The Argument · al-Mujadilah · سورة المجادلة · 22 ayahs

القرآن الكريمAfrica Academy

بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።

قَدْ سَمِعَ اللَّهُ قَوْلَ الَّتِي تُجَادِلُكَ فِي زَوْجِهَا وَتَشْتَكِي إِلَى اللَّهِ وَاللَّهُ يَسْمَعُ تَحَاوُرَكُمَا ۚ إِنَّ اللَّهَ سَمِيعٌ بَصِيرٌ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ የዚያችን በባሏ ጉዳይ ላይ የምትከራከርህንና ወደ አላህ ስሞታን የምታሰማውን ሴት ቃል ሰማ። አላህ በንግግር መመላለሳችሁን (መወያየታችሁን) ይሰማል። አላህ (ለሚባለው ሁሉ) ሰሚ (ለሚፈጸመው ሁሉ) ተመልካች ነውና።

الَّذِينَ يُظَاهِرُونَ مِنْكُمْ مِنْ نِسَائِهِمْ مَا هُنَّ أُمَّهَاتِهِمْ ۖ إِنْ أُمَّهَاتُهُمْ إِلَّا اللَّائِي وَلَدْنَهُمْ ۚ وَإِنَّهُمْ لَيَقُولُونَ مُنْكَرًا مِنَ الْقَوْلِ وَزُورًا ۚ وَإِنَّ اللَّهَ لَعَفُوٌّ غَفُورٌ

እነዚያ ከናንተ መካከል ሚስቶቻቸውን እንደእናቶቻቸው ጀርባዎች ይሁኑብን በማለት የሚምሉ ሰዎች እነርሱ እናቶቻቸው አይደሉም። ትክክለኛ እናቶቻቸው እነዚያ የወለዷቸው ሴቶች ብቻ ናቸው። እነርሱ በዚህ ቃል የተጠላ ንግግርንና ውሸትን በእርግጥ ይናገራሉ። አላህ (ለሚጸጸት ሰው ሁሉ) ይቅር ባይና መሀሪ ነው።

وَالَّذِينَ يُظَاهِرُونَ مِنْ نِسَائِهِمْ ثُمَّ يَعُودُونَ لِمَا قَالُوا فَتَحْرِيرُ رَقَبَةٍ مِنْ قَبْلِ أَنْ يَتَمَاسَّا ۚ ذَٰلِكُمْ تُوعَظُونَ بِهِ ۚ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرٌ

እነዚያ ሚስቶቻቸውን እንደእናቶቻቸው ጀርባዎች ይሁኑብን በማለት የሚምሉና ከዚያም ወደ ተናገሩት የሚመለሱ ሰዎች ሳይነካኩ በፊት ባሪያን (ጫንቃን) ነፃ ማውጣት ግዴታ አለባቸው። ይህ (የተጠቀሰው ህግ) በእርሱ የምትገሰጹበት ነው። አላህ በምትሰሩት ነገር ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው።

فَمَنْ لَمْ يَجِدْ فَصِيَامُ شَهْرَيْنِ مُتَتَابِعَيْنِ مِنْ قَبْلِ أَنْ يَتَمَاسَّا ۖ فَمَنْ لَمْ يَسْتَطِعْ فَإِطْعَامُ سِتِّينَ مِسْكِينًا ۚ ذَٰلِكَ لِتُؤْمِنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ ۚ وَتِلْكَ حُدُودُ اللَّهِ ۗ وَلِلْكَافِرِينَ عَذَابٌ أَلِيمٌ

ይህን ላላገኘም ሰው ከመነካካታቸው በፊት ሁለት ተከታታይ ወሮችን መፆም አለበት። ይህን ላልቻለም ሰው ስልሳ ድሆችን ማብላት አለበት። ይህ በአላህና በመልዕክተኛው እንድታምኑ ነው። እነኚህ ህግጋት የአላህ ህግጋት ናቸው። (እናም አትተላለፏቸው።) ለከሓዲያንም ሁሉ አሳማሚ ቅጣት አለባቸው።

إِنَّ الَّذِينَ يُحَادُّونَ اللَّهَ وَرَسُولَهُ كُبِتُوا كَمَا كُبِتَ الَّذِينَ مِنْ قَبْلِهِمْ ۚ وَقَدْ أَنْزَلْنَا آيَاتٍ بَيِّنَاتٍ ۚ وَلِلْكَافِرِينَ عَذَابٌ مُهِينٌ

