سَبَّحَ لِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ
በሰማያትና በምድር ውስጥ ያሉ ሁሉ አላህን አጠሩ። እርሱም ኃያሉና ጥበበኛው ነው።
القرآن الكريمAfrica Academy
بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።
سَبَّحَ لِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ
በሰማያትና በምድር ውስጥ ያሉ ሁሉ አላህን አጠሩ። እርሱም ኃያሉና ጥበበኛው ነው።
لَهُ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ يُحْيِي وَيُمِيتُ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
የሰማያትና የምድር ንግስና የእርሱው ብቻ ነው። ሕይወትን የሚሰጥና ሕይወትን የሚነሳ እሱው ብቻ ነው። እርሱ ሁሉንም ነገር ቻይ ነውና።
هُوَ الْأَوَّلُ وَالْآخِرُ وَالظَّاهِرُ وَالْبَاطِنُ ۖ وَهُوَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ
እርሱ ( ከበፊቱ ምንም ያልቀደመው) የመጀመሪያ (ፊት ያለ)፣ (ከኋላው ምንም የሌለ) የመጨረሻ፣ ብቻዉን ቀሪ፤ (ከበላዩ ማንም የሌለ) ግልጽና (የበላይ)፣ ስውርም (ድብቅ) ነው። እርሱ (በምድርም ሆነ በሰማይ ያለን) ሁሉ ነገር አዋቂ ነው።
هُوَ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ ثُمَّ اسْتَوَىٰ عَلَى الْعَرْشِ ۚ يَعْلَمُ مَا يَلِجُ فِي الْأَرْضِ وَمَا يَخْرُجُ مِنْهَا وَمَا يَنْزِلُ مِنَ السَّمَاءِ وَمَا يَعْرُجُ فِيهَا ۖ وَهُوَ مَعَكُمْ أَيْنَ مَا كُنْتُمْ ۚ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ
እርሱ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት የፈጠረ ነው። ከዚያ በዐርሹ ላይ ከፍ አለ። ወደ ምድር የሚገባውንና ከእርሷ የሚወጣውን ያውቃል። ከሰማይ የሚወርደውንና ወደ እርሷ የሚወጣውን ያውቃል። እርሱ የትም ብትሆኑ (በእውቀቱ) ከናንተው ጋር ነው። አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና።
لَهُ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ وَإِلَى اللَّهِ تُرْجَعُ الْأُمُورُ
የሰማያትና የምድር ንግስና የእርሱ ብቻ ነው። ነገሮች ሁሉ ወደ አላህ ይመለሳሉ።
يُولِجُ اللَّيْلَ فِي النَّهَارِ وَيُولِجُ النَّهَارَ فِي اللَّيْلِ ۚ وَهُوَ عَلِيمٌ بِذَاتِ الصُّدُورِ
ሌሊትን በቀን ውስጥ ያስገባል። ቀንንም በሌሊት ውስጥ ያስገባል። እርሱም በልቦች ውስጥ የተደበቁትን ሁሉ አዋቂ ነው።
آمِنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ وَأَنْفِقُوا مِمَّا جَعَلَكُمْ مُسْتَخْلَفِينَ فِيهِ ۖ فَالَّذِينَ آمَنُوا مِنْكُمْ وَأَنْفَقُوا لَهُمْ أَجْرٌ كَبِيرٌ
(ሰዎች ሆይ!) በአላህና በመልዕክተኛው እመኑ። አላህ በእርሱ ላይ ተተካኪዎች ካደረጋችሁ ገንዘብ ዉስጥም ለግሱ። እነዚያ ከእናንተ መካከል በአላህ ያመኑትና የለገሱት ሁሉ ለእነርሱ ታላቅ ምንዳ አለላቸው።
وَمَا لَكُمْ لَا تُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ ۙ وَالرَّسُولُ يَدْعُوكُمْ لِتُؤْمِنُوا بِرَبِّكُمْ وَقَدْ أَخَذَ مِيثَاقَكُمْ إِنْ كُنْتُمْ مُؤْمِنِينَ
(ሰዎች ሆይ!) ጌታችሁም ቃልኪዳናችሁን የያዘባችሁ ሲሆን መልዕክተኛውም በጌታችሁ እንድታምኑ የሚጠራችሁ ሲሆን በአላህ የማታምኑበት ምን ምክኒያት አላችሁ? እናንተ በትክክል የምታምኑ ከሆናችሁ?
