The Dunes · al-Ahqaf · سورة الأحقاف · 35 ayahs

القرآن الكريمAfrica Academy

بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።

حم

ሓ፤ ሚይም፤

تَنْزِيلُ الْكِتَابِ مِنَ اللَّهِ الْعَزِيزِ الْحَكِيمِ

የመጽሐፉ መወረድ አሸናፊ፤ ጥበበኛ ከሆነው አላህ ነው።

مَا خَلَقْنَا السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا إِلَّا بِالْحَقِّ وَأَجَلٍ مُسَمًّى ۚ وَالَّذِينَ كَفَرُوا عَمَّا أُنْذِرُوا مُعْرِضُونَ

ሰማያትን፤ ምድርን እና በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በምር እና በተወሰነ ጊዜንም በመለካት እንጂ ለቀልድ አልፈጠርናቸዉም። እነዚያ በአላህ የካዱት የተስፈራሩትን ነገር ደንታ አይሰጡትም።

قُلْ أَرَأَيْتُمْ مَا تَدْعُونَ مِنْ دُونِ اللَّهِ أَرُونِي مَاذَا خَلَقُوا مِنَ الْأَرْضِ أَمْ لَهُمْ شِرْكٌ فِي السَّمَاوَاتِ ۖ ائْتُونِي بِكِتَابٍ مِنْ قَبْلِ هَٰذَا أَوْ أَثَارَةٍ مِنْ عِلْمٍ إِنْ كُنْتُمْ صَادِقِينَ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከአላህ ሌላ የምትገዟቸውን አላያችሁምን? ከምድር ምንን እንደፈጠሩ እስቲ አሳዩኝ። ወይስ በሰማያት መፍጠር ለእነርሱ ከአላህ ጋር መጋራት አላቸውን? (ያማልዱናል በማለታችሁ) እውነተኞች እንደሆናችሁ ይህንን ጉዳይ ከዚህ (ቁርኣን) በፊት የሆነን መጽሐፍ ወይም ከእውቀት ቅሪት እስቲ አምጡልኝ» በላቸው።

وَمَنْ أَضَلُّ مِمَّنْ يَدْعُو مِنْ دُونِ اللَّهِ مَنْ لَا يَسْتَجِيبُ لَهُ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ وَهُمْ عَنْ دُعَائِهِمْ غَافِلُونَ

እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስም ለእርሱ የማይመልሱለትን ጣዖታት ከአላህ ሌላ ከሚጠራ ሰው ይበልጥ የተሳሳተ ማን ነው? እነርሱም ከጥሪያቸው ዘንጊዎች ናቸው።

وَإِذَا حُشِرَ النَّاسُ كَانُوا لَهُمْ أَعْدَاءً وَكَانُوا بِعِبَادَتِهِمْ كَافِرِينَ

ሰዎችም በተሰበሰቡ ጊዜ ጣኦቶቹ ለእነርሱ ጠላቶች ይሆናሉ። እነርሱን መገዛታቸውንም ይክዳሉ።

وَإِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ آيَاتُنَا بَيِّنَاتٍ قَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا لِلْحَقِّ لَمَّا جَاءَهُمْ هَٰذَا سِحْرٌ مُبِينٌ

በእነርሱም ላይ አንቀፆቻችን ግልፆች ሆነው በተነበቡ ጊዜ እነዚያ እውነቱ በመጣላቸው ጊዜ የካዱት ክፍሎች «ይህ ግልጽ ድግምት ነው» አሉ።

أَمْ يَقُولُونَ افْتَرَاهُ ۖ قُلْ إِنِ افْتَرَيْتُهُ فَلَا تَمْلِكُونَ لِي مِنَ اللَّهِ شَيْئًا ۖ هُوَ أَعْلَمُ بِمَا تُفِيضُونَ فِيهِ ۖ كَفَىٰ بِهِ شَهِيدًا بَيْنِي وَبَيْنَكُمْ ۖ وَهُوَ الْغَفُورُ الرَّحِيمُ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይልቁንም «(ሙሐመድ ራሱ) ቀጠፈው» ይላሉን? «ብቀጥፈው ኖሮ እኔን ከአላህ ቅጣት ለማዳን በምንም አትችሉም። እርሱ ያንን የምትቀባዥሩበትን ነገር ሁሉ አዋቂ ነው። በእኔና በእናንተ መካከል መስካሪነት እሱው በቃ። እርሱ መሀሪ እና አዛኝ ነውና» በላቸው።

قُلْ مَا كُنْتُ بِدْعًا مِنَ الرُّسُلِ وَمَا أَدْرِي مَا يُفْعَلُ بِي وَلَا بِكُمْ ۖ إِنْ أَتَّبِعُ إِلَّا مَا يُوحَىٰ إِلَيَّ وَمَا أَنَا إِلَّا نَذِيرٌ مُبِينٌ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከመልዕክተኞች የተለየሁ ብጤ የሌለኝ አይደለሁም። በእኔም በእናንተም ላይ ምን እንደሚሰራብንም አላውቅም። ወደ እኔ የሚወረደውን እንጂ ሌላን መመሪያ አልከተልም። እኔም ግልጽ አስፈራሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም» በላቸው።

قُلْ أَرَأَيْتُمْ إِنْ كَانَ مِنْ عِنْدِ اللَّهِ وَكَفَرْتُمْ بِهِ وَشَهِدَ شَاهِدٌ مِنْ بَنِي إِسْرَائِيلَ عَلَىٰ مِثْلِهِ فَآمَنَ وَاسْتَكْبَرْتُمْ ۖ إِنَّ اللَّهَ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الظَّالِمِينَ

«(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እስቲ ንገሩኝ ቁርኣኑ ከአላህ ዘንድ ቢሆንና በእርሱ ብትክዱ ከኢስራኢል ልጆች የሆነ መስካሪ ደግሞ በቢጤው (እውነተኛነት) ቢመሰክርና ቢያምን እናንተ (ግን) ብትኮሩ (በዳይ አትሆኑምን)? አላህ በእርግጥ በደለኛ ህዝቦችን ሁሉ አያቀናም» በላቸው።

وَقَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا لِلَّذِينَ آمَنُوا لَوْ كَانَ خَيْرًا مَا سَبَقُونَا إِلَيْهِ ۚ وَإِذْ لَمْ يَهْتَدُوا بِهِ فَسَيَقُولُونَ هَٰذَا إِفْكٌ قَدِيمٌ

እነዚያም የካዱት ሰዎች ስላመኑት ሰዎች «እምነቱ መልካም ነገር በሆነ ኖሮ ወደ እርሱ ባልቀደሙን ነበር» አሉ። በእርሱም ባልተቀኑ ጊዜ «ይህ ቁርኣን ጥንታዊ ቅጥፈት ነው» ይላሉ።

وَمِنْ قَبْلِهِ كِتَابُ مُوسَىٰ إِمَامًا وَرَحْمَةً ۚ وَهَٰذَا كِتَابٌ مُصَدِّقٌ لِسَانًا عَرَبِيًّا لِيُنْذِرَ الَّذِينَ ظَلَمُوا وَبُشْرَىٰ لِلْمُحْسِنِينَ

ከፊቱም የሙሳን መጽሐፍ ለሰዎች መሪና የአላህ ጸጋ ሆኖ (ወርዷል)። ይህ ቁርኣን እነዚያን የበደሉትን ሊያስፈራራ በዐረብኛ ቋንቋ የወረደ ሲሆን የፊቶቹንም መጽሐፍት አረጋጋጭ እና ለበጎ አድራጊዎችም ሁሉ የብስራት መጽሐፍ ነው።

إِنَّ الَّذِينَ قَالُوا رَبُّنَا اللَّهُ ثُمَّ اسْتَقَامُوا فَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ

እነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ያሉና ከዚያም በዚሁ ቃላቸው ላይ ቀጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ በእነርሱ ላይ ምንም (ይደርስብናል ብለው) ፍርሀት የለባቸዉም። ምንም (ነገር ያመልጠናል ብለው) አያዝኑምም።

أُولَٰئِكَ أَصْحَابُ الْجَنَّةِ خَالِدِينَ فِيهَا جَزَاءً بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ

እነዚያ የገነት ጓዶች ናቸው። በእርሷ ውስጥ ዘወታሪዎች ሲሆኑ በዚያ በዱንያ ይሰሩት በነበሩት መልካም ተግባር ምክንያት ያገኙት ምንዳ ነው።

وَوَصَّيْنَا الْإِنْسَانَ بِوَالِدَيْهِ إِحْسَانًا ۖ حَمَلَتْهُ أُمُّهُ كُرْهًا وَوَضَعَتْهُ كُرْهًا ۖ وَحَمْلُهُ وَفِصَالُهُ ثَلَاثُونَ شَهْرًا ۚ حَتَّىٰ إِذَا بَلَغَ أَشُدَّهُ وَبَلَغَ أَرْبَعِينَ سَنَةً قَالَ رَبِّ أَوْزِعْنِي أَنْ أَشْكُرَ نِعْمَتَكَ الَّتِي أَنْعَمْتَ عَلَيَّ وَعَلَىٰ وَالِدَيَّ وَأَنْ أَعْمَلَ صَالِحًا تَرْضَاهُ وَأَصْلِحْ لِي فِي ذُرِّيَّتِي ۖ إِنِّي تُبْتُ إِلَيْكَ وَإِنِّي مِنَ الْمُسْلِمِينَ

የሰውን ልጅ ለወላጆቹ በጎ መዋል እንዳለበት በጥብቅ አዘዝነው። እናቱ በችግር ላይ ሆና አረገዘችው። በችግርም ላይ ሆና ወለደችው። እርግዝናውና (ከጡት) መለያው ሙሉ ሰላሳ ወር ነው። ከዚያም የጥንካሬውን ወቅት በደረሰና አርባ ዓመት በሞላው ጊዜ «ጌታዬ ሆይ! ያን በእኔ ላይና በወላጆቼ ላይ የለገስከዉን ጸጋህን እንዳመሰግንህና የምትወደውን መልካም ስራም እንድሰራ ወደ ቀናው መንገድ ምራኝ። ዘሮቼንም ለእኔ አብጅልኝ። እኔ ወደ አንተ ብቻ ተመለስኩ። እኔ ከሙስሊሞች አንዱ ነኝ» አለ።

أُولَٰئِكَ الَّذِينَ نَتَقَبَّلُ عَنْهُمْ أَحْسَنَ مَا عَمِلُوا وَنَتَجَاوَزُ عَنْ سَيِّئَاتِهِمْ فِي أَصْحَابِ الْجَنَّةِ ۖ وَعْدَ الصِّدْقِ الَّذِي كَانُوا يُوعَدُونَ

እነዚያ (ይህንን ባዩች ሁሉ) ከገነት ጓዶች መካከል ሲሆኑ እነዚያ ከሰሩት ስራ መልካሙን የምንቀበላቸውና ከኃጢአቶቻቸዉም የምናልፋቸው ሰዎች ናቸው። ያንን ተስፋ ይሰጡት የነበሩትን እውነተኛ ቀጠሮ እንሞላላቸዋለን።

وَالَّذِي قَالَ لِوَالِدَيْهِ أُفٍّ لَكُمَا أَتَعِدَانِنِي أَنْ أُخْرَجَ وَقَدْ خَلَتِ الْقُرُونُ مِنْ قَبْلِي وَهُمَا يَسْتَغِيثَانِ اللَّهَ وَيْلَكَ آمِنْ إِنَّ وَعْدَ اللَّهِ حَقٌّ فَيَقُولُ مَا هَٰذَا إِلَّا أَسَاطِيرُ الْأَوَّلِينَ

ያም ለሁለቱ ወላጆቹ አላህን የሚለምኑ ሲሆኑ «ወዮልህ! በአላህ እመን፤ የአላህ ቀጠሮ እርግጠኛ ነው፤» ሲሉት «ኡፍ! ከእኔ በፊት የብዙ ክፍለ ዘመናት ሰዎች ሳይወጡ በእርግጥ ያለፉ ሲሆኑ ከመቃብር እንደምወጣ ታስፈራሩኛላችሁን?» ይላልም: "ይህ የቀደምቶች ተረት እንጅ ሌላ አይደለም" ይላል።

أُولَٰئِكَ الَّذِينَ حَقَّ عَلَيْهِمُ الْقَوْلُ فِي أُمَمٍ قَدْ خَلَتْ مِنْ قَبْلِهِمْ مِنَ الْجِنِّ وَالْإِنْسِ ۖ إِنَّهُمْ كَانُوا خَاسِرِينَ

እነዚህ እነዚያ ከአጋንንትም ከሰዉም ከእነርሱ በፊት ካለፉት ህዝቦች ጋር የአላህ ቃሉ በእነርሱ ላይ የተረጋገጠባቸው ናቸው። እነርሱ ከሳሪዎች ነበሩና።

وَلِكُلٍّ دَرَجَاتٌ مِمَّا عَمِلُوا ۖ وَلِيُوَفِّيَهُمْ أَعْمَالَهُمْ وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ

ለሁሉም በሰሩት ስራ ልክ ተገቢ የሆኑ ደረጃዎች አሏቸው። ስራዎቻቸውንም ይሞላላቸው ዘንድ (ይህንን መነዳቸው።) እነርሱም አይበደሉም።

وَيَوْمَ يُعْرَضُ الَّذِينَ كَفَرُوا عَلَى النَّارِ أَذْهَبْتُمْ طَيِّبَاتِكُمْ فِي حَيَاتِكُمُ الدُّنْيَا وَاسْتَمْتَعْتُمْ بِهَا فَالْيَوْمَ تُجْزَوْنَ عَذَابَ الْهُونِ بِمَا كُنْتُمْ تَسْتَكْبِرُونَ فِي الْأَرْضِ بِغَيْرِ الْحَقِّ وَبِمَا كُنْتُمْ تَفْسُقُونَ

እነዚያም የካዱት በእሳት ላይ በሚጋፈጡበት ቀን ጣፋጮቻችሁን በአነስተኛይቱ ሕይወታችሁ አሳለፋችሁ። በእርሷም ተጣቀማችሁ። ስለዚህ በምድር ላይ ያለ አግባብ ትኮሩ በነበራችሁትና ታምጹ በነበራችሁት ምክኒያት ዛሬ የውርደትን ቅጣት ትመነዳላችሁ ይባላሉ፡

وَاذْكُرْ أَخَا عَادٍ إِذْ أَنْذَرَ قَوْمَهُ بِالْأَحْقَافِ وَقَدْ خَلَتِ النُّذُرُ مِنْ بَيْنِ يَدَيْهِ وَمِنْ خَلْفِهِ أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا اللَّهَ إِنِّي أَخَافُ عَلَيْكُمْ عَذَابَ يَوْمٍ عَظِيمٍ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአል አሕቃፍ የነበረው የዓድ ወንድም የሆነው ሁድ ከእርሱ በፊትም ሆነ ከእርሱ በኋላም አስፈራሪዎች በእርግጥ ያለፉ ሲሆኑ «ከአላህ ውጪ ሌሎች አማልክትን አታምልኩ። የታላቁን ቀን ቅጣት እፈራላችኋለሁ።» በሚል ሲያስጠነቅቃቸው (የነበረውን አስታውስ)

قَالُوا أَجِئْتَنَا لِتَأْفِكَنَا عَنْ آلِهَتِنَا فَأْتِنَا بِمَا تَعِدُنَا إِنْ كُنْتَ مِنَ الصَّادِقِينَ

«ከአማልክቶቻችን ልታሸሸን መጣህን? እውነተኛ ከሆንክ ያንን የምታስፈራራን ቅጣት አሁን እንዲከሰት አድርግ» አሉት።

قَالَ إِنَّمَا الْعِلْمُ عِنْدَ اللَّهِ وَأُبَلِّغُكُمْ مَا أُرْسِلْتُ بِهِ وَلَٰكِنِّي أَرَاكُمْ قَوْمًا تَجْهَلُونَ

«የቅጣቱ መከሰቻ ትክክለኛ ወቅት እውቀት ያለው ከአላህ ዘንድ ብቻ ነው። የተላኩበትን መልዕክት ብቻ አደርስላችኋለሁ። ግና እንደማያችሁ መሀይማን ህዝቦች ናችሁ።» አላቸው።

فَلَمَّا رَأَوْهُ عَارِضًا مُسْتَقْبِلَ أَوْدِيَتِهِمْ قَالُوا هَٰذَا عَارِضٌ مُمْطِرُنَا ۚ بَلْ هُوَ مَا اسْتَعْجَلْتُمْ بِهِ ۖ رِيحٌ فِيهَا عَذَابٌ أَلِيمٌ

ለቅጣት የተላከባቸውን (ዳመና) ወደ ሸለቆዎቻቸው አቅጣጫ ሲጓዝ ባዩ ጊዜ «ይህ ዝናብ የሚያወርድልን ዳመና ነው» አሉ። «አይደለም። ይልቁንም ያ በፍጥነት ይከሰት ዘንድ የጠየቃችሁት ቅጣት ነው። አሳማሚ ቅጣት ያዘለ ንፋስ ነው።

تُدَمِّرُ كُلَّ شَيْءٍ بِأَمْرِ رَبِّهَا فَأَصْبَحُوا لَا يُرَىٰ إِلَّا مَسَاكِنُهُمْ ۚ كَذَٰلِكَ نَجْزِي الْقَوْمَ الْمُجْرِمِينَ

በጌታዋ ትዕዛዝ ሁሉን ነገር ታጠፋለች» (አላቸው)። ባዶ ቤቶቻቸው እንጂ ሌላ ነገር የማይታይ ሆነው አነጉ። አመጸኞች ህዝቦችን በዚህ መልኩ እንቀጣለን።

وَلَقَدْ مَكَّنَّاهُمْ فِيمَا إِنْ مَكَّنَّاكُمْ فِيهِ وَجَعَلْنَا لَهُمْ سَمْعًا وَأَبْصَارًا وَأَفْئِدَةً فَمَا أَغْنَىٰ عَنْهُمْ سَمْعُهُمْ وَلَا أَبْصَارُهُمْ وَلَا أَفْئِدَتُهُمْ مِنْ شَيْءٍ إِذْ كَانُوا يَجْحَدُونَ بِآيَاتِ اللَّهِ وَحَاقَ بِهِمْ مَا كَانُوا بِهِ يَسْتَهْزِئُونَ

ለእናንተ ያልሰጠነውን ኃይልና ምቾት ለእነርሱ ሰጥተናል። መስሚያ ጆሮዎችን፤ መመልከቻ ዓይኖችን እና ማሰቢያ አእምሮንም ለግሰናቸዋል። ግና ጆሮዎቻቸዉም፤ ዓይኖቻቸዉም፤ አእምሮዎቻቸዉም የፈየዷቸው ነገር አልነበረም። የአላህን አናቅጽ ያስተባብሉ ነበርና። በመሆኑም በእነርሱ ላይ ያ ያፌዙበት የነበረው ቅጣት ወረደባቸው።

وَلَقَدْ أَهْلَكْنَا مَا حَوْلَكُمْ مِنَ الْقُرَىٰ وَصَرَّفْنَا الْآيَاتِ لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ

በዙሪያችሁ የነበሩ ከተሞችንም አጠፋን። ይመለሱ ዘንድም ተደጋጋሚ ታዐምራትን አሳይተናቸው ነበር።

فَلَوْلَا نَصَرَهُمُ الَّذِينَ اتَّخَذُوا مِنْ دُونِ اللَّهِ قُرْبَانًا آلِهَةً ۖ بَلْ ضَلُّوا عَنْهُمْ ۚ وَذَٰلِكَ إِفْكُهُمْ وَمَا كَانُوا يَفْتَرُونَ

እነዚያ መቃረቢያ ይሆናቸው ዘንድ ከአላህ ሌላ በረዳትነት የያዟቸው አማልክት በመከራቸው ወቅት ለምን አልረዷቸዉም? ይልቁንም ከእነርሱ ራቁ። ይህ ሀሰታቸውና ይቀጥፉት የነበረው ነውና።

وَإِذْ صَرَفْنَا إِلَيْكَ نَفَرًا مِنَ الْجِنِّ يَسْتَمِعُونَ الْقُرْآنَ فَلَمَّا حَضَرُوهُ قَالُوا أَنْصِتُوا ۖ فَلَمَّا قُضِيَ وَلَّوْا إِلَىٰ قَوْمِهِمْ مُنْذِرِينَ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከአጋንንት የሆኑ ቡድኖች ቁርኣንን የሚያደምጡ ሁነው በላክንልህ ጊዜ የሆነውን አስታውስ። ሲነበብ በደረሱ ጊዜ «ዝም በሉ» ተባባሉ። ንባቡ ሲጠናቀቅም ወገኖቻቸውን ለማስጠንቀቅ ወደ ህዝቦቻቸው ተመለሱ።

قَالُوا يَا قَوْمَنَا إِنَّا سَمِعْنَا كِتَابًا أُنْزِلَ مِنْ بَعْدِ مُوسَىٰ مُصَدِّقًا لِمَا بَيْنَ يَدَيْهِ يَهْدِي إِلَى الْحَقِّ وَإِلَىٰ طَرِيقٍ مُسْتَقِيمٍ

አሉም ለወገኖቻቸው: «ወገኖቻችን ሆይ! ከሙሳ ተውራት በኋላ የተወረደንና ከእርሱ በፊት የወረዱትን መጽሐፍት አጽዳቂ ወደ እውነትና ወደ ቀጥተኛው ጎዳና መሪም የሆነን መጽሐፍ አደመጥን።

يَا قَوْمَنَا أَجِيبُوا دَاعِيَ اللَّهِ وَآمِنُوا بِهِ يَغْفِرْ لَكُمْ مِنْ ذُنُوبِكُمْ وَيُجِرْكُمْ مِنْ عَذَابٍ أَلِيمٍ

«ወገኖቻችን ሆይ! ለዚህ ወደ አላህ ለሚጠራችሁ ሰው በጎ ምላሽ ስጡ። በእርሱ እመኑም። ይህን ካረጋችሁ (አላህ) ከኀጢአቶቻችሁ ለእናንተ ይምራልና። ከአሳማሚ ቅጣትም ይጠብቃችኋል።

وَمَنْ لَا يُجِبْ دَاعِيَ اللَّهِ فَلَيْسَ بِمُعْجِزٍ فِي الْأَرْضِ وَلَيْسَ لَهُ مِنْ دُونِهِ أَوْلِيَاءُ ۚ أُولَٰئِكَ فِي ضَلَالٍ مُبِينٍ

ወደ አላህ ለሚጠራ ሰው ሁሉ በጎ ምላሽ ያልሰጠ በምድር ላይ ከአላህ ቅጣት አያመልጥም። ከእርሱ ሌላም ረዳት አይኖረዉም። እንዲህ አይነት ሰዎች ግልጽ ጥመት ውስጥ ናቸው።» (አሉ)

أَوَلَمْ يَرَوْا أَنَّ اللَّهَ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَلَمْ يَعْيَ بِخَلْقِهِنَّ بِقَادِرٍ عَلَىٰ أَنْ يُحْيِيَ الْمَوْتَىٰ ۚ بَلَىٰ إِنَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረው እርሱም በመፍጠሩም ድካም ያልተሰማው አላህ ሙታንን ህያው ማድረግ እንደሚችል አላዩምን ? በእርግጥም ይህን ማድረግ የሚሳነው አይደለም ። እርሱ ሁሉንም ነገር ቻይ ነውና።

وَيَوْمَ يُعْرَضُ الَّذِينَ كَفَرُوا عَلَى النَّارِ أَلَيْسَ هَٰذَا بِالْحَقِّ ۖ قَالُوا بَلَىٰ وَرَبِّنَا ۚ قَالَ فَذُوقُوا الْعَذَابَ بِمَا كُنْتُمْ تَكْفُرُونَ

እነዚያም የካዱት ሰዎች ሁሉ ወደ እሳት እንዲቀርቡ በሚደረጉ ጊዜ የሚሆነውን አስታውስ። «ይህ እውነት አይደለምን ?» ይባላሉ ። «አዎ እውነት መሆኑን በጌታችን በመማል እናረጋግጣለን» ይላሉ። እርሱም «ታስተባብሉት በነበራችሁት ሰበብ ቅጣትን ቅመሱ» ይላቸዋል።

فَاصْبِرْ كَمَا صَبَرَ أُولُو الْعَزْمِ مِنَ الرُّسُلِ وَلَا تَسْتَعْجِلْ لَهُمْ ۚ كَأَنَّهُمْ يَوْمَ يَرَوْنَ مَا يُوعَدُونَ لَمْ يَلْبَثُوا إِلَّا سَاعَةً مِنْ نَهَارٍ ۚ بَلَاغٌ ۚ فَهَلْ يُهْلَكُ إِلَّا الْقَوْمُ الْفَاسِقُونَ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከመልዕክተኞች መካከል የጽናት ባለቤቶች እንደታገሱት ሁሉ አንተም ታገስ።(በህዝቦችህ ላይ) ቅጣቱ ይፋጠንባቸው ዘንድም አትጠይቅ። ያን ቃል የተገባላቸውን ቅጣት በሚያዩ ጊዜ ምድር ላይ ከቀን ውስጥ የተወሰነ ወቅት ብቻ እንጂ እንዳልቆዩ ይሰማቸዋል። ይህ የማስጠንቀቂያ መልዕክት ነው። ከአመጸኞች ህዝቦች ውጪ ሌሎች እንዲጠፉ ይደረጋልን?