ግልጽ ማስረጃዎችን ያወረድን ስንሆን እነዚያ አላህንና መልዕክተኛውን የሚቃረኑ ሰዎች እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩ ሰዎች እንደተዋረዱት ሁሉ ተዋርደዋል። ለከሓዲያን አዋራጅ ቅጣት አለባቸው።

يَوْمَ يَبْعَثُهُمُ اللَّهُ جَمِيعًا فَيُنَبِّئُهُمْ بِمَا عَمِلُوا ۚ أَحْصَاهُ اللَّهُ وَنَسُوهُ ۚ وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ شَهِيدٌ

አላህ ሁላቸውንም በአንድ አድርጎ (አንድም ሳይቀር በአንድ ዓይነት) በሚቀሰቅሳቸው ቀን (ይቀጣቸዋል)። ከዚያም በዚህ ዓለም የሰሩትን ነገር ሁሉ ይነግራቸዋል። እነርሱ የረሱት ሲሆን (መዝገባቸው ተመዝግቦ ያገኙታል) አላህ ግን አንድም ሳይቀር አውቆታል። አላህ ሁሉንም ነገር ተመልካች ነውና።

أَلَمْ تَرَ أَنَّ اللَّهَ يَعْلَمُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۖ مَا يَكُونُ مِنْ نَجْوَىٰ ثَلَاثَةٍ إِلَّا هُوَ رَابِعُهُمْ وَلَا خَمْسَةٍ إِلَّا هُوَ سَادِسُهُمْ وَلَا أَدْنَىٰ مِنْ ذَٰلِكَ وَلَا أَكْثَرَ إِلَّا هُوَ مَعَهُمْ أَيْنَ مَا كَانُوا ۖ ثُمَّ يُنَبِّئُهُمْ بِمَا عَمِلُوا يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۚ إِنَّ اللَّهَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅ መሆኑን አታውቅምን? (በእውነቱ ሁሉንም አካቧል።) የሶስት ሰዎች መንሾካሾክ አይከሰትም፤ አላህ አራተኛው ቢሆን እንጂ፤ የአምስትም ሰዎች መንሾካሾክ አይከሰትም እርሱ ስድስተኛ ቢሆን እንጂ፤ ከዚያ ያነሰም ይሁን የበዛ ሰው መንሾካሾክ አይከሰትም እርሱ ባሉበት ቦታ አብሯቸው ቢሆን እንጂ። ከዚያ በትንሳኤ ቀን የሰሩትን ሁሉ ይነግራቸዋል። አላህ ሁሉን ነገር አዋቂ ነው።

أَلَمْ تَرَ إِلَى الَّذِينَ نُهُوا عَنِ النَّجْوَىٰ ثُمَّ يَعُودُونَ لِمَا نُهُوا عَنْهُ وَيَتَنَاجَوْنَ بِالْإِثْمِ وَالْعُدْوَانِ وَمَعْصِيَتِ الرَّسُولِ وَإِذَا جَاءُوكَ حَيَّوْكَ بِمَا لَمْ يُحَيِّكَ بِهِ اللَّهُ وَيَقُولُونَ فِي أَنْفُسِهِمْ لَوْلَا يُعَذِّبُنَا اللَّهُ بِمَا نَقُولُ ۚ حَسْبُهُمْ جَهَنَّمُ يَصْلَوْنَهَا ۖ فَبِئْسَ الْمَصِيرُ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እነዚያ በመጥፎ ነገር ከመመሳጠር ወደ ተከለከሉት፤ ከዚያ ከእርሱ ወደ ተከለከሉት ነገር የሚመለሱትንና በኃጢአት፣ በጠላትነትና መልዕክተኛውን በመቃወም ወደ ሚመሳጠሩ አላየህምን? (ሰላም ሊሉ) ወደ አንተ በመጡ ጊዜ አላህ ሰላምታ ባልሰጠህ ቃል ሰላምታ ይሰጡሃል። በውስጣቸዉም «በምንለው ነገር አላህ ለምን አይቀጣንም?» ይላሉ። ገሀነም የሚገቡባት ሲሆኑ (ከአሁኑ ሞት ይልቅ) በቂያቸው ናት። ገሀነምም መመለሻነቷ ከፋች!

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا تَنَاجَيْتُمْ فَلَا تَتَنَاجَوْا بِالْإِثْمِ وَالْعُدْوَانِ وَمَعْصِيَتِ الرَّسُولِ وَتَنَاجَوْا بِالْبِرِّ وَالتَّقْوَىٰ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ الَّذِي إِلَيْهِ تُحْشَرُونَ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በተመሳጠራችሁ ጊዜ በኃጢአት ወሰንን በማለፍና መልዕክተኛውንