وَالذَّارِيَاتِ ذَرْوًا
መበተንን በታኝ በሆኑት (ንፋሶች) እምላለሁ
القرآن الكريمAfrica Academy
بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።
وَالذَّارِيَاتِ ذَرْوًا
መበተንን በታኝ በሆኑት (ንፋሶች) እምላለሁ
فَالْحَامِلَاتِ وِقْرًا
ከባድ ዝናብን ተሸካሚዎች በሆኑትም (ዳመናዎች)፤
فَالْجَارِيَاتِ يُسْرًا
ገር መንሻለልን ተንሻላዮች በሆኑትም (መርከቦች) እምላለሁ።
فَالْمُقَسِّمَاتِ أَمْرًا
ጉዳይን ሁሉ አከፋፋዮች በሆኑትም (መላዕክት) እምላለሁ።
إِنَّمَا تُوعَدُونَ لَصَادِقٌ
የምትቀጠሩት (ትንሳኤ) እውነት ነው።
وَإِنَّ الدِّينَ لَوَاقِعٌ
(እንደየስራው) ዋጋን ማግኘትም የማይቀር ነው።
وَالسَّمَاءِ ذَاتِ الْحُبُكِ
የ(ከዋክብት) መንገዶች ባለቤት በሆነችው ሰማይ እምላለሁ።
إِنَّكُمْ لَفِي قَوْلٍ مُخْتَلِفٍ
እናንተ በተለያየ ቃል ውስጥ ናችሁ።
يُؤْفَكُ عَنْهُ مَنْ أُفِكَ
ከእርሱ (በአላህ ውሳኔ) የተመለሰ ሰው ይመለሳል።
قُتِلَ الْخَرَّاصُونَ
በግምት የሚናገሩ ውሸታሞች ተረገሙ።
الَّذِينَ هُمْ فِي غَمْرَةٍ سَاهُونَ
እነዚያ እነርሱ በሚሸፍን ስህተት ውስጥ ዘንጊዎች የሆኑት።
يَسْأَلُونَ أَيَّانَ يَوْمُ الدِّينِ
የዋጋ መስጫው ቀን መቼ እንደሆነ ይጠይቃሉ።
يَوْمَ هُمْ عَلَى النَّارِ يُفْتَنُونَ
(እነርሱ) በእሳት ላይ በሚፈተኑበት ቀን ነው።
ذُوقُوا فِتْنَتَكُمْ هَٰذَا الَّذِي كُنْتُمْ بِهِ تَسْتَعْجِلُونَ
«መከራችሁን ቅመሱ ይህ ያ በእርሱ ትቻኮሉበት የነበራችሁት ነው» (ይባላሉ)።
إِنَّ الْمُتَّقِينَ فِي جَنَّاتٍ وَعُيُونٍ
አላህን ፈሪዎቹ በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው።
آخِذِينَ مَا آتَاهُمْ رَبُّهُمْ ۚ إِنَّهُمْ كَانُوا قَبْلَ ذَٰلِكَ مُحْسِنِينَ
ያንን ጌታቸው የሰጣቸውን ተቀባዮች ሆነው (በገነት ውስጥ ይሆናሉ)። እነርሱ ከዚህ በፊት መልካም ሰሪዎች ነበሩና።
كَانُوا قَلِيلًا مِنَ اللَّيْلِ مَا يَهْجَعُونَ
ከሌሊቱ ጥቂቱን ብቻ ይተኙ ነበር።
وَبِالْأَسْحَارِ هُمْ يَسْتَغْفِرُونَ
በሌሊቱ መጨረሻዎችም እነርሱ ምህረትን ይለምናሉ።
وَفِي أَمْوَالِهِمْ حَقٌّ لِلسَّائِلِ وَالْمَحْرُومِ
በገንዘቦቻቸዉም ውስጥ ለለማኝና ከልመና ለተከለከለም (በችሮታቸው) መብት አለ።
وَفِي الْأَرْضِ آيَاتٌ لِلْمُوقِنِينَ
በምድርም ውስጥ ለሚያረጋግጡ ሰዎች አያሌ ምልክቶች አሉ።
وَفِي أَنْفُسِكُمْ ۚ أَفَلَا تُبْصِرُونَ
(ሰዎች ሆይ!) በነፍሶቻችሁም ውስጥ አያሌ ምልክቶች አሉ። ታዲያ አትመለከቱምን?
وَفِي السَّمَاءِ رِزْقُكُمْ وَمَا تُوعَدُونَ
ሲሳያችሁም የምትቀጠሩትም (ፍዳና ምንዳ) በሰማይ ነው።
فَوَرَبِّ السَّمَاءِ وَالْأَرْضِ إِنَّهُ لَحَقٌّ مِثْلَ مَا أَنَّكُمْ تَنْطِقُونَ
በሰማይና በምድር ጌታም እምላለሁ። እርሱ እናንተ እንደምትናገሩት ብጤ እርግጠኛ (እውነት) ነው።
هَلْ أَتَاكَ حَدِيثُ ضَيْفِ إِبْرَاهِيمَ الْمُكْرَمِينَ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የተከበሩት የኢብራሂም እንግዶች ወሬ መጥቶሃልን?
إِذْ دَخَلُوا عَلَيْهِ فَقَالُوا سَلَامًا ۖ قَالَ سَلَامٌ قَوْمٌ مُنْكَرُونَ
በእርሱም ላይ በገቡና «ሰላም» ባሉት ጊዜ ምን እንደሆነ አስታውስ። ሰላም ግና ያልታወቃችሁ ህዝቦች ናችሁ አላቸው።
فَرَاغَ إِلَىٰ أَهْلِهِ فَجَاءَ بِعِجْلٍ سَمِينٍ
ወደ ቤተሰቡም ተዘነበለና ወዲያውም የሰባ ወይፈን አመጣ።
فَقَرَّبَهُ إِلَيْهِمْ قَالَ أَلَا تَأْكُلُونَ
ከዚያ ወደ እነርሱ (አዘጋጅቶ) አቀረበውና «አትበሉም ወይ?» አላቸው።
فَأَوْجَسَ مِنْهُمْ خِيفَةً ۖ قَالُوا لَا تَخَفْ ۖ وَبَشَّرُوهُ بِغُلَامٍ عَلِيمٍ
ከእነርሱ መፍራትን በልቡ አሳደረ። «አትፍራ» አሉትም በአዋቂ ልጅም አበስሩት።
فَأَقْبَلَتِ امْرَأَتُهُ فِي صَرَّةٍ فَصَكَّتْ وَجْهَهَا وَقَالَتْ عَجُوزٌ عَقِيمٌ
ሚስቱም (በደስታ) እየጮኸች መጣች፤ ፊቷንም መታች «መካን አሮጊት (ነኝ)» አለችም።
قَالُوا كَذَٰلِكِ قَالَ رَبُّكِ ۖ إِنَّهُ هُوَ الْحَكِيمُ الْعَلِيمُ
እነርሱም «ጌታሽ 'እንዲሁ (ይሁን)' ብሏል። እነሆ እርሱ ጥበበኛና ሁሉን አዋቂ ነው» አሏት።
قَالَ فَمَا خَطْبُكُمْ أَيُّهَا الْمُرْسَلُونَ
«እናንተ መልዕክተኞች ሆይ! ታዲያ ነገራችሁ ምንድን ነው?» አላቸው።
قَالُوا إِنَّا أُرْسِلْنَا إِلَىٰ قَوْمٍ مُجْرِمِينَ
እነርሱም አሉ: «እኛ ወደ አመጸኞች ህዝቦች ተልከናል።
لِنُرْسِلَ عَلَيْهِمْ حِجَارَةً مِنْ طِينٍ
«በእነርሱ ላይ ከጭቃ የሆኑ ድንጋዮችን ልንለቅባቸው ተላክን።
مُسَوَّمَةً عِنْدَ رَبِّكَ لِلْمُسْرِفِينَ
«በጌታህ ዘንድ ለድንበር አላፊዎቹ (በየስማቸው) ምልክት የተደረገባት ስትሆን።» አሉ
فَأَخْرَجْنَا مَنْ كَانَ فِيهَا مِنَ الْمُؤْمِنِينَ
ከምዕመናንም በእርሷ (በከተማቸው) ውስጥ የነበሩትን አወጣን።
فَمَا وَجَدْنَا فِيهَا غَيْرَ بَيْتٍ مِنَ الْمُسْلِمِينَ
በውስጧም ከአንድ ቤት ቤተሰቦች በስተቀር ሙስሊሞችን አላገኘንም።
وَتَرَكْنَا فِيهَا آيَةً لِلَّذِينَ يَخَافُونَ الْعَذَابَ الْأَلِيمَ
በውስጧም ለእነዚያ አሳማሚውን ቅጣት ለሚፈሩት ምልክትን አስቀረን።
وَفِي مُوسَىٰ إِذْ أَرْسَلْنَاهُ إِلَىٰ فِرْعَوْنَ بِسُلْطَانٍ مُبِينٍ
በሙሳ ወሬ ውስጥም ወደ ፈርዖን በግልጽ ማስረጃ በላክነው ጊዜ (ምልክትን አደረግን)።
فَتَوَلَّىٰ بِرُكْنِهِ وَقَالَ سَاحِرٌ أَوْ مَجْنُونٌ
ከድጋፉ (ከሰራዊቱ) ጋርም (ከእምነት) ዞረ። «እርሱ ድግምተኛ ወይም እብድ ነው» አለ።
فَأَخَذْنَاهُ وَجُنُودَهُ فَنَبَذْنَاهُمْ فِي الْيَمِّ وَهُوَ مُلِيمٌ
እርሱንም ሰራዊቱንም ያዝናቸው እርሱ ተወቃሽ ሲሆን በባህር ውስጥ ጣልናቸውም።
وَفِي عَادٍ إِذْ أَرْسَلْنَا عَلَيْهِمُ الرِّيحَ الْعَقِيمَ
በዓድም በእነርሱ ላይ መካን (የሆነች) ንፋስን በላክን ጊዜ ምልክት አለ።
مَا تَذَرُ مِنْ شَيْءٍ أَتَتْ عَلَيْهِ إِلَّا جَعَلَتْهُ كَالرَّمِيمِ
በላዩ ላይ የመጣችበትን ማንኛዉንም ነገር እንደበሰበሰ አጥንት ያደረገችው ብትሆን እንጂ አትተወዉም።
وَفِي ثَمُودَ إِذْ قِيلَ لَهُمْ تَمَتَّعُوا حَتَّىٰ حِينٍ
በሰሙድም ለእነርሱ «እስከ ጊዜ (ሞታችሁ) ድረስ ተጠቀሙ።» በተባሉ ጊዜ (ምልክት አለ)።
فَعَتَوْا عَنْ أَمْرِ رَبِّهِمْ فَأَخَذَتْهُمُ الصَّاعِقَةُ وَهُمْ يَنْظُرُونَ
ከጌታቸው ትዕዛዝም ኮሩ። እነርሱም እያዩ (የመብረቅ) ጩኸት ያዘቻቸው።
فَمَا اسْتَطَاعُوا مِنْ قِيَامٍ وَمَا كَانُوا مُنْتَصِرِينَ
መቆምንም አልቻሉም። እርዳታ የሚደረግላቸውም አልነበሩም።
وَقَوْمَ نُوحٍ مِنْ قَبْلُ ۖ إِنَّهُمْ كَانُوا قَوْمًا فَاسِقِينَ
የኑህንም ህዝቦች ከዚህ በፊት (አጠፋን) እነርሱ አመጸኞች ህዝቦች ነበሩና።
وَالسَّمَاءَ بَنَيْنَاهَا بِأَيْدٍ وَإِنَّا لَمُوسِعُونَ
ሰማይንም በሀይል ገነባናት። እኛም በእርግጥ የምናስፋት ነን።
وَالْأَرْضَ فَرَشْنَاهَا فَنِعْمَ الْمَاهِدُونَ
ምድርንም ዘረጋናት ምን ያማርንም ዘርጊዎች ነን።
وَمِنْ كُلِّ شَيْءٍ خَلَقْنَا زَوْجَيْنِ لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ
ትገነዘቡም ዘንድ ከነገሩ ሁሉ ሁለት ተቃራኒ አይነትን ፈጠርን።
فَفِرُّوا إِلَى اللَّهِ ۖ إِنِّي لَكُمْ مِنْهُ نَذِيرٌ مُبِينٌ
ወደ አላህም ሽሹ እኔ ለእናንተ ከእርሱ ግልጽ አስጠንቃቂ ነኝ።
وَلَا تَجْعَلُوا مَعَ اللَّهِ إِلَٰهًا آخَرَ ۖ إِنِّي لَكُمْ مِنْهُ نَذِيرٌ مُبِينٌ
ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አታድርጉ። እኔ ለእናንተ ከእርሱ ግልጽ አስጠንቃቂ ነኝና።
كَذَٰلِكَ مَا أَتَى الَّذِينَ مِنْ قَبْلِهِمْ مِنْ رَسُولٍ إِلَّا قَالُوا سَاحِرٌ أَوْ مَجْنُونٌ
ልክ እንደዚሁ እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ከመልዕክተኛ ማንም አልመጣቸዉም። «እርሱ ድግምተኛ ወይም እብድ ነው» ያሉ ቢሆን እንጂ።
أَتَوَاصَوْا بِهِ ۚ بَلْ هُمْ قَوْمٌ طَاغُونَ
በእርሱ (በዚህ ቃል) አደራ ተባብለዋልን? ይልቁን እነርሱ ጥጋበኞች ህዝቦች ናቸው።
فَتَوَلَّ عَنْهُمْ فَمَا أَنْتَ بِمَلُومٍ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱም ዘወር በል (ተዋቸው)፤ አንተ ምንም ተወቃሽ አይደለህምና።
وَذَكِّرْ فَإِنَّ الذِّكْرَىٰ تَنْفَعُ الْمُؤْمِنِينَ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ገስጽም ግሳጼ አማኞችን ትጠቅማለችና።
وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنْسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ
ጋኔንና ሰዉን ሊገዙኝ እንጂ ለሌላ አልፈጠርኳቸዉም።
مَا أُرِيدُ مِنْهُمْ مِنْ رِزْقٍ وَمَا أُرِيدُ أَنْ يُطْعِمُونِ
ከእነርሱም ምንም ሲሳይን አልፈልግም። እንዲመግቡኝም አልፈልግም።
إِنَّ اللَّهَ هُوَ الرَّزَّاقُ ذُو الْقُوَّةِ الْمَتِينُ
አላህ እርሱ ብቻ ሲሳይን በጣም ሰጪና የብርቱ ሀይል ባለቤት ነውና።
فَإِنَّ لِلَّذِينَ ظَلَمُوا ذَنُوبًا مِثْلَ ذَنُوبِ أَصْحَابِهِمْ فَلَا يَسْتَعْجِلُونِ
ለእነዚያም ለበደሉት እንደ ጓደኞቻቸው ፋንታ ብጤ የቅጣት ፋንታ አለላቸው። ስለዚህ አያስቸኩሉኝ።
فَوَيْلٌ لِلَّذِينَ كَفَرُوا مِنْ يَوْمِهِمُ الَّذِي يُوعَدُونَ
ለእነዚያም ለካዱት ሰዎች ከዚያ ከሚቀጠሩት ቀናቸው ወዮላቸው።