حم
ሓ፤ሚይም፤
القرآن الكريمAfrica Academy
بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።
حم
ሓ፤ሚይም፤
عسق
ዐይን፤ ሲን፤ ቃፍ።
كَذَٰلِكَ يُوحِي إِلَيْكَ وَإِلَى الَّذِينَ مِنْ قَبْلِكَ اللَّهُ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልክ እንደዚሁ በዚህ ምዕራፍ ውስጥ እንዳለው አሸናፊውና ጥበበኛው አላህ ወደ አንተ ያወርዳል። ወደ እነዚያም ካንተ በፊት ወደ ነበሩት (መልዕክተኞችም) አውርዷል።
لَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۖ وَهُوَ الْعَلِيُّ الْعَظِيمُ
በሰማያትና በምድር ዉስጥ ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው። እርሱም የበላዩ ታላቁ ነው።
تَكَادُ السَّمَاوَاتُ يَتَفَطَّرْنَ مِنْ فَوْقِهِنَّ ۚ وَالْمَلَائِكَةُ يُسَبِّحُونَ بِحَمْدِ رَبِّهِمْ وَيَسْتَغْفِرُونَ لِمَنْ فِي الْأَرْضِ ۗ أَلَا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْغَفُورُ الرَّحِيمُ
(ከአላህ ፍራቻ የተነሳ) ሰማያት ከበላያቸው ሊቀደዱ ይቀርባሉ፤ መላእክትም ጌታቸውን እያመሰገኑ ያጠራሉ። በምድር ላለው ፍጡርም ምህረትን ይለምናሉ። (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተዉሉ። መሀሪውና አዛኙ አላህ ነው።
وَالَّذِينَ اتَّخَذُوا مِنْ دُونِهِ أَوْلِيَاءَ اللَّهُ حَفِيظٌ عَلَيْهِمْ وَمَا أَنْتَ عَلَيْهِمْ بِوَكِيلٍ
እነዚያም ከእርሱ ሌላ ጣዖታትን ረዳቶች አድርገው የያዙ ሁሉ አላህ በእነርሱ ላይ ተጠባባቂ ነው። አንተም በእነርሱ ላይ ሀላፊ አይደለህም።
وَكَذَٰلِكَ أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لِتُنْذِرَ أُمَّ الْقُرَىٰ وَمَنْ حَوْلَهَا وَتُنْذِرَ يَوْمَ الْجَمْعِ لَا رَيْبَ فِيهِ ۚ فَرِيقٌ فِي الْجَنَّةِ وَفَرِيقٌ فِي السَّعِيرِ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልክ እንደዚሁም የከተሞች እናት የሆነችውን የመካን ሰዎችና በአካባቢዋ ያሉትን ህዝቦች ልታስፈራራ የመሰብሰቢያውንም ቀን በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲሆን ልታስጠነቅቅ በዐረበኛ ቋንቋ የሆነን ቁርኣንን ወደ አንተ አወረድን። ከእነርሱም ከፊሉ በገነት ውስጥ ከፊሉም ደግሞ በእሳት ውስጥ ነው።
وَلَوْ شَاءَ اللَّهُ لَجَعَلَهُمْ أُمَّةً وَاحِدَةً وَلَٰكِنْ يُدْخِلُ مَنْ يَشَاءُ فِي رَحْمَتِهِ ۚ وَالظَّالِمُونَ مَا لَهُمْ مِنْ وَلِيٍّ وَلَا نَصِيرٍ
አላህ በፈለገ ኖሮ ሰዎችን በአንድ ሃይማኖት ላይ የሆኑ አንድ ህዝብ ባደረጋቸው ነበር። ግን የሚፈልገውን ሰው በእዝነቱ ውስጥ ያስገባዋል። በዳዮች ሁሉ ምንም ወዳጅና ረዳት የላቸዉም።
أَمِ اتَّخَذُوا مِنْ دُونِهِ أَوْلِيَاءَ ۖ فَاللَّهُ هُوَ الْوَلِيُّ وَهُوَ يُحْيِي الْمَوْتَىٰ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
ከእርሱ ሌላ ረዳቶች ያዙን? (እነርሱ ረዳቶች አይደሉም) ትክክለኛ ረዳት አላህ ብቻ ነው። እርሱ ሙታንን ህያው ያደርጋል። እርሱም በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነውና።
وَمَا اخْتَلَفْتُمْ فِيهِ مِنْ شَيْءٍ فَحُكْمُهُ إِلَى اللَّهِ ۚ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبِّي عَلَيْهِ تَوَكَّلْتُ وَإِلَيْهِ أُنِيبُ
«ያ የተለያያችሁበት ነገር ሁሉ ፍርዱ ወደ አላህ ብቻ ነው። እርሱ (አላህ) ጌታዬ ነው። በእርሱ ላይ ተመካሁ። ወደ እርሱም ብቻ እመለሳለሁ» በላቸው።
فَاطِرُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ جَعَلَ لَكُمْ مِنْ أَنْفُسِكُمْ أَزْوَاجًا وَمِنَ الْأَنْعَامِ أَزْوَاجًا ۖ يَذْرَؤُكُمْ فِيهِ ۚ لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ ۖ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ
ሰማያትንና ምድርን የፈጠረው አላህ ከነፍሶቻችሁ ጥንዶችን ከቤት እንሰሳዎችም አይነቶችን (ወንዶችና ሴቶችን) ለእናንተ ፈጠረላችሁ። በዚህ ድርጊቱም ያባዛችኋል። የሚመስለው ምንም ነገር የለም። እርሱ ሁሉን ነገር ሰሚና ሁሉን ተመልካች ነው።
لَهُ مَقَالِيدُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ يَبْسُطُ الرِّزْقَ لِمَنْ يَشَاءُ وَيَقْدِرُ ۚ إِنَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ
የሰማያትና የምድር (ድልቦች) መክፈቻዎች የእርሱ ብቻ ናቸው። ሲሳይን ለሚፈልገው ሰው ያሰፋል። ለሚፈልገዉም ያጠባል። እርሱ ሁሉን ነገር አዋቂ ነውና።
شَرَعَ لَكُمْ مِنَ الدِّينِ مَا وَصَّىٰ بِهِ نُوحًا وَالَّذِي أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ وَمَا وَصَّيْنَا بِهِ إِبْرَاهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَىٰ ۖ أَنْ أَقِيمُوا الدِّينَ وَلَا تَتَفَرَّقُوا فِيهِ ۚ كَبُرَ عَلَى الْمُشْرِكِينَ مَا تَدْعُوهُمْ إِلَيْهِ ۚ اللَّهُ يَجْتَبِي إِلَيْهِ مَنْ يَشَاءُ وَيَهْدِي إِلَيْهِ مَنْ يُنِيبُ
(ሰዎች ሆይ!) ለእናንተ ከሃይማኖት ያንን በእርሱ ኑህን ያዘዘበትን ያንንም ወደ አንተ ያወረድነውን ያንንም ኢብራሂምን፤ ሙሳንና ዒሳንም በእርሱ ያዘዝንበት የሆነውን ሃይማኖትን በትክክል አቋቁሙ በእርሱም ላይ አትለያዩ በማለት ደነገገላችሁ።(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህ አጋሪዎች ያ ወደ እርሱ የምትጠራቸው ነገር (ኢስላም) ከበዳቸው። አላህ የሚፈልገውን ሰው ወደ እርሱ እምነት ይመርጣል። የሚመለስንም ሰው ወደ እርሱ ይመራል።
وَمَا تَفَرَّقُوا إِلَّا مِنْ بَعْدِ مَا جَاءَهُمُ الْعِلْمُ بَغْيًا بَيْنَهُمْ ۚ وَلَوْلَا كَلِمَةٌ سَبَقَتْ مِنْ رَبِّكَ إِلَىٰ أَجَلٍ مُسَمًّى لَقُضِيَ بَيْنَهُمْ ۚ وَإِنَّ الَّذِينَ أُورِثُوا الْكِتَابَ مِنْ بَعْدِهِمْ لَفِي شَكٍّ مِنْهُ مُرِيبٍ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሃይማኖት ሰዎች እውቀት ከመጣላቸው በኋላ በመካከላቸው ባለ ወሰን አላፊነት እንጂ በሌላ አልተለያዩም። እስከተወሰነ ጊዜ በማቆየት ከጌታህ ያለፈች ቃል ባልነበረች ኖሮ በእነርሱ መካከል አሁኑኑ በተፈረደ ነበር። እነዚያም ከኋላቸው መጽሐፍን እንዲወርሱ የተደረጉት ከእርሱ በእርግጥ ባወላዋይ ጥርጣሬ ውስጥ ናቸው።
فَلِذَٰلِكَ فَادْعُ ۖ وَاسْتَقِمْ كَمَا أُمِرْتَ ۖ وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَاءَهُمْ ۖ وَقُلْ آمَنْتُ بِمَا أَنْزَلَ اللَّهُ مِنْ كِتَابٍ ۖ وَأُمِرْتُ لِأَعْدِلَ بَيْنَكُمُ ۖ اللَّهُ رَبُّنَا وَرَبُّكُمْ ۖ لَنَا أَعْمَالُنَا وَلَكُمْ أَعْمَالُكُمْ ۖ لَا حُجَّةَ بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمُ ۖ اللَّهُ يَجْمَعُ بَيْنَنَا ۖ وَإِلَيْهِ الْمَصِيرُ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እዚህ መንገድም (ጋኔንንና ሰዎችን) ጥራ። ልክ እንደታዘዝከዉም ቀጥ በል። ዝንባሌያቸውን አትከተል። «ከመጽሐፍም አላህ ባወረደው ሁሉ አመንኩ። በመካከላችሁ በፍርድ ላስተካክልም ታዘዝኩ። አላህ ጌታችን ጌታችሁም ነው። ለእኛ ስራዎቻችን አሉን። ለእናንተም እንዲሁ ስራዎቻችሁ አሏችሁ። በእኛና በእናንተ መካከል ክርክር የለም። አላህ በመካከላችን ይሰበስባል። መመለሻው ወደ እርሱ ብቻ ነው።» በላቸው።
وَالَّذِينَ يُحَاجُّونَ فِي اللَّهِ مِنْ بَعْدِ مَا اسْتُجِيبَ لَهُ حُجَّتُهُمْ دَاحِضَةٌ عِنْدَ رَبِّهِمْ وَعَلَيْهِمْ غَضَبٌ وَلَهُمْ عَذَابٌ شَدِيدٌ
እነዚያም በአላህ ሃይማኖት ተቀባይነት ካገኘ በኋላ የሚከራከሩት ሰዎች ማስረጃዎቻቸው በጌታቸው ዘንድ ብልሹ (ዉድቅ) ናቸው። በእነርሱም ላይ የአላህ ቁጣ አለባቸው (ወደቀባቸው)። ለእነርሱም ብርቱ ቅጣት አለባቸው።
اللَّهُ الَّذِي أَنْزَلَ الْكِتَابَ بِالْحَقِّ وَالْمِيزَانَ ۗ وَمَا يُدْرِيكَ لَعَلَّ السَّاعَةَ قَرِيبٌ
አላህ ያ መጽሐፉን በእውነት ያወረደ ነው። ሚዛንንም ልክ እንደዚሁ ያወረደ ነው። ሰዓቲቱ ምን አልባት ቅርብ ብትሆንስ ምን አሳወቀህ?
يَسْتَعْجِلُ بِهَا الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِهَا ۖ وَالَّذِينَ آمَنُوا مُشْفِقُونَ مِنْهَا وَيَعْلَمُونَ أَنَّهَا الْحَقُّ ۗ أَلَا إِنَّ الَّذِينَ يُمَارُونَ فِي السَّاعَةِ لَفِي ضَلَالٍ بَعِيدٍ
እነዚያ በእርሷ የማያምኑት በእርሷ ያቻኩላሉ። እነዚያ በአላህ ያመኑት ግን ከእርሷ ፈሪዎች ናቸው። እርሷ እውነት መሆኗንም በትክክል ያውቃሉ። (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተውሉ። እነዚያ በሰዓቲቱ የሚከራከሩ ሰዎች ሁሉ በእርግጥ ከእውነት በራቀ ስህተት ውስጥ ናቸው።
اللَّهُ لَطِيفٌ بِعِبَادِهِ يَرْزُقُ مَنْ يَشَاءُ ۖ وَهُوَ الْقَوِيُّ الْعَزِيزُ
አላህ ለባሮቹ እዝነቱ ረቂቅ ነው። ለሚፈልገው ሰው ሲሳይን ይሰጣል። እርሱም ብርቱዉ እና አሸናፊው ነው።
مَنْ كَانَ يُرِيدُ حَرْثَ الْآخِرَةِ نَزِدْ لَهُ فِي حَرْثِهِ ۖ وَمَنْ كَانَ يُرِيدُ حَرْثَ الدُّنْيَا نُؤْتِهِ مِنْهَا وَمَا لَهُ فِي الْآخِرَةِ مِنْ نَصِيبٍ
በስራው የኋለኛይቱን ዓለም አዝመራ የሚፈልግ ሰው ሁሉ ለእርሱ በአዝመራው ላይ ሌላን እንጨምርለታለን። የቅርቢቱን ዓለም አዝመራ የሚፈልግ ሰው ግን በእርሷ የተወሰነለትን ብቻ እንሰጠዋለን። ለእርሱም በኋለኛይቱ ዓለም ምንም ድርሻ የለዉም።
أَمْ لَهُمْ شُرَكَاءُ شَرَعُوا لَهُمْ مِنَ الدِّينِ مَا لَمْ يَأْذَنْ بِهِ اللَّهُ ۚ وَلَوْلَا كَلِمَةُ الْفَصْلِ لَقُضِيَ بَيْنَهُمْ ۗ وَإِنَّ الظَّالِمِينَ لَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ
ከሓዲያን ከአላህ ያልተፈቀደውን ሃይማኖት የደነገጉ ተጋሪዎች ለእነርሱ አሏቸውን? የፍርዱ ቃል ባልነበረ ኖሮ በመካከላቸው ወዲያውኑ በተፈረደ ነበር። በደለኞችም አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ አለባቸው።
تَرَى الظَّالِمِينَ مُشْفِقِينَ مِمَّا كَسَبُوا وَهُوَ وَاقِعٌ بِهِمْ ۗ وَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ فِي رَوْضَاتِ الْجَنَّاتِ ۖ لَهُمْ مَا يَشَاءُونَ عِنْدَ رَبِّهِمْ ۚ ذَٰلِكَ هُوَ الْفَضْلُ الْكَبِيرُ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በደለኞችን በሰሩት ስራ ዋጋ በትንሳኤ ቀን ፈሪዎች ሆነው ታያቸዋለህ። እርሱም በእነርሱ ላይ የማይቀር ወዳቂ ነው። (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያም በአላህ ያመኑና መልካም ስራን የሰሩ ሁሉ በገነት ጨፌዎች ዉስጥ ናቸው። ለእነርሱም በጌታቸው ዘንድ የሚፈልጉት ሁሉ አለላቸው። ይህ ታላቅ ችሮታ ነው።
ذَٰلِكَ الَّذِي يُبَشِّرُ اللَّهُ عِبَادَهُ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ ۗ قُلْ لَا أَسْأَلُكُمْ عَلَيْهِ أَجْرًا إِلَّا الْمَوَدَّةَ فِي الْقُرْبَىٰ ۗ وَمَنْ يَقْتَرِفْ حَسَنَةً نَزِدْ لَهُ فِيهَا حُسْنًا ۚ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ شَكُورٌ
(ይህ ታላቅ ችሮታ) ያ አላህ እነዚያን በትክክል ያመኑትንና መልካሞችን የሰሩት ባሮቹን የሚያበስርበት ነው።(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መልዕክቴን በማድረሴ ላይ የዝምድና ውዴታየን እንጂ ሌላ ዋጋ አልጠይቃችሁም በላቸው። መልካም ስራ የሚሰራ ሰው ሁሉ ለእርሱ በእርሷ ላይ መልካምን ነገርን እንጨምርለታለን። አላህ መሀሪ እና አመስጋኝ ነውና።
أَمْ يَقُولُونَ افْتَرَىٰ عَلَى اللَّهِ كَذِبًا ۖ فَإِنْ يَشَإِ اللَّهُ يَخْتِمْ عَلَىٰ قَلْبِكَ ۗ وَيَمْحُ اللَّهُ الْبَاطِلَ وَيُحِقُّ الْحَقَّ بِكَلِمَاتِهِ ۚ إِنَّهُ عَلِيمٌ بِذَاتِ الصُّدُورِ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይልቁንም «በአላህ ላይ ውሸትን ቀጠፈ» ይላሉን? አላህም ቢፈልግ በልብህ ላይ ያትማል። አላህ ውሸትን ያብሳል። እውነትንም በቃላቱ ያረጋግጣል። እርሱ በይፋ የተነገሩት ቀርቶ በልቦች ውስጥ ያለውን ሁሉ አዋቂ ነውና።
وَهُوَ الَّذِي يَقْبَلُ التَّوْبَةَ عَنْ عِبَادِهِ وَيَعْفُو عَنِ السَّيِّئَاتِ وَيَعْلَمُ مَا تَفْعَلُونَ
እርሱም አላህ ያ ሁልጊዜም ከባሮቹ ንስሀን የሚቀበል ኃጢአቶችንም ይቅር የሚል የምትሰሩትንም ሁሉ የሚያውቅ ጌታ ነው።
وَيَسْتَجِيبُ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ وَيَزِيدُهُمْ مِنْ فَضْلِهِ ۚ وَالْكَافِرُونَ لَهُمْ عَذَابٌ شَدِيدٌ
እነዚያም በአላህ ያመኑትና መልካም ተግባሮችን የሰሩትን ልመናቸውን ይቀበላል። ከችሮታዉም ይጨምርላቸዋል። ከሓዲያንም ለእነርሱ ብርቱ ቅጣት አለባቸው።
وَلَوْ بَسَطَ اللَّهُ الرِّزْقَ لِعِبَادِهِ لَبَغَوْا فِي الْأَرْضِ وَلَٰكِنْ يُنَزِّلُ بِقَدَرٍ مَا يَشَاءُ ۚ إِنَّهُ بِعِبَادِهِ خَبِيرٌ بَصِيرٌ
አላህም ለባሮቹ ሁሉ ሲሳይን በዘረጋ ኖሮ በምድር ውስጥ ሁሉም ወሰን ባለፉ ነበር። ግን የሚፈልገውን በልክ ያወርዳል። እርሱ በባሮቹ ውስጠ አዋቂ፤ ተመልካች ነውና።
وَهُوَ الَّذِي يُنَزِّلُ الْغَيْثَ مِنْ بَعْدِ مَا قَنَطُوا وَيَنْشُرُ رَحْمَتَهُ ۚ وَهُوَ الْوَلِيُّ الْحَمِيدُ
አላህ ያ ተስፋ ከቆረጡ በኋላ ዝናብን የሚያወርድ ችሮታውንም የሚዘረጋ ነው። እርሱም ረዳቱና ምስጉኑ ነውና።
وَمِنْ آيَاتِهِ خَلْقُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا بَثَّ فِيهِمَا مِنْ دَابَّةٍ ۚ وَهُوَ عَلَىٰ جَمْعِهِمْ إِذَا يَشَاءُ قَدِيرٌ
ሰማያትንና ምድርን መፍጠሩ ከተንቀሳቃሽም በሁለቱ ውስጥ የበተነውን ፍጡር መፍጠሩ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ከፊሎቹ ናቸው። እርሱም በሚፈልግ ጊዜ እነርሱን በመሰብሰብ ላይ ቻይ ነው።
وَمَا أَصَابَكُمْ مِنْ مُصِيبَةٍ فَبِمَا كَسَبَتْ أَيْدِيكُمْ وَيَعْفُو عَنْ كَثِيرٍ
(ሰዎች ሆይ!) ማንኛዉም መከራ (ያገኛችሁ ነገር) እጆቻችሁ በሰሩት ኃጢአት ምክንያት ነው። ብዙውንም ይቅር ይላል።
وَمَا أَنْتُمْ بِمُعْجِزِينَ فِي الْأَرْضِ ۖ وَمَا لَكُمْ مِنْ دُونِ اللَّهِ مِنْ وَلِيٍّ وَلَا نَصِيرٍ
(ሰዎች ሆይ!) እናንተ በምድር ውስጥ የምትሳኑን (አምላጮች) አይደላችሁም። ለእናንተም ከአላህ ሌላ ወዳጅም ሆነ ረዳት ምንም የላችሁም።
وَمِنْ آيَاتِهِ الْجَوَارِ فِي الْبَحْرِ كَالْأَعْلَامِ
በባህር ላይ እንደ ጋራዎች ሆነው ተንሻላዮቹ መርከቦችም ከአስደናቂ ምልክቶቹ ናቸው።
إِنْ يَشَأْ يُسْكِنِ الرِّيحَ فَيَظْلَلْنَ رَوَاكِدَ عَلَىٰ ظَهْرِهِ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِكُلِّ صَبَّارٍ شَكُورٍ
ቢፈልግ ንፋሱን የረጋ ያደርገዋል። ከዚያም መርከቦች በባህሩ ጀርባ ላይ የረጉ ይሆናሉ። በዚህ ውስጥ በጣም ታጋሽ፤ አመስጋኝ ለሆኑ ሁሉ በእርግጥም ብዙ ተዓምራት አሉ።
أَوْ يُوبِقْهُنَّ بِمَا كَسَبُوا وَيَعْفُ عَنْ كَثِيرٍ
ወይም (ተሳፋሪዎች) በሰሩት ኃጢአት (ምክንያት እነርሱን በባህሩ በማስመጥ) ያጠፋቸዋል። ከብዙ ጥፋቶችም ይቅርታ ያደርጋል።
وَيَعْلَمَ الَّذِينَ يُجَادِلُونَ فِي آيَاتِنَا مَا لَهُمْ مِنْ مَحِيصٍ
ከእነርሱ መካከል እነዚያን በአናቅጻችን የሚከራከሩት ሰዎችም ለማወቅ (ያጠፋቸዋል)። (ይህም ከቅጣቱ) ምንም መሸሻ የሌላቸው መሆኑን ነው።
فَمَا أُوتِيتُمْ مِنْ شَيْءٍ فَمَتَاعُ الْحَيَاةِ الدُّنْيَا ۖ وَمَا عِنْدَ اللَّهِ خَيْرٌ وَأَبْقَىٰ لِلَّذِينَ آمَنُوا وَعَلَىٰ رَبِّهِمْ يَتَوَكَّلُونَ
(ሰዎች ሆይ!) የተሰጣችሁት ነገር ሁሉ የቅርቢቱ ሕይወት መጠቃቀሚያ ብቻ ነው። በአላህ ዘንድ ያለው ምንዳ ግን ለእነዚያ በትክክል በእሱ ላመኑትና በጌታቸው ላይ ብቻ ለሚመኩት ሁሉ በላጭና ሁልጊዜ ነዋሪ ነው።
وَالَّذِينَ يَجْتَنِبُونَ كَبَائِرَ الْإِثْمِ وَالْفَوَاحِشَ وَإِذَا مَا غَضِبُوا هُمْ يَغْفِرُونَ
ለእነዚያም ታላላቅ ሃጢያቶችንና አጸያፊ ተግባሮችን የሚርቁ፤ በተቆጡም ጊዜ የሚምሩ ለሆኑት፤
وَالَّذِينَ اسْتَجَابُوا لِرَبِّهِمْ وَأَقَامُوا الصَّلَاةَ وَأَمْرُهُمْ شُورَىٰ بَيْنَهُمْ وَمِمَّا رَزَقْنَاهُمْ يُنْفِقُونَ
ለእነዚያም የጌታቸውን ጥሪ ለተቀበሉት፤ ሶላትንም ላዘወተሩት፤ በነገራቸው ላይም በመካከላቸው መመካከር ልምዳቸው ለሆነው፤ ከሰጠናቸዉም ሲሳይ ለሚለግሱት፤
وَالَّذِينَ إِذَا أَصَابَهُمُ الْبَغْيُ هُمْ يَنْتَصِرُونَ
ለእነዚያም በደል በደረሰባቸው ጊዜ በመሰሉ የሚመልሱ ለሆኑት (በላጭና ነዋሪ ነው)።
وَجَزَاءُ سَيِّئَةٍ سَيِّئَةٌ مِثْلُهَا ۖ فَمَنْ عَفَا وَأَصْلَحَ فَأَجْرُهُ عَلَى اللَّهِ ۚ إِنَّهُ لَا يُحِبُّ الظَّالِمِينَ
የመጥፎ ነገሮች ሁሉ ዋጋው ተመሳሳዩ መጥፎ ነው። ይቅር ያለና ያሳመረ ሰው ደግሞ ምንዳው በአላህ ላይ ብቻ ነው። እርሱ በደለኞችን አይወድምና።
وَلَمَنِ انْتَصَرَ بَعْدَ ظُلْمِهِ فَأُولَٰئِكَ مَا عَلَيْهِمْ مِنْ سَبِيلٍ
እነዚያ ከተበደሉ በኋላ በመሰሉ የተበቀሉ በእነርሱ ላይ ምንም የወቀሳ መንገድ የለባቸዉም።
إِنَّمَا السَّبِيلُ عَلَى الَّذِينَ يَظْلِمُونَ النَّاسَ وَيَبْغُونَ فِي الْأَرْضِ بِغَيْرِ الْحَقِّ ۚ أُولَٰئِكَ لَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ
የወቀሳ መንገዱ በእነዚያ ሰዎችን በሚበድሉት እና በምድር ውስጥም ያለ ህግ ወሰንን በሚያልፉት ሰዎች ላይ ብቻ ነው። እነዚያ ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣት አለባቸው።
وَلَمَنْ صَبَرَ وَغَفَرَ إِنَّ ذَٰلِكَ لَمِنْ عَزْمِ الْأُمُورِ
የታገሰና ምህረት ያደረገ፤ ይህ ተግባር በእርግጥ ቁርጠኝነትን ከሚጠይቁ ነገሮች ነው።
وَمَنْ يُضْلِلِ اللَّهُ فَمَا لَهُ مِنْ وَلِيٍّ مِنْ بَعْدِهِ ۗ وَتَرَى الظَّالِمِينَ لَمَّا رَأَوُا الْعَذَابَ يَقُولُونَ هَلْ إِلَىٰ مَرَدٍّ مِنْ سَبِيلٍ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ የሚያጠመውን ሰው ከእርሱ ማጥመም በኋላ ለእርሱ ምንም ወዳጅ የለዉም። በደለኞችም ቅጣትን ባዩ ጊዜ «ለመመለስ መንገድ አለን?» የሚሉ ሲሆኑ ታያቸዋለህ።
وَتَرَاهُمْ يُعْرَضُونَ عَلَيْهَا خَاشِعِينَ مِنَ الذُّلِّ يَنْظُرُونَ مِنْ طَرْفٍ خَفِيٍّ ۗ وَقَالَ الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّ الْخَاسِرِينَ الَّذِينَ خَسِرُوا أَنْفُسَهُمْ وَأَهْلِيهِمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۗ أَلَا إِنَّ الظَّالِمِينَ فِي عَذَابٍ مُقِيمٍ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከውርደት የተነሳ ፈሪዎች ሆነው በዓይን ስርቆት ወደ እሳት እያስተዋሉ በእርሷ ላይ የሚቀርቡ ሁነው ታያቸዋለህ። እነዚያም በአላህ ያመኑት፡- «በእርግጥ ከሳሪዎች ማለት እነዚያ ነፍሶቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን በትንሳኤ ቀን የከሰሩት ናቸው» ይላሉ። (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተዉሉ። በደለኞች በእርግጥ ዘወታሪ ስቃይ ውስጥ ናቸው።
وَمَا كَانَ لَهُمْ مِنْ أَوْلِيَاءَ يَنْصُرُونَهُمْ مِنْ دُونِ اللَّهِ ۗ وَمَنْ يُضْلِلِ اللَّهُ فَمَا لَهُ مِنْ سَبِيلٍ
ለእነርሱም ከአላህ ሌላ የሚረዷቸው ረዳቶች ምንም አልነበሯቸዉም። አላህ የሚያጠመው ሰው ሁሉ ለእርሱ ወደ እውነት የሚመለስበት ምንም መንገድ የለዉም።
اسْتَجِيبُوا لِرَبِّكُمْ مِنْ قَبْلِ أَنْ يَأْتِيَ يَوْمٌ لَا مَرَدَّ لَهُ مِنَ اللَّهِ ۚ مَا لَكُمْ مِنْ مَلْجَإٍ يَوْمَئِذٍ وَمَا لَكُمْ مِنْ نَكِيرٍ
ያ ከአላህ ከመጣ መላሽ የሌለው ቀን ከመምጣቱ በፊት ለጌታችሁ ታዘዙ። በዚያ ቀን ለእናንተ ምንም መጠጊያም ሆነ መቃወም የላችሁም።
فَإِنْ أَعْرَضُوا فَمَا أَرْسَلْنَاكَ عَلَيْهِمْ حَفِيظًا ۖ إِنْ عَلَيْكَ إِلَّا الْبَلَاغُ ۗ وَإِنَّا إِذَا أَذَقْنَا الْإِنْسَانَ مِنَّا رَحْمَةً فَرِحَ بِهَا ۖ وَإِنْ تُصِبْهُمْ سَيِّئَةٌ بِمَا قَدَّمَتْ أَيْدِيهِمْ فَإِنَّ الْإِنْسَانَ كَفُورٌ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢዞሩም (ወቀሳ የለብህም።) በእነርሱ ላይ ጠባቂ አድርገን አላክንህምና። ባንተ ላይ ማድረስ እንጂ ሌላ የለብህም። እኛም ሰውን ከእኛ የሆነን ጸጋ ባቀመስነው ጊዜ በእርሷ ይደሰታል። እጆቻቸው ባስቀደሙት ኃጢአት ምክንያት መከራ ብትደርስባቸው ደግሞ (ይክዳሉ)። ሰው በጣም ውለታን ከሓዲ ነውና።
لِلَّهِ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ يَهَبُ لِمَنْ يَشَاءُ إِنَاثًا وَيَهَبُ لِمَنْ يَشَاءُ الذُّكُورَ
የሰማያትና የምድር ንግስና የአላህ ብቻ ነው። የሚፈልገውን ይፈጥራል። ለሚፈልገው ሴቶችን ልጆች ይሰጣል። ለሚፈልገዉም ወንዶችን ይሰጣል።
أَوْ يُزَوِّجُهُمْ ذُكْرَانًا وَإِنَاثًا ۖ وَيَجْعَلُ مَنْ يَشَاءُ عَقِيمًا ۚ إِنَّهُ عَلِيمٌ قَدِيرٌ
ወይም ወንዶችንና ሴቶችን አድርጎ ያጠናዳቸዋል። የሚፈልገውንም መካን ያደርገዋል። እርሱ ሁሉን አዋቂና ሁሉን ቻይ ነውና።
وَمَا كَانَ لِبَشَرٍ أَنْ يُكَلِّمَهُ اللَّهُ إِلَّا وَحْيًا أَوْ مِنْ وَرَاءِ حِجَابٍ أَوْ يُرْسِلَ رَسُولًا فَيُوحِيَ بِإِذْنِهِ مَا يَشَاءُ ۚ إِنَّهُ عَلِيٌّ حَكِيمٌ
ሰውን አላህ በራዕይ ወይም ከግርዶሹ ወዲያ ወይም መልዕክተኛን በመላክና በፈቃዱ የሚፈልገውን ነገር የሚያወርድለት ቢሆን እንጂ በገሀድ ሊያናግረው ተገቢ አይደለም። እርሱ የበላይና ጥበበኛ ነውና።
وَكَذَٰلِكَ أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ رُوحًا مِنْ أَمْرِنَا ۚ مَا كُنْتَ تَدْرِي مَا الْكِتَابُ وَلَا الْإِيمَانُ وَلَٰكِنْ جَعَلْنَاهُ نُورًا نَهْدِي بِهِ مَنْ نَشَاءُ مِنْ عِبَادِنَا ۚ وَإِنَّكَ لَتَهْدِي إِلَىٰ صِرَاطٍ مُسْتَقِيمٍ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልክ እንደዚሁ ወደ አንተ ከትዕዛዛችን ሲሆን ሂወት የሆነውን (ቁርአን) አወረድነው። መጽሐፉም ሆነ እምነቱ ምን እንደሆነ የምታውቅ አልነበርክም። ግን ቁርኣንን ከባሮቻችን የምንሻውን ሰው በእርሱ የምንመራበት ብርሃን አደረግነው። አንተም ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ትመራለህ።
صِرَاطِ اللَّهِ الَّذِي لَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۗ أَلَا إِلَى اللَّهِ تَصِيرُ الْأُمُورُ
ወደዚያ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ወደ ሆነው ወደ አላህ መንገድ (ትመራለህ)። (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተውሉ። ነገሮች ሁሉ ወደ አላህ ብቻ ይመለሳሉ።