Muhammad · Muhammad · سورة محمد · 38 ayahs

القرآن الكريمAfrica Academy

بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።

الَّذِينَ كَفَرُوا وَصَدُّوا عَنْ سَبِيلِ اللَّهِ أَضَلَّ أَعْمَالَهُمْ

እነዚያ የካዱ እና ከአላህ መንገድ ሌሎችን የከለከሉ አላህ ስራዎቻቸውን አጠፋባቸው።

وَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ وَآمَنُوا بِمَا نُزِّلَ عَلَىٰ مُحَمَّدٍ وَهُوَ الْحَقُّ مِنْ رَبِّهِمْ ۙ كَفَّرَ عَنْهُمْ سَيِّئَاتِهِمْ وَأَصْلَحَ بَالَهُمْ

እነዚያም ያመኑ በጎዎችንም ተግባራት የሰሩ በሙሐመድ ላይም የተወረደው እርሱ ከጌታቸው ሲሆን እውነት ስለሆነ ያመኑ ከእነርሱ ላይ ኃጢአቶቻቸውን ያብሳል። ሁኔታቸውንም ሁሉ ያበጃል።

ذَٰلِكَ بِأَنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا اتَّبَعُوا الْبَاطِلَ وَأَنَّ الَّذِينَ آمَنُوا اتَّبَعُوا الْحَقَّ مِنْ رَبِّهِمْ ۚ كَذَٰلِكَ يَضْرِبُ اللَّهُ لِلنَّاسِ أَمْثَالَهُمْ

ይህ እነዚያ የካዱት ውሸትን የተከተሉ በመሆናቸውና እነዚያም ያመኑት ከጌታቸው የሆነን እውነት ስለተከተሉ ነው። ልክ እንደዚሁ አላህ ለሰዎች ምሳሌዎቻቸውን ያብራራል።

فَإِذَا لَقِيتُمُ الَّذِينَ كَفَرُوا فَضَرْبَ الرِّقَابِ حَتَّىٰ إِذَا أَثْخَنْتُمُوهُمْ فَشُدُّوا الْوَثَاقَ فَإِمَّا مَنًّا بَعْدُ وَإِمَّا فِدَاءً حَتَّىٰ تَضَعَ الْحَرْبُ أَوْزَارَهَا ۚ ذَٰلِكَ وَلَوْ يَشَاءُ اللَّهُ لَانْتَصَرَ مِنْهُمْ وَلَٰكِنْ لِيَبْلُوَ بَعْضَكُمْ بِبَعْضٍ ۗ وَالَّذِينَ قُتِلُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ فَلَنْ يُضِلَّ أَعْمَالَهُمْ

አማኞች ሆይ! እነዚያንም የካዱትን ሰዎች በጦር ላይ ባገኛችኋቸው ጊዜ ጫንቃዎችን በሀይል ምቱ። ባደከማችኋቸው ጊዜም አትግደሏቸው፤ ማርኳቸው። ማሰሪያውንም አጥብቁ። በኋላም በነጻ ትለቋቸዋላችሁ። ወይም ፊዳ ታስከፍሏቸዋላችሁ። ይህም ጦሩ መሳሪያዉን እስከሚጥል ድረስ ነው። ነገሩ ይህ ነው። አላህም ቢፈልግ ከእነርሱ ያለ ጦር በተበቀለ ነበር ግን ከፊላችሁን በከፊሉ ሊሞክር (በዚህ አዘዛችሁ)። እነዚያንም በአላህ መንገድ ላይ የተገደሉት ሰዎች ስራዎቻቸውን ፈጽሞ አያጠፋባቸዉም።

سَيَهْدِيهِمْ وَيُصْلِحُ بَالَهُمْ

በእርግጥ ይመራቸዋል። ሁኔታቸውንም ሁሉ ያበጃል።

وَيُدْخِلُهُمُ الْجَنَّةَ عَرَّفَهَا لَهُمْ

ገነትንም ያገባቸዋል። ለእነርሱ አስታውቋታል።

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِنْ تَنْصُرُوا اللَّهَ يَنْصُرْكُمْ وَيُثَبِّتْ أَقْدَامَكُمْ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የአላህን ሃይማኖት ብትረዱ ይረዳችኋል። ጫማዎቻችሁንም ያደላድላል።ያጸናላችኋል።

وَالَّذِينَ كَفَرُوا فَتَعْسًا لَهُمْ وَأَضَلَّ أَعْمَالَهُمْ

እነዚያም የካዱት ለእነርሱ ጥፋት ተገባቸው። ስራዎቻቸውንም አጠፋባቸው።

ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ كَرِهُوا مَا أَنْزَلَ اللَّهُ فَأَحْبَطَ أَعْمَالَهُمْ

ይህ እነርሱ አላህ ያወረደውን ስለጠሉ ነው። ስለዚህ ስራዎቻቸውን አበላሸባቸው።

أَفَلَمْ يَسِيرُوا فِي الْأَرْضِ فَيَنْظُرُوا كَيْفَ كَانَ عَاقِبَةُ الَّذِينَ مِنْ قَبْلِهِمْ ۚ دَمَّرَ اللَّهُ عَلَيْهِمْ ۖ وَلِلْكَافِرِينَ أَمْثَالُهَا

የእነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩ ከሓዲያን ሁሉ መጨረሻ እንዴት እንደነበር ያዩ ዘንድ በምድር ላይ አልሄዱምን? አላህ ያላቸውን ሁሉ አጠፋባቸው። ለካሓዲያንም ሁሉ የዚሁ ተመሳሳይ አለባቸው።

ذَٰلِكَ بِأَنَّ اللَّهَ مَوْلَى الَّذِينَ آمَنُوا وَأَنَّ الْكَافِرِينَ لَا مَوْلَىٰ لَهُمْ

ይህ አላህ የእነዚያ ያመኑት ረዳት ስለሆነና ከሓዲያንም ለእነርሱ ረዳት ስለሌላቸው ነው።

إِنَّ اللَّهَ يُدْخِلُ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِنْ تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ ۖ وَالَّذِينَ كَفَرُوا يَتَمَتَّعُونَ وَيَأْكُلُونَ كَمَا تَأْكُلُ الْأَنْعَامُ وَالنَّارُ مَثْوًى لَهُمْ

አላህ እነዚያን በእሱ ያመኑትንና መልካሞችን ተግባራት የሰሩትን ሁሉ ከስሮቻቸው ወንዞች ወደ ሚፈሱባቸው ገነቶች ያስገባቸዋል። እነዚያም በአላህ የካዱት በቅርቢቱ ዓለም ብቻ ይጣቀማሉ። እንሰሳዎች እንደሚበሉም ይበላሉ። የገሀነም እሳትም ለእነርሱ (የሁል ጊዜ) መኖሪያቸው ናት።

وَكَأَيِّنْ مِنْ قَرْيَةٍ هِيَ أَشَدُّ قُوَّةً مِنْ قَرْيَتِكَ الَّتِي أَخْرَجَتْكَ أَهْلَكْنَاهُمْ فَلَا نَاصِرَ لَهُمْ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከዚያች አንተን ካወጣችህ ከተማህ ይበልጥ በሀይል ጠንካራ የሆኑ ባለቤቶቻቸዉን ያጠፋናቸው ብዙ ከተሞች አሉ። ለእነርሱም ረዳት አልነበራቸዉም።

أَفَمَنْ كَانَ عَلَىٰ بَيِّنَةٍ مِنْ رَبِّهِ كَمَنْ زُيِّنَ لَهُ سُوءُ عَمَلِهِ وَاتَّبَعُوا أَهْوَاءَهُمْ

ከጌታው በሆነች አስረጅ ላይ የሆነ ምዕመን ክፉ ስራቸው ለእነርሱ እንደተሸለመላቸውና ዝንባሌዎቻቸውን እንደ ተከተሉ ክፍሎች ነውን?

مَثَلُ الْجَنَّةِ الَّتِي وُعِدَ الْمُتَّقُونَ ۖ فِيهَا أَنْهَارٌ مِنْ مَاءٍ غَيْرِ آسِنٍ وَأَنْهَارٌ مِنْ لَبَنٍ لَمْ يَتَغَيَّرْ طَعْمُهُ وَأَنْهَارٌ مِنْ خَمْرٍ لَذَّةٍ لِلشَّارِبِينَ وَأَنْهَارٌ مِنْ عَسَلٍ مُصَفًّى ۖ وَلَهُمْ فِيهَا مِنْ كُلِّ الثَّمَرَاتِ وَمَغْفِرَةٌ مِنْ رَبِّهِمْ ۖ كَمَنْ هُوَ خَالِدٌ فِي النَّارِ وَسُقُوا مَاءً حَمِيمًا فَقَطَّعَ أَمْعَاءَهُمْ

ያች አላህን ለሚፈሩ ሰዎች ቃል የተገባችው ገነት (ይህን ትመስላለች)፤ በውስጧ ሽታው ከማይለወጥ የውሃ ወንዞች፤ ጣዕሙ የማይለወጥ የወተት ወንዞች፤ ለጠጪዎች ሁሉ እጅግ ጣፋጭ የሆኑ የወይን ጠጅ ወንዞችና የንጹህ(የተነጠረ) ማር ወንዞች አሉባት። በውስጧ ሁሉም የፍራፍሬ አይነቶች ከጌታቸዉም ምህረት ተዘጋጅተውላቸዋል። በእነዚህ ገነቶች የሆነ እንደነዚያ እሳት ውስጥ ዘወትር እንደሚኖሩ የፈላ ውሃም እንዲጠጡ እንደሚደረጉትና ውሃዉም የሆድ ዕቃቸውን እንደሚበጣጥስባቸው ነውን? አይደለም።

وَمِنْهُمْ مَنْ يَسْتَمِعُ إِلَيْكَ حَتَّىٰ إِذَا خَرَجُوا مِنْ عِنْدِكَ قَالُوا لِلَّذِينَ أُوتُوا الْعِلْمَ مَاذَا قَالَ آنِفًا ۚ أُولَٰئِكَ الَّذِينَ طَبَعَ اللَّهُ عَلَىٰ قُلُوبِهِمْ وَاتَّبَعُوا أَهْوَاءَهُمْ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱም መካከል ወደ አንተ የሚያዳምጡ አሉ። ካንተ ዘንድ በወጡ ጊዜ ለእነዚያ እውቀት ለተሰጡት «አሁን ምን አለ?» ይላሉ። እነዚያ እነዚህ በልቦቻቸው ላይ አላህ ያተማቸው ዝንባሌዎቻቸውን የተከተሉ ናቸው።

وَالَّذِينَ اهْتَدَوْا زَادَهُمْ هُدًى وَآتَاهُمْ تَقْوَاهُمْ

እነዚያም ወደ ቀናው መንገድ የተመሩት አላህ መመራትን ጨመረላቸው። (ከእሳት) መጠበቂያቸውንም ሰጣቸው።

فَهَلْ يَنْظُرُونَ إِلَّا السَّاعَةَ أَنْ تَأْتِيَهُمْ بَغْتَةً ۖ فَقَدْ جَاءَ أَشْرَاطُهَا ۚ فَأَنَّىٰ لَهُمْ إِذَا جَاءَتْهُمْ ذِكْرَاهُمْ

የሰዓቲቱንም በድንገት መምጣት እንጂ ሌላን ይጠባበቃሉን? ምልክቶቿም በእርግጥ መጥተዋል። በመጣችባቸዉም ጊዜ ማስታወሳቸው ለእነርሱ እንዴት ይጠቅማቸዋል።

فَاعْلَمْ أَنَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا اللَّهُ وَاسْتَغْفِرْ لِذَنْبِكَ وَلِلْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ ۗ وَاللَّهُ يَعْلَمُ مُتَقَلَّبَكُمْ وَمَثْوَاكُمْ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነሆ ከአላህ ሌላ ትክክለኛ አምላክ አለመኖሩንም እወቅ። ስለ ስህተትህም ሆነ ለወንድም ለሴትም አማኞች ስህተት ምህረትን ለምን። አላህም መዘዋወሪያችሁንም ሆነ መርጊያችሁን ያውቃል።

وَيَقُولُ الَّذِينَ آمَنُوا لَوْلَا نُزِّلَتْ سُورَةٌ ۖ فَإِذَا أُنْزِلَتْ سُورَةٌ مُحْكَمَةٌ وَذُكِرَ فِيهَا الْقِتَالُ ۙ رَأَيْتَ الَّذِينَ فِي قُلُوبِهِمْ مَرَضٌ يَنْظُرُونَ إِلَيْكَ نَظَرَ الْمَغْشِيِّ عَلَيْهِ مِنَ الْمَوْتِ ۖ فَأَوْلَىٰ لَهُمْ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ ያመኑት ሰዎች (ለዲን ለመታገል ግፊት ያለበት)« የቁርኣን ምዕራፍ አይወረድም ኖሯልን?» ይላሉ። የጠነከረም ምዕራፍ በወረደና በውስጡም መጋደል በተወሳ ጊዜ እነዚያን በልቦቻቸው ውስጥ የንፍቅና በሽታ ያለባቸውን ሰዎች ከሞት የሆነ መከራ በእርሱ ላይ እንደወደቀበት ሰው አስተያያት ወደ አንተ ሲመለከቱ ታያቸዋለህ። ለእነርሱው ተገባቸው።

طَاعَةٌ وَقَوْلٌ مَعْرُوفٌ ۚ فَإِذَا عَزَمَ الْأَمْرُ فَلَوْ صَدَقُوا اللَّهَ لَكَانَ خَيْرًا لَهُمْ

ታዛዥነትና መልካም ንግግር ይሻላቸዋል። ትዕዛዙም ቁርጥ በሆነ ጊዜ ለአላህ ትእዛዝ እውነተኞች በሆኑ ኖሮ ለእነርሱ የተሻለ በሆነ ነበር።

فَهَلْ عَسَيْتُمْ إِنْ تَوَلَّيْتُمْ أَنْ تُفْسِدُوا فِي الْأَرْضِ وَتُقَطِّعُوا أَرْحَامَكُمْ

ብትሸሹም በምድር ላይ ማበላሸትን ዝምድናችሁንም መቁረጥን ከጀላችሁን?

أُولَٰئِكَ الَّذِينَ لَعَنَهُمُ اللَّهُ فَأَصَمَّهُمْ وَأَعْمَىٰ أَبْصَارَهُمْ

እነዚህ እነዚያ አላህ የረገማቸው ያደነቆራቸዉም ዓይኖቻቸውንም ያሳወራቸው ናቸው።

أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ أَمْ عَلَىٰ قُلُوبٍ أَقْفَالُهَا

ቁርኣንንም አያስተነትኑምን? በእውነቱ በልቦቻቸው ላይ ቁልፎቿ አሉባቸውን?

إِنَّ الَّذِينَ ارْتَدُّوا عَلَىٰ أَدْبَارِهِمْ مِنْ بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُمُ الْهُدَى ۙ الشَّيْطَانُ سَوَّلَ لَهُمْ وَأَمْلَىٰ لَهُمْ

እነዚያ ለእነርሱ ቅኑው መንገድ ከተብራራላቸው በኋላ ወደ ኋላቸው የተመለሱት ሰይጣን መቀልበሳቸውን ለእነርሱ ሸለመላቸው። ለእነርሱም አዘናጋቸው።

ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ قَالُوا لِلَّذِينَ كَرِهُوا مَا نَزَّلَ اللَّهُ سَنُطِيعُكُمْ فِي بَعْضِ الْأَمْرِ ۖ وَاللَّهُ يَعْلَمُ إِسْرَارَهُمْ

ይህ እነርሱ ለእነዚያ አላህ ያወረደውን ለጠሉት «በነገሩ ከፊሉን እንታዘዛችኃለን» ያሉ በመሆናቸው ነው። አላህም ምስጢራቸውንም ያውቃል።

فَكَيْفَ إِذَا تَوَفَّتْهُمُ الْمَلَائِكَةُ يَضْرِبُونَ وُجُوهَهُمْ وَأَدْبَارَهُمْ

መላዕክት ፊቶቻቸውንና ጀርባዎቻቸውን የሚመቱ ሲሆኑ ነፍሶቻቸውን በወሰዱ ጊዜ (ሁኔታቸው እንዴት ይሆናል?)

ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمُ اتَّبَعُوا مَا أَسْخَطَ اللَّهَ وَكَرِهُوا رِضْوَانَهُ فَأَحْبَطَ أَعْمَالَهُمْ

ይህ እነርሱ አላህን ያስቆጣውን ነገር ሁሉ ስለተከተሉ ውዴታውንም ስለጠሉ ነው። ስለዚህ ስራዎቻቸውን አበላሸባቸው።

أَمْ حَسِبَ الَّذِينَ فِي قُلُوبِهِمْ مَرَضٌ أَنْ لَنْ يُخْرِجَ اللَّهُ أَضْغَانَهُمْ

እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው ሰዎች በሙስሊሞች ላይ የነበራቸዉን ቂሞቻቸውን አላህ ፈጽሞ እንደማያወጣ ጠረጠሩን?

وَلَوْ نَشَاءُ لَأَرَيْنَاكَهُمْ فَلَعَرَفْتَهُمْ بِسِيمَاهُمْ ۚ وَلَتَعْرِفَنَّهُمْ فِي لَحْنِ الْقَوْلِ ۚ وَاللَّهُ يَعْلَمُ أَعْمَالَكُمْ

(ሙሐመድ ሆይ!) ብንፈልግ ኖሮ እነርሱን ባሳየንህና በምልክታቸዉም በእርግጥ ባወቅካቸው ነበር። ንግግርንም በማሸሞራቸው በእርግጥ ታውቃቸዋለህ። አላህም ስራዎቻችሁን ሁሉ ያውቃልና።

وَلَنَبْلُوَنَّكُمْ حَتَّىٰ نَعْلَمَ الْمُجَاهِدِينَ مِنْكُمْ وَالصَّابِرِينَ وَنَبْلُوَ أَخْبَارَكُمْ

(አማኞች ሆይ!) ከናንተ መካከል ተዋጊዎችንና ታጋሾቹን እስከምንገልጽ ድረስ በእርግጥ እንሞክራችኋለን። ወሬዎቻችሁንም (እስከምንገልጽ ድረስ) እንሞክራችኋለን።

إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا وَصَدُّوا عَنْ سَبِيلِ اللَّهِ وَشَاقُّوا الرَّسُولَ مِنْ بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُمُ الْهُدَىٰ لَنْ يَضُرُّوا اللَّهَ شَيْئًا وَسَيُحْبِطُ أَعْمَالَهُمْ

እነዚያ የካዱና ከአላህም መንገድ ሰዎችን ያገዱ ለእነርሱም ቅኑ መንገድ ከተገለጸላቸው በኋላ መልዕክተኛውን የተከራከሩ ሁሉ አላህን በምንም አይጎዱትም። ስራዎቻቸውንም በእርግጥ ያበላሻል።

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَطِيعُوا اللَّهَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ وَلَا تُبْطِلُوا أَعْمَالَكُمْ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ታዘዙ። መልዕክተኛውንም ታዘዙ። ስራዎቻችሁንም አታበላሹ።

إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا وَصَدُّوا عَنْ سَبِيلِ اللَّهِ ثُمَّ مَاتُوا وَهُمْ كُفَّارٌ فَلَنْ يَغْفِرَ اللَّهُ لَهُمْ

እነዚያ የካዱ ከአላህ መንገድ ሌሎችን ያገዱና ከዚያም እነርሱ ከሓዲያን ሆነው የሞቱ አላህ ለእነርሱ በፍጹም አይምርም።

فَلَا تَهِنُوا وَتَدْعُوا إِلَى السَّلْمِ وَأَنْتُمُ الْأَعْلَوْنَ وَاللَّهُ مَعَكُمْ وَلَنْ يَتِرَكُمْ أَعْمَالَكُمْ

እናንተ አሸናፊዎች ስትሆኑና አላህም ከናንተ ጋር ሲሆን አትድከሙ። ወደ እርቅም አትጥሩ። ስራዎቻችሁን ፈጽሞ አያጎድልባችሁም።

إِنَّمَا الْحَيَاةُ الدُّنْيَا لَعِبٌ وَلَهْوٌ ۚ وَإِنْ تُؤْمِنُوا وَتَتَّقُوا يُؤْتِكُمْ أُجُورَكُمْ وَلَا يَسْأَلْكُمْ أَمْوَالَكُمْ

ቅርቢቱ ሕይወት ጫወታና ዛዛታ ብቻ ናት። ብታምኑና ቅጣቱንም ብትጠነቀቁ ምንዳዎቻችሁን ይሰጣችኋል። ገንዘቦቻችሁንም ሁሉ አይጠይቃችሁም።

إِنْ يَسْأَلْكُمُوهَا فَيُحْفِكُمْ تَبْخَلُوا وَيُخْرِجْ أَضْغَانَكُمْ

እርሷን ቢጠይቃችሁና ችክ ቢልባችሁ ትሰስታላችሁ። ቂሞቻችሁንም ያወጣል።

هَا أَنْتُمْ هَٰؤُلَاءِ تُدْعَوْنَ لِتُنْفِقُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ فَمِنْكُمْ مَنْ يَبْخَلُ ۖ وَمَنْ يَبْخَلْ فَإِنَّمَا يَبْخَلُ عَنْ نَفْسِهِ ۚ وَاللَّهُ الْغَنِيُّ وَأَنْتُمُ الْفُقَرَاءُ ۚ وَإِنْ تَتَوَلَّوْا يَسْتَبْدِلْ قَوْمًا غَيْرَكُمْ ثُمَّ لَا يَكُونُوا أَمْثَالَكُمْ

(አማኞች ሆይ!) አስተውሉ። እናንተ እነዚያ በአላህ መንገድ ትለግሱ ዘንድ የምትጠሩ ናችሁ። ከናንተም መካከልም የሚሰስት ሰው አለ። የሚሰስት ሰው ሁሉ የሚሰስተው በራሱ ላይ ብቻ ነው። አላህ በራሱ ተብቃቂ ነውና። እናንተ ግን ድሆች ናችሁ። ብትሸሹም ሌሎችን ህዝቦች በቦታችሁ ይለውጣል። ከዚያም ባለመታዘዝ እንደናንተ ብጤዎቻችሁ አይሆኑም።