Women · an-Nisa' · سورة النساء · 176 ayahs

القرآن الكريمAfrica Academy

بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።

يَا أَيُّهَا النَّاسُ اتَّقُوا رَبَّكُمُ الَّذِي خَلَقَكُمْ مِنْ نَفْسٍ وَاحِدَةٍ وَخَلَقَ مِنْهَا زَوْجَهَا وَبَثَّ مِنْهُمَا رِجَالًا كَثِيرًا وَنِسَاءً ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ الَّذِي تَسَاءَلُونَ بِهِ وَالْأَرْحَامَ ۚ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَلَيْكُمْ رَقِيبًا

እናንተ ሰዎች ሆይ! ያንን ከአንዲት ነፍስ (ከአደም) የፈጠራችሁን፤ ከእርሷም መቀናጆዋን (ሀዋን) የፈጠረውንና ከሁለቱም ብዙ ወንዶችንና ብዙ ሴቶችን የበተነውን ጌታችሁን (አላህን) ፍሩ። ያንንም በእርሱ የምትጠያየቁበትን አላህን (ከሚያስቆጡ) ተግባራትና ዝምድናዎችን (ከመቁረጥ) ተጠንቀቁ። አላህ በእናንተ ላይ ተጠባባቂ ነውና።

وَآتُوا الْيَتَامَىٰ أَمْوَالَهُمْ ۖ وَلَا تَتَبَدَّلُوا الْخَبِيثَ بِالطَّيِّبِ ۖ وَلَا تَأْكُلُوا أَمْوَالَهُمْ إِلَىٰ أَمْوَالِكُمْ ۚ إِنَّهُ كَانَ حُوبًا كَبِيرًا

(እናንተ ኑዛዜ ተቀባዮች ሆይ! ) ለየቲሞች ገንዘቦቻቸውን ስጡ። (ከመሀከሉም) መጥፎውንም በመልካሙ አትለውጡ። ገንዘቦቻቸውን ወደ ገንዘቦቻችሁ (በመቀላቀል) አትብሉ። እርሱ ትልቅ ኃጢአት ነውና።

وَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تُقْسِطُوا فِي الْيَتَامَىٰ فَانْكِحُوا مَا طَابَ لَكُمْ مِنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۖ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَلَّا تَعُولُوا

(እናንተ ሙስሊም ወንዶች ሆይ) በናንተ ስር ያሉት ሴት የቲሞችን በማግባታችሁ አለማስተካከላችሁን ብትፈሩ ከሴቶች መካከል ለእናንተ የመረጣችሁትን (ደስ ያሏችሁን) ሁለት ሁለት ሶስት ሶስትና አራት አራት አግቡ። በሚስቶች መካከል አለማስተካከላችሁን ብትፈሩ ግን አንዲትን ሴት ብቻ ወይም ንብረታችሁ የሆኑት ሴት ባሪያዎችን ብቻ ያዙ። ይህም (ሴትን ልጅ) እንዳትበድሉ በጣም የቀረበ ተግባር ነው።

وَآتُوا النِّسَاءَ صَدُقَاتِهِنَّ نِحْلَةً ۚ فَإِنْ طِبْنَ لَكُمْ عَنْ شَيْءٍ مِنْهُ نَفْسًا فَكُلُوهُ هَنِيئًا مَرِيئًا

ለሴቶች መህሮቻቸውን ደስተኞች ሆናችሁ ስጧቸው። ለእናንተ ከእርሱ የተወሰነን ነገር ራሳቸው ቢለግሱላችሁ ግን በእርካታና በምቾት ሆናችሁ ብሉት (ተጠቀሙበት)።

وَلَا تُؤْتُوا السُّفَهَاءَ أَمْوَالَكُمُ الَّتِي جَعَلَ اللَّهُ لَكُمْ قِيَامًا وَارْزُقُوهُمْ فِيهَا وَاكْسُوهُمْ وَقُولُوا لَهُمْ قَوْلًا مَعْرُوفًا

(ኃላፊዎች ሆይ!) ያን አላህ ለእናንተ መቋቋሚያ (መጠቃቀሚያ) ያደረገላችሁን ገንዘባችሁን (የያዛችሁላቸውን) ለቂሎች (ለአዕምሮ ደካሞች) አትስጧቸው። ከእርሷም መግቧቸው። ከእርሷ አልብሷቸዉም። ለእነርሱም መልካምን ንግግር ተናገሯቸው።

وَابْتَلُوا الْيَتَامَىٰ حَتَّىٰ إِذَا بَلَغُوا النِّكَاحَ فَإِنْ آنَسْتُمْ مِنْهُمْ رُشْدًا فَادْفَعُوا إِلَيْهِمْ أَمْوَالَهُمْ ۖ وَلَا تَأْكُلُوهَا إِسْرَافًا وَبِدَارًا أَنْ يَكْبَرُوا ۚ وَمَنْ كَانَ غَنِيًّا فَلْيَسْتَعْفِفْ ۖ وَمَنْ كَانَ فَقِيرًا فَلْيَأْكُلْ بِالْمَعْرُوفِ ۚ فَإِذَا دَفَعْتُمْ إِلَيْهِمْ أَمْوَالَهُمْ فَأَشْهِدُوا عَلَيْهِمْ ۚ وَكَفَىٰ بِاللَّهِ حَسِيبًا

(ሙስሊሞች ሆይ!) የቲሞችን ለጋብቻ እስከደረሱ ድረስ ፈትኗቸው። ከእነርሱም ብልህነትን ብታውቁ ገንዘቦቻቸውን ስጧቸው። በማባከንና ማደጋቸውን በመሽቀዳደም ገንዘቦቻቸውን አትብሉባቸው። (ከአሳዳጊዎቹ መካከል) ሀብታም የሆነ ሰው ከገንዘቦቻቸው (ቅንጣት ያህል እንኳን ከመቅረብ) ይከልከል። ደሃ የሆነ ሰዉም ቢሆን ለድካሙ ብቻ በአግባቡ ይብላ። ገንዘቦቻቸውን ወደ እነርሱ በሰጣችሁም ጊዜ በእነርሱ ላይ አስመስክሩ። በተጠባባቂነትም አላህ በቂ ነው።

لِلرِّجَالِ نَصِيبٌ مِمَّا تَرَكَ الْوَالِدَانِ وَالْأَقْرَبُونَ وَلِلنِّسَاءِ نَصِيبٌ مِمَّا تَرَكَ الْوَالِدَانِ وَالْأَقْرَبُونَ مِمَّا قَلَّ مِنْهُ أَوْ كَثُرَ ۚ نَصِيبًا مَفْرُوضًا

ለወንዶች ወላጆችና የቅርብ ዘመዶች ሲሞቱ ከተውት (ጥሪት ገንዘብ የውርስ) ድርሻ አላቸው። ለሴቶችም ወላጆችና የቅርብ ዘመዶች ከተውት ከእርሱ ይነስም ይብዛም (የውርስ) ድርሻ አላቸው። ለሁሉም የተወሰነ ድርሻ ተደንግጓል።

وَإِذَا حَضَرَ الْقِسْمَةَ أُولُو الْقُرْبَىٰ وَالْيَتَامَىٰ وَالْمَسَاكِينُ فَارْزُقُوهُمْ مِنْهُ وَقُولُوا لَهُمْ قَوْلًا مَعْرُوفًا

የውርስ ክፍፍልን (ወራሽ ያልሆኑ) የዝምድና ባለቤቶች፤ የቲሞችና ሚስኪኖች በተገኙበት ጊዜ ከእርሱ ለግሱላቸው። መልካምንም ንግግር ተናገሯቸው።

وَلْيَخْشَ الَّذِينَ لَوْ تَرَكُوا مِنْ خَلْفِهِمْ ذُرِّيَّةً ضِعَافًا خَافُوا عَلَيْهِمْ فَلْيَتَّقُوا اللَّهَ وَلْيَقُولُوا قَوْلًا سَدِيدًا

እነዚያ ከኋላቸው ደካማ ዝርያዎችን ቢተው ኖሮ በእነርሱ ላይ ምን ይደርስባቸው ይሆን ብለው የሚሰጉ ሰዎች ሁሉ (በየቲሞችም ላይ) ይህንኑ ይፍሩ። አላህንም ይፍሩ። ትክክለኛንም ቃል ይናገሩ።

إِنَّ الَّذِينَ يَأْكُلُونَ أَمْوَالَ الْيَتَامَىٰ ظُلْمًا إِنَّمَا يَأْكُلُونَ فِي بُطُونِهِمْ نَارًا ۖ وَسَيَصْلَوْنَ سَعِيرًا

እነዚያ የየቲሞችን ገንዘቦች በግፍ የሚበሉ ሁሉ በሆዶቻቸው ውስጥ የሚበሉት እሳትን ብቻ ነው። የገሀነም እሳትንም በእርግጥ ይገባሉ።

يُوصِيكُمُ اللَّهُ فِي أَوْلَادِكُمْ ۖ لِلذَّكَرِ مِثْلُ حَظِّ الْأُنْثَيَيْنِ ۚ فَإِنْ كُنَّ نِسَاءً فَوْقَ اثْنَتَيْنِ فَلَهُنَّ ثُلُثَا مَا تَرَكَ ۖ وَإِنْ كَانَتْ وَاحِدَةً فَلَهَا النِّصْفُ ۚ وَلِأَبَوَيْهِ لِكُلِّ وَاحِدٍ مِنْهُمَا السُّدُسُ مِمَّا تَرَكَ إِنْ كَانَ لَهُ وَلَدٌ ۚ فَإِنْ لَمْ يَكُنْ لَهُ وَلَدٌ وَوَرِثَهُ أَبَوَاهُ فَلِأُمِّهِ الثُّلُثُ ۚ فَإِنْ كَانَ لَهُ إِخْوَةٌ فَلِأُمِّهِ السُّدُسُ ۚ مِنْ بَعْدِ وَصِيَّةٍ يُوصِي بِهَا أَوْ دَيْنٍ ۗ آبَاؤُكُمْ وَأَبْنَاؤُكُمْ لَا تَدْرُونَ أَيُّهُمْ أَقْرَبُ لَكُمْ نَفْعًا ۚ فَرِيضَةً مِنَ اللَّهِ ۗ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَلِيمًا حَكِيمًا

(ሰዎች ሆይ) አላህ በልጆቻችሁ ውርስ (በሚከተለው መልኩ) ያዛችኋል። ለወንዱ የሁለት ሴቶች ድርሻ ያህል አለው። (ሁለት ወይም) ከሁለት በላይ የሆኑ ሴቶች ልጆች ብቻ ወራሽ ቢሆኑ ለእነርሱ (ሟቹ) ከተወው (ሀብት) ከሶስት ሁለት እጁ ያገኛሉ (አላቸው)። አንዲት ሴት ወራሽ ብትሆን ደግሞ ለእርሷ የሀብቱ ግማሽ አላት። ለሟቹ ልጅ ካለው ለአባቱና ለእናቱ ከሁለቱ ለእያንዳንዱ ከስድስት አንድ አላቸው። ለእርሱ ልጅ ባይኖረውና ወላጆቹ ብቻ ቢወርሱት ለእናቱ ሲሶው አላት። ለእርሱም ወንድሞችና እህቶች ቢኖሩት ለእናቱ ከስድስት አንድ አላት። (ይህም ውርስ) የሚከፋፈለው ከተናዘዘው ኑዛዜ ወይም ከእዳው ክፍያ በኋላ ነው። አባቶቻችሁና ልጆቻችሁ ለእናንተ በመጥቀም ማንኛቸው ይበልጥ ቅርብ እንደሆኑ አታውቁም። ይህም ከአላህ የተደነገገ ነው። አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነዉና።

وَلَكُمْ نِصْفُ مَا تَرَكَ أَزْوَاجُكُمْ إِنْ لَمْ يَكُنْ لَهُنَّ وَلَدٌ ۚ فَإِنْ كَانَ لَهُنَّ وَلَدٌ فَلَكُمُ الرُّبُعُ مِمَّا تَرَكْنَ ۚ مِنْ بَعْدِ وَصِيَّةٍ يُوصِينَ بِهَا أَوْ دَيْنٍ ۚ وَلَهُنَّ الرُّبُعُ مِمَّا تَرَكْتُمْ إِنْ لَمْ يَكُنْ لَكُمْ وَلَدٌ ۚ فَإِنْ كَانَ لَكُمْ وَلَدٌ فَلَهُنَّ الثُّمُنُ مِمَّا تَرَكْتُمْ ۚ مِنْ بَعْدِ وَصِيَّةٍ تُوصُونَ بِهَا أَوْ دَيْنٍ ۗ وَإِنْ كَانَ رَجُلٌ يُورَثُ كَلَالَةً أَوِ امْرَأَةٌ وَلَهُ أَخٌ أَوْ أُخْتٌ فَلِكُلِّ وَاحِدٍ مِنْهُمَا السُّدُسُ ۚ فَإِنْ كَانُوا أَكْثَرَ مِنْ ذَٰلِكَ فَهُمْ شُرَكَاءُ فِي الثُّلُثِ ۚ مِنْ بَعْدِ وَصِيَّةٍ يُوصَىٰ بِهَا أَوْ دَيْنٍ غَيْرَ مُضَارٍّ ۚ وَصِيَّةً مِنَ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ حَلِيمٌ

ለእናንተም ሚስቶቻችሁ ከተውት ንብረት ለእነርሱ ልጅ ካልኖራቸው ግማሹ አላችሁ። ለእነርሱም ልጅ ቢኖራቸው ከተውት ሀብት ከአራት አንድ አላችሁ ። (ይህም) በእርሷ ከሚናዘዙባት ኑዛዜ ወይም ከእዳ ክፍያ በኋላ ነው። ለእናንተም ልጅ ከሌላችሁ ከተዋችሁት ንብረት ለእነርሱ (ለሚስቶቻችሁ) አንድ አራተኛ አላቸው። ለእናንተም ልጅ ቢኖራችሁ ከተዋችሁት ንብረት ለእነርሱ (ለሚስቶቻችሁ) ከስምንት አንድ አላቸው። (ይህም) ከምትናዘዙበት ኑዛዜ ወይም ከእዳ ክፍያ በኋላ ነው። ወላጆችም ልጅም የሌለውና የጎን ወራሾች የሚወርሱት ወንድ ወይም ሴት ቢገኝ ለእርሱም (ለሟቹ) ከእናቱ በኩል ብቻ የሆኑ ወንድም ወይም እህት ቢኖሩት ከሁለቱ ለእያንዳንዳቸው ከስድስት አንድ አላቸው። ከአንድ የበዙ ቢሆኑ ደግሞ በሲሶው ላይ ተጋሪዎች ናቸው። ይህም ወራሾቹን የማይጎዳ ሆኖ ከእርሷ ከሚናዘዙባት ኑዛዜ ወይም ከእዳ በኋላ ነው። ከአላህም የሆነን ኑዛዜ ያዛችኋል። አላህ ሁሉን አዋቂና ታጋሽ ነውና።

تِلْكَ حُدُودُ اللَّهِ ۚ وَمَنْ يُطِعِ اللَّهَ وَرَسُولَهُ يُدْخِلْهُ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِنْ تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا ۚ وَذَٰلِكَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ

እነዚህ የአላህ ውሳኔዎች ናቸው። አላህንና መልዕክተኛውን የሚታዘዙ ሰዎች ሁሉ ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ ያስገባቸዋል። ይህም ትልቅ እድል ነው።

وَمَنْ يَعْصِ اللَّهَ وَرَسُولَهُ وَيَتَعَدَّ حُدُودَهُ يُدْخِلْهُ نَارًا خَالِدًا فِيهَا وَلَهُ عَذَابٌ مُهِينٌ

በአላህና በመልዕክተኛው ላይ የሚያምጽ ወሰኖችንም የሚተላለፍ ሁሉ በውስጧ ዘውታሪ ሲሆን ወደ ገሀነም እሳት ያስገባዋል። ለእርሱም አዋራጅ ቅጣት አለበት።

وَاللَّاتِي يَأْتِينَ الْفَاحِشَةَ مِنْ نِسَائِكُمْ فَاسْتَشْهِدُوا عَلَيْهِنَّ أَرْبَعَةً مِنْكُمْ ۖ فَإِنْ شَهِدُوا فَأَمْسِكُوهُنَّ فِي الْبُيُوتِ حَتَّىٰ يَتَوَفَّاهُنَّ الْمَوْتُ أَوْ يَجْعَلَ اللَّهُ لَهُنَّ سَبِيلًا

እነዚያ ከሴቶቻችሁ መካከል ዝሙትን የሚሰሩ በእነርሱ ላይ ከናንተ የሆነን አራት ታማኝ ወንዶችን አስመስክሩባቸው። ከመሰከሩባቸዉም ሞት እስከሚደርስባቸው ወይም አላህ ለእነርሱ ሌላ መንገድን እስከሚያደርግ ድረስ በቤቶች ውስጥ ያዟቸው (እሰሯቸው።)

وَاللَّذَانِ يَأْتِيَانِهَا مِنْكُمْ فَآذُوهُمَا ۖ فَإِنْ تَابَا وَأَصْلَحَا فَأَعْرِضُوا عَنْهُمَا ۗ إِنَّ اللَّهَ كَانَ تَوَّابًا رَحِيمًا

እነዚያ ከእናንተ ውስጥ ዝሙትን የሚሰሩትን ሁለቱን አሰቃዩዋቸው (በሚገባ ቅጧቸው)። ቢጸጸቱና ስራቸውን ቢያሳምሩ ግን እነርሱን ተዋቸው (አታሰቃዩዋቸው።) አላህ ጸጸትን ተቀባይና አዛኝ ነውና።

إِنَّمَا التَّوْبَةُ عَلَى اللَّهِ لِلَّذِينَ يَعْمَلُونَ السُّوءَ بِجَهَالَةٍ ثُمَّ يَتُوبُونَ مِنْ قَرِيبٍ فَأُولَٰئِكَ يَتُوبُ اللَّهُ عَلَيْهِمْ ۗ وَكَانَ اللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمًا

ጸጸትን መቀበል ከአላህ በኩል ለእነዚያ ኃጢአትን በአላዋቂነት (በስንፍና) ለሚሰሩና ከዚያም ወዲያውኑ ለሚጸጸቱ ነው። እነዚያንማ አላህ ከእነርሱ ጸጸትን ይቀበላል። አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና።

وَلَيْسَتِ التَّوْبَةُ لِلَّذِينَ يَعْمَلُونَ السَّيِّئَاتِ حَتَّىٰ إِذَا حَضَرَ أَحَدَهُمُ الْمَوْتُ قَالَ إِنِّي تُبْتُ الْآنَ وَلَا الَّذِينَ يَمُوتُونَ وَهُمْ كُفَّارٌ ۚ أُولَٰئِكَ أَعْتَدْنَا لَهُمْ عَذَابًا أَلِيمًا

ጸጸትን መቀበል ለእነዚያ ኃጢአቶችን ለሚሰሩና ልክ ሞት በመጣባቸው ጊዜ «አሁን ተጸጸትኩ።» ለሚሉና ለእነዚያም ከሓዲያን ሆነው ለሚሞቱ አይደለም። ለእነርሱማ አሳማሚን ቅጣት አዘጋጅተናል።

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا يَحِلُّ لَكُمْ أَنْ تَرِثُوا النِّسَاءَ كَرْهًا ۖ وَلَا تَعْضُلُوهُنَّ لِتَذْهَبُوا بِبَعْضِ مَا آتَيْتُمُوهُنَّ إِلَّا أَنْ يَأْتِينَ بِفَاحِشَةٍ مُبَيِّنَةٍ ۚ وَعَاشِرُوهُنَّ بِالْمَعْرُوفِ ۚ فَإِنْ كَرِهْتُمُوهُنَّ فَعَسَىٰ أَنْ تَكْرَهُوا شَيْئًا وَيَجْعَلَ اللَّهُ فِيهِ خَيْرًا كَثِيرًا

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሴቶችን ያስገደዳችሁ ሆናችሁ ልትወርሱና ግልጽ የሆነ መጥፎ ስራ ካልሰሩ በስተቀር ከሰጣችኋቸው ከፊሉን ልትወስዱባቸውና ልታጉላሏዋቸው አይፈቀድላችሁም። በመልካም ተኗኗሯቸው። ብትጠሏቸዉም እንኳን ታገሱ። አንድ ነገር ብትጠሉትም አላህ በእርሱ ዉስጥ ብዙ ደግ ነገሮችን ሊያደርግላችሁ ይችላልና።

وَإِنْ أَرَدْتُمُ اسْتِبْدَالَ زَوْجٍ مَكَانَ زَوْجٍ وَآتَيْتُمْ إِحْدَاهُنَّ قِنْطَارًا فَلَا تَأْخُذُوا مِنْهُ شَيْئًا ۚ أَتَأْخُذُونَهُ بُهْتَانًا وَإِثْمًا مُبِينًا

(ባሎች ሆይ!) በሚስት ቦታ ሌላ ሚስትን ለመለወጥ ብትፈልጉ (ለምትፈታው ሴት ቀደም ሲል) ብዙን ገንዘብ የሰጣችኋት እንደሆነ ከእርሷ ምንንም አትውሰዱባት። በመበደልና ግልጽ በሆነ ኃጢአት ትወስዱታላችሁን?

وَكَيْفَ تَأْخُذُونَهُ وَقَدْ أَفْضَىٰ بَعْضُكُمْ إِلَىٰ بَعْضٍ وَأَخَذْنَ مِنْكُمْ مِيثَاقًا غَلِيظًا

ከፊላችሁ ወደ ከፊሉ የደረሰ ሲሆንና ከናንተ ላይም (ሴቶች) የጠበቀ ቃል ኪዳንን የያዙባችሁ ሲሆኑ እንዴት ትወስዱታላችሁ?

وَلَا تَنْكِحُوا مَا نَكَحَ آبَاؤُكُمْ مِنَ النِّسَاءِ إِلَّا مَا قَدْ سَلَفَ ۚ إِنَّهُ كَانَ فَاحِشَةً وَمَقْتًا وَسَاءَ سَبِيلًا

(ወንዶች ሆይ!) ከሴቶች መካከል አባቶቻችሁ ያገቧቸውን አታግቡ። ያለፈው ሲቀር። እርሱ መጥፎና የተጠላ ስራ ነውና። መንገድነቱም ከፋ።

حُرِّمَتْ عَلَيْكُمْ أُمَّهَاتُكُمْ وَبَنَاتُكُمْ وَأَخَوَاتُكُمْ وَعَمَّاتُكُمْ وَخَالَاتُكُمْ وَبَنَاتُ الْأَخِ وَبَنَاتُ الْأُخْتِ وَأُمَّهَاتُكُمُ اللَّاتِي أَرْضَعْنَكُمْ وَأَخَوَاتُكُمْ مِنَ الرَّضَاعَةِ وَأُمَّهَاتُ نِسَائِكُمْ وَرَبَائِبُكُمُ اللَّاتِي فِي حُجُورِكُمْ مِنْ نِسَائِكُمُ اللَّاتِي دَخَلْتُمْ بِهِنَّ فَإِنْ لَمْ تَكُونُوا دَخَلْتُمْ بِهِنَّ فَلَا جُنَاحَ عَلَيْكُمْ وَحَلَائِلُ أَبْنَائِكُمُ الَّذِينَ مِنْ أَصْلَابِكُمْ وَأَنْ تَجْمَعُوا بَيْنَ الْأُخْتَيْنِ إِلَّا مَا قَدْ سَلَفَ ۗ إِنَّ اللَّهَ كَانَ غَفُورًا رَحِيمًا

(ወንዶች ሆይ!) እናቶቻችሁ፤ ሴት ልጆቻችሁ፤ እህቶቻችሁ፤ አክስቶቻችሁ (የአባቶቻችሁ እህቶች)፣ አክስቶቻችሁ (የእናቶቻችሁ እህቶች)፤ የወንድም ሴት ልጆች፤ የእህት ሴት ልጆች፤ እነዚያም ያጠቧችሁ የጡት እናቶቻችሁ፤ የጡት እህቶቻችሁ፤ የሚስቶቻችሁ እናቶች፤ እነዚያም ከጉያዎቻችሁ ያሉት የእነዚያ ግብረ ስጋ ግንኙነት የፈጸማችሁባቸው ሚስቶቻችሁ ሴት ልጆች ልታገቧቸው በእናንተ ላይ እርም ተደረጉባችሁ። ግብረ ስጋ ግንኙነት ያልፈጸማችሁባቸው የሚስቶቻችሁ ሴት ልጆቻቸውን ብታገቡ ግን በእናንተ ላይ ኃጢአት የለባችሁም። የእነዚያ ከጀርባዎቻችሁ የሆኑት ወንዶች ልጆቻችሁ ሚስቶችም ሁለት እህትማማቾችን በአንድ መሰብሰብም እንደዚሁ እርም ነው። ከዚህ በፊት ያለፈው ሲቀር። እርሱንስ ተምራችኋል። አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና።

وَالْمُحْصَنَاتُ مِنَ النِّسَاءِ إِلَّا مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۖ كِتَابَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ ۚ وَأُحِلَّ لَكُمْ مَا وَرَاءَ ذَٰلِكُمْ أَنْ تَبْتَغُوا بِأَمْوَالِكُمْ مُحْصِنِينَ غَيْرَ مُسَافِحِينَ ۚ فَمَا اسْتَمْتَعْتُمْ بِهِ مِنْهُنَّ فَآتُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ فَرِيضَةً ۚ وَلَا جُنَاحَ عَلَيْكُمْ فِيمَا تَرَاضَيْتُمْ بِهِ مِنْ بَعْدِ الْفَرِيضَةِ ۚ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَلِيمًا حَكِيمًا

ባል ያገቡ ሴቶችም በጦርነት እጆቻችሁ በምርኮ የያዟቸው ሲቀሩ (በእናንተ ላይ እርም ናቸው)። ይህን ህግ አላህ በእናንተ ላይ ደነገገ። ከነዚህ ከተከለከሉት ሌላ ጥብቆች ሆናችሁና ዝሙተኞች ሳትሆኑ በገንዘባችሁ ጋብቻን ልትፈልጉ ለእናንተ ተፈቀደ። እናም ከእነርሱም መገናኘት የተጠቀማችሁባቸውን ሴቶች መህሮቻቸውን ልትሰጧቸው ግዴታ ነው። ከመወሰን በኋላ በተስማማችሁበት ነገር በእናንተ ላይ ኃጢአት የለም። አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና።

وَمَنْ لَمْ يَسْتَطِعْ مِنْكُمْ طَوْلًا أَنْ يَنْكِحَ الْمُحْصَنَاتِ الْمُؤْمِنَاتِ فَمِنْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ مِنْ فَتَيَاتِكُمُ الْمُؤْمِنَاتِ ۚ وَاللَّهُ أَعْلَمُ بِإِيمَانِكُمْ ۚ بَعْضُكُمْ مِنْ بَعْضٍ ۚ فَانْكِحُوهُنَّ بِإِذْنِ أَهْلِهِنَّ وَآتُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ بِالْمَعْرُوفِ مُحْصَنَاتٍ غَيْرَ مُسَافِحَاتٍ وَلَا مُتَّخِذَاتِ أَخْدَانٍ ۚ فَإِذَا أُحْصِنَّ فَإِنْ أَتَيْنَ بِفَاحِشَةٍ فَعَلَيْهِنَّ نِصْفُ مَا عَلَى الْمُحْصَنَاتِ مِنَ الْعَذَابِ ۚ ذَٰلِكَ لِمَنْ خَشِيَ الْعَنَتَ مِنْكُمْ ۚ وَأَنْ تَصْبِرُوا خَيْرٌ لَكُمْ ۗ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَحِيمٌ

(ወንዶች ሆይ!) ከናንተ መካከል ጥብቆች ምዕመናትን ለማግባት ሀብትን ያልቻለ ሰው እጆቻችሁ ንብረት ካደረጓቸው ከምዕመናት መካከል ወጣቶቻችሁን አገልጋዮች የመረጠውን ያግባ። አላህ የውስጥ እምነታችሁን ምንነት አዋቂ ነውና። ከፊላችሁ ከከፊሉ የተገኘ ነው። ባሮችንም ቢሆን እንደዚሁ በአሳዳሪዎቻቸው ፈቃድ ብቻ አግቧቸው። መህሮቻቸውንም በመልካም መንገድ ስጧቸው። ጥብቆች ሆነው ዝሙተኛ ያልሆኑ የስርቆሽ ወዳጅንም ያልያዙ እንደሆኑ አግቧቸው። በማግባት በተጠበቁም ጊዜ መጥፎን ስራ ቢሰሩ በእነርሱ ላይ የተደነገገው ቅጣት በነፃዎቹ ላይ ከተደነገገው ቅጣት ግማሹ ቅጣት አለባቸው። ያ ከናንተ መካከል ዝሙትን ለፈራ ብቻ ነው። መታገሳችሁ የተሻለ ነው። አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና።

يُرِيدُ اللَّهُ لِيُبَيِّنَ لَكُمْ وَيَهْدِيَكُمْ سُنَنَ الَّذِينَ مِنْ قَبْلِكُمْ وَيَتُوبَ عَلَيْكُمْ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ

(አማኞች ሆይ!) አላህ የሃይማኖታችሁን ህግጋት ሊያብራራላችሁ፤ ከናንተ በፊትም የነበሩትን ነብያት ፈለጎች ሊመራችሁ፤ በእናንተም ላይ ጸጸትን ሊቀበል ይሻል። አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው።

وَاللَّهُ يُرِيدُ أَنْ يَتُوبَ عَلَيْكُمْ وَيُرِيدُ الَّذِينَ يَتَّبِعُونَ الشَّهَوَاتِ أَنْ تَمِيلُوا مَيْلًا عَظِيمًا

አላህ በእናንተ ላይ ጸጸትን ሊቀበል ይሻል። እነዚያ ፍላጎታቸውን የሚከተሉ ግን ከእውነት ትልቅን መዘንበል እንድትዘነበሉ ይፈልጋሉ።

يُرِيدُ اللَّهُ أَنْ يُخَفِّفَ عَنْكُمْ ۚ وَخُلِقَ الْإِنْسَانُ ضَعِيفًا

አላህ ከናንተ ሊያቃልልላችሁ ይሻል። ሰው ደካማ ሆኖ የተፈጠረ ነውና።

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَأْكُلُوا أَمْوَالَكُمْ بَيْنَكُمْ بِالْبَاطِلِ إِلَّا أَنْ تَكُونَ تِجَارَةً عَنْ تَرَاضٍ مِنْكُمْ ۚ وَلَا تَقْتُلُوا أَنْفُسَكُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ كَانَ بِكُمْ رَحِيمًا

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ገንዘቦቻችሁን በመካከላችሁ ያለ አግባብ አትብሉ። በእናንተ መካከል በመስማማት የሆነችውን ንግድ ካልሆነች በስተቀር (እሷን ግን ብሉ) ። ነፍሶቻችሁን በራሳችሁ አትግደሉ። አላህ ለእናንተ አዛኝ ነውና።

وَمَنْ يَفْعَلْ ذَٰلِكَ عُدْوَانًا وَظُلْمًا فَسَوْفَ نُصْلِيهِ نَارًا ۚ وَكَانَ ذَٰلِكَ عَلَى اللَّهِ يَسِيرًا

ወሰን በማለፍ እና በመበደል ይህን የሰራ ሁሉ እሳት እናስገባዋለን። ይህም በአላህ ላይ ገር ነውና።

إِنْ تَجْتَنِبُوا كَبَائِرَ مَا تُنْهَوْنَ عَنْهُ نُكَفِّرْ عَنْكُمْ سَيِّئَاتِكُمْ وَنُدْخِلْكُمْ مُدْخَلًا كَرِيمًا

(አማኞች ሆይ!) ከተከለከላችሁት ወንጀሎች መካከል ታላላቆችን ብትርቁ ትናንሽ ኃጢአቶቻችሁን እናብስላችኋለን። የተከበረውንም መግቢያ (ገነት) እናስገባችኋለን።

وَلَا تَتَمَنَّوْا مَا فَضَّلَ اللَّهُ بِهِ بَعْضَكُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ ۚ لِلرِّجَالِ نَصِيبٌ مِمَّا اكْتَسَبُوا ۖ وَلِلنِّسَاءِ نَصِيبٌ مِمَّا اكْتَسَبْنَ ۚ وَاسْأَلُوا اللَّهَ مِنْ فَضْلِهِ ۗ إِنَّ اللَّهَ كَانَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمًا

አላህ ከፊላችሁን በከፊሉ ያበለጠበትን ጸጋ አትመኙ። ለወንዶችም ከሰሩት ስራ እድል አለላቸው። ለሴቶችም ከሰሩት ስራ እንዲሁ እድል አለላቸው። አላህን ከችሮታው ለምኑት። አላህ በሁሉ ነገር አዋቂ ነውና።

وَلِكُلٍّ جَعَلْنَا مَوَالِيَ مِمَّا تَرَكَ الْوَالِدَانِ وَالْأَقْرَبُونَ ۚ وَالَّذِينَ عَقَدَتْ أَيْمَانُكُمْ فَآتُوهُمْ نَصِيبَهُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ شَهِيدًا

ለሁላችሁም ወላጆችና የቅርብ ዘመዶች ከተውት ሀብት ወራሾችን አድርገናል። እነዚያንም (ለመረዳዳትና ለመዋረስ) በመሐላዎቻችሁ የተዋዋላችኋቸውን (ከእርዳታ፣ ከምክርና ከኑዛዜ) ድርሻቸውን ስጧቸው። አላህ በነገሩ ሁሉ አዋቂ (መስካሪ) ነው።

الرِّجَالُ قَوَّامُونَ عَلَى النِّسَاءِ بِمَا فَضَّلَ اللَّهُ بَعْضَهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ وَبِمَا أَنْفَقُوا مِنْ أَمْوَالِهِمْ ۚ فَالصَّالِحَاتُ قَانِتَاتٌ حَافِظَاتٌ لِلْغَيْبِ بِمَا حَفِظَ اللَّهُ ۚ وَاللَّاتِي تَخَافُونَ نُشُوزَهُنَّ فَعِظُوهُنَّ وَاهْجُرُوهُنَّ فِي الْمَضَاجِعِ وَاضْرِبُوهُنَّ ۖ فَإِنْ أَطَعْنَكُمْ فَلَا تَبْغُوا عَلَيْهِنَّ سَبِيلًا ۗ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَلِيًّا كَبِيرًا

ወንዶች ለሴቶች ቋሚና የበላይ አስተዳዳሪዎች ናቸው። አላህ ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ በማብለጡና ወንዶች ከገንዘቦቻቸው ለሴቶች በመስጠታቸው ምክኒያት ነው። መልካሞቹ ሴቶች ማለት ለባሎቻቸው ታዛዦች፤ አላህ ባስጠበቀው ነገር ከባሎቻቸው ሩቅ የሆነውን ጠባቂዎች ናቸው። እነዚያን ማመፃቸውን የምትፈሩትን ሴቶች መጀመሪያ ገስጿቸው። ከዚያም በመኝታቸው ተለዩዋቸው። ከዚያም (በአካሎቻቸው ላይ ጉዳት ሳታደርሱ) ምቷቸው። ከታዘዟችሁ ለመጨቆን ስትሉ በእነርሱ ላይ መንገድን አትፈልጉ። አላህ ከሁሉም በላይና ታላቅ ነውና።

وَإِنْ خِفْتُمْ شِقَاقَ بَيْنِهِمَا فَابْعَثُوا حَكَمًا مِنْ أَهْلِهِ وَحَكَمًا مِنْ أَهْلِهَا إِنْ يُرِيدَا إِصْلَاحًا يُوَفِّقِ اللَّهُ بَيْنَهُمَا ۗ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَلِيمًا خَبِيرًا

በመካከላቸውም ጭቅጭቅ መኖሩን ብትፈሩ (ብታውቁ) ከቤተሰቡ አንድ ሸምጋይን ከቤተሰቦቿም አንድ ሸምጋይን ላኩ። ሁለቱም እርቅን ቢሹ አላህ በመካከላቸው ያስማማቸዋል። አላህ ግልጽንም ሆነ ውስጥንም አዋቂ ነውና።

وَاعْبُدُوا اللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا ۖ وَبِالْوَالِدَيْنِ إِحْسَانًا وَبِذِي الْقُرْبَىٰ وَالْيَتَامَىٰ وَالْمَسَاكِينِ وَالْجَارِ ذِي الْقُرْبَىٰ وَالْجَارِ الْجُنُبِ وَالصَّاحِبِ بِالْجَنْبِ وَابْنِ السَّبِيلِ وَمَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ مَنْ كَانَ مُخْتَالًا فَخُورًا

አላህን ተገዙ። በእርሱ ምንንም አታጋሩ። ለወላጆች፣ ለቅርብ ዝምድና ባለቤቶች፣ ለየቲሞች፣ ለምስኪኖች፣ ለቅርብ ጎረቤት፣ ለሩቅ ጎረቤት፣ ለጎን ባልደረባ፣ ለመንገደኛ፣ እጆቻችሁ ንብረት ላደረጓቸው ባሮች መልካምን ስሩ። አላህ ኩራተኞችንና ጉረኞችን አይወድምና።

الَّذِينَ يَبْخَلُونَ وَيَأْمُرُونَ النَّاسَ بِالْبُخْلِ وَيَكْتُمُونَ مَا آتَاهُمُ اللَّهُ مِنْ فَضْلِهِ ۗ وَأَعْتَدْنَا لِلْكَافِرِينَ عَذَابًا مُهِينًا

እነዚያ የሚሰስቱ ንፉጎችና ሰዎችንም በመሰሰት (በንፍግና) የሚያዝዙ አላህ ከችሮታው የሰጣቸውን ጸጋ የሚደብቁ (ብርቱን ቅጣት ይቀጣቸዋል)። ለከሓዲያንም አዋራጅን ቅጣት አዘጋጅተናል።

وَالَّذِينَ يُنْفِقُونَ أَمْوَالَهُمْ رِئَاءَ النَّاسِ وَلَا يُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَلَا بِالْيَوْمِ الْآخِرِ ۗ وَمَنْ يَكُنِ الشَّيْطَانُ لَهُ قَرِينًا فَسَاءَ قَرِينًا

እነዚያ ለሰዎች ይዩልን ሲሉ ገንዘቦቻቸውን የሚሰጡ በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የማያምኑ (ይቀጣሉ)። ሰይጣንም የእሱ ጓደኛው የሆነለት ሁሉ ጓደኛነቱ ከፋ!

وَمَاذَا عَلَيْهِمْ لَوْ آمَنُوا بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ وَأَنْفَقُوا مِمَّا رَزَقَهُمُ اللَّهُ ۚ وَكَانَ اللَّهُ بِهِمْ عَلِيمًا

በአላህና በመጨረሻው ቀን ባመኑና አላህ ከሰጣቸዉም ሲሳይ በለገሱ ኖሮ በእነርሱ ላይ ምን ጉዳት ነበረ? አላህ በእነርሱ ሁኔታ አዋቂ ነውና።

إِنَّ اللَّهَ لَا يَظْلِمُ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ ۖ وَإِنْ تَكُ حَسَنَةً يُضَاعِفْهَا وَيُؤْتِ مِنْ لَدُنْهُ أَجْرًا عَظِيمًا

አላህ የብናኝን ክብደት ያህል እንኳን አይበድልም። መልካም ስራ ብትሆንም ይደራርባታል። ከእርሱም ዘንድ ታላቅን ምንዳ ይሰጣል።

فَكَيْفَ إِذَا جِئْنَا مِنْ كُلِّ أُمَّةٍ بِشَهِيدٍ وَجِئْنَا بِكَ عَلَىٰ هَٰؤُلَاءِ شَهِيدًا

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሕዝቦች ሁሉ መስካሪን ባመጣንና አንተንም በእነዚህ (ባንተ ህዝቦች) ላይ መስካሪ አድርገን በምናመጣህ ጊዜ የከሓዲያን ሁኔታ እንዴት ይሆን?

يَوْمَئِذٍ يَوَدُّ الَّذِينَ كَفَرُوا وَعَصَوُا الرَّسُولَ لَوْ تُسَوَّىٰ بِهِمُ الْأَرْضُ وَلَا يَكْتُمُونَ اللَّهَ حَدِيثًا

በዚያ ቀን እነዚያ በአላህ የካዱ ሰዎችና መልዕክተኛውን ያልታዘዙት ምድር በእነርሱ ላይ ብትደፋባቸው ይመኛሉ። ከአላህም ወሬን አይደብቁም።

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَقْرَبُوا الصَّلَاةَ وَأَنْتُمْ سُكَارَىٰ حَتَّىٰ تَعْلَمُوا مَا تَقُولُونَ وَلَا جُنُبًا إِلَّا عَابِرِي سَبِيلٍ حَتَّىٰ تَغْتَسِلُوا ۚ وَإِنْ كُنْتُمْ مَرْضَىٰ أَوْ عَلَىٰ سَفَرٍ أَوْ جَاءَ أَحَدٌ مِنْكُمْ مِنَ الْغَائِطِ أَوْ لَامَسْتُمُ النِّسَاءَ فَلَمْ تَجِدُوا مَاءً فَتَيَمَّمُوا صَعِيدًا طَيِّبًا فَامْسَحُوا بِوُجُوهِكُمْ وَأَيْدِيكُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَفُوًّا غَفُورًا

(እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) የምትሉትን ነገር ለይታችሁ እስከምታውቁ ድረስ የሰከራችሁ ሆናችሁ ወደ ሶላት አትቅረቡ። ጀናባ ስትሆኑም መንገድን አላፊዎች ካልሆናችሁ በስተቀር ሙሉ አካላታችሁን እስከምትታጥቡ ድረስ መስጊድን አትቅረቡ። በሽተኞች ወይም በጉዞ ላይ ብትሆኑ ወይም ከናንተ አንዱ ከአይነ ምድር ቢጸዳዳ ወይም ከሴቶች ጋር ብትነካኩና ( የግብረስጋ ግንኙነት ብትፈጽሙና) ውሃን ባታገኙ ንጹህ የሆነን የምድር ገጽ (አፈርን) አስቡ (ተጠቀሙ)። ከዚያ ፊቶቻችሁንና እጆቻችሁን በእርሱ አብሱ። አላህ ይቅር ባይና መሀሪ ነውና።

أَلَمْ تَرَ إِلَى الَّذِينَ أُوتُوا نَصِيبًا مِنَ الْكِتَابِ يَشْتَرُونَ الضَّلَالَةَ وَيُرِيدُونَ أَنْ تَضِلُّوا السَّبِيلَ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እነዚያ ከመጽሐፉ የእውቀት ድርሻን ወደ ተሰጡት ክፍሎች አላየህም? ጥመትን በቅንነት ይገዛሉ። መንገድንም እንድትሳሳቱ ይፈልጋሉ።

وَاللَّهُ أَعْلَمُ بِأَعْدَائِكُمْ ۚ وَكَفَىٰ بِاللَّهِ وَلِيًّا وَكَفَىٰ بِاللَّهِ نَصِيرًا

(ትክክለኛ አማኞች ሆይ!) አላህ ጠላቶቻችሁን ከናንተ በበለጠ አዋቂ ነው። ጠባቂነትም በአላህ በቃ። ረዳትነትም በአላህ በቃ።

مِنَ الَّذِينَ هَادُوا يُحَرِّفُونَ الْكَلِمَ عَنْ مَوَاضِعِهِ وَيَقُولُونَ سَمِعْنَا وَعَصَيْنَا وَاسْمَعْ غَيْرَ مُسْمَعٍ وَرَاعِنَا لَيًّا بِأَلْسِنَتِهِمْ وَطَعْنًا فِي الدِّينِ ۚ وَلَوْ أَنَّهُمْ قَالُوا سَمِعْنَا وَأَطَعْنَا وَاسْمَعْ وَانْظُرْنَا لَكَانَ خَيْرًا لَهُمْ وَأَقْوَمَ وَلَٰكِنْ لَعَنَهُمُ اللَّهُ بِكُفْرِهِمْ فَلَا يُؤْمِنُونَ إِلَّا قَلِيلًا

ከእነዚያ ከአይሁዳውያን መካከል ንግግሮችን ከስፍራዎቹ የሚያጣምሙ አሉ። «ንግግርህን ሰማንና ትእዛዝህን አመጽን፤ የማትሰማም ስትሆን እስቲ ስማ።» ይላሉ። በምላሶቻቸዉም ለማጣመምና ሃይማኖትንም ለመዝለፍ በማሰብ "ራዒና" ይላሉ። እነርሱም «ሰማንና ታዘዝን፤ ስማን ተመልከተንም።» ባሉ ኖሮ ለእነርሱም መልካምና ትክክለኛ በሆነ ነበር። ግን በክህደታቸው ምክንያት አላህ ረገማቸው። ከእነርሱም መካከል ጥቂቶች እንጂ አያምኑም።

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ آمِنُوا بِمَا نَزَّلْنَا مُصَدِّقًا لِمَا مَعَكُمْ مِنْ قَبْلِ أَنْ نَطْمِسَ وُجُوهًا فَنَرُدَّهَا عَلَىٰ أَدْبَارِهَا أَوْ نَلْعَنَهُمْ كَمَا لَعَنَّا أَصْحَابَ السَّبْتِ ۚ وَكَانَ أَمْرُ اللَّهِ مَفْعُولًا

እናንተ መጽሐፉ የተሰጣችሁ ሰዎች ሆይ! ፊቶችን ሳናብስና በጀርባዎች ላይ ሳንመልሳቸው ወይም የሠንበትን ባለቤቶች እንደረገምን ሳንረግማችሁ በፊት ከናንተ ጋር ያለውን የሚያረጋግጥ ሆኖ በአወረድነው ቁርኣን እመኑ። የአላህም ትዕዛዝ ተፈፃሚ ነው።

إِنَّ اللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَنْ يُشْرَكَ بِهِ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ لِمَنْ يَشَاءُ ۚ وَمَنْ يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدِ افْتَرَىٰ إِثْمًا عَظِيمًا

አላህ በእርሱ ማጋራትን ፈጽሞ አይምርም። ከዚህ በታች (ውጭ) ያለውን ኃጢአት ግን ለሚሻው ሁሉ ይምራል። በአላህ የሚያጋራ ሁሉ ታላቅን ኃጢአት በእርግጥ ቀጠፈ።

أَلَمْ تَرَ إِلَى الَّذِينَ يُزَكُّونَ أَنْفُسَهُمْ ۚ بَلِ اللَّهُ يُزَكِّي مَنْ يَشَاءُ وَلَا يُظْلَمُونَ فَتِيلًا

ወደ እነዚያ ነፍሶቻቸውን ወደ ሚያጠሩት (ሚያወድሱት) አላየህምን? ይልቁንም አላህ ነው የሚፈልገውን የሚያጠራው። በተምር ፍሬ ስንጥቅ ላይ ያለችን ክር መሳይ ያህልም ቢሆን አይበደሉም።

انْظُرْ كَيْفَ يَفْتَرُونَ عَلَى اللَّهِ الْكَذِبَ ۖ وَكَفَىٰ بِهِ إِثْمًا مُبِينًا

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህ ላይ ውሸትን እንዴት እንደሚቀጥፉ ተመልከት። ግልጽ ወንጀል በርሱ በቃ።

أَلَمْ تَرَ إِلَى الَّذِينَ أُوتُوا نَصِيبًا مِنَ الْكِتَابِ يُؤْمِنُونَ بِالْجِبْتِ وَالطَّاغُوتِ وَيَقُولُونَ لِلَّذِينَ كَفَرُوا هَٰؤُلَاءِ أَهْدَىٰ مِنَ الَّذِينَ آمَنُوا سَبِيلًا

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እነዚያ ከመጽሐፉ ድርሻን ወደ ተሰጡት አላየህምን? በድግምትና በጣዖት ያምናሉ። ለእነዚያ በአላህ ለካዱትም እነዚህ (ከሓዲያን) በሃይማኖት ከእነዚያ በሙሐመድ ካመኑት ይበልጥ ቀና እንደሆኑ ይናገራሉ።

أُولَٰئِكَ الَّذِينَ لَعَنَهُمُ اللَّهُ ۖ وَمَنْ يَلْعَنِ اللَّهُ فَلَنْ تَجِدَ لَهُ نَصِيرًا

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ አላህ የረገማቸው ናቸው። አላህ የረገመውን ደግሞ ለርሱ ፈጽሞ ረዳት አታገኝለትም።

أَمْ لَهُمْ نَصِيبٌ مِنَ الْمُلْكِ فَإِذًا لَا يُؤْتُونَ النَّاسَ نَقِيرًا

በእውነቱ ለእነርሱ ከንግስናው ፈንታ አላቸውን? ያን ጊዜማ ለሰዎች በተምር ፍሬ ላይ ያለችውን ነጥብ ያህል እንኳን አይሰጡም ነበር።

أَمْ يَحْسُدُونَ النَّاسَ عَلَىٰ مَا آتَاهُمُ اللَّهُ مِنْ فَضْلِهِ ۖ فَقَدْ آتَيْنَا آلَ إِبْرَاهِيمَ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَآتَيْنَاهُمْ مُلْكًا عَظِيمًا

ይልቁንም ለሰዎች አላህ ከችሮታው በሰጣቸው ነገር ላይ ይመቀኛሉን? ለኢብራሂምም ቤተሰቦች መጽሐፍንና ጥበብን በእርግጥ ሰጠን። ታላቅንም ንግስናን ሰጠናቸው።

فَمِنْهُمْ مَنْ آمَنَ بِهِ وَمِنْهُمْ مَنْ صَدَّ عَنْهُ ۚ وَكَفَىٰ بِجَهَنَّمَ سَعِيرًا

ከነሱም (ከአይሁድ) መካከል በእርሱ (በነብዩ ሙሐመድ) ያመነ አለ። ከእነርሱም ከዚህ እምነት ያፈገፈገ አለ። አቃጣይነት በገሀነም በቃ።

إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا بِآيَاتِنَا سَوْفَ نُصْلِيهِمْ نَارًا كُلَّمَا نَضِجَتْ جُلُودُهُمْ بَدَّلْنَاهُمْ جُلُودًا غَيْرَهَا لِيَذُوقُوا الْعَذَابَ ۗ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَزِيزًا حَكِيمًا

እነዚያን በተዐምራታችን የካዱትን ሁሉ በእርግጥ እሳትን እናስገባቸዋለን። ስቃይን እንዲቀምሱም ቆዳዎቻቸው በተቃጠሉ ቁጥር ሌሎችን ቆዳዎች እንለውጥላቸዋለን። አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነው።

وَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ سَنُدْخِلُهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِنْ تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا ۖ لَهُمْ فِيهَا أَزْوَاجٌ مُطَهَّرَةٌ ۖ وَنُدْخِلُهُمْ ظِلًّا ظَلِيلًا

እነዚያ በአላህ አንድነት ያመኑና መልካም ስራዎችን የሰሩ ከስራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች ዘላለም በውስጣቸው ዘወታሪዎች ሲሆኑ በእርግጥ እናስገባቸዋለን። ለእነርሱ በውስጧ ንጹህ ሚስቶችም አሏቸው። የምታስጠልልን ጥላም እናስገባቸዋለን።

إِنَّ اللَّهَ يَأْمُرُكُمْ أَنْ تُؤَدُّوا الْأَمَانَاتِ إِلَىٰ أَهْلِهَا وَإِذَا حَكَمْتُمْ بَيْنَ النَّاسِ أَنْ تَحْكُمُوا بِالْعَدْلِ ۚ إِنَّ اللَّهَ نِعِمَّا يَعِظُكُمْ بِهِ ۗ إِنَّ اللَّهَ كَانَ سَمِيعًا بَصِيرًا

አላህ አደራዎችን ወደ ባለቤቶቻቸው እንድታደርሱና በሰዎች መካከል በፈረዳችሁ ጊዜም በትክክል እንድትፈርዱ ያዛችኋል። አላህ በእርሱ የሚገስፃችሁ ነገር ምን ያምር ነው! አላህ ሁሉን ሰሚ እና ሁሉን ተመልካች ነውና።

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَطِيعُوا اللَّهَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ وَأُولِي الْأَمْرِ مِنْكُمْ ۖ فَإِنْ تَنَازَعْتُمْ فِي شَيْءٍ فَرُدُّوهُ إِلَى اللَّهِ وَالرَّسُولِ إِنْ كُنْتُمْ تُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ ۚ ذَٰلِكَ خَيْرٌ وَأَحْسَنُ تَأْوِيلًا

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ታዘዙ። መልዕክተኛውን እና ከመካከላችሁም የስልጣን ባለቤቶችን ታዘዙ። በማንኛዉም ነገር ብትከራከሩም በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ከሆናችሁ የተከራከራችሁበትን ነገር ወደ አላህና ወደ መልዕክተኛው መልሱት። ይህ የተሻለ እና መጨረሻዉም ያማረ ነው።

أَلَمْ تَرَ إِلَى الَّذِينَ يَزْعُمُونَ أَنَّهُمْ آمَنُوا بِمَا أُنْزِلَ إِلَيْكَ وَمَا أُنْزِلَ مِنْ قَبْلِكَ يُرِيدُونَ أَنْ يَتَحَاكَمُوا إِلَى الطَّاغُوتِ وَقَدْ أُمِرُوا أَنْ يَكْفُرُوا بِهِ وَيُرِيدُ الشَّيْطَانُ أَنْ يُضِلَّهُمْ ضَلَالًا بَعِيدًا

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እነዚያ «ባንተ ላይ በተወረደውና ካንተ በፊትም በተወረደው አምነናል ብለው ወደሚሞግቱት (ወደሚያስመስሉት) አላየህምን?» ወደ ሚሉት አላየህምን? በእርሱ እንዲክዱ በእርግጥ የታዘዙ ሲሆኑ ወደ ጣኦት መፋረድን ይፈልጋሉ። ሰይጣንም ከእውነት የራቀን መሳሳት ሊያሳስታቸው ይፈልጋል።

وَإِذَا قِيلَ لَهُمْ تَعَالَوْا إِلَىٰ مَا أَنْزَلَ اللَّهُ وَإِلَى الرَّسُولِ رَأَيْتَ الْمُنَافِقِينَ يَصُدُّونَ عَنْكَ صُدُودًا

ለእነርሱም፡- «አላህ ወደ አወረደው ቁርኣንና ወደ መልዕክተኛው ኑ።» በተባሉ ጊዜ አስመሳዮችን ካንተ በሀይል ሲሸሹ ታያቸዋለህ።

فَكَيْفَ إِذَا أَصَابَتْهُمْ مُصِيبَةٌ بِمَا قَدَّمَتْ أَيْدِيهِمْ ثُمَّ جَاءُوكَ يَحْلِفُونَ بِاللَّهِ إِنْ أَرَدْنَا إِلَّا إِحْسَانًا وَتَوْفِيقًا

እጆቻቸዉም ባስቀደሙት ጥፋት ምክንያት መከራ በደረሰባቸውና ከዚያ «ደግን ሀሳብና ማስማማትን እንጂ ሌላን አልፈለግንም።» በማለት በአላህ የሚምሉ ሆነው ወደ አንተ በመጡ ጊዜ እንዴት ይሆናል?

أُولَٰئِكَ الَّذِينَ يَعْلَمُ اللَّهُ مَا فِي قُلُوبِهِمْ فَأَعْرِضْ عَنْهُمْ وَعِظْهُمْ وَقُلْ لَهُمْ فِي أَنْفُسِهِمْ قَوْلًا بَلِيغًا

እነዚያ አላህ በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅባቸው ናቸው። ከእነርሱ ራስህን አግልል። ገስፃቸዉም። ለእነርሱም በነፍሶቻቸው ውስጥ ጠልቆ የሚገባ ጠንካራ ቃል ተናገራቸው።

وَمَا أَرْسَلْنَا مِنْ رَسُولٍ إِلَّا لِيُطَاعَ بِإِذْنِ اللَّهِ ۚ وَلَوْ أَنَّهُمْ إِذْ ظَلَمُوا أَنْفُسَهُمْ جَاءُوكَ فَاسْتَغْفَرُوا اللَّهَ وَاسْتَغْفَرَ لَهُمُ الرَّسُولُ لَوَجَدُوا اللَّهَ تَوَّابًا رَحِيمًا

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ማንንም መልዕክተኛ በአላህ ፈቃድ ሊታዘዙት እንጂ አልላክንም። እነርሱም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ ወደ አንተ መጥተው አላህን ምህረት በለመኑና መልዕክተኛዉም ለእነርሱ ምህረትን በለመነላቸው ኖሮ አላህን ጸጸትን ተቀባይና አዛኝ ሆኖ ባገኙት ነበር።

فَلَا وَرَبِّكَ لَا يُؤْمِنُونَ حَتَّىٰ يُحَكِّمُوكَ فِيمَا شَجَرَ بَيْنَهُمْ ثُمَّ لَا يَجِدُوا فِي أَنْفُسِهِمْ حَرَجًا مِمَّا قَضَيْتَ وَيُسَلِّمُوا تَسْلِيمًا

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጉዳዩ እነርሱ እንዳሉት አይደለም። በጌታህ እምላለሁ በመካከላቸው በተከራከሩበት ፍርድ የሚያስፈርዱህ ሆነው ከዚያ ከፈረድከው ነገር በነፍሶቻቸው ውስጥ ጭንቀትን እስከማያገኙና ፍጹም መታዘዝንም እስከሚታዘዙ ድረስ አማኝ አይሆኑም።

وَلَوْ أَنَّا كَتَبْنَا عَلَيْهِمْ أَنِ اقْتُلُوا أَنْفُسَكُمْ أَوِ اخْرُجُوا مِنْ دِيَارِكُمْ مَا فَعَلُوهُ إِلَّا قَلِيلٌ مِنْهُمْ ۖ وَلَوْ أَنَّهُمْ فَعَلُوا مَا يُوعَظُونَ بِهِ لَكَانَ خَيْرًا لَهُمْ وَأَشَدَّ تَثْبِيتًا

እኛም በእነርሱ ላይ፡- «ነፍሶቻችሁን ግደሉ» ወይም «ከአገሮቻችሁ ውጡ» ማለትን በፃፍን ኖሮ ከእነርሱ ጥቂቶቹ እንጂ ባልሰሩት (ባልተገበሩት) ነበር። የሚገሰጹበትን ነገር በተገበሩት ኖሮ ለእነርሱ መልካምና በእምነታቸው ላይ ለመርጋትም በጣም የበረታ በሆነ ነበር።

وَإِذًا لَآتَيْنَاهُمْ مِنْ لَدُنَّا أَجْرًا عَظِيمًا

ያን ጊዜ ደግሞ ከእኛ ዘንድ ታላቅን ምንዳ በሰጠናቸው ነበር።

وَلَهَدَيْنَاهُمْ صِرَاطًا مُسْتَقِيمًا

ቀጥተኛውንም መንገድ በእርግጥ በመራናቸው ነበር።

وَمَنْ يُطِعِ اللَّهَ وَالرَّسُولَ فَأُولَٰئِكَ مَعَ الَّذِينَ أَنْعَمَ اللَّهُ عَلَيْهِمْ مِنَ النَّبِيِّينَ وَالصِّدِّيقِينَ وَالشُّهَدَاءِ وَالصَّالِحِينَ ۚ وَحَسُنَ أُولَٰئِكَ رَفِيقًا

አላህንና መልዕክተኛውን የሚታዘዝ ሁሉ ከእነዚያ አላህ በእነርሱ ላይ ፀጋውን ከዋለላቸው ከነብያት፤ ከፃድቃን፤ ከሰማዕታትና ከመልካሞቹ ጋር ይሆናሉ። የእነዚያም ጓደኝነት አማረ።

ذَٰلِكَ الْفَضْلُ مِنَ اللَّهِ ۚ وَكَفَىٰ بِاللَّهِ عَلِيمًا

ይህ ችሮታ ከአላህ የተለገሰ ነው። አዋቂነትም በአላህ በቃ።

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا خُذُوا حِذْرَكُمْ فَانْفِرُوا ثُبَاتٍ أَوِ انْفِرُوا جَمِيعًا

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ጥንቃቄያችሁን ያዙ። ክፍልፍልም ወይም በአንድ ሆናችሁ ለዘመቻ ውጡ።

وَإِنَّ مِنْكُمْ لَمَنْ لَيُبَطِّئَنَّ فَإِنْ أَصَابَتْكُمْ مُصِيبَةٌ قَالَ قَدْ أَنْعَمَ اللَّهُ عَلَيَّ إِذْ لَمْ أَكُنْ مَعَهُمْ شَهِيدًا

ከናንተ ውስጥ በእርግጥ ከዘመቻ ወደ ኋላ የሚንጓደድ (የሚጎተት) ሰው አለ። አደጋም ካገኛችሁ «ከእነርሱ ጋር ተሳታፊ ባለመሆኔ አላህ በእኔ ላይ በእርግጥ ጸጋውን ዋለልኝ።» ይላል።

وَلَئِنْ أَصَابَكُمْ فَضْلٌ مِنَ اللَّهِ لَيَقُولَنَّ كَأَنْ لَمْ تَكُنْ بَيْنَكُمْ وَبَيْنَهُ مَوَدَّةٌ يَا لَيْتَنِي كُنْتُ مَعَهُمْ فَأَفُوزَ فَوْزًا عَظِيمًا

ከአላህ የሆነ ችሮታ ካገኛችሁ ደግሞ በእናንተና በእርሱ መካከል ፍቅር አንዳልነበረ ሆኖ «ታላቅ እድል አገኝ ዘንድ ምን ነው ከእነርሱ ጋር በሆንኩ?» ይላል።

فَلْيُقَاتِلْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ الَّذِينَ يَشْرُونَ الْحَيَاةَ الدُّنْيَا بِالْآخِرَةِ ۚ وَمَنْ يُقَاتِلْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ فَيُقْتَلْ أَوْ يَغْلِبْ فَسَوْفَ نُؤْتِيهِ أَجْرًا عَظِيمًا

እናም እነዚያ ቅርቧን ህይወት በመጨረሻይቱ ሕይወት የሚለውጡ (የሚሸጡ) በአላህ መንገድ ይጋደሉ። በአላህ መንገድ የሚጋደልና ከዚያ የሚገደል ወይም የሚያሸንፍ ሁሉ ታላቅ ምንዳን በእርግጥ እንሰጠዋለን።

وَمَا لَكُمْ لَا تُقَاتِلُونَ فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَالْمُسْتَضْعَفِينَ مِنَ الرِّجَالِ وَالنِّسَاءِ وَالْوِلْدَانِ الَّذِينَ يَقُولُونَ رَبَّنَا أَخْرِجْنَا مِنْ هَٰذِهِ الْقَرْيَةِ الظَّالِمِ أَهْلُهَا وَاجْعَلْ لَنَا مِنْ لَدُنْكَ وَلِيًّا وَاجْعَلْ لَنَا مِنْ لَدُنْكَ نَصِيرًا

(አማኞች ሆይ!) በአላህ መንገድና ከወንዶች፣ ከሴቶችና ከልጆችም የሆኑትን እነዚያን፡- «ጌታችን ሆይ! ከዚህች ባለቤቶቿ በዳይ ከሆኑባት ከተማ አውጣን፤ ካንተም ዘንድ ለእኛ አሳዳሪን አድርግልን፤ ካንተ ዘንድም ለእኛ ረዳትን አድርግልን።» የሚሉትን ደካሞች ሰዎች ለማዳን የማትዋጉት ለምንድ ነው?

الَّذِينَ آمَنُوا يُقَاتِلُونَ فِي سَبِيلِ اللَّهِ ۖ وَالَّذِينَ كَفَرُوا يُقَاتِلُونَ فِي سَبِيلِ الطَّاغُوتِ فَقَاتِلُوا أَوْلِيَاءَ الشَّيْطَانِ ۖ إِنَّ كَيْدَ الشَّيْطَانِ كَانَ ضَعِيفًا

እነዚያ ያመኑት በአላህ መንገድ ይዋጋሉ። እነዚያ በአላህ የካዱት ደግሞ በጣኦት መንገድ ይዋጋሉ። እናም (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) የሰይጣን ቡድኖችን ተፋለሙ። የሰይጣን ተንኮል ደካማ ነውና።

أَلَمْ تَرَ إِلَى الَّذِينَ قِيلَ لَهُمْ كُفُّوا أَيْدِيَكُمْ وَأَقِيمُوا الصَّلَاةَ وَآتُوا الزَّكَاةَ فَلَمَّا كُتِبَ عَلَيْهِمُ الْقِتَالُ إِذَا فَرِيقٌ مِنْهُمْ يَخْشَوْنَ النَّاسَ كَخَشْيَةِ اللَّهِ أَوْ أَشَدَّ خَشْيَةً ۚ وَقَالُوا رَبَّنَا لِمَ كَتَبْتَ عَلَيْنَا الْقِتَالَ لَوْلَا أَخَّرْتَنَا إِلَىٰ أَجَلٍ قَرِيبٍ ۗ قُلْ مَتَاعُ الدُّنْيَا قَلِيلٌ وَالْآخِرَةُ خَيْرٌ لِمَنِ اتَّقَىٰ وَلَا تُظْلَمُونَ فَتِيلًا

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እነዚያ ለእነርሱ፡- «እጆቻችሁን ከመጋደል ሰብስቡ፤ ሶላትን ደንቡን ጠብቃችሁ ስገዱ፤ ግዴታ ምጽዋትን ስጡ።» ወደ ተባሉት አላየህምን? በእነርሱ ላይ መጋደል ግዴታ በሆነባቸው ጊዜ ደግሞ ከእነርሱ መካከል ከፊሎቹ ወዲያውኑ ሰዎችን ልክ አላህን እንደሚፈሩ ወይም የበለጠ ይፈራሉ። «ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ መጋደልን ለምን ደነገግህ? እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አታቆየንም ኖሯልን?» ይላሉ። «የቅርቢቱ ሕይወት ጥቅም አነስተኛ ነው። የመጨረሻይቱ ዓለም ጥቅም ግን አላህን ለሚፈራ ሁሉ በላጭ ነው። በተምር ፍሬ ውስጥ ያለችን ክር መሰል ያህል እንኳ አትበደሉም።» በላቸው።

أَيْنَمَا تَكُونُوا يُدْرِكْكُمُ الْمَوْتُ وَلَوْ كُنْتُمْ فِي بُرُوجٍ مُشَيَّدَةٍ ۗ وَإِنْ تُصِبْهُمْ حَسَنَةٌ يَقُولُوا هَٰذِهِ مِنْ عِنْدِ اللَّهِ ۖ وَإِنْ تُصِبْهُمْ سَيِّئَةٌ يَقُولُوا هَٰذِهِ مِنْ عِنْدِكَ ۚ قُلْ كُلٌّ مِنْ عِنْدِ اللَّهِ ۖ فَمَالِ هَٰؤُلَاءِ الْقَوْمِ لَا يَكَادُونَ يَفْقَهُونَ حَدِيثًا

የትም ስፍራ ብትሆኑ ሞት ያገኛችኋል። በጠነከሩ ህንፃዎች ውስጥም ብትሆኑ እንኳን። ደግ ነገር ካገኛቸው «ይህ ከአላህ ዘንድ የመጣ ነው።» ይላሉ። መከራ ካገኛቸው ግን «ይህ ካንተ ዘንድ የመጣ ነው።» ይላሉ። (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሁሉም (ደጉም ክፉዉም) ከአላህ ዘንድ የመጣ ነው።» በላቸው። እነዚህ ሰዎች ንግግርን ሊረዱ የማይቀርቡት ለምንድን ነው?

مَا أَصَابَكَ مِنْ حَسَنَةٍ فَمِنَ اللَّهِ ۖ وَمَا أَصَابَكَ مِنْ سَيِّئَةٍ فَمِنْ نَفْسِكَ ۚ وَأَرْسَلْنَاكَ لِلنَّاسِ رَسُولًا ۚ وَكَفَىٰ بِاللَّهِ شَهِيدًا

(የሰው ልጅ ሆይ!) ደግ ነገር የሚያገኝህ ከአላህ ችሮታ ነው። የሚደርስብህ መከራ ግን ከራስህ ጥፋት የተነሳ ነው። (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለሰዎች ሁሉ መልዕክተኛ አድርገን ላክንህ። መስካሪነትም በአላህ በቃ።

مَنْ يُطِعِ الرَّسُولَ فَقَدْ أَطَاعَ اللَّهَ ۖ وَمَنْ تَوَلَّىٰ فَمَا أَرْسَلْنَاكَ عَلَيْهِمْ حَفِيظًا

መልዕክተኛውን የሚታዘዝ ሁሉ በእርግጥ አላህን ታዘዘ። ከትዕዛዝም የሸሸው ጉዳዩ አያሳስብህ። በእነርሱ ላይ ጠባቂ አድርገን አላክንህምና።

وَيَقُولُونَ طَاعَةٌ فَإِذَا بَرَزُوا مِنْ عِنْدِكَ بَيَّتَ طَائِفَةٌ مِنْهُمْ غَيْرَ الَّذِي تَقُولُ ۖ وَاللَّهُ يَكْتُبُ مَا يُبَيِّتُونَ ۖ فَأَعْرِضْ عَنْهُمْ وَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ ۚ وَكَفَىٰ بِاللَّهِ وَكِيلًا

አጠገብህ ሲሆኑ የአንተ ታዛዥ ነን ይላሉ። ካንተ ዘንድ በወጡ ጊዜ ከእነርሱ ከፊሎቹ ከዚያ በአጠገብህ ከሚሉት ሌላን በልቦቻቸው ያሳድራሉ። አላህ በልቦቻቸው የሚያሳድሩትን ነገር ሁሉ ይጽፋል። ስለዚህ ተዋቸውና በአላህ ላይ ብቻ ተመካ። መመኪያነትም በአላህ በቃ።

أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِنْدِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ቁርኣንን አያስተነትኑምን? ከአላህ ሌላ ዘንድ የመጣ በነበረ ኖሮ በውስጡ ብዙ መለያየትን ባገኙ ነበር።

وَإِذَا جَاءَهُمْ أَمْرٌ مِنَ الْأَمْنِ أَوِ الْخَوْفِ أَذَاعُوا بِهِ ۖ وَلَوْ رَدُّوهُ إِلَى الرَّسُولِ وَإِلَىٰ أُولِي الْأَمْرِ مِنْهُمْ لَعَلِمَهُ الَّذِينَ يَسْتَنْبِطُونَهُ مِنْهُمْ ۗ وَلَوْلَا فَضْلُ اللَّهِ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَتُهُ لَاتَّبَعْتُمُ الشَّيْطَانَ إِلَّا قَلِيلًا

ሰላምን ወይም ስጋትን የሚመለከት ወሬ በመጣላቸው ጊዜ እርሱን ያሰራጫሉ (ያጋንናሉ)። ወደ መልዕክተኛውና ከእነርሱ መካከል የጉዳይ ባለቤቶች ወደ ሆኑት አዋቂዎቹ በመለሱት ኖሮ እነዚያ ከእነርሱ መካከል ነገሩን በትክክል የሚረዱት ክፍሎች ባወቁት ነበር። በእናንተ ላይ የአላህ ችሮታና እዝነቱ ባልነበረ ኖሮ ከጥቂቶቹ በስተቀር ሰይጣንን በተከተላችሁ ነበር።

فَقَاتِلْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ لَا تُكَلَّفُ إِلَّا نَفْسَكَ ۚ وَحَرِّضِ الْمُؤْمِنِينَ ۖ عَسَى اللَّهُ أَنْ يَكُفَّ بَأْسَ الَّذِينَ كَفَرُوا ۚ وَاللَّهُ أَشَدُّ بَأْسًا وَأَشَدُّ تَنْكِيلًا

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህ መንገድ ተዋጋ። ራስህን እንጂ ሌላን አትገደድም። አማኞችንም በአላህ መንገድ ላይ በመዋጋት ላይ አደፋፍራቸው። አላህ የእነዚያን የካዱትን ሰዎች ኃይል ሊከለክል ይከጀላል። አላህ በሃይል በመያዙ የበረታና ቅጣቱም የጠነከረ ነው።

مَنْ يَشْفَعْ شَفَاعَةً حَسَنَةً يَكُنْ لَهُ نَصِيبٌ مِنْهَا ۖ وَمَنْ يَشْفَعْ شَفَاعَةً سَيِّئَةً يَكُنْ لَهُ كِفْلٌ مِنْهَا ۗ وَكَانَ اللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ مُقِيتًا

መልካም መታደግን የሚታደግ (ሽምግልናን የሚሸመግል) ሰው ሁሉ ለራሱ ከእርሷ እድል ይኖረዋል። መጥፎ መታደግንም የሚታደግ ሰው ለእርሱ ከእርሷ ድርሻ ይኖረዋል። አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው።

وَإِذَا حُيِّيتُمْ بِتَحِيَّةٍ فَحَيُّوا بِأَحْسَنَ مِنْهَا أَوْ رُدُّوهَا ۗ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ حَسِيبًا

(እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ሰላምታ በቀረበላችሁ ጊዜ ከእርሷ ይበልጥ ባማረ ሰላምታ መልሱ። ወይም እርሷኑ ራሷን መልሷት። አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ተቆጣጣሪ ነውና።

اللَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ لَيَجْمَعَنَّكُمْ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ لَا رَيْبَ فِيهِ ۗ وَمَنْ أَصْدَقُ مِنَ اللَّهِ حَدِيثًا

አላህ ከእርሱ በስተቀር ትክክለኛ አምላክ የለም። ወደ ትንሳኤ ቀን በእርሱ ጥርጥር የሌለበት ሲሆን በእርግጥ ይሰበስባችኋል። በንግግርም ከአላህ ይበልጥ እውነተኛ ማን ነው?

فَمَا لَكُمْ فِي الْمُنَافِقِينَ فِئَتَيْنِ وَاللَّهُ أَرْكَسَهُمْ بِمَا كَسَبُوا ۚ أَتُرِيدُونَ أَنْ تَهْدُوا مَنْ أَضَلَّ اللَّهُ ۖ وَمَنْ يُضْلِلِ اللَّهُ فَلَنْ تَجِدَ لَهُ سَبِيلًا

(አማኞች ሆይ) አላህ በስራዎቻቸው ምክንያት ወደ ክህደት የመለሳቸው ሲሆኑ በአስመሳዮች ጉዳይ እናንተ ለሁለት ቡድን የተከፈላችሁት ምን ሆናችሁ ነው? አላህ ያጠመመውን ሰው ልታቀኑ ታስባላችሁን? (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ያጠመመውን ሰው ለእርሱ መንገድ ፈጽሞ አታገኝለትም።

وَدُّوا لَوْ تَكْفُرُونَ كَمَا كَفَرُوا فَتَكُونُونَ سَوَاءً ۖ فَلَا تَتَّخِذُوا مِنْهُمْ أَوْلِيَاءَ حَتَّىٰ يُهَاجِرُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ ۚ فَإِنْ تَوَلَّوْا فَخُذُوهُمْ وَاقْتُلُوهُمْ حَيْثُ وَجَدْتُمُوهُمْ ۖ وَلَا تَتَّخِذُوا مِنْهُمْ وَلِيًّا وَلَا نَصِيرًا

(አማኞች ሆይ) በአላህ እንደ ካዱ ሁሉ እናንተም እንድትክዱና ከእነርሱ ጋር እኩል እንድትሆኑ ተመኙ። በአላህ መንገድ እስከሚሰደዱ ድረስ ከእነርሱ መካከል ወዳጆችን አትያዙ። ከእምነት ካፈገፈጉም ማርኳቸው። ባገኛችኋቸው ስፍራ ሁሉ ግደሏቸው። ከእነርሱም ወዳጅንና ረዳትን አትያዙ።

إِلَّا الَّذِينَ يَصِلُونَ إِلَىٰ قَوْمٍ بَيْنَكُمْ وَبَيْنَهُمْ مِيثَاقٌ أَوْ جَاءُوكُمْ حَصِرَتْ صُدُورُهُمْ أَنْ يُقَاتِلُوكُمْ أَوْ يُقَاتِلُوا قَوْمَهُمْ ۚ وَلَوْ شَاءَ اللَّهُ لَسَلَّطَهُمْ عَلَيْكُمْ فَلَقَاتَلُوكُمْ ۚ فَإِنِ اعْتَزَلُوكُمْ فَلَمْ يُقَاتِلُوكُمْ وَأَلْقَوْا إِلَيْكُمُ السَّلَمَ فَمَا جَعَلَ اللَّهُ لَكُمْ عَلَيْهِمْ سَبِيلًا

እነዚያ በእናንተና በእነርሱ መካከል ቃል ኪዳን ወዳላቸው ህዝቦች የሚጠጉ፤ ወይም እናንተን ለመጋደልም ይሁን ወገኖቻቸውን ለመጋደል ልቦቻቸው የተጨነቁ ሆነው ወደ እናንተ የመጡ ሲቀሩ እነዚያንማ አትጋደሏቸው። አላህ በፈለገ ኖሮ በእናንተ ላይ ሀይል በሰጣቸውና በተዋጓችሁ ነበር። ቢተዋችሁ ባይዋጓችሁ ወደ እናንተ የእርቅን ሀሳብ ቢያቀርቡ አላህ ለእናንተ በእነርሱ ላይ የመዋጋት መንገድን አላደረገም።

سَتَجِدُونَ آخَرِينَ يُرِيدُونَ أَنْ يَأْمَنُوكُمْ وَيَأْمَنُوا قَوْمَهُمْ كُلَّ مَا رُدُّوا إِلَى الْفِتْنَةِ أُرْكِسُوا فِيهَا ۚ فَإِنْ لَمْ يَعْتَزِلُوكُمْ وَيُلْقُوا إِلَيْكُمُ السَّلَمَ وَيَكُفُّوا أَيْدِيَهُمْ فَخُذُوهُمْ وَاقْتُلُوهُمْ حَيْثُ ثَقِفْتُمُوهُمْ ۚ وَأُولَٰئِكُمْ جَعَلْنَا لَكُمْ عَلَيْهِمْ سُلْطَانًا مُبِينًا

ከናንተም ሆነ ከወገኖቻቸው ለመዳን የሚፈልጉ ሌሎች ቡድኖችም ታገኛላችሁ። ወደ ፈተና (ወደ ማጋራት) እንዲመለሱ በተጠሩ ቁጥር በእርሷ ውስጥ ይዘፈቃሉ። ባይተዋችሁና እርቅን ካላቀረቡላችሁ እጆቻቸውንም ባይሰበስቡ ባገኛችኋቸው ስፍራ ሁሉ ማርኳቸው። ግደሏቸዉም። እነዚያ፤ በእነርሱ ላይ ለእናንተ ግልጽ ማስረጃን አድርገንላችኋል።

وَمَا كَانَ لِمُؤْمِنٍ أَنْ يَقْتُلَ مُؤْمِنًا إِلَّا خَطَأً ۚ وَمَنْ قَتَلَ مُؤْمِنًا خَطَأً فَتَحْرِيرُ رَقَبَةٍ مُؤْمِنَةٍ وَدِيَةٌ مُسَلَّمَةٌ إِلَىٰ أَهْلِهِ إِلَّا أَنْ يَصَّدَّقُوا ۚ فَإِنْ كَانَ مِنْ قَوْمٍ عَدُوٍّ لَكُمْ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَتَحْرِيرُ رَقَبَةٍ مُؤْمِنَةٍ ۖ وَإِنْ كَانَ مِنْ قَوْمٍ بَيْنَكُمْ وَبَيْنَهُمْ مِيثَاقٌ فَدِيَةٌ مُسَلَّمَةٌ إِلَىٰ أَهْلِهِ وَتَحْرِيرُ رَقَبَةٍ مُؤْمِنَةٍ ۖ فَمَنْ لَمْ يَجِدْ فَصِيَامُ شَهْرَيْنِ مُتَتَابِعَيْنِ تَوْبَةً مِنَ اللَّهِ ۗ وَكَانَ اللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمًا

አማኝ በስህተት ካልሆነ በስተቀር አማኝን መግደል አይገባዉም። አማኝን በስህተት የገደለም አማኝ ባሪያን ነፃ ማውጣትና ምህረት ካላደረጉለት በስተቀር ለቤተሰቦቹ የምትሰጥ ጉማ መክፈል አለበት። ተገዳዩ ምዕመን ሆኖ ለእናንተ ጠላት ከሆኑ ህዝቦች ዘንድ ቢሆንም አማኝን ባሪያ ነፃ ማውጣት አለበት። ተገዳዩ በእናንተ እና በእነርሱ መካከል ቃል ኪዳን ካላቸዉም ህዝቦች ጋር ቢሆን ለቤተሰቦቹ የምትሰጥ ጉማና አማኝን ባሪያ ነፃ ማውጣት አለበት። ይህንን ያላገኘም በተከታታይ ሁለት ወሮችን መፆም አለበት። (ይህ) ከአላህ የሆነ ጸጸትን መቀበያ (ነው)። አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው።

وَمَنْ يَقْتُلْ مُؤْمِنًا مُتَعَمِّدًا فَجَزَاؤُهُ جَهَنَّمُ خَالِدًا فِيهَا وَغَضِبَ اللَّهُ عَلَيْهِ وَلَعَنَهُ وَأَعَدَّ لَهُ عَذَابًا عَظِيمًا

አማኝን አስቦ የሚገድል ቅጣቱ በውስጧ ዘወታሪ ሲሆን ገሀነም ናት። አላህ በእርሱ ላይ ተቆጣ። ረገመዉም። ለእርሱ ከባድ ቅጣትን አዘጋጅቶለታል።

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا ضَرَبْتُمْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ فَتَبَيَّنُوا وَلَا تَقُولُوا لِمَنْ أَلْقَىٰ إِلَيْكُمُ السَّلَامَ لَسْتَ مُؤْمِنًا تَبْتَغُونَ عَرَضَ الْحَيَاةِ الدُّنْيَا فَعِنْدَ اللَّهِ مَغَانِمُ كَثِيرَةٌ ۚ كَذَٰلِكَ كُنْتُمْ مِنْ قَبْلُ فَمَنَّ اللَّهُ عَلَيْكُمْ فَتَبَيَّنُوا ۚ إِنَّ اللَّهَ كَانَ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرًا

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህ መንገድ ለመዋጋት በተጓዛችሁ ጊዜ አረጋግጡ። ሰላምታን ወደ እናንተ ላቀረበ ሰው የቅርቢቱን ሕይወት ጥቅም የምትፈልጉ ሆናችሁ «ትክክለኛ አማኝ አይደለህም።» አትበሉት። አላህ ዘንድ ብዙ ምርኮዎች አሉና። እናንተም ከዚህ በፊት ልክ እንደዚሁ ነበራችሁ። አላህ በእናንተ ላይ ለገሰ። ስለዚህም አረጋግጡ። አላህ በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነውና።

لَا يَسْتَوِي الْقَاعِدُونَ مِنَ الْمُؤْمِنِينَ غَيْرُ أُولِي الضَّرَرِ وَالْمُجَاهِدُونَ فِي سَبِيلِ اللَّهِ بِأَمْوَالِهِمْ وَأَنْفُسِهِمْ ۚ فَضَّلَ اللَّهُ الْمُجَاهِدِينَ بِأَمْوَالِهِمْ وَأَنْفُسِهِمْ عَلَى الْقَاعِدِينَ دَرَجَةً ۚ وَكُلًّا وَعَدَ اللَّهُ الْحُسْنَىٰ ۚ وَفَضَّلَ اللَّهُ الْمُجَاهِدِينَ عَلَى الْقَاعِدِينَ أَجْرًا عَظِيمًا

ከአማኞች የጉዳት ባለቤት ከሆኑት በስተቀር ተቀማጮቹ እና በአላህ መንገድ በገንዘቦቻቸውም በነፍሶቻቸውም የሚታገሉት አይስተካከሉም። በገንዘቦቻቸውም በነፍሶቻቸውም የሚታገሉትን አላህ በተቀማጮቹ ላይ በደረጃ አበለጠ። ለሁሉም አላህ መልካሚቱን (ገነት) ተስፋ ሰጠ (ቃል ኪዳን ገባ)። ታጋዮቹንም በተቀማጮቹ ላይ አላህ በታላቅ ምንዳ አበለጠ።

دَرَجَاتٍ مِنْهُ وَمَغْفِرَةً وَرَحْمَةً ۚ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَحِيمًا

ከእርሱ ዘንድ በሆኑ ደረጃዎች አበለጠ። ምህረትንም አደረገ። እዝነትንም አዘነላቸው። አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና።

إِنَّ الَّذِينَ تَوَفَّاهُمُ الْمَلَائِكَةُ ظَالِمِي أَنْفُسِهِمْ قَالُوا فِيمَ كُنْتُمْ ۖ قَالُوا كُنَّا مُسْتَضْعَفِينَ فِي الْأَرْضِ ۚ قَالُوا أَلَمْ تَكُنْ أَرْضُ اللَّهِ وَاسِعَةً فَتُهَاجِرُوا فِيهَا ۚ فَأُولَٰئِكَ مَأْوَاهُمْ جَهَنَّمُ ۖ وَسَاءَتْ مَصِيرًا

እነዚያ ለእምነት ሲሉ ባለመሰደድ ነፍሶቻቸውን በዳዮች ሆነው መላዕክት ነፍሳቸውን የወሰዷቸው፤ (መላዕክቱ) ለእነርሱ «በምን ነገር ላይ ነበራችሁ?» ይሏቸዋል። «በምድር ውስጥ ደካሞች ነበርን።» ይላሉ። «የአላህ ምድር ትሰደዱባት ዘንድ ሰፊ አልነበረችምን?» ይሏቸዋል። እነዚያም መኖሪያቸው ገሀነም ናት። ገሀነምም መመለሻነቷ ከፋች።

إِلَّا الْمُسْتَضْعَفِينَ مِنَ الرِّجَالِ وَالنِّسَاءِ وَالْوِلْدَانِ لَا يَسْتَطِيعُونَ حِيلَةً وَلَا يَهْتَدُونَ سَبِيلًا

ከወንዶችና ከሴቶች ከህፃኖችም ሲሆኑ ከሀገራቸው ለመውጣት መላን የማይችሉና መንገድንም የማይመሩ ደካሞች (ባለመሰደዳቸው ግን ምንም ቅጣት የለባቸዉም።)

فَأُولَٰئِكَ عَسَى اللَّهُ أَنْ يَعْفُوَ عَنْهُمْ ۚ وَكَانَ اللَّهُ عَفُوًّا غَفُورًا

እነዚያ አላህ ከእነርሱ ይቅርታ ሊያደርግ ይሻል። አላህም ይቅር ባይና መሀሪ ነውና።

وَمَنْ يُهَاجِرْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ يَجِدْ فِي الْأَرْضِ مُرَاغَمًا كَثِيرًا وَسَعَةً ۚ وَمَنْ يَخْرُجْ مِنْ بَيْتِهِ مُهَاجِرًا إِلَى اللَّهِ وَرَسُولِهِ ثُمَّ يُدْرِكْهُ الْمَوْتُ فَقَدْ وَقَعَ أَجْرُهُ عَلَى اللَّهِ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَحِيمًا

በአላህ መንገድ የሚሰደድ ሁሉ በምድር ውስጥ ብዙ መሰደጃንና ምቾትን ያገኛል። ወደ አላህና ወደ መልዕክተኛው ስደተኛ ሆኖ ከቤቱ የሚወጣና ከዚያ በመንገድ ላይ ሞት የሚያገኘው ምንዳው በእርግጥ በአላህ ዘንድ ተረጋገጠ። አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና።

وَإِذَا ضَرَبْتُمْ فِي الْأَرْضِ فَلَيْسَ عَلَيْكُمْ جُنَاحٌ أَنْ تَقْصُرُوا مِنَ الصَّلَاةِ إِنْ خِفْتُمْ أَنْ يَفْتِنَكُمُ الَّذِينَ كَفَرُوا ۚ إِنَّ الْكَافِرِينَ كَانُوا لَكُمْ عَدُوًّا مُبِينًا

(አማኞች ሆይ!) በምድር ላይ በተጓዛችሁ ጊዜ እነዚያ የካዱት ሊያውኳችሁ እንደሆነ ብትፈሩ ከሶላቶች መካከል ከፊሎችን (ባለ አራት አራት ረካአ የሆኑትን ቁጥራቸውን ወደ ሁለት ሁለት በመቀነስ) ብታሳጥሩ በእናንተ ላይ ኃጢአት የለም። ከሓዲያን ለእናንተ በእርግጥ ግልጽ ጠላቶች ናቸውና።

وَإِذَا كُنْتَ فِيهِمْ فَأَقَمْتَ لَهُمُ الصَّلَاةَ فَلْتَقُمْ طَائِفَةٌ مِنْهُمْ مَعَكَ وَلْيَأْخُذُوا أَسْلِحَتَهُمْ فَإِذَا سَجَدُوا فَلْيَكُونُوا مِنْ وَرَائِكُمْ وَلْتَأْتِ طَائِفَةٌ أُخْرَىٰ لَمْ يُصَلُّوا فَلْيُصَلُّوا مَعَكَ وَلْيَأْخُذُوا حِذْرَهُمْ وَأَسْلِحَتَهُمْ ۗ وَدَّ الَّذِينَ كَفَرُوا لَوْ تَغْفُلُونَ عَنْ أَسْلِحَتِكُمْ وَأَمْتِعَتِكُمْ فَيَمِيلُونَ عَلَيْكُمْ مَيْلَةً وَاحِدَةً ۚ وَلَا جُنَاحَ عَلَيْكُمْ إِنْ كَانَ بِكُمْ أَذًى مِنْ مَطَرٍ أَوْ كُنْتُمْ مَرْضَىٰ أَنْ تَضَعُوا أَسْلِحَتَكُمْ ۖ وَخُذُوا حِذْرَكُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ أَعَدَّ لِلْكَافِرِينَ عَذَابًا مُهِينًا

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ) በጦርነት ላይ በመካከላቸው በሆንክና ሶላትን ለእነርሱ ባሰገድካቸው ጊዜ ከእነርሱ አንዱ ቡድን ካንተ ጋር ይቁም። መሳሪያዎቻቸውንም ይያዙ። ሱጁድ ባደረጉ ጊዜ ከበስተኋላችሁ ይሁኑ። ከዚያም እነዚያ ቡድኖች ወደ ግንባር ይሂዱና ያልሰገዱት ሌሎች ቡድኖች ይምጡ ። ከዚያም ካንተ ጋር ይስገዱ። ጥንቃቄያቸውንና መሳሪያዎቻቸውንም ይያዙ። እነዚያ በአላህ የካዱት ከትጥቅና ስንቃችሁ ብትዘናጉና በአንድ ጊዜ ቢወሯችሁ ይመኛሉ። ዝናብ አውኳችሁ ወይም በሽተኛ ሆናችሁ ትጥቃችሁን ብታስቀምጡ በእናንተ ላይ ኃጢአት የለባችሁም። ጥንቃቄ አድርጉ። አላህ ለከሐዲያን ሁሉ አዋራጅን ቅጣት አዘጋጀ።

فَإِذَا قَضَيْتُمُ الصَّلَاةَ فَاذْكُرُوا اللَّهَ قِيَامًا وَقُعُودًا وَعَلَىٰ جُنُوبِكُمْ ۚ فَإِذَا اطْمَأْنَنْتُمْ فَأَقِيمُوا الصَّلَاةَ ۚ إِنَّ الصَّلَاةَ كَانَتْ عَلَى الْمُؤْمِنِينَ كِتَابًا مَوْقُوتًا

ሶላትንም በፈጸማችሁ (በጨረሳችሁ) ጊዜ ቆማችሁ፣ ተቀምጣችሁና በጎኖቻችሁም ተጋድማችሁ አላህን አውሱ። በተረጋጋችሁ ጊዜ ግን ሶላትን ደንቧን አሟልታችሁ ስገዱ። ሶላት በአማኞች ላይ በጊዜያት የተወሰነች ግዴታ ናትና።

وَلَا تَهِنُوا فِي ابْتِغَاءِ الْقَوْمِ ۖ إِنْ تَكُونُوا تَأْلَمُونَ فَإِنَّهُمْ يَأْلَمُونَ كَمَا تَأْلَمُونَ ۖ وَتَرْجُونَ مِنَ اللَّهِ مَا لَا يَرْجُونَ ۗ وَكَانَ اللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمًا

ሰዎቹንም ከመፈለግ አትስነፉ። ስትቆስሉ የምትታመሙ ብትሆኑም እናንተ እንደምትታመሙ ሁሉ እነርሱም ይታመማሉ። እናንተ ግን እነርሱ የማይከጅሉትን ከአላህ ትከጅላላችሁ። አላህም ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው።

إِنَّا أَنْزَلْنَا إِلَيْكَ الْكِتَابَ بِالْحَقِّ لِتَحْكُمَ بَيْنَ النَّاسِ بِمَا أَرَاكَ اللَّهُ ۚ وَلَا تَكُنْ لِلْخَائِنِينَ خَصِيمًا

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በሰዎች መካከል አላህ ባሳወቀህ ልትፈርድ ወደ አንተ መጽሐፉን በእውነት አወረድን። እናም ለከዳተኞች ተከራካሪ አትሁን።

وَاسْتَغْفِرِ اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ كَانَ غَفُورًا رَحِيمًا

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህን ምህረት ለምነው። አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና።

وَلَا تُجَادِلْ عَنِ الَّذِينَ يَخْتَانُونَ أَنْفُسَهُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ مَنْ كَانَ خَوَّانًا أَثِيمًا

ለእነዚያ ነፍሶቻቸውን ስለሚያታልሉት ሰዎች አትከራከር። አላህ ከዳተኛንና ኃጢአተኛን ሰው አይወድምና።

يَسْتَخْفُونَ مِنَ النَّاسِ وَلَا يَسْتَخْفُونَ مِنَ اللَّهِ وَهُوَ مَعَهُمْ إِذْ يُبَيِّتُونَ مَا لَا يَرْضَىٰ مِنَ الْقَوْلِ ۚ وَكَانَ اللَّهُ بِمَا يَعْمَلُونَ مُحِيطًا

ከሰው ይደበቃሉ። አላህ በዕውቀቱ ከእነርሱ ጋር ሲሆን ከንግግር የማይወደውን ነገር በልቦቻቸው በሚያሳድሩ ጊዜ ከእርሱ አይደበቁም። አላህ በሚሰሩት ሁሉ በእውቀቱ ከባቢ ነውና።

هَا أَنْتُمْ هَٰؤُلَاءِ جَادَلْتُمْ عَنْهُمْ فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا فَمَنْ يُجَادِلُ اللَّهَ عَنْهُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ أَمْ مَنْ يَكُونُ عَلَيْهِمْ وَكِيلًا

እነሆ እናንተ እነዚያ በቅርቢቱ ሕይወት ውስጥ ስለ እነርሱ ተከራከራችሁላቸው። በትንሳኤ ቀን አላህን ስለ እነርሱ የሚከራከርላቸው ማን ነው? ወይስ ለእነርሱ ሀላፊ የሚሆን ማን ነው?

وَمَنْ يَعْمَلْ سُوءًا أَوْ يَظْلِمْ نَفْسَهُ ثُمَّ يَسْتَغْفِرِ اللَّهَ يَجِدِ اللَّهَ غَفُورًا رَحِيمًا

መጥፎ ነገር የሚሰራ ወይም ነፍሱን የሚበድልና ከዚያም ተጸጽቶ አላህን ምህረት የሚለምን ሁሉ አላህን መሀሪና አዛኝ ሆኖ ያገኘዋል።

وَمَنْ يَكْسِبْ إِثْمًا فَإِنَّمَا يَكْسِبُهُ عَلَىٰ نَفْسِهِ ۚ وَكَانَ اللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمًا

ኃጢአት የሚሰራም የሚሰራው ጥፋት ጉዳቱ በራሱ ላይ ብቻ ነው። አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና።

وَمَنْ يَكْسِبْ خَطِيئَةً أَوْ إِثْمًا ثُمَّ يَرْمِ بِهِ بَرِيئًا فَقَدِ احْتَمَلَ بُهْتَانًا وَإِثْمًا مُبِينًا

ኃጢአትን ወይም ወንጀልን የሚሰራና ከዚያም በእርሱ ንጹህን ሰው የሚወነጅል ቅጥፈትንና ግልጽ ኃጢአትን በቁርጥ ተሸከመ።

وَلَوْلَا فَضْلُ اللَّهِ عَلَيْكَ وَرَحْمَتُهُ لَهَمَّتْ طَائِفَةٌ مِنْهُمْ أَنْ يُضِلُّوكَ وَمَا يُضِلُّونَ إِلَّا أَنْفُسَهُمْ ۖ وَمَا يَضُرُّونَكَ مِنْ شَيْءٍ ۚ وَأَنْزَلَ اللَّهُ عَلَيْكَ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَعَلَّمَكَ مَا لَمْ تَكُنْ تَعْلَمُ ۚ وَكَانَ فَضْلُ اللَّهِ عَلَيْكَ عَظِيمًا

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የአላህ ችሮታና እዝነቱ ባንተ ላይ ባልነበረ ኖሮ ከእነርሱ የሆነ ቡድን ሊያሳስቱህ ባሰቡ ነበር። ነፍሶቻቸውን እንጂ ሌላ አያሳስቱም። በምንም አይጎዱህም። አላህ ባንተ ላይ መጽሐፍንና ጥበብን አወረደ። የማታውቀውን ሁሉ አስተማረህ። የአላህ ችሮታ ባንተ ላይ ታላቅ ነው።

لَا خَيْرَ فِي كَثِيرٍ مِنْ نَجْوَاهُمْ إِلَّا مَنْ أَمَرَ بِصَدَقَةٍ أَوْ مَعْرُوفٍ أَوْ إِصْلَاحٍ بَيْنَ النَّاسِ ۚ وَمَنْ يَفْعَلْ ذَٰلِكَ ابْتِغَاءَ مَرْضَاتِ اللَّهِ فَسَوْفَ نُؤْتِيهِ أَجْرًا عَظِيمًا

ከውይይቶቻቸው መካከል በምጽዋት ወይም በበጎ ስራ ወይም በሰዎች መካከል በማስታረቅ ከሚያዙ ሰዎች ውይይት በስተቀር በብዙው ውይይት ውስጥ ደግ ነገር የለበትም። ይህንንም የተባለውን የአላህን ውዴታ በመፈለግ ለሚሰራ ሁሉ ታላቅ ምንዳን እንሰጠዋለን።

وَمَنْ يُشَاقِقِ الرَّسُولَ مِنْ بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُ الْهُدَىٰ وَيَتَّبِعْ غَيْرَ سَبِيلِ الْمُؤْمِنِينَ نُوَلِّهِ مَا تَوَلَّىٰ وَنُصْلِهِ جَهَنَّمَ ۖ وَسَاءَتْ مَصِيرًا

ቅኑ መንገድ ለእርሱ ከተገለጸለት በኋላ መልዕክተኛውን የሚቃረንና ከምዕመናኖቹ መንገድ ሌላ የሆነን የሚከተል ሁሉ በመረጠው ጥመት ላይ እንተወዋለን። ወደ ገሀነምም እናስገባዋለን። መመለሻይቱም ገሀነም ከፋች።

إِنَّ اللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَنْ يُشْرَكَ بِهِ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ لِمَنْ يَشَاءُ ۚ وَمَنْ يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدْ ضَلَّ ضَلَالًا بَعِيدًا

አላህ በእርሱ ማጋራትን ፈጽሞ አይምርም። ከሽርክ በታች (ሌላ) ያለውን ጥፋት ግን ለሚሻው ይምራል። በአላህ የሚያጋራም ከእውነት የራቀን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ።

إِنْ يَدْعُونَ مِنْ دُونِهِ إِلَّا إِنَاثًا وَإِنْ يَدْعُونَ إِلَّا شَيْطَانًا مَرِيدًا

ከእርሱ ሌላ እንስት (ጣኦታትን) እንጂ አይገዙም። አመጸኛ ሰይጣንንም እንጂ ሌላን አይገዙም።

لَعَنَهُ اللَّهُ ۘ وَقَالَ لَأَتَّخِذَنَّ مِنْ عِبَادِكَ نَصِيبًا مَفْرُوضًا

አላህም የረገመውን (እንዲህ) ያለውንም (ሰይጣን እንጂ አይከተሉም።) «ከባሮችህ የተወሰነን ድርሻ በእርግጥ እይዛለሁ።

وَلَأُضِلَّنَّهُمْ وَلَأُمَنِّيَنَّهُمْ وَلَآمُرَنَّهُمْ فَلَيُبَتِّكُنَّ آذَانَ الْأَنْعَامِ وَلَآمُرَنَّهُمْ فَلَيُغَيِّرُنَّ خَلْقَ اللَّهِ ۚ وَمَنْ يَتَّخِذِ الشَّيْطَانَ وَلِيًّا مِنْ دُونِ اللَّهِ فَقَدْ خَسِرَ خُسْرَانًا مُبِينًا

በእርግጥ አጠማቸዋለሁ። ከንቱን ምኞትም አስመኛቸዋለሁ። አዛቸዉምና የእንስሶችን ጆሮዎች ይተለትላሉ። አዛቸዉምና የአላህን ፍጥረት ይለውጣሉ።» (ያለውን ይከተላሉ።) ከአላህ ሌላ ሰይጣንን ረዳት አድርጎ የሚይዝ ግልጽ ኪሳራን በእርግጥ ከሰረ።

يَعِدُهُمْ وَيُمَنِّيهِمْ ۖ وَمَا يَعِدُهُمُ الشَّيْطَانُ إِلَّا غُرُورًا

የማይፈጽመውን ከንቱ ተስፋ ይሰጣቸዋል። ያስመኛቸዋልም። ሰይጣን ለማታለል እንጂ ቃል አይገባላቸዉም።

أُولَٰئِكَ مَأْوَاهُمْ جَهَنَّمُ وَلَا يَجِدُونَ عَنْهَا مَحِيصًا

እነዚያ የመጨረሻ መኖሪያቸው ገሀነም ናት። ከእርሷም መሸሻን አያገኙም።

وَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ سَنُدْخِلُهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِنْ تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا ۖ وَعْدَ اللَّهِ حَقًّا ۚ وَمَنْ أَصْدَقُ مِنَ اللَّهِ قِيلًا

እነዚያ በአላህ ያመኑትና በጎ ስራዎችን የሰሩ ሁሉ በስራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች ዘላለም በውስጣቸው ዘወታሪዎች ሲሆኑ እናስገባቸዋለን። አላህ እውነተኛን ተስፋ ሰጣቸው። በንግግርም ከአላህ ይበልጥ እውነተኛ ማን ነው?

لَيْسَ بِأَمَانِيِّكُمْ وَلَا أَمَانِيِّ أَهْلِ الْكِتَابِ ۗ مَنْ يَعْمَلْ سُوءًا يُجْزَ بِهِ وَلَا يَجِدْ لَهُ مِنْ دُونِ اللَّهِ وَلِيًّا وَلَا نَصِيرًا

ነገሩ በምኞታችሁና በመጽሐፉ ሰዎች ምኞት አይደለም። መጥፎን የሚሰራ ሁሉ በእርሱ ይመነዳል። ለእርሱም ከአላህ ሌላ ጠባቂን ረዳትንም አያገኝም።

وَمَنْ يَعْمَلْ مِنَ الصَّالِحَاتِ مِنْ ذَكَرٍ أَوْ أُنْثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَأُولَٰئِكَ يَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ وَلَا يُظْلَمُونَ نَقِيرًا

ከወንድ ወይም ከሴት አማኝ ሆነው ከበጎ ስራዎች አንድንም ነገር የሚሰሩ ገነት ይገባሉ። በተምር ፍሬ ላይ ያለችን ነጥብ ያክል እንኳን አይበደሉም።

وَمَنْ أَحْسَنُ دِينًا مِمَّنْ أَسْلَمَ وَجْهَهُ لِلَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ وَاتَّبَعَ مِلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا ۗ وَاتَّخَذَ اللَّهُ إِبْرَاهِيمَ خَلِيلًا

መልካም ሰሪ ሆኖ ፊቱን ለአላህ ከሰጠና የኢብራሂምን መንገድ ቀጥተኛ ሲሆን ከተከተለ ሰው ይበልጥ ሃይማኖቱ ያማረ ማን አለ? አላህ ኢብራሂምን ፍጹም ወዳጅ አድርጎ ያዘው።

وَلِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۚ وَكَانَ اللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ مُحِيطًا

በሰማያትና በምድር ያለው ነገር ሁሉ የአላህ ነው። አላህ በነገሩ ሁሉ በእውቀት ከባቢ ነው።

وَيَسْتَفْتُونَكَ فِي النِّسَاءِ ۖ قُلِ اللَّهُ يُفْتِيكُمْ فِيهِنَّ وَمَا يُتْلَىٰ عَلَيْكُمْ فِي الْكِتَابِ فِي يَتَامَى النِّسَاءِ اللَّاتِي لَا تُؤْتُونَهُنَّ مَا كُتِبَ لَهُنَّ وَتَرْغَبُونَ أَنْ تَنْكِحُوهُنَّ وَالْمُسْتَضْعَفِينَ مِنَ الْوِلْدَانِ وَأَنْ تَقُومُوا لِلْيَتَامَىٰ بِالْقِسْطِ ۚ وَمَا تَفْعَلُوا مِنْ خَيْرٍ فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ بِهِ عَلِيمًا

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ) ስለ ሴቶች ጉዳይ ይጠይቁሃል። «አላህ ስለነሱ ይነግራችኋል። ያም በመጽሐፍ ውስጥ በእናንተ ላይ የሚነበበው ሲሆን በእነዚያ ከውርስ የተደነገገላቸውን ድርሻ በማትሰጧቸውና ልታገቧቸው በማትፈልጉት የቲሞች ሴቶች ይህንን እንዳታደርጉ፤ ህፃናት ለሆኑትም ደካሞች መብታቸውን እንድትሰጡ፤ ለየቲሞች በትክክል እንድትቆሙ ይነገራችኋል።» በላቸው። ከበጎም ስራ የሆነን ማንኛውንም ስራ ብትሰሩ አላህ እርሱን አዋቂ ነው።

وَإِنِ امْرَأَةٌ خَافَتْ مِنْ بَعْلِهَا نُشُوزًا أَوْ إِعْرَاضًا فَلَا جُنَاحَ عَلَيْهِمَا أَنْ يُصْلِحَا بَيْنَهُمَا صُلْحًا ۚ وَالصُّلْحُ خَيْرٌ ۗ وَأُحْضِرَتِ الْأَنْفُسُ الشُّحَّ ۚ وَإِنْ تُحْسِنُوا وَتَتَّقُوا فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرًا

ሴት ልጅ ከባሏ ጥላቻን ወይም ከእርሷ ፊቱን ማዞሩን ብታውቅ እና ከዚያ በመካከላቸው እንደገና ቢስማሙ በሁለቱ ላይ ኃጢአት የለባቸዉም። መታረቅ መልካም ነውና። ነፍሶች ሁሉ ንፍገት ተጣለባቸው። (ባሎች ሆይ!) መልካም ነገር ብትሰሩና ብትጠነቀቁ ግን አላህ በምትሰሩት ነገር ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው።

وَلَنْ تَسْتَطِيعُوا أَنْ تَعْدِلُوا بَيْنَ النِّسَاءِ وَلَوْ حَرَصْتُمْ ۖ فَلَا تَمِيلُوا كُلَّ الْمَيْلِ فَتَذَرُوهَا كَالْمُعَلَّقَةِ ۚ وَإِنْ تُصْلِحُوا وَتَتَّقُوا فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ غَفُورًا رَحِيمًا

(ባሎች ሆይ! ) በሁለትና ከዚያ በላይ በሆኑ ሴቶች መካከል ምንም እንኳን ብትጓጉ በፍቅር ለማስተካከል አትችሉም። ሆኖም (ባል እንደሌላትና እንዳልተፈታች ሴት) እንደተንጠለጠለች አድርጋችሁ ትተዋት ዘንድ ወደምትወዷት ሴት ሙሉ መዘንበልን አትዘንበሉ። ብታበጁና ብትጠነቀቁ አላህ መሀሪና አዛኝ ነው።

وَإِنْ يَتَفَرَّقَا يُغْنِ اللَّهُ كُلًّا مِنْ سَعَتِهِ ۚ وَكَانَ اللَّهُ وَاسِعًا حَكِيمًا

ባልና ሚስት በመሀከላቸው በተፈጠረው ችግር ቢለያዩ አላህ ሁሉንም በችሮታው ያብቃቃቸዋል። አላህ ችሮታው ሰፊና ጥበበኛ ነውና።

وَلِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۗ وَلَقَدْ وَصَّيْنَا الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ مِنْ قَبْلِكُمْ وَإِيَّاكُمْ أَنِ اتَّقُوا اللَّهَ ۚ وَإِنْ تَكْفُرُوا فَإِنَّ لِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۚ وَكَانَ اللَّهُ غَنِيًّا حَمِيدًا

በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው። እነዚያንም ከበፊታችሁ መጽሐፍ የተሰጡትን እናንተንም አላህን ፍሩ በማለት በእርግጥ አዘዝን። ብትክዱም በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው (አትጎዱትም።) አላህ በራሱ ተብቃቂና ምስጉን ነውና።

وَلِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۚ وَكَفَىٰ بِاللَّهِ وَكِيلًا

በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ብቻ ነው። መመኪያነትም በአላህ በቃ።

إِنْ يَشَأْ يُذْهِبْكُمْ أَيُّهَا النَّاسُ وَيَأْتِ بِآخَرِينَ ۚ وَكَانَ اللَّهُ عَلَىٰ ذَٰلِكَ قَدِيرًا

(እናንተ ሰዎች ሆይ!) አላህ ቢሻ ያስወግዳችሁና ሌሎችን በቦታችሁ ላይ ይተካል። አላህም በዚህ ላይ ቻይ ነው።

مَنْ كَانَ يُرِيدُ ثَوَابَ الدُّنْيَا فَعِنْدَ اللَّهِ ثَوَابُ الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ ۚ وَكَانَ اللَّهُ سَمِيعًا بَصِيرًا

የቅርቢቱን አለም ምንዳ የሚፈልግ ሁሉ አላህ ዘንድ የቅርቢቱና የመጨረሻይቱ ምንዳ አለ። አላህ ሁሉን ሰሚ እና ሁሉን ተመልካች ነውና።

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ بِالْقِسْطِ شُهَدَاءَ لِلَّهِ وَلَوْ عَلَىٰ أَنْفُسِكُمْ أَوِ الْوَالِدَيْنِ وَالْأَقْرَبِينَ ۚ إِنْ يَكُنْ غَنِيًّا أَوْ فَقِيرًا فَاللَّهُ أَوْلَىٰ بِهِمَا ۖ فَلَا تَتَّبِعُوا الْهَوَىٰ أَنْ تَعْدِلُوا ۚ وَإِنْ تَلْوُوا أَوْ تُعْرِضُوا فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرًا

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በነፍሶቻችሁ ወይም በወላጆችና በቅርብ ዘመዶች ላይ ቢሆንም እንኳ በትክክል ለፍትህ ቋሚዎች ለአላህ መስካሪዎች ሁኑ። ሀብታም ወይም ድሃ ቢሆንም አላህ ለሁለቱም (ከእናንተ) ይበልጥ ተገቢ ነው። እንዳታዳሉም ዝንባሌን አትከተሉ። ምስክርን ብታጣምሙ ወይም መመስከርን ብትተው አላህ በምትሰሩት ነገር ላይ ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው።

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا آمِنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ وَالْكِتَابِ الَّذِي نَزَّلَ عَلَىٰ رَسُولِهِ وَالْكِتَابِ الَّذِي أَنْزَلَ مِنْ قَبْلُ ۚ وَمَنْ يَكْفُرْ بِاللَّهِ وَمَلَائِكَتِهِ وَكُتُبِهِ وَرُسُلِهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ فَقَدْ ضَلَّ ضَلَالًا بَعِيدًا

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህና በመልዕክተኛው በዚያ በመልዕክተኛው ላይ ባወረደው መጽሐፍም ከዚያ በፊትም ባወረደው መጽሐፍ እመኑ። በአላህ፣ በመላዕክቱ፣ በመጽሐፍቱ፣ በመልዕክተኞቹና በመጨረሻውም ቀን የካደ ሁሉ ከእውነት የራቀን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ።

إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا ثُمَّ كَفَرُوا ثُمَّ آمَنُوا ثُمَّ كَفَرُوا ثُمَّ ازْدَادُوا كُفْرًا لَمْ يَكُنِ اللَّهُ لِيَغْفِرَ لَهُمْ وَلَا لِيَهْدِيَهُمْ سَبِيلًا

እነዚያ ያመኑና ከዚያም የካዱ ከዚያም ያመኑ ከዚያም የካዱ ከዚያም ክህደትን የጨመሩ አላህ ለእነርሱ የሚምራቸውና ቅኑን መንገድም የሚመራቸው አይደለም።

بَشِّرِ الْمُنَافِقِينَ بِأَنَّ لَهُمْ عَذَابًا أَلِيمًا

አስመሳዮችን ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣት ያላቸው መሆኑን አብስራቸው።

الَّذِينَ يَتَّخِذُونَ الْكَافِرِينَ أَوْلِيَاءَ مِنْ دُونِ الْمُؤْمِنِينَ ۚ أَيَبْتَغُونَ عِنْدَهُمُ الْعِزَّةَ فَإِنَّ الْعِزَّةَ لِلَّهِ جَمِيعًا

እነዚያ ከአማኞች ሌላ ከሓዲያንን ወዳጆች አድርገው የሚይዙ ሰዎች እነርሱ ዘንድ ልቅናን ይፈልጋሉን? ልቅና ሁሉ ለአላህ ብቻ ነው።

وَقَدْ نَزَّلَ عَلَيْكُمْ فِي الْكِتَابِ أَنْ إِذَا سَمِعْتُمْ آيَاتِ اللَّهِ يُكْفَرُ بِهَا وَيُسْتَهْزَأُ بِهَا فَلَا تَقْعُدُوا مَعَهُمْ حَتَّىٰ يَخُوضُوا فِي حَدِيثٍ غَيْرِهِ ۚ إِنَّكُمْ إِذًا مِثْلُهُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ جَامِعُ الْمُنَافِقِينَ وَالْكَافِرِينَ فِي جَهَنَّمَ جَمِيعًا

በእናንተ ላይ በመጽሐፉ ውስጥ የአላህን አናቅጽ በእርሷ ሲካድባት በእርሷም ሲላገጥባት በሰማችሁ ጊዜ በሌላ ወሬ ውስጥ እስከሚገቡ ድረስ ከእነርሱ ጋር አትቀመጡ ማለትን በእርግጥ አወረደ። እናንተ ያን ጊዜ ቢጤያቸው ናችሁና። አላህ አስመሳዮችንም ከሓዲያንንም በገሀነም ውስጥ ሁሉንም ሰብሳቢ ነውና።

الَّذِينَ يَتَرَبَّصُونَ بِكُمْ فَإِنْ كَانَ لَكُمْ فَتْحٌ مِنَ اللَّهِ قَالُوا أَلَمْ نَكُنْ مَعَكُمْ وَإِنْ كَانَ لِلْكَافِرِينَ نَصِيبٌ قَالُوا أَلَمْ نَسْتَحْوِذْ عَلَيْكُمْ وَنَمْنَعْكُمْ مِنَ الْمُؤْمِنِينَ ۚ فَاللَّهُ يَحْكُمُ بَيْنَكُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۗ وَلَنْ يَجْعَلَ اللَّهُ لِلْكَافِرِينَ عَلَى الْمُؤْمِنِينَ سَبِيلًا

እነዚያ (አስመሳዮች) በእናንተ ላይ የጊዜ መዘዋወርን የሚጠባበቁ ናቸው። ለእናንተም ከአላህ የሆነ አሸናፊነት ሲኖራችሁ «ከናንተ ጋር አልነበርንምን?» ይላሉ። ለከሓዲያን እድል ሲኖር ደግሞ «ከአሁን በፊት እኛ በእናንተ ላይ የበላይ አልነበርንምን? (አልተውናችሁምን?) ከአማኞች አደጋስ አልከለከልናችሁምን?» ይላሉ። አላህ በትንሳኤ ቀን በመካከላችሁ ይፈርዳል። አላህ ለከሓዲያን በአማኞች ላይ መንገድን በፍጹም አያደርግም።

إِنَّ الْمُنَافِقِينَ يُخَادِعُونَ اللَّهَ وَهُوَ خَادِعُهُمْ وَإِذَا قَامُوا إِلَى الصَّلَاةِ قَامُوا كُسَالَىٰ يُرَاءُونَ النَّاسَ وَلَا يَذْكُرُونَ اللَّهَ إِلَّا قَلِيلًا

አስመሳዮች አላህን ያታልላሉ። እርሱም አታላያቸው ነው። ወደ ሶላትም በቆሙ ጊዜ ታካቾችና ሰዎችን የሚያሳዩ ሆነው ይቆማሉ። አላህንም ጥቂትን እንጂ አያወሱም።

مُذَبْذَبِينَ بَيْنَ ذَٰلِكَ لَا إِلَىٰ هَٰؤُلَاءِ وَلَا إِلَىٰ هَٰؤُلَاءِ ۚ وَمَنْ يُضْلِلِ اللَّهُ فَلَنْ تَجِدَ لَهُ سَبِيلًا

በዚህ መካከል ወላዋዮች ሆነው ይታያሉ። ወደ እነዚህም ወደ እነዚያም አይደሉም። አላህም ያሳሳተውን ለእርሱ የቅንነት መንገድን በፍጹም አታገኝለትም።

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا الْكَافِرِينَ أَوْلِيَاءَ مِنْ دُونِ الْمُؤْمِنِينَ ۚ أَتُرِيدُونَ أَنْ تَجْعَلُوا لِلَّهِ عَلَيْكُمْ سُلْطَانًا مُبِينًا

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከአማኞች ሌላ ከሓዲያንን ወዳጆች አድርጋችሁ አትያዙ። ለአላህ በእናንተ ላይ ግልጽ ማስረጃን ልታደርጉ ትፈልጋላችሁን?

إِنَّ الْمُنَافِقِينَ فِي الدَّرْكِ الْأَسْفَلِ مِنَ النَّارِ وَلَنْ تَجِدَ لَهُمْ نَصِيرًا

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አስመሳዮች በእርግጥ ከእሳት በታችኛዋ አዘቅት ውስጥ ናቸው። እናም ለእነርሱ ረዳትን አታገኝላቸዉም።

إِلَّا الَّذِينَ تَابُوا وَأَصْلَحُوا وَاعْتَصَمُوا بِاللَّهِ وَأَخْلَصُوا دِينَهُمْ لِلَّهِ فَأُولَٰئِكَ مَعَ الْمُؤْمِنِينَ ۖ وَسَوْفَ يُؤْتِ اللَّهُ الْمُؤْمِنِينَ أَجْرًا عَظِيمًا

እነዚያ የተመለሱና ስራቸውን ያሳመሩ በአላህ የተጠበቁ ሃይማኖታቸውንም ለአላህ ፍጹም ያደረጉት ሲቀሩ። እነዚያስ ከአማኞች ጋር ናቸው። ለአማኞችም አላህ ታላቅን ምንዳ በእርግጥ ይሰጣል።

مَا يَفْعَلُ اللَّهُ بِعَذَابِكُمْ إِنْ شَكَرْتُمْ وَآمَنْتُمْ ۚ وَكَانَ اللَّهُ شَاكِرًا عَلِيمًا

ብታመሰግኑና ብታምኑ አላህ እናንተን በመቅጣት ምን ያደርጋል? አላህም ወረታን መላሽ አዋቂ ነው።

لَا يُحِبُّ اللَّهُ الْجَهْرَ بِالسُّوءِ مِنَ الْقَوْلِ إِلَّا مَنْ ظُلِمَ ۚ وَكَانَ اللَّهُ سَمِيعًا عَلِيمًا

አላህ በክፉ ንግግር መጮህን ከተበደለ ሰው (ጩኸት) በስተቀር አይወድም። አላህ ሁሉን ሰሚ እና ሁሉን አዋቂ ነውና።

إِنْ تُبْدُوا خَيْرًا أَوْ تُخْفُوهُ أَوْ تَعْفُوا عَنْ سُوءٍ فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ عَفُوًّا قَدِيرًا

ደግ ነገርን ብትገልጹ ወይም ብትደብቁት ወይም ከመጥፎ ነገር (በደል) ይቅርታ ብታደርጉ አላህ ይቅር ባይ እና ቻይ ነው።

إِنَّ الَّذِينَ يَكْفُرُونَ بِاللَّهِ وَرُسُلِهِ وَيُرِيدُونَ أَنْ يُفَرِّقُوا بَيْنَ اللَّهِ وَرُسُلِهِ وَيَقُولُونَ نُؤْمِنُ بِبَعْضٍ وَنَكْفُرُ بِبَعْضٍ وَيُرِيدُونَ أَنْ يَتَّخِذُوا بَيْنَ ذَٰلِكَ سَبِيلًا

እነዚያ በአላህና በመልዕክተኞቹ የሚክዱ፤ በአላህና በመልዕክተኞቹም መካከል መለየትን የሚፈልጉና «በከፊሉ እናምናለን በከፊሉ ደግሞ እንክዳለን» የሚሉ ሁሉ በዚህ መካከል መንገድን ሊይዙ የሚፈልጉ፣

أُولَٰئِكَ هُمُ الْكَافِرُونَ حَقًّا ۚ وَأَعْتَدْنَا لِلْكَافِرِينَ عَذَابًا مُهِينًا

በእውነቱ እነዚያ ከሓዲያን እነርሱው ናቸው። ለከሓዲያንም አዋራጅን ቅጣት አዘጋጅተናል።

وَالَّذِينَ آمَنُوا بِاللَّهِ وَرُسُلِهِ وَلَمْ يُفَرِّقُوا بَيْنَ أَحَدٍ مِنْهُمْ أُولَٰئِكَ سَوْفَ يُؤْتِيهِمْ أُجُورَهُمْ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَحِيمًا

እነዚያ በአላህና በመልዕክተኞቹ ያመኑ፤ ከእነርሱም መካከል በአንዱም ያልለዩ ሰዎች እነዚያ ምንዳዎቻቸው በእርግጥ ይሰጣቸዋል። አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና።

يَسْأَلُكَ أَهْلُ الْكِتَابِ أَنْ تُنَزِّلَ عَلَيْهِمْ كِتَابًا مِنَ السَّمَاءِ ۚ فَقَدْ سَأَلُوا مُوسَىٰ أَكْبَرَ مِنْ ذَٰلِكَ فَقَالُوا أَرِنَا اللَّهَ جَهْرَةً فَأَخَذَتْهُمُ الصَّاعِقَةُ بِظُلْمِهِمْ ۚ ثُمَّ اتَّخَذُوا الْعِجْلَ مِنْ بَعْدِ مَا جَاءَتْهُمُ الْبَيِّنَاتُ فَعَفَوْنَا عَنْ ذَٰلِكَ ۚ وَآتَيْنَا مُوسَىٰ سُلْطَانًا مُبِينًا

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የመጽሐፉ ባለቤቶች እነርሱ ላይ ከሰማይ መጽሐፍን እንድታወርድ ይጠይቁሃል። ከዚህም የከበደን ጥያቄ ከዚህ በፊት ሙሳን በእርግጥ ጠይቀዋል። «አላህን በግልጽ አሳየን።» ብለዋል። በበደላቸዉም ምክንያት መብረቅ ያዘቻቸው። ከዚያም ተዓምራት ከመጡላቸው በኋላ ወይፈኑን አምላክ አድርገው ያዙ። ከዚያ ያንን ይቅር አልን። ሙሳንም ግልጽ ስልጣን ሰጠነው።

وَرَفَعْنَا فَوْقَهُمُ الطُّورَ بِمِيثَاقِهِمْ وَقُلْنَا لَهُمُ ادْخُلُوا الْبَابَ سُجَّدًا وَقُلْنَا لَهُمْ لَا تَعْدُوا فِي السَّبْتِ وَأَخَذْنَا مِنْهُمْ مِيثَاقًا غَلِيظًا

በቃል ኪዳናቸው ምክንያት የጡር ተራራን ከበላያቸው አነሳን። ለእነርሱም «ደጃፍን ስትገቡ አጎንብሳችሁ ግቡ።» አልን። ለእነርሱም «በሰንበት ቀን ትዕዛዝን አትተላለፉ።» አልን። ከእነርሱም ከባድን ቃል ኪዳን ያዝን።

فَبِمَا نَقْضِهِمْ مِيثَاقَهُمْ وَكُفْرِهِمْ بِآيَاتِ اللَّهِ وَقَتْلِهِمُ الْأَنْبِيَاءَ بِغَيْرِ حَقٍّ وَقَوْلِهِمْ قُلُوبُنَا غُلْفٌ ۚ بَلْ طَبَعَ اللَّهُ عَلَيْهَا بِكُفْرِهِمْ فَلَا يُؤْمِنُونَ إِلَّا قَلِيلًا

ቃል ኪዳናቸውን በማፍረሳቸው፤ በአላህ አናቅጽ በመካዳቸው፤ ነብያትን ያለ አግባብ በመግደላቸውና «ልቦቻችን ሽፍን ናቸው።» በማለታቸውም ምክንያት (ረገምናቸው)። በእውነቱ በክህደታቸው ምክንያት አላህ በእርሷ ላይ አተመ። ስለዚህ ጥቂትን እንጂ አያምኑም።

وَبِكُفْرِهِمْ وَقَوْلِهِمْ عَلَىٰ مَرْيَمَ بُهْتَانًا عَظِيمًا

በመካዳቸዉም በመርየም ላይ ከባድ ቅጥፈትን በመናገራቸው ምክንያት ረገምናቸው።

وَقَوْلِهِمْ إِنَّا قَتَلْنَا الْمَسِيحَ عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ رَسُولَ اللَّهِ وَمَا قَتَلُوهُ وَمَا صَلَبُوهُ وَلَٰكِنْ شُبِّهَ لَهُمْ ۚ وَإِنَّ الَّذِينَ اخْتَلَفُوا فِيهِ لَفِي شَكٍّ مِنْهُ ۚ مَا لَهُمْ بِهِ مِنْ عِلْمٍ إِلَّا اتِّبَاعَ الظَّنِّ ۚ وَمَا قَتَلُوهُ يَقِينًا

«እኛ የአላህ መልዕክተኛ የመርየም ልጅ አል መሲህ ዒሳን ገደልን።» በማለታቸውም ረገምናቸው። አልገደሉትም። አልሰቀሉትምም። ግን (የተገደለው ሰው ለእነርሱ በዒሳ) ተመሰለባቸው። እነዚያ በእርሱ ጉዳይ የተለያዩት በእርሱ መገደል በመጠራጠር ውስጥ ናቸው። ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በእርሱ ነገር ምንም እርግጠኛ እውቀት የላቸዉም። በእርግጥም አልገደሉትም።

بَلْ رَفَعَهُ اللَّهُ إِلَيْهِ ۚ وَكَانَ اللَّهُ عَزِيزًا حَكِيمًا

ይልቁንስ አላህ ወደ እርሱ አነሳው። አላህም አሸናፊና ጥበበኛ ነው።

وَإِنْ مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ إِلَّا لَيُؤْمِنَنَّ بِهِ قَبْلَ مَوْتِهِ ۖ وَيَوْمَ الْقِيَامَةِ يَكُونُ عَلَيْهِمْ شَهِيدًا

ከመጽሐፉ ባለቤቶች መካከልም ከነብዩ ዒሳ ሞት በፊት በነብዩ ዒሳ በእርግጥ በትክክል የሚያምን እንጂ አንድም የለም። በትንሳኤ ቀንም ዒሳ በእነርሱ ላይ መስካሪ ይሆናል።

فَبِظُلْمٍ مِنَ الَّذِينَ هَادُوا حَرَّمْنَا عَلَيْهِمْ طَيِّبَاتٍ أُحِلَّتْ لَهُمْ وَبِصَدِّهِمْ عَنْ سَبِيلِ اللَّهِ كَثِيرًا

ከእነዚያ ከአይሁዳውያን መካከል በፈጸሙት በደልና ሰዎችን ከአላህ መንገድ በብዙ በመከላከላቸው ምክንያት ለእነርሱ ተፈቅደው የነበሩ ጣፋጭ ምግቦችን እርም አደረግንባቸው።

وَأَخْذِهِمُ الرِّبَا وَقَدْ نُهُوا عَنْهُ وَأَكْلِهِمْ أَمْوَالَ النَّاسِ بِالْبَاطِلِ ۚ وَأَعْتَدْنَا لِلْكَافِرِينَ مِنْهُمْ عَذَابًا أَلِيمًا

ከእርሱ በቁርጥ የተከለከሉ ሲሆኑ አራጣን በመያዛቸውና የሰዎችን ገንዘቦች ያለ አግባቡ በመብላታቸዉም ምክንያት የተፈቀደላቸውን እርም አደረግንባቸው። ከእነርሱም መካከል ለከሓዲያን አሳማሚ ቅጣት አዘጋጀን።

لَٰكِنِ الرَّاسِخُونَ فِي الْعِلْمِ مِنْهُمْ وَالْمُؤْمِنُونَ يُؤْمِنُونَ بِمَا أُنْزِلَ إِلَيْكَ وَمَا أُنْزِلَ مِنْ قَبْلِكَ ۚ وَالْمُقِيمِينَ الصَّلَاةَ ۚ وَالْمُؤْتُونَ الزَّكَاةَ وَالْمُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ أُولَٰئِكَ سَنُؤْتِيهِمْ أَجْرًا عَظِيمًا

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ግን ከእነርሱ ውስጥ በእውቀት የጠለቁት ክፍሎችና ትክክለኛ ምዕመናኖቹ ባንተ ላይ በተወረደውና ካንተ በፊት በተወረደው መጽሐፍ ያምናሉ። ሶላትንም ደንቡን ጠብቀው ሰጋጆቹ፣ ዘካንም ሰጪዎቹ በአላህና በመጨረሻው ቀንም ትክክለኛ አማኞቹን እነዚያ ታላቅ ምንዳን በእርግጥ እንሰጣቸዋለን።

إِنَّا أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ كَمَا أَوْحَيْنَا إِلَىٰ نُوحٍ وَالنَّبِيِّينَ مِنْ بَعْدِهِ ۚ وَأَوْحَيْنَا إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَعِيسَىٰ وَأَيُّوبَ وَيُونُسَ وَهَارُونَ وَسُلَيْمَانَ ۚ وَآتَيْنَا دَاوُودَ زَبُورًا

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ ወደ ኑህና ከእርሱ በኋላ ወደ ነበሩት ነብያት መልዕክታችንን እንዳወረድን ሁሉ ወደ አንተም ቁርኣንን አወረድን። ወደ ነብዩ ኢብራሂም፤ ወደ ነብዩ ኢስማኢልም፤ ወደ ነብዩ ኢስሃቅም፤ ወደ ነብዩ የዕቆብም፤ ወደ ነገዶችም፤ ወደ ነብዩ ዒሳም፤ ወደ ነብዩ አዩብም፤ ወደ ነብዩ ዩኑስም፤ ወደ ነብዩ ሃሩንና ወደ ነብዩ ሱለይማን አወረድን። ለነብዩ ዳውድም ዘቡርን ሰጠነው።

وَرُسُلًا قَدْ قَصَصْنَاهُمْ عَلَيْكَ مِنْ قَبْلُ وَرُسُلًا لَمْ نَقْصُصْهُمْ عَلَيْكَ ۚ وَكَلَّمَ اللَّهُ مُوسَىٰ تَكْلِيمًا

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከዚህም በፊት በአንተ ላይ በእርግጥ የተረክናቸውን መልዕክተኞች ባንተ ላይም ያልተረክናቸውንም መልዕክተኞች እንደላክን ሁሉ አንተን ላክንህ። አላህ ነብዩ ሙሳንም ማነጋገርን አነጋገረው።

رُسُلًا مُبَشِّرِينَ وَمُنْذِرِينَ لِئَلَّا يَكُونَ لِلنَّاسِ عَلَى اللَّهِ حُجَّةٌ بَعْدَ الرُّسُلِ ۚ وَكَانَ اللَّهُ عَزِيزًا حَكِيمًا

ከመልዕክተኞች በኋላ ለሰዎች በአላህ ላይ ምንም አስረጂ እንዳይኖራቸው አብሳሪዎችና አስፈራሪዎች አድርገን መልዕክተኞችን ላክን። አላህ ሁሉን አሸናፊ፤ ጥበበኛ ነውና።

لَٰكِنِ اللَّهُ يَشْهَدُ بِمَا أَنْزَلَ إِلَيْكَ ۖ أَنْزَلَهُ بِعِلْمِهِ ۖ وَالْمَلَائِكَةُ يَشْهَدُونَ ۚ وَكَفَىٰ بِاللَّهِ شَهِيدًا

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ግን ባንተ ላይ ባወረደው ቁርኣን ይመሰክራል። በእውቀቱ አወረደው። መላዕክቱም ይመሰክራሉ። መስካሪነትም በአላህ ብቻ በቃ።

إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا وَصَدُّوا عَنْ سَبِيلِ اللَّهِ قَدْ ضَلُّوا ضَلَالًا بَعِيدًا

እነዚያ በአላህ የካዱና ከአላህ መንገድም ሰዎችን ያገዱ ሰዎች ከእውነት የራቀን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳቱ።

إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا وَظَلَمُوا لَمْ يَكُنِ اللَّهُ لِيَغْفِرَ لَهُمْ وَلَا لِيَهْدِيَهُمْ طَرِيقًا

እነዚያ የካዱና የበደሉ አላህ የሚምራቸውና ቅን መንገድን የሚመራቸው አይደለም።

إِلَّا طَرِيقَ جَهَنَّمَ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا ۚ وَكَانَ ذَٰلِكَ عَلَى اللَّهِ يَسِيرًا

ግን በውስጧ ለዘልዓለም ዘወታሪዎች ሲሆኑ የገሀነምን መንገድ ይመራቸዋል። ይህም በአላህ ላይ ገር ነው።

يَا أَيُّهَا النَّاسُ قَدْ جَاءَكُمُ الرَّسُولُ بِالْحَقِّ مِنْ رَبِّكُمْ فَآمِنُوا خَيْرًا لَكُمْ ۚ وَإِنْ تَكْفُرُوا فَإِنَّ لِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ وَكَانَ اللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمًا

እናንተ ሰዎች ሆይ! መልዕክተኛው እውነትን ከጌታችሁ አመጣላችሁ። እናም ባመጣው እመኑ ለእናንተ የተሻለ ይሆናል። በአላህ ብትክዱም (እሱን ቅንጣት አትጎዱትም።) በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነውና። አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው።

يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لَا تَغْلُوا فِي دِينِكُمْ وَلَا تَقُولُوا عَلَى اللَّهِ إِلَّا الْحَقَّ ۚ إِنَّمَا الْمَسِيحُ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ رَسُولُ اللَّهِ وَكَلِمَتُهُ أَلْقَاهَا إِلَىٰ مَرْيَمَ وَرُوحٌ مِنْهُ ۖ فَآمِنُوا بِاللَّهِ وَرُسُلِهِ ۖ وَلَا تَقُولُوا ثَلَاثَةٌ ۚ انْتَهُوا خَيْرًا لَكُمْ ۚ إِنَّمَا اللَّهُ إِلَٰهٌ وَاحِدٌ ۖ سُبْحَانَهُ أَنْ يَكُونَ لَهُ وَلَدٌ ۘ لَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۗ وَكَفَىٰ بِاللَّهِ وَكِيلًا

እናንተ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ። በአላህም ላይ እውነትን እንጂ አትናገሩ። የመርየም ልጅ አል መሲህ ዒሳ የአላህ መልዕክተኛ ወደ መርየም የጣላት የሁን ቃሉና ከእርሱ የሆነ መንፈስ ብቻ ነው። በአላህና በመልዕክተኞቹ እመኑ። «አማልክት ሶስት ናቸው።» አትበሉ። ተከልከሉ። ለእናንተ የተሻለ ይሆናልና። አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው። ለእርሱም ልጅ ያለው ከመሆን የጠራ ነው። በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው። መመኪያነትም በአላህ በቃ።

لَنْ يَسْتَنْكِفَ الْمَسِيحُ أَنْ يَكُونَ عَبْدًا لِلَّهِ وَلَا الْمَلَائِكَةُ الْمُقَرَّبُونَ ۚ وَمَنْ يَسْتَنْكِفْ عَنْ عِبَادَتِهِ وَيَسْتَكْبِرْ فَسَيَحْشُرُهُمْ إِلَيْهِ جَمِيعًا

አል መሲህ ለአላህ ባሪያ ከመሆን (አላህን ከመገዛት) ፈጽሞ አይጸየፍም። ቀራቢዎች የሆኑ መላዕክትም እንዲሁ ለአላህ ባሪያ ከመሆን ፈጽሞ አይጸየፉም። እርሱን ከመገዛት የሚጸየፉና የሚኮሩ ሁሉ (አላህ) ሁሉንም ወደ እርሱ በእርግጥ ይሰበስባቸዋል።

فَأَمَّا الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ فَيُوَفِّيهِمْ أُجُورَهُمْ وَيَزِيدُهُمْ مِنْ فَضْلِهِ ۖ وَأَمَّا الَّذِينَ اسْتَنْكَفُوا وَاسْتَكْبَرُوا فَيُعَذِّبُهُمْ عَذَابًا أَلِيمًا وَلَا يَجِدُونَ لَهُمْ مِنْ دُونِ اللَّهِ وَلِيًّا وَلَا نَصِيرًا

እነዚያ በአላህ ያመኑና መልካም ተግባራትን የሰሩትን ምንዳዎቻቸውን ይሞላላቸዋል። ከችሮታዉም ይጨምርላቸዋል። እነዚያን የተጸየፉትና የኮሩትን ግን አሳማሚውን ቅጣት ይቀጣቸዋል። ከአላህ ሌላ ለእነርሱ ጠባቂንና ረዳት አያገኙም።

يَا أَيُّهَا النَّاسُ قَدْ جَاءَكُمْ بُرْهَانٌ مِنْ رَبِّكُمْ وَأَنْزَلْنَا إِلَيْكُمْ نُورًا مُبِينًا

እናንተ ሰዎች ሆይ! ከጌታችሁ ዘንድ በእርግጥም አስረጅ መጣላችሁ። ወደ እናንተም ገላጭ የሆነን ብርሃንን (ቁርኣንን) አወረድን።

فَأَمَّا الَّذِينَ آمَنُوا بِاللَّهِ وَاعْتَصَمُوا بِهِ فَسَيُدْخِلُهُمْ فِي رَحْمَةٍ مِنْهُ وَفَضْلٍ وَيَهْدِيهِمْ إِلَيْهِ صِرَاطًا مُسْتَقِيمًا

እነዚያማ በአላህ ያመኑና በእርሱ የተጠበቁ ሰዎች ከእርሱ በሆነው እዝነትና ችሮታ ውስጥ እርግጥ ያስገባቸዋል። ወደ እርሱም ቀጥተኛ መንገድን ይመራቸዋልም።

يَسْتَفْتُونَكَ قُلِ اللَّهُ يُفْتِيكُمْ فِي الْكَلَالَةِ ۚ إِنِ امْرُؤٌ هَلَكَ لَيْسَ لَهُ وَلَدٌ وَلَهُ أُخْتٌ فَلَهَا نِصْفُ مَا تَرَكَ ۚ وَهُوَ يَرِثُهَا إِنْ لَمْ يَكُنْ لَهَا وَلَدٌ ۚ فَإِنْ كَانَتَا اثْنَتَيْنِ فَلَهُمَا الثُّلُثَانِ مِمَّا تَرَكَ ۚ وَإِنْ كَانُوا إِخْوَةً رِجَالًا وَنِسَاءً فَلِلذَّكَرِ مِثْلُ حَظِّ الْأُنْثَيَيْنِ ۗ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمْ أَنْ تَضِلُّوا ۗ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይጠይቁሃል: «ወላጆችና ልጅ ሳይኖረው በሚወረስ ሟች ሰው ጉዳይ አላህ ይነግራችኋል።» በላቸው። ልጅ የሌለው ሰው ቢሞትና ለእርሱ እህት ብትኖረው ለእርሷ ከተወው ንብረት ግማሽ አላት። እርሱም ለእርሷ ልጅ የሌላት እንደሆነች በሙሉ ይወርሳታል። ሁለት እህቶች (ወይም ከሁለት በላይ) ቢሆኑ ግን ከተወው ንብረት ከሶስት ሁለት እጅ አላቸው ። ወንድሞችና እህቶች ወንዶችና ሴቶች ቢሆኑ ደግሞ ለወንድ የሁለት ሴቶች ድርሻ ያህል አለው ። አላህ እንዳትሳሳቱ ህግጋትን ለእናንተ ያብራራል ። አላህ በነገሩ ሁሉ አዋቂ ነውና።