هُوَ الَّذِي يُنَزِّلُ عَلَىٰ عَبْدِهِ آيَاتٍ بَيِّنَاتٍ لِيُخْرِجَكُمْ مِنَ الظُّلُمَاتِ إِلَى النُّورِ ۚ وَإِنَّ اللَّهَ بِكُمْ لَرَءُوفٌ رَحِيمٌ
እርሱ ከጨለማዎች ወደ ብርሀን ሊያወጣችሁ ግልፆች የሆኑን አናቅጽ በባሪያው ላይ የሚያወርድ ነው። አላህ ለእናንተ በእርግጥ ሩህሩህ አዛኝ ነው።
وَمَا لَكُمْ أَلَّا تُنْفِقُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَلِلَّهِ مِيرَاثُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ لَا يَسْتَوِي مِنْكُمْ مَنْ أَنْفَقَ مِنْ قَبْلِ الْفَتْحِ وَقَاتَلَ ۚ أُولَٰئِكَ أَعْظَمُ دَرَجَةً مِنَ الَّذِينَ أَنْفَقُوا مِنْ بَعْدُ وَقَاتَلُوا ۚ وَكُلًّا وَعَدَ اللَّهُ الْحُسْنَىٰ ۚ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرٌ
የሰማያትና የምድር ውርስ ለአላህ ብቻ ሲሆን በአላህ መንገድ የማትለግሱበት ምን ምክንያት አላችሁ? ከናንተ መካከል ከመካ መከፈት በፊት የለገሰና የተጋደለ ሰው ከተከፈተ በኋላ ከለገሰና ከተጋደለ ሰው ጋር አይስተካከልም። ከእነዚያ በኋላ ከለገሱትና ከተጋደሉት እነዚህ በደረጃ በጣም የላቁ ናቸውና። ሁሉንም አላህ የመልካሚቱን ተስፋ ቃል ገብቶላቸዋል። አላህ በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው።
مَنْ ذَا الَّذِي يُقْرِضُ اللَّهَ قَرْضًا حَسَنًا فَيُضَاعِفَهُ لَهُ وَلَهُ أَجْرٌ كَرِيمٌ
ያ ለአላህ መልካም ብድርን የሚያበድርና ለእርሱ አላህ ምንዳውን የሚያነባብርለት ሰው ማን ነው? ለእርሱም መልካም ምንዳ አለው።
يَوْمَ تَرَى الْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ يَسْعَىٰ نُورُهُمْ بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَبِأَيْمَانِهِمْ بُشْرَاكُمُ الْيَوْمَ جَنَّاتٌ تَجْرِي مِنْ تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا ۚ ذَٰلِكَ هُوَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ
ወንድ ትክክለኛ አማኞችንና ሴት ትክክለኛ አማኞችን በስተፊቶቻቸው በቀኞቻቸዉም ብርሀናቸው የሚሮጥ ሲሆን በምታያቸው ቀን (ታላቅ ምንዳ አለላቸው።) "ዛሬ ብስራታችሁ በውስጦቻቸው ዘውታሪዎች ስትኾኑ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈስሱባቸው ገነቶች ናቸው" (ይባላሉ)። ይህ እርሱ ታላቅ እድል ነው።
يَوْمَ يَقُولُ الْمُنَافِقُونَ وَالْمُنَافِقَاتُ لِلَّذِينَ آمَنُوا انْظُرُونَا نَقْتَبِسْ مِنْ نُورِكُمْ قِيلَ ارْجِعُوا وَرَاءَكُمْ فَالْتَمِسُوا نُورًا فَضُرِبَ بَيْنَهُمْ بِسُورٍ لَهُ بَابٌ بَاطِنُهُ فِيهِ الرَّحْمَةُ وَظَاهِرُهُ مِنْ قِبَلِهِ الْعَذَابُ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የወንድ አስመሳዮችና የሴት አስመሳዮች ለእነዚያ በአላህ ላመኑት "ጠብቁን ከብርሀናችሁ እናበራለንና" የሚሉበትን ቀን አስታውስ። "ወደ ኋላችሁ ተመለሱ። ብርሀንንም እዚያው ፈልጉ" ይባላሉ። በመካከላቸዉም ለእርሱ ደጃፍ ባለው አጥር ይከለላል። ግቢው በውስጡ ገነት ያለበት ከውጪዉም በኩሉ ደግሞ የእሳት (ስቃይ) ያለበት የሆነ (ደጃፍ ባለው አጥር ይከለላል)።
يُنَادُونَهُمْ أَلَمْ نَكُنْ مَعَكُمْ ۖ قَالُوا بَلَىٰ وَلَٰكِنَّكُمْ فَتَنْتُمْ أَنْفُسَكُمْ وَتَرَبَّصْتُمْ وَارْتَبْتُمْ وَغَرَّتْكُمُ الْأَمَانِيُّ حَتَّىٰ جَاءَ أَمْرُ اللَّهِ وَغَرَّكُمْ بِاللَّهِ الْغَرُورُ
"ከናንተ ጋር አልነበርንምን?" በማለት ይጠሯቸዋል። "እውነት ነው እኛ ጋር ነበራችሁ። ግን እናንተ ነፍሶቻችሁን አጠፋችሁ። በነብዩ አደጋዎችን ተጠባበቃችሁ ተጠራጠራችሁም። የአላህ ትዕዛዝ እስከ መጣ ድረስ ከንቱ ምኞቶች አታለሏችሁ። አታላዩም ሰይጣን በአላህ መታገስ ሸነገላችሁ ይሏቸዋል።
فَالْيَوْمَ لَا يُؤْخَذُ مِنْكُمْ فِدْيَةٌ وَلَا مِنَ الَّذِينَ كَفَرُوا ۚ مَأْوَاكُمُ النَّارُ ۖ هِيَ مَوْلَاكُمْ ۖ وَبِئْسَ الْمَصِيرُ
በመሆኑም ዛሬ ከናንተም ሆነ በአላህ ከካዱት ሰዎች የገንዘብ ክፍያ (ቤዛ) አይወሰድም። መኖሪያችሁ የገሀነም እሳት ብቻ ናት። እርሷ ተገቢያችሁ ናትና። የገሀነም እሳት መመለሻነቷ ምን ትከፋም" (ይሏቸዋል)።
أَلَمْ يَأْنِ لِلَّذِينَ آمَنُوا أَنْ تَخْشَعَ قُلُوبُهُمْ لِذِكْرِ اللَّهِ وَمَا نَزَلَ مِنَ الْحَقِّ وَلَا يَكُونُوا كَالَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ مِنْ قَبْلُ فَطَالَ عَلَيْهِمُ الْأَمَدُ فَقَسَتْ قُلُوبُهُمْ ۖ وَكَثِيرٌ مِنْهُمْ فَاسِقُونَ
ለእነዚያ (በአላህ) ላመኑት ለአላህ ተግሳጽና ከቁርኣንም ለወረደው እውነታ ልቦቻቸው ሊፈሩ፤ እንደነዚያ በፊት መጽሐፍን እንደ ተሰጡትና በእነርሱ ላይ ጊዜ ስለ ረዘመባቸው ልቦቻቸውም እንደ ደረቁባቸው ህዝቦች የማይሆኑበት ጊዜ አልቀረበምን? ከእነርሱም ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው።
اعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ يُحْيِي الْأَرْضَ بَعْدَ مَوْتِهَا ۚ قَدْ بَيَّنَّا لَكُمُ الْآيَاتِ لَعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ
(ሰዎች ሆይ!) አላህ ምድርን ከሞተች በኋላ ህያው የሚያደርጋት መሆኑን እወቁ። ታውቁም ዘንድ አናቅጽን ለእናንተ በእርግጥ አብራራንላችሁ።
إِنَّ الْمُصَّدِّقِينَ وَالْمُصَّدِّقَاتِ وَأَقْرَضُوا اللَّهَ قَرْضًا حَسَنًا يُضَاعَفُ لَهُمْ وَلَهُمْ أَجْرٌ كَرِيمٌ
የመጸወቱ ወንዶችና የመጸወቱ ሴቶች ለአላህ መልካምን ብድር ያበደሩ ሁሉ ለእነርሱም ምንዳ ይደራረብላቸዋል። ለእነርሱም መልካም የተከበረ ምንዳ አለላቸው።
وَالَّذِينَ آمَنُوا بِاللَّهِ وَرُسُلِهِ أُولَٰئِكَ هُمُ الصِّدِّيقُونَ ۖ وَالشُّهَدَاءُ عِنْدَ رَبِّهِمْ لَهُمْ أَجْرُهُمْ وَنُورُهُمْ ۖ وَالَّذِينَ كَفَرُوا وَكَذَّبُوا بِآيَاتِنَا أُولَٰئِكَ أَصْحَابُ الْجَحِيمِ
እነዚያ በአላህና በመልዕክተኞቹ ያመኑ ሰዎች እነዚያ እነርሱ በጣም እውነተኞች በጌታቸዉም ዘንድ መስካሪዎች ናቸው። ለእነርሱ ምንዳቸውም ብርሀናቸዉም አለላቸው። እነዚያ (በአላህ) የካዱትና በአናቅጻችን ያስተባበሉ ሰዎች ደግሞ የእሳት ጓዶች ናቸው።
اعْلَمُوا أَنَّمَا الْحَيَاةُ الدُّنْيَا لَعِبٌ وَلَهْوٌ وَزِينَةٌ وَتَفَاخُرٌ بَيْنَكُمْ وَتَكَاثُرٌ فِي الْأَمْوَالِ وَالْأَوْلَادِ ۖ كَمَثَلِ غَيْثٍ أَعْجَبَ الْكُفَّارَ نَبَاتُهُ ثُمَّ يَهِيجُ فَتَرَاهُ مُصْفَرًّا ثُمَّ يَكُونُ حُطَامًا ۖ وَفِي الْآخِرَةِ عَذَابٌ شَدِيدٌ وَمَغْفِرَةٌ مِنَ اللَّهِ وَرِضْوَانٌ ۚ وَمَا الْحَيَاةُ الدُّنْيَا إِلَّا مَتَاعُ الْغُرُورِ
(ሰዎች ሆይ!) ቅርቢቱን ሕይወት ጨዋታና ዛዛታ፤ ማጌጫም፤ በመካከላችሁም መፎካከሪያ፤ በገንዘቦችና በልጆችም ብዛት መበላለጫ ብቻ መሆኗን እወቁ። እርሷ በቃዩ ገበሬዎችን ቡቃያው እንደሚያስደስት ዝናብና ከዚያም በቃዩ እንደሚደርቅና ገርጥቶ እንደሚታየው ከዚያም የተሰባበረ እንደሚሆን ብጤ ነው። በመጨረሻይቱም ዓለም ለአጥፊዎች ብርቱ ቅጣት፤ (ለትክክለኛ) አማኞች ከአላህ ምህረትና ውዴታ አለ። የቅርቢቱ ሕይወት እኮ የመታለያ ጥቅም እንጂ ሌላ አይደለችም።
سَابِقُوا إِلَىٰ مَغْفِرَةٍ مِنْ رَبِّكُمْ وَجَنَّةٍ عَرْضُهَا كَعَرْضِ السَّمَاءِ وَالْأَرْضِ أُعِدَّتْ لِلَّذِينَ آمَنُوا بِاللَّهِ وَرُسُلِهِ ۚ ذَٰلِكَ فَضْلُ اللَّهِ يُؤْتِيهِ مَنْ يَشَاءُ ۚ وَاللَّهُ ذُو الْفَضْلِ الْعَظِيمِ
(እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) በአላህና በመልዕክተኞች ላመኑት ወደ ተዘጋጀችውና የወርዷ ስፋት እንደ ሰማይና ምድር ወደ ሆነችም ገነትና ከጌታችሁ ወደ ሆነው ምህረት ተሸቀዳደሙ። ይህ የአላህ ችሮታ ነው። ለሚፈልገው ሰው ብቻ ይሰጠዋል። አላህ የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነውና።
مَا أَصَابَ مِنْ مُصِيبَةٍ فِي الْأَرْضِ وَلَا فِي أَنْفُسِكُمْ إِلَّا فِي كِتَابٍ مِنْ قَبْلِ أَنْ نَبْرَأَهَا ۚ إِنَّ ذَٰلِكَ عَلَى اللَّهِ يَسِيرٌ
በምድርም ሆነ በነፍሶቻችሁ መከራ ማንንም አታጋጥምም ሳንፈጥራት በፊት በመጽሐፍ የተመዘገበች ብትሆን እንጂ። ይህ በአላህ ላይ ቀላል ነው።
لِكَيْلَا تَأْسَوْا عَلَىٰ مَا فَاتَكُمْ وَلَا تَفْرَحُوا بِمَا آتَاكُمْ ۗ وَاللَّهُ لَا يُحِبُّ كُلَّ مُخْتَالٍ فَخُورٍ
(ይህን ማሳወቃችን) ባመለጣችሁ ጸጋ ላይ እንዳታዝኑና አላህ በሰጣችሁ ነገር (በትዕቢት) እንዳትደሰቱ ነው። አላህ ኩራተኛንና ጉረኛን ሁሉ አይወድምና።
الَّذِينَ يَبْخَلُونَ وَيَأْمُرُونَ النَّاسَ بِالْبُخْلِ ۗ وَمَنْ يَتَوَلَّ فَإِنَّ اللَّهَ هُوَ الْغَنِيُّ الْحَمِيدُ
እነርሱም እነዚያ የሚሰስቱና ሰዎችንም በስስት ላይ የሚያዙ ናቸው። ከእውነት የሚሸሽ (ሰው) ሁሉ (ጉዳቱ ለራሱ ብቻ ነው።) አላህ ተብቃቂና ምስጉን ነውና።
لَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلَنَا بِالْبَيِّنَاتِ وَأَنْزَلْنَا مَعَهُمُ الْكِتَابَ وَالْمِيزَانَ لِيَقُومَ النَّاسُ بِالْقِسْطِ ۖ وَأَنْزَلْنَا الْحَدِيدَ فِيهِ بَأْسٌ شَدِيدٌ وَمَنَافِعُ لِلنَّاسِ وَلِيَعْلَمَ اللَّهُ مَنْ يَنْصُرُهُ وَرُسُلَهُ بِالْغَيْبِ ۚ إِنَّ اللَّهَ قَوِيٌّ عَزِيزٌ
መልዕክተኞቻችንን በግልጽ ማስረጃዎች አጠናክረን በእርግጥ ላክን። ሰዎችም በትክክል ቀጥ እንዲሉ መጽሐፎችንና ሚዛንን ወደ እነርሱ አወረድን። ብረትንም ከውስጡ ብርቱ ኃይልና ለሰዎችም መጠቃቀሚያዎች ያሉበት ሲሆን አወረድን። አላህ ሃይማኖትንና መልዕክተኞችን በሩቁ ሆኖ የሚረዳውን (ሰው) ሊያውቅ (ሊገልጽ) አወረደው። አላህ ብርቱና አሸናፊ ነውና።
وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا نُوحًا وَإِبْرَاهِيمَ وَجَعَلْنَا فِي ذُرِّيَّتِهِمَا النُّبُوَّةَ وَالْكِتَابَ ۖ فَمِنْهُمْ مُهْتَدٍ ۖ وَكَثِيرٌ مِنْهُمْ فَاسِقُونَ
