Detailed · Fussilat · سورة فصلت · 54 ayahs

القرآن الكريمAfrica Academy

بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።

حم

ሓ፤ ሚይም፤

تَنْزِيلٌ مِنَ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

ይህ ቁርኣን እጅግ በጣም ሩህሩህና በጣም አዛኝ ከሆነው ጌታ ከአላህ የተወረደ ነው።

كِتَابٌ فُصِّلَتْ آيَاتُهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لِقَوْمٍ يَعْلَمُونَ

አናቅጾቹ የተብራሩ የሆነ መጽሐፍ ነው። ዐረበኛ ቁርኣን ሲሆን ለሚያውቁ ሕዝቦች የተብራራ ነው።

بَشِيرًا وَنَذِيرًا فَأَعْرَضَ أَكْثَرُهُمْ فَهُمْ لَا يَسْمَعُونَ

አብሳሪና አስፈራሪ ሲሆን ተወረደ። አብዛኞቻቸዉም ተውት። እነርሱም አይሰሙም።

وَقَالُوا قُلُوبُنَا فِي أَكِنَّةٍ مِمَّا تَدْعُونَا إِلَيْهِ وَفِي آذَانِنَا وَقْرٌ وَمِنْ بَيْنِنَا وَبَيْنِكَ حِجَابٌ فَاعْمَلْ إِنَّنَا عَامِلُونَ

አሉም፡- «ልቦቻችን ከዚያ ወደርሱ ከምትጠራን እምነት በመሸፈኛዎች ውስጥ ናቸው። በጆሮቻችንም ላይ ድንቁርና አለ። በእኛና በአንተ መካከል ግርዶሽ አለ። በሃይማኖትህ ስራ እኛም ሰሪዎች ነንና።»

قُلْ إِنَّمَا أَنَا بَشَرٌ مِثْلُكُمْ يُوحَىٰ إِلَيَّ أَنَّمَا إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌ وَاحِدٌ فَاسْتَقِيمُوا إِلَيْهِ وَاسْتَغْفِرُوهُ ۗ وَوَيْلٌ لِلْمُشْرِكِينَ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እንዲህ በላቸው «እኔ መሰላችሁ ሰው ብቻ ነኝ። ወደ እኔ ‹አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው። ወደ እርሱም ቀጥ በሉ። ምህረትንም ለምኑት› ተብሎ ይወርድልኛል።» ለአጋሪዎችም ወዮላቸው።

الَّذِينَ لَا يُؤْتُونَ الزَّكَاةَ وَهُمْ بِالْآخِرَةِ هُمْ كَافِرُونَ

ለእነዚያ ዘካን ለማይሰጡ እነርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም እነርሱ ከሓዲያን ለሆኑት (ወዮላቸው)።

إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ لَهُمْ أَجْرٌ غَيْرُ مَمْنُونٍ

እነዚያ ያመኑትና በጎ ስራዎችንም የሰሩት ሁሉ ለእነርሱ የማይቋረጥ ምንዳ አላቸው።

قُلْ أَئِنَّكُمْ لَتَكْفُرُونَ بِالَّذِي خَلَقَ الْأَرْضَ فِي يَوْمَيْنِ وَتَجْعَلُونَ لَهُ أَنْدَادًا ۚ ذَٰلِكَ رَبُّ الْعَالَمِينَ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ !) «እናንተ በዚያ ምድርን በሁለት ቀናት ውስጥ በፈጠረው አምላክ በእርግጥ ትክዳላችሁን? ለእርሱም ባላንጣዎች ታደርጋላችሁን? ያ (ይህንን የሰራው) የዓለማቱ ጌታ ነው።» በላቸው።

وَجَعَلَ فِيهَا رَوَاسِيَ مِنْ فَوْقِهَا وَبَارَكَ فِيهَا وَقَدَّرَ فِيهَا أَقْوَاتَهَا فِي أَرْبَعَةِ أَيَّامٍ سَوَاءً لِلسَّائِلِينَ

