُّهُمْ أَنِّي لَا أُضِيعُ عَمَلَ عَامِلٍ مِنْكُمْ مِنْ ذَكَرٍ أَوْ أُنْثَىٰ ۖ بَعْضُكُمْ مِنْ بَعْضٍ ۖ فَالَّذِينَ هَاجَرُوا وَأُخْرِجُوا مِنْ دِيَارِهِمْ وَأُوذُوا فِي سَبِيلِي وَقَاتَلُوا وَقُتِلُوا لَأُكَفِّرَنَّ عَنْهُمْ سَيِّئَاتِهِمْ وَلَأُدْخِلَنَّهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِنْ تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ ثَوَابًا مِنْ عِنْدِ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ عِنْدَهُ حُسْنُ الثَّوَابِ

እናም ጌታቸው «እኔ ከናንተ ውስጥ የወንድንም ሆነ የሴትን መልካም ስራ ወሮታ አላጠፋም። ከፊላችሁ የከፊሉ አካል ነው።» በማለት ልመናቸውን ተቀበላቸው። እነዚያ ለዲን ሲሉ የተሰደዱ፣ ከአገሮቻቸዉም በግፍ የተባረሩ፣ በመንገዴም (ሁከት የደረሰባቸው)፣ የተጠቁ፣ የተጋደሉ እና የተገደሉም ክፉ ስራዎቻቸውን አብስላቸዋለሁ። በስሮቻቸዉም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች አስገባቸዋለሁ። እነርሱም ከአላህ ዘንድ የሆነን ከፍተኛ ምንዳ ይመነዳሉ። አላህ እርሱ ዘንድ መልካም ምንዳ አለና።

لَا يَغُرَّنَّكَ تَقَلُّبُ الَّذِينَ كَفَرُوا فِي الْبِلَادِ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የእነዚያ በአላህ የካዱ ሰዎች በየአገሮች መንፈላሰስ አያታልህ።

مَتَاعٌ قَلِيلٌ ثُمَّ مَأْوَاهُمْ جَهَنَّمُ ۚ وَبِئْسَ الْمِهَادُ

አነስተኛ ጥቅም ነው። ከዚያ መኖሪያቸው ገሀነም ናት። ገሀነም ደግሞ ማረፊያነቷ ምን ትከፋ!

لَٰكِنِ الَّذِينَ اتَّقَوْا رَبَّهُمْ لَهُمْ جَنَّاتٌ تَجْرِي مِنْ تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا نُزُلًا مِنْ عِنْدِ اللَّهِ ۗ وَمَا عِنْدَ اللَّهِ خَيْرٌ لِلْأَبْرَارِ

እነዚያ ጌታቸውን የፈሩት ግን ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች በውስጧ ዘወታሪዎች ሲሆኑ አላህ ዘንድ የተሰጡ መስተንግዶዎች አሏቸው። አላህ ዘንድ ያለውም ምንዳ ለበጎ ሰሪዎች ሁሉ በላጭ ነው።

وَإِنَّ مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ لَمَنْ يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَمَا أُنْزِلَ إِلَيْكُمْ وَمَا أُنْزِلَ إِلَيْهِمْ خَاشِعِينَ لِلَّهِ لَا يَشْتَرُونَ بِآيَاتِ اللَّهِ ثَمَنًا قَلِيلًا ۗ أُولَٰئِكَ لَهُمْ أَجْرُهُمْ عِنْدَ رَبِّهِمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ سَرِيعُ الْحِسَابِ

ከመጽሐፉ ባለቤቶች መካከል አላህን ፈሪዎችና በአላህ አናቅጽም ጥቂትን ዋጋ የማይለውጡ ሲሆኑ በአላህና በዚያ ወደ እናንተ በተወረደው ቁርኣን በዚያም ወደ እነርሱ በተወረዱት ልዩ ልዩ መጽሐፍት የሚያምኑ ሰዎች አሉ። እነዚያ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ተገቢው ምንዳቸው አለላቸው። አላህ ምርመራው ፈጣን ነው።

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اصْبِرُوا وَصَابِرُوا وَرَابِطُوا وَاتَّقُوا اللَّهَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእሳት ቅጣት ትድኑ ዘንድ ታገሱ፣ ተበራቱም፣ በጦር ኬላዎችም ላይ ተጠባበቁ (ዘብ ቁሙ)። አላህንም በትክክል ፍሩ።