ኑህንና ኢብራሂምን በእርግጥ ላክን። በዘሮቻቸዉም ውስጥ ነብይነትንና መጽሐፍትን አደረግን። ከእነርሱም መካከል ቅን ሰው አለ። ከእነርሱም መካከል ብዙዎቹ ግን አመጸኞች ናቸው።
ثُمَّ قَفَّيْنَا عَلَىٰ آثَارِهِمْ بِرُسُلِنَا وَقَفَّيْنَا بِعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ وَآتَيْنَاهُ الْإِنْجِيلَ وَجَعَلْنَا فِي قُلُوبِ الَّذِينَ اتَّبَعُوهُ رَأْفَةً وَرَحْمَةً وَرَهْبَانِيَّةً ابْتَدَعُوهَا مَا كَتَبْنَاهَا عَلَيْهِمْ إِلَّا ابْتِغَاءَ رِضْوَانِ اللَّهِ فَمَا رَعَوْهَا حَقَّ رِعَايَتِهَا ۖ فَآتَيْنَا الَّذِينَ آمَنُوا مِنْهُمْ أَجْرَهُمْ ۖ وَكَثِيرٌ مِنْهُمْ فَاسِقُونَ
ከዚያም በእነርሱ ፈለጋቸው ላይ መልዕክተኞችን አከታተልን። የመርየም ልጅን ዒሳንም አስከተልን። ኢንጂልንም ሰጠነው። በእነዚያም በተከተሉት ሰዎች ልቦች ውስጥ መለዘብንና እዝነትን አደረግን፤ አዲስ የፈጠሯትንም ምንኩስና በእነርሱ ላይ አልደነገግንም። ግን የአላህን ውዴታ ለመፈለግ ሲሉ ከራሳቸው ፈጠሯት። ተገቢ አጠባበቅንም አልጠበቋትም። ከእነርሱም መካከል በአላህ ላመኑት ምንዳቸውን ሰጠናቸው። ከእነርሱ ብዙዎቹ ግን አመጸኞች ናቸው።
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَآمِنُوا بِرَسُولِهِ يُؤْتِكُمْ كِفْلَيْنِ مِنْ رَحْمَتِهِ وَيَجْعَلْ لَكُمْ نُورًا تَمْشُونَ بِهِ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ۚ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَحِيمٌ
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ። በመልክተኛዉም እመኑ። ከእዝነቱ ሁለትን ክፍሎች ይሰጣችኋልና። ለእናንተም የምትሄዱበትን ብርሃን ያደርግላችኋል። ለእናንተም ወንጀላችሁን ይምራል። አላህ መሀሪና አዛኝ ነው።
لِئَلَّا يَعْلَمَ أَهْلُ الْكِتَابِ أَلَّا يَقْدِرُونَ عَلَىٰ شَيْءٍ مِنْ فَضْلِ اللَّهِ ۙ وَأَنَّ الْفَضْلَ بِيَدِ اللَّهِ يُؤْتِيهِ مَنْ يَشَاءُ ۚ وَاللَّهُ ذُو الْفَضْلِ الْعَظِيمِ
(ይህም) የመጽሐፍ ሰዎች ከአላህ ችሮታ በምንም ላይ የማይችሉ መሆናቸውንና ችሮታዉም አላህ ለሚሻው ሰው ብቻ የሚሰጠው በእርሱ እጅ ብቻ መሆኑን እንዲያውቁ ነው። አላህ የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው።