ق ۚ وَالْقُرْآنِ الْمَجِيدِ
ቃፍ ፤ በተከበረው ቁርኣን እምላለሁ።
القرآن الكريمAfrica Academy
بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።
ق ۚ وَالْقُرْآنِ الْمَجِيدِ
ቃፍ ፤ በተከበረው ቁርኣን እምላለሁ።
بَلْ عَجِبُوا أَنْ جَاءَهُمْ مُنْذِرٌ مِنْهُمْ فَقَالَ الْكَافِرُونَ هَٰذَا شَيْءٌ عَجِيبٌ
ይልቁንም ከእነርሱ መካከል የሆነ አስፈራሪ ስለ መጣላቸው ተደነቁ። ከሓዲያንም አሉ: «ይህ አስደናቂ ነገር ነው።
أَإِذَا مِتْنَا وَكُنَّا تُرَابًا ۖ ذَٰلِكَ رَجْعٌ بَعِيدٌ
«በሞትንና አፈር በሆንን ጊዜ እንመለሳለንን? ይህ ሩቅ የሆነ መመለስ ነው።» አሉ።
قَدْ عَلِمْنَا مَا تَنْقُصُ الْأَرْضُ مِنْهُمْ ۖ وَعِنْدَنَا كِتَابٌ حَفِيظٌ
ከእነርሱ አካል ምድር የምታጎድለውን በእርግጥ አውቀናል። እኛም ዘንድ ጠባቂ መጽሐፍ አለ።
بَلْ كَذَّبُوا بِالْحَقِّ لَمَّا جَاءَهُمْ فَهُمْ فِي أَمْرٍ مَرِيجٍ
ይልቁንም እውነቱን (ቁርኣንን) በመጣላቸው ጊዜ አስተባበሉ። እነርሱም በተምታታ ነገር ውስጥ ናቸው።
أَفَلَمْ يَنْظُرُوا إِلَى السَّمَاءِ فَوْقَهُمْ كَيْفَ بَنَيْنَاهَا وَزَيَّنَّاهَا وَمَا لَهَا مِنْ فُرُوجٍ
ወደ ሰማይም ከበላያቸው ስትሆን ለእርሷ ምንም ቀዳዳዎች የሌሏት ሆና እንዴት እንደገነባናትና በከዋክብት እንዳጌጥናት አልተመለከቱምን?
وَالْأَرْضَ مَدَدْنَاهَا وَأَلْقَيْنَا فِيهَا رَوَاسِيَ وَأَنْبَتْنَا فِيهَا مِنْ كُلِّ زَوْجٍ بَهِيجٍ
ምድርም ዘረጋናት በእርሷም ውስጥ ጋራዎችን ጣልንባት ። በውስጧም ከሚያስደስት አይነት ሁሉ አበቀልን።
تَبْصِرَةً وَذِكْرَىٰ لِكُلِّ عَبْدٍ مُنِيبٍ
ይህንን ያደረግነው ተመላሽ ለሆነ ባሪያ ሁሉ ለማሳየትና ለማስገንዘብ ነው።
وَنَزَّلْنَا مِنَ السَّمَاءِ مَاءً مُبَارَكًا فَأَنْبَتْنَا بِهِ جَنَّاتٍ وَحَبَّ الْحَصِيدِ
ከሰማይም ብሩክን ውሃ አወረድን በእርሱም አትክልቶችንና የሚታጨድን አዝመራ ፍሬ አበቀልን።
وَالنَّخْلَ بَاسِقَاتٍ لَهَا طَلْعٌ نَضِيدٌ
ዘንባባንም ረዣዥም ለእርሷ የተደራረበ እንቡጥ ያላት ስትሆን አበቀልን።
رِزْقًا لِلْعِبَادِ ۖ وَأَحْيَيْنَا بِهِ بَلْدَةً مَيْتًا ۚ كَذَٰلِكَ الْخُرُوجُ
ለባሮቹ ሲሳይ ትሆን ዘንድ (አዘጋጀናት)። በእርሱም የሞተችን ሀገር ሕያው አደረግንበት። ከመቃብር መውጣትም ልክ እንደዚሁ ነው።
كَذَّبَتْ قَبْلَهُمْ قَوْمُ نُوحٍ وَأَصْحَابُ الرَّسِّ وَثَمُودُ
ከእነርሱ በፊት የኑህ ህዝቦችና የረስ ሰዎችም ሰሙድም አስተባበሉ።
وَعَادٌ وَفِرْعَوْنُ وَإِخْوَانُ لُوطٍ
ዓድም ፈርዖንም የሉጥ ወንድሞችም፤
وَأَصْحَابُ الْأَيْكَةِ وَقَوْمُ تُبَّعٍ ۚ كُلٌّ كَذَّبَ الرُّسُلَ فَحَقَّ وَعِيدِ
የጫካው ባለቤቶችም የቱበዕ ህዝቦችም ሁሉ መልዕክተኞችን አስተባበሉ። ዛቻየም ተረጋገጠባቸው።
أَفَعَيِينَا بِالْخَلْقِ الْأَوَّلِ ۚ بَلْ هُمْ فِي لَبْسٍ مِنْ خَلْقٍ جَدِيدٍ
በመጀመሪያው መፍጠር ደከምን? በእውነቱ እነርሱ ከአዲስ መፍጠር በመጠራጠር ውስጥ ናቸው።
وَلَقَدْ خَلَقْنَا الْإِنْسَانَ وَنَعْلَمُ مَا تُوَسْوِسُ بِهِ نَفْسُهُ ۖ وَنَحْنُ أَقْرَبُ إِلَيْهِ مِنْ حَبْلِ الْوَرِيدِ
ሰውንም ነፍሱ በሀሳቡ የምታጫውተውን የምናውቅ ስንሆን ፈጠርነው። እኛም ከደም ጋኑ ጅማት ይበልጥ ወደ እርሱ ቅርብ ነን።
إِذْ يَتَلَقَّى الْمُتَلَقِّيَانِ عَنِ الْيَمِينِ وَعَنِ الشِّمَالِ قَعِيدٌ
ሁለት ቃል ተቀባዮች መላዕክት ከቀኝና ከግራ ተቀማጮች ሆነው በሚቀበሉ ጊዜ አስታውስ።
مَا يَلْفِظُ مِنْ قَوْلٍ إِلَّا لَدَيْهِ رَقِيبٌ عَتِيدٌ
ከቃል ምንም አይናገርም ከአጠገቡ ተጠባባቂ እና ዝግጁ የሆኑ መላዕክት ያሉበት ቢሆን እንጂ።
وَجَاءَتْ سَكْرَةُ الْمَوْتِ بِالْحَقِّ ۖ ذَٰلِكَ مَا كُنْتَ مِنْهُ تَحِيدُ
የሞትም መከራ እውነቱን ነገር ታመጣለች። «(ሰው ሆይ!) ይህ ያ ከእርሱ ትሸሸው የነበርከው ነው» ይባላል።
وَنُفِخَ فِي الصُّورِ ۚ ذَٰلِكَ يَوْمُ الْوَعِيدِ
በቀንዱም ውስጥ ይነፋል። ያ ቀን የዛቻው መፈጸሚያ ቀን ነው።
وَجَاءَتْ كُلُّ نَفْسٍ مَعَهَا سَائِقٌ وَشَهِيدٌ
ነፍስም ሁሉ ከእርሷ ጋር ነጅና መስካሪ ያለባት ሆና ትመጣለች።
لَقَدْ كُنْتَ فِي غَفْلَةٍ مِنْ هَٰذَا فَكَشَفْنَا عَنْكَ غِطَاءَكَ فَبَصَرُكَ الْيَوْمَ حَدِيدٌ
«ከዚህ ነገር በእርግጥ የዘነጋህ ነበርክ። ሽፋንህንም ካንተ ላይ ገለጥንልህ። ስለዚህ ዛሬ ዓይንህ ስለታም ነው» (ይባላል)።
وَقَالَ قَرِينُهُ هَٰذَا مَا لَدَيَّ عَتِيدٌ
ቁራኛዉም (መልዓክ) «ይህ ያ እኔ ዘንድ ያለው የተዘጋጀ ነው።» ይላል።
أَلْقِيَا فِي جَهَنَّمَ كُلَّ كَفَّارٍ عَنِيدٍ
(አላህም ይላል): «ሞገደኛ ከሓዲን ሁሉ በገሀነም ውስጥ ጣሉ።
مَنَّاعٍ لِلْخَيْرِ مُعْتَدٍ مُرِيبٍ
«ለበጎ ስራ ከልካይ በዳይ ተጠራጣሪ የሆነን ሁሉ ጣሉ።
الَّذِي جَعَلَ مَعَ اللَّهِ إِلَٰهًا آخَرَ فَأَلْقِيَاهُ فِي الْعَذَابِ الشَّدِيدِ
«ያንን ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ ያደረገውን በብርቱ ቅጣት ውስጥ ጣሉት» ይባላል።
قَالَ قَرِينُهُ رَبَّنَا مَا أَطْغَيْتُهُ وَلَٰكِنْ كَانَ فِي ضَلَالٍ بَعِيدٍ
ቁራኛው (ሰይጣን) «ጌታችን ሆይ! እኔ አላሳሳትኩትም ግን ራሱ በሩቅ ስህተት ውስጥ ነበር» ይላል።
قَالَ لَا تَخْتَصِمُوا لَدَيَّ وَقَدْ قَدَّمْتُ إِلَيْكُمْ بِالْوَعِيدِ
(አላህም) ይላል: «ወደ እናንተ ዛቻን በእርግጥ ያስቀደምኩ ስሆን እኔ ዘንድ አትጨቃጨቁ።
مَا يُبَدَّلُ الْقَوْلُ لَدَيَّ وَمَا أَنَا بِظَلَّامٍ لِلْعَبِيدِ
«ቃሉ እኔ ዘንድ አይለወጥም እኔም ለባሮቼ ፈጽሞ በዳይ አይደለሁም» (ይላቸዋል)።
يَوْمَ نَقُولُ لِجَهَنَّمَ هَلِ امْتَلَأْتِ وَتَقُولُ هَلْ مِنْ مَزِيدٍ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለገሀነም «ሞላሽን?» የምንልበትንና (ገሀነምም) «ጭማሪ አለን?» የምትልበትን ቀን አስጠንቅቃቸው።
وَأُزْلِفَتِ الْجَنَّةُ لِلْمُتَّقِينَ غَيْرَ بَعِيدٍ
ገነትም አላህን ለፈሩት ሁሉ ሩቅ ባልሆነ ስፍራ ትቀረባለች።
هَٰذَا مَا تُوعَدُونَ لِكُلِّ أَوَّابٍ حَفِيظٍ
(ይባላሉም) «ይህ ወደ አላህ ተመላሽና ህግጋቱን ጠባቂ ለሆነ ሁሉ የተቀጠራችሁት ነው።
مَنْ خَشِيَ الرَّحْمَٰنَ بِالْغَيْبِ وَجَاءَ بِقَلْبٍ مُنِيبٍ
«አር-ረህማንን በሩቅ ሆኖ ለፈራና በተመላሽ ልብ ለመጣ ትቀረባለች።
ادْخُلُوهَا بِسَلَامٍ ۖ ذَٰلِكَ يَوْمُ الْخُلُودِ
«በሰላም ግቧታ ይህ የመዘውተሪያ ቀን ነው» (ይባላሉ)።
لَهُمْ مَا يَشَاءُونَ فِيهَا وَلَدَيْنَا مَزِيدٌ
ለእነርሱ በውስጧ ሲሆኑ የሚሹት ሁሉ አላቸው እኛም ዘንድ ጭማሪ አለ።
وَكَمْ أَهْلَكْنَا قَبْلَهُمْ مِنْ قَرْنٍ هُمْ أَشَدُّ مِنْهُمْ بَطْشًا فَنَقَّبُوا فِي الْبِلَادِ هَلْ مِنْ مَحِيصٍ
ከእነርሱም (ከቁረይሾች) በፊት ከክፍለ ዘመናት ህዝቦች በሀያልነት ከእነርሱ ይበልጥ የበረቱ ሆነው ማምለጫ ፍለጋ በየሀገሮቹ የመረመሩ ብዙዎችንም አጥፍተናል። ማምለጫ አለን?
إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَذِكْرَىٰ لِمَنْ كَانَ لَهُ قَلْبٌ أَوْ أَلْقَى السَّمْعَ وَهُوَ شَهِيدٌ
በዚሁ ውስጥ ልብ ላለው ወይም እርሱ በህሊናው ጆሮውን የሰጠ ሆኖ ወደ ሚነበብለት ጆሮውን ለጣለ ሰው ሁሉ ግሳጼ አለበት።
وَلَقَدْ خَلَقْنَا السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ وَمَا مَسَّنَا مِنْ لُغُوبٍ
ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ በእርግጥ ፈጠርን። ድካምም ምንም አልነካንም።
فَاصْبِرْ عَلَىٰ مَا يَقُولُونَ وَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ قَبْلَ طُلُوعِ الشَّمْسِ وَقَبْلَ الْغُرُوبِ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በሚሉትም ላይ ታገስ ጌታህንም ከማመስገን ጋር ጸሐይ ከመውጣቷ በፊትና ከመግባቷም በፊት አጥራው።
وَمِنَ اللَّيْلِ فَسَبِّحْهُ وَأَدْبَارَ السُّجُودِ
ከሌሊትም አጥራው፤ ከስግደቶችም በኋላዎች አጥራው።
وَاسْتَمِعْ يَوْمَ يُنَادِ الْمُنَادِ مِنْ مَكَانٍ قَرِيبٍ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (የሚነገርህን) አዳምጥም፤ ጠሪው ከቅርብ ስፍራ በሚጠራበት ቀን (የሚሆነውን)።
يَوْمَ يَسْمَعُونَ الصَّيْحَةَ بِالْحَقِّ ۚ ذَٰلِكَ يَوْمُ الْخُرُوجِ
ጩኸቲቱን በእውነቱ የሚሰሙበት ቀን፤ ያ ከመቃብር የመውጫው ቀን ነው።
إِنَّا نَحْنُ نُحْيِي وَنُمِيتُ وَإِلَيْنَا الْمَصِيرُ
እኛው ሕያው እናደርጋለን። እንገድላለንም። በመጨረሻም ጊዜ መመለሻው ወደ እኛ ብቻ ነው።
يَوْمَ تَشَقَّقُ الْأَرْضُ عَنْهُمْ سِرَاعًا ۚ ذَٰلِكَ حَشْرٌ عَلَيْنَا يَسِيرٌ
የሚፈጥኑ ሆነው ምድር ከእነርሱ ላይ የምትሰነጣጠቅበት ቀን (የመውጫ ቀን ነው)። ይህ በእኛ ላይ ገር የሆነ መሰብሰብ ነው።
نَحْنُ أَعْلَمُ بِمَا يَقُولُونَ ۖ وَمَا أَنْتَ عَلَيْهِمْ بِجَبَّارٍ ۖ فَذَكِّرْ بِالْقُرْآنِ مَنْ يَخَافُ وَعِيدِ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ የሚሉትን ሁሉ አዋቂ ነን። አንተም በእነርሱ ላይ አስገዳጅ አይደለህም። ስለዚህ ዛቻየን የሚፈራን ሰው ሁሉ በቁርኣን አስታውስ።