በእርሷም ከበላይዋ የረጉ ጋራዎችን አደረገ። በእርሷም በረከትን አደረገ። በውስጧም ምግቦችዋን (ካለፉት ሁለት ቀኖች ጋር) በአራት ቀናት ውስጥ ለጠያቂዎች ትክክል ሲሆን ወሰነ።

ثُمَّ اسْتَوَىٰ إِلَى السَّمَاءِ وَهِيَ دُخَانٌ فَقَالَ لَهَا وَلِلْأَرْضِ ائْتِيَا طَوْعًا أَوْ كَرْهًا قَالَتَا أَتَيْنَا طَائِعِينَ

ከዚያም እርሷ ጭስ ሆና ሳለች ወደ ሰማይ አሰበ። ለእርሷም ለምድርም «ወዳችሁም ሆነ ጠልታችሁ ኑ» አላቸው። «ታዛዦች ሆነን መጣን» አሉ።

فَقَضَاهُنَّ سَبْعَ سَمَاوَاتٍ فِي يَوْمَيْنِ وَأَوْحَىٰ فِي كُلِّ سَمَاءٍ أَمْرَهَا ۚ وَزَيَّنَّا السَّمَاءَ الدُّنْيَا بِمَصَابِيحَ وَحِفْظًا ۚ ذَٰلِكَ تَقْدِيرُ الْعَزِيزِ الْعَلِيمِ

በሁለት ቀናትም ውስጥ ሰባት ሰማያት አደረጋቸው። በሰማያትም ሁሉ ነገሯን አዘጋጀ። ቅርቢቱንም ሰማይ በመብራቶች አጌጥን። (ከሰይጣናት) መጠበቅንም ጠበቅናት። ይህ የአሸናፊውና የአዋቂው ጌታ ውሳኔ ነው።

فَإِنْ أَعْرَضُوا فَقُلْ أَنْذَرْتُكُمْ صَاعِقَةً مِثْلَ صَاعِقَةِ عَادٍ وَثَمُودَ

ከእምነት እምቢ ቢሉም (እንዲህ) በላቸው: «እንደ ዓድና ሰሙድ መቅሰፍት ብጤ የሆነን መቅሰፍት አስጠነቅቄያችኋለሁ።»

إِذْ جَاءَتْهُمُ الرُّسُلُ مِنْ بَيْنِ أَيْدِيهِمْ وَمِنْ خَلْفِهِمْ أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا اللَّهَ ۖ قَالُوا لَوْ شَاءَ رَبُّنَا لَأَنْزَلَ مَلَائِكَةً فَإِنَّا بِمَا أُرْسِلْتُمْ بِهِ كَافِرُونَ

መልዕክተኞቹ «አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ» በማለት ከበስተፊታቸዉም ከበስተኋላቸዉም በመጡባቸው ጊዜ «ጌታችን በሻ ኖሮ መላዕክትን ባወረደ ነበር። ስለዚህ እኛ በዚህ በእርሱ በተላካችሁት ከሓዲያን ነን።» አሉ።

فَأَمَّا عَادٌ فَاسْتَكْبَرُوا فِي الْأَرْضِ بِغَيْرِ الْحَقِّ وَقَالُوا مَنْ أَشَدُّ مِنَّا قُوَّةً ۖ أَوَلَمْ يَرَوْا أَنَّ اللَّهَ الَّذِي خَلَقَهُمْ هُوَ أَشَدُّ مِنْهُمْ قُوَّةً ۖ وَكَانُوا بِآيَاتِنَا يَجْحَدُونَ

የዓድም ነገዶችም በምድር ላይ ያለ አግባብ ኮሩ፤ ከእኛ ይበልጥ በኃይል ብርቱ ማን ነው ? አሉም ያ የፈጠራቸው አላህ እርሱ በኃይል ከእነርሱ ይበልጥ የበረታ መሆኑን አያውቁምን? በታዐምራታችንም ይክዱ ነበር።

فَأَرْسَلْنَا عَلَيْهِمْ رِيحًا صَرْصَرًا فِي أَيَّامٍ نَحِسَاتٍ لِنُذِيقَهُمْ عَذَابَ الْخِزْيِ فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا ۖ وَلَعَذَابُ الْآخِرَةِ أَخْزَىٰ ۖ وَهُمْ لَا يُنْصَرُونَ

በቅርቢቱ ሕይወት የውርደትን ቅጣት ልናቀምሳቸዉም በእነርሱ ላይ የሚንሻሻ ብርቱ ነፋስ መናጢዎች በሆኑ ቀናት ውስጥ ላክንባቸው። የመጨረሻይቱም ዓለም ስቃይ በጣም አዋራጅ ነው። እነርሱም አይረዱም።

وَأَمَّا ثَمُودُ فَهَدَيْنَاهُمْ فَاسْتَحَبُّوا الْعَمَىٰ عَلَى الْهُدَىٰ فَأَخَذَتْهُمْ صَاعِقَةُ الْعَذَابِ الْهُونِ بِمَا كَانُوا يَكْسِبُونَ

ሰሙዶችማ ወደ ቀናው መንገድ መራናቸው። እነርሱ ግን እውርነትን ከቅንነት ይልቅ መረጡ። ይሰሩትም በነበሩት ኃጢአት አዋራጅ የሆነችው የመብረቅ ቅጣት ያዘቻቸው።

وَنَجَّيْنَا الَّذِينَ آمَنُوا وَكَانُوا يَتَّقُونَ

እነዚያንም ያመኑትንና ይጠነቀቁ የነበሩትንም አዳንናቸው።

وَيَوْمَ يُحْشَرُ أَعْدَاءُ اللَّهِ إِلَى النَّارِ فَهُمْ يُوزَعُونَ

የአላህም ጠላቶች ወደ እሳት የሚሰበሰቡበትን ቀን አስታውሱ። የሚከመከሙ ሆነውም ይነዳሉ።

حَتَّىٰ إِذَا مَا جَاءُوهَا شَهِدَ عَلَيْهِمْ سَمْعُهُمْ وَأَبْصَارُهُمْ وَجُلُودُهُمْ بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ

በመጧትም ጊዜ ጆሮዎቻቸው፤ ዓይኖቻቸውና ቆዳዎቻቸዉም ይሰሩት በነበረ ነገር በእነርሱ ላይ ይመሰክሩባቸዋል።

وَقَالُوا لِجُلُودِهِمْ لِمَ شَهِدْتُمْ عَلَيْنَا ۖ قَالُوا أَنْطَقَنَا اللَّهُ الَّذِي أَنْطَقَ كُلَّ شَيْءٍ وَهُوَ خَلَقَكُمْ أَوَّلَ مَرَّةٍ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ

ለቆዳዎቻቸዉም «በእኛ ላይ ለምን መሰከራችሁብን?» ይላሉ። «ያ ሁሉን ነገር ያናገረው አላህ አናገረን። እርሱም (ነው) በመጀመሪያ ጊዜ የፈጠራችሁ። ወደ እርሱም ብቻ ትመለሳላችሁ» ይሏቸዋል።

وَمَا كُنْتُمْ تَسْتَتِرُونَ أَنْ يَشْهَدَ عَلَيْكُمْ سَمْعُكُمْ وَلَا أَبْصَارُكُمْ وَلَا جُلُودُكُمْ وَلَٰكِنْ ظَنَنْتُمْ أَنَّ اللَّهَ لَا يَعْلَمُ كَثِيرًا مِمَّا تَعْمَلُونَ

ጆሮዎቻችሁ ዓይኖቻችሁና ቆዳዎቻችሁ በእናንተ ላይ እንዳይመሰክሩባችሁ የምትደበቁባቸው አልነበራችሁም። ግን አላህ ከምትሰሩት ብዙውን አያውቅም ብላችሁ ጠረጠራችሁ።

وَذَٰلِكُمْ ظَنُّكُمُ الَّذِي ظَنَنْتُمْ بِرَبِّكُمْ أَرْدَاكُمْ فَأَصْبَحْتُمْ مِنَ الْخَاسِرِينَ

ይህም በጌታችሁ የጠረጣችሁት ጥርጣሬያችሁ አጠፋችሁ። ከከሳሪዎችም ሆናችሁ ይባላሉ።

فَإِنْ يَصْبِرُوا فَالنَّارُ مَثْوًى لَهُمْ ۖ وَإِنْ يَسْتَعْتِبُوا فَمَا هُمْ مِنَ الْمُعْتَبِينَ

ቢታገሱም እሳት ለእነርሱ መኖሪያቸው ናት። ወደ ሚወዱት መመለስንም ቢጠይቁ እነርሱ ተቀባይ የሚያገኙ አይደሉም።

وَقَيَّضْنَا لَهُمْ قُرَنَاءَ فَزَيَّنُوا لَهُمْ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَحَقَّ عَلَيْهِمُ الْقَوْلُ فِي أُمَمٍ قَدْ خَلَتْ مِنْ قَبْلِهِمْ مِنَ الْجِنِّ وَالْإِنْسِ ۖ إِنَّهُمْ كَانُوا خَاسِرِينَ

ለእነርሱም ቁራኛዎችን አዘጋጀንላቸው። በፊታቸው ያለውንና በኋላቸው ያለውንም ሁሉ ለእነርሱ ሸለሙላቸው። ከአጋንንትና ከሰዉም ከእነርሱ በፊት በእርግጥ ካለፉት ህዝቦች ጋር ሆነው ቃሉ በእነርሱ ላይ ተረጋገጠባቸው። እነርሱ በእርግጥ ከሳሪዎች ነበሩና።

وَقَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا لَا تَسْمَعُوا لِهَٰذَا الْقُرْآنِ وَالْغَوْا فِيهِ لَعَلَّكُمْ تَغْلِبُونَ

እነዚያም በአላህ የካዱት ሰዎች «ይህንን ቁርኣን አታዳምጡ ታሸንፉም ዘንድ ሲነበብም ተንጫጩበት።» አሉ።

فَلَنُذِيقَنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا عَذَابًا شَدِيدًا وَلَنَجْزِيَنَّهُمْ أَسْوَأَ الَّذِي كَانُوا يَعْمَلُونَ

እነዚያንም በአላህ የካዱትን ብርቱ ቅጣት እናቀምሳቸዋለን። የእነዚያንም ይሰሩት በነበሩት እጅግ መጥፎ ስራ ፍዳ እንመነዳቸዋለን።

ذَٰلِكَ جَزَاءُ أَعْدَاءِ اللَّهِ النَّارُ ۖ لَهُمْ فِيهَا دَارُ الْخُلْدِ ۖ جَزَاءً بِمَا كَانُوا بِآيَاتِنَا يَجْحَدُونَ

ይህ የአላህ ጠላቶች ፍዳ እሳት ነው። በውስጧም ለእነርሱ የዘላለም መኖሪያ አገር አላቸው። በአንቀፆቻችን ይክዱ በነበሩት ምንዳ ይመነዳሉ።

وَقَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا رَبَّنَا أَرِنَا اللَّذَيْنِ أَضَلَّانَا مِنَ الْجِنِّ وَالْإِنْسِ نَجْعَلْهُمَا تَحْتَ أَقْدَامِنَا لِيَكُونَا مِنَ الْأَسْفَلِينَ

እነዚያም በአላህ የካዱት (በእሳት ውስጥ ሆነው) «ጌታችን ሆይ! እነዚያ ከአጋንንትና ከሰው ያሳሳቱንን ሁለቱን አሳየን። ከታችኞች ይሆኑ ዘንድ ከጫማዎቻችን ስር እናደርጋቸዋለንና» ይላሉ።

إِنَّ الَّذِينَ قَالُوا رَبُّنَا اللَّهُ ثُمَّ اسْتَقَامُوا تَتَنَزَّلُ عَلَيْهِمُ الْمَلَائِكَةُ أَلَّا تَخَافُوا وَلَا تَحْزَنُوا وَأَبْشِرُوا بِالْجَنَّةِ الَّتِي كُنْتُمْ تُوعَدُونَ

እነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ያሉና ከዚያም ቀጥ ያሉ። እንዲህ እያሉ መላዕክቱ በነርሱ ላይ ይወርዳሉ። «አትፍሩ አትዘኑ። በዚያች ተስፋ ቃል ትደረጉባት በነበራችሁት ገነት ተበሰሩ።

نَحْنُ أَوْلِيَاؤُكُمْ فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا وَفِي الْآخِرَةِ ۖ وَلَكُمْ فِيهَا مَا تَشْتَهِي أَنْفُسُكُمْ وَلَكُمْ فِيهَا مَا تَدَّعُونَ

«እኛ በቅርቢቱም ሕይወት በመጨረሻይቱም ረዳቶቻችሁ ነን! ለእናንተም በእርሷ ውስጥ ነፍሶቻችሁ የሚሹት ሁሉ አላችሁ። ለእናንተም በእርሷ ውስጥ የምታዙት ሁሉ አለላችሁ።

نُزُلًا مِنْ غَفُورٍ رَحِيمٍ

«መሀሪና አዛኝ ከሆነው አላህ መስተንግዶ ሲሆን» ይባላሉ።

وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًا مِمَّنْ دَعَا إِلَى اللَّهِ وَعَمِلَ صَالِحًا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ الْمُسْلِمِينَ

ወደ አላህ ከጠራና መልካምንም ከሰራ፤ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለው ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?

وَلَا تَسْتَوِي الْحَسَنَةُ وَلَا السَّيِّئَةُ ۚ ادْفَعْ بِالَّتِي هِيَ أَحْسَنُ فَإِذَا الَّذِي بَيْنَكَ وَبَيْنَهُ عَدَاوَةٌ كَأَنَّهُ وَلِيٌّ حَمِيمٌ

መልካሚቱና ክፉይቱም ጸባይ አይስተካከሉም በዚያች እርሷ መልካም በሆነችው ጸባይ መጥፎይቱን ገፍትር፤ ያን ጊዜ ባንተና በእርሱ መካከል ጠብ ያለው ሰው እርሱ ልክ እንደ ወዳጅ ዘመድ ይሆናል።

وَمَا يُلَقَّاهَا إِلَّا الَّذِينَ صَبَرُوا وَمَا يُلَقَّاهَا إِلَّا ذُو حَظٍّ عَظِيمٍ

ይህችንም ጸባይ እነዚያ የታገሱት እንጂ ሌላው አያገኛትም። የትልቅም እድል ባለቤት እንጂ ማንም አያገኛትም።

وَإِمَّا يَنْزَغَنَّكَ مِنَ الشَّيْطَانِ نَزْغٌ فَاسْتَعِذْ بِاللَّهِ ۖ إِنَّهُ هُوَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ

ከሰይጣን ጉትጎታ ቢያገኝህ (ከመልካም ጸባይ ቢመልስህ) በአላህ ተጠበቅ እነሆ እርሱ ሁሉን ሰሚና ሁሉን አዋቂ ነውና።

وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِنْ كُنْتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُونَ

ሌሊትና ቀንም ጸሀይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው። ለጸሐይና ለጨረቃ አትስገዱ፤ ለዚያም ለፈጠራቸው አላህ ስገዱ። እርሱን ብቻ የምትገዙ እንደሆናችሁ (ለሌላ አትስገዱ)።

فَإِنِ اسْتَكْبَرُوا فَالَّذِينَ عِنْدَ رَبِّكَ يُسَبِّحُونَ لَهُ بِاللَّيْلِ وَالنَّهَارِ وَهُمْ لَا يَسْأَمُونَ ۩

ቢኮሩም እነዚያ በጌታህ ዘንድ ያሉት መላዕክት በቀንም በሌሊትም ለእርሱ ያወድሳሉ። እነርሱም አይሰለቹም።

وَمِنْ آيَاتِهِ أَنَّكَ تَرَى الْأَرْضَ خَاشِعَةً فَإِذَا أَنْزَلْنَا عَلَيْهَا الْمَاءَ اهْتَزَّتْ وَرَبَتْ ۚ إِنَّ الَّذِي أَحْيَاهَا لَمُحْيِي الْمَوْتَىٰ ۚ إِنَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

አንተ (ሰው ሆይ!) ምድርን ደረቅ ሆና ማየትህም ከምልክቶቹ ነው። በእርሷም ላይ ውሃን ባወረድን ጊዜ በቡቃያዎችዋ ትላወሳለች፤ ትነፋለችም። ያ ህያው ያደረጋት ጌታ በእርግጥ ሙታንንም ህያው አድራጊ ነው። እርሱ በነገሩ ሁሉ ቻይ ነውና።

إِنَّ الَّذِينَ يُلْحِدُونَ فِي آيَاتِنَا لَا يَخْفَوْنَ عَلَيْنَا ۗ أَفَمَنْ يُلْقَىٰ فِي النَّارِ خَيْرٌ أَمْ مَنْ يَأْتِي آمِنًا يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۚ اعْمَلُوا مَا شِئْتُمْ ۖ إِنَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ

እነዚያ አናቅጻችንን የሚያጣምሙ በእኛ ላይ አይደበቁም። (የሚያጣምም) በእሳት ውስጥ የሚጣለው ይበልጣልን? ወይስ በትንሳኤ ቀን ደህነኛ ሆኖ የሚመጣው? የሻችሁትን ስሩ (ዋጋችሁን ታገላችሁ)። እርሱም (አላህ) የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና።

إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا بِالذِّكْرِ لَمَّا جَاءَهُمْ ۖ وَإِنَّهُ لَكِتَابٌ عَزِيزٌ

እነዚያ በቁርኣን እርሱ አሸናፊው መጽሐፍ ሲሆን በመጣላቸው ጊዜ የካዱ ሁሉ (ጠፊዎች ናቸው።)

لَا يَأْتِيهِ الْبَاطِلُ مِنْ بَيْنِ يَدَيْهِ وَلَا مِنْ خَلْفِهِ ۖ تَنْزِيلٌ مِنْ حَكِيمٍ حَمِيدٍ

ከኋላዉም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም። ጥበበኛ ምስጉን ከሆነው ጌታ የተወረደ ነው።

مَا يُقَالُ لَكَ إِلَّا مَا قَدْ قِيلَ لِلرُّسُلِ مِنْ قَبْلِكَ ۚ إِنَّ رَبَّكَ لَذُو مَغْفِرَةٍ وَذُو عِقَابٍ أَلِيمٍ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊት ለነበሩት መልዕክተኞች የተባለው ቢጤ እንጂ ላንተ ሌላ አይባልም። ጌታህ በእርግጥ የምህረት ባለቤትና የአሳማሚ ቅጣትም ባለቤት ነው።

وَلَوْ جَعَلْنَاهُ قُرْآنًا أَعْجَمِيًّا لَقَالُوا لَوْلَا فُصِّلَتْ آيَاتُهُ ۖ أَأَعْجَمِيٌّ وَعَرَبِيٌّ ۗ قُلْ هُوَ لِلَّذِينَ آمَنُوا هُدًى وَشِفَاءٌ ۖ وَالَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ فِي آذَانِهِمْ وَقْرٌ وَهُوَ عَلَيْهِمْ عَمًى ۚ أُولَٰئِكَ يُنَادَوْنَ مِنْ مَكَانٍ بَعِيدٍ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአዕጀምኛ የሆነ ቁርኣን ባደረግነው ኖሮ «አናቅጹ በምናውቀው ቋንቋ አይብራሩም ኖሯልን? (ቁርኣኑ) አዕጀምኛና (መልዕክተኛው) አረባዊ ይሆናልን?» ባሉ ነበር። እርሱ ለእነዚያ በአላህ ላመኑት ሰዎች መመሪያና መፈወሻ ነው በላቸው። እነዚያም የማያምኑት በጆሮዎቻቸው ውስጥ ድንቁርና ነው (አይሰሙትም)። እርሱ በእነርሱ ላይ እውርነት ነው። እነዚያ ከሩቅ ስፍራ እንደሚጠሩ ናቸው።

وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَى الْكِتَابَ فَاخْتُلِفَ فِيهِ ۗ وَلَوْلَا كَلِمَةٌ سَبَقَتْ مِنْ رَبِّكَ لَقُضِيَ بَيْنَهُمْ ۚ وَإِنَّهُمْ لَفِي شَكٍّ مِنْهُ مُرِيبٍ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሙሳንም መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው። በእርሱም ተለያዩበት። ከጌታህም ያለፈች ቃል ባልነበረች ኖሮ በመካከላቸው በተፈረደ ነበር፤ እነርሱም በእርሱ አወላዋይ በሆነ ጥርጣሬ ውስጥ ናቸው።

مَنْ عَمِلَ صَالِحًا فَلِنَفْسِهِ ۖ وَمَنْ أَسَاءَ فَعَلَيْهَا ۗ وَمَا رَبُّكَ بِظَلَّامٍ لِلْعَبِيدِ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መልካምን የሰራ ለነፍሱ ነው። ያጠፋም በእርሷው ላይ ነው። ጌታህም ለባሮቹ በዳይ አይደለም።

إِلَيْهِ يُرَدُّ عِلْمُ السَّاعَةِ ۚ وَمَا تَخْرُجُ مِنْ ثَمَرَاتٍ مِنْ أَكْمَامِهَا وَمَا تَحْمِلُ مِنْ أُنْثَىٰ وَلَا تَضَعُ إِلَّا بِعِلْمِهِ ۚ وَيَوْمَ يُنَادِيهِمْ أَيْنَ شُرَكَائِي قَالُوا آذَنَّاكَ مَا مِنَّا مِنْ شَهِيدٍ

የትንሳኤ መከሰቻ ሰዐቱን ማወቅ ወደ እርሱ ብቻ ይመለሳል። ከፍሬዎችም ከሽፋኖቻቸው አይወጡም ከሴትም አንዲትም አታረግዝም፤ አትወልድምም በእውቀቱ ቢሆን እንጂ። «ተጋሪዎቼ የት ናቸው?» በማለት በሚጠራቸው ቀንም «ከእኛ ውስጥ (‹ተጋሪ አለህ› ብሎ) ምንም መስካሪ አለመኖሩን አሳውቀንሃል» ይላሉ።

وَضَلَّ عَنْهُمْ مَا كَانُوا يَدْعُونَ مِنْ قَبْلُ ۖ وَظَنُّوا مَا لَهُمْ مِنْ مَحِيصٍ

ያም በፊት ይገዙት የነበሩት ጣዖት ከእነርሱ ይጠፋቸዋል። ለእነርሱም ምንም መሸሻ የሌላቸው መሆኑን ያረጋግጣሉ።

لَا يَسْأَمُ الْإِنْسَانُ مِنْ دُعَاءِ الْخَيْرِ وَإِنْ مَسَّهُ الشَّرُّ فَيَئُوسٌ قَنُوطٌ

ሰው በጎ ነገርን ከመለመን አይሰለችም። ክፋት ቢያገኘው (ግን) ወዲያውኑ በጣም ተስፋ ቆራጭ ተበሳጭ ይሆናል።

وَلَئِنْ أَذَقْنَاهُ رَحْمَةً مِنَّا مِنْ بَعْدِ ضَرَّاءَ مَسَّتْهُ لَيَقُولَنَّ هَٰذَا لِي وَمَا أَظُنُّ السَّاعَةَ قَائِمَةً وَلَئِنْ رُجِعْتُ إِلَىٰ رَبِّي إِنَّ لِي عِنْدَهُ لَلْحُسْنَىٰ ۚ فَلَنُنَبِّئَنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا بِمَا عَمِلُوا وَلَنُذِيقَنَّهُمْ مِنْ عَذَابٍ غَلِيظٍ

ካገኘችዉም መከራ በኋላ ከእኛ የሆነን እዝነት ብናቀምሰው «ይህ ለእኔ በስራየ የተገባኝ ነው፤ ሰዓቲቱም መጪ ናት ብየ አላስብም። ወደ ጌታየ ብመለስ (እንኳ) ለእኔ እርሱ ዘንድ መልካሚቱ ገነት በእርግጥ አለችኝ» ይላል። እነዚያንም የካዱትን በሰሩት ስራ በእርግጥ እንነግራቸዋለን። ከበረታዉም ስቃይም በእርግጥ እናቀምሳቸዋለን።

وَإِذَا أَنْعَمْنَا عَلَى الْإِنْسَانِ أَعْرَضَ وَنَأَىٰ بِجَانِبِهِ وَإِذَا مَسَّهُ الشَّرُّ فَذُو دُعَاءٍ عَرِيضٍ

በሰዉም ላይ ጸጋችንን በለገስን ጊዜ ከማመስገን ይዞራል በጎኑም ይርቃል። መከራም ባገኘው ጊዜ የብዙ ልመና ባለቤት ይሆናል።

قُلْ أَرَأَيْتُمْ إِنْ كَانَ مِنْ عِنْدِ اللَّهِ ثُمَّ كَفَرْتُمْ بِهِ مَنْ أَضَلُّ مِمَّنْ هُوَ فِي شِقَاقٍ بَعِيدٍ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በላቸው: «እስቲ ንገሩኝ ቁርኣን ከአላህ ዘንድ ቢሆንና ከዚያም በእርሱ ብትክዱ፤ ከእውነት በራቀ ጭቅጭቅ ላይ ከሆነ ሰው ይበልጥ የተሳሳተ ማን ነው?»

سَنُرِيهِمْ آيَاتِنَا فِي الْآفَاقِ وَفِي أَنْفُسِهِمْ حَتَّىٰ يَتَبَيَّنَ لَهُمْ أَنَّهُ الْحَقُّ ۗ أَوَلَمْ يَكْفِ بِرَبِّكَ أَنَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ شَهِيدٌ

እርሱም (ቁርኣን) እውነት መሆኑ ለእነርሱ እስከሚገለጽላቸው ድረስ በአጽናፎችና በነፍሶቻቸዉም ውስጥ ያሉትን ታዐምራቶቻችንን በእርግጥ እናሳያቸዋለን። ጌታህም እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ መስካሪ መሆኑ አይበቃቸዉምን?

أَلَا إِنَّهُمْ فِي مِرْيَةٍ مِنْ لِقَاءِ رَبِّهِمْ ۗ أَلَا إِنَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ مُحِيطٌ

(ሙስሊሞች ሆይ!) አስተውሉ! እነርሱ ከጌታቸው ጋር መገናኘትን በመጠራጠር ውስጥ ናቸው። (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተውሉ! እርሱ በነገሩ ሁሉ በእውቀቱ ከባቢ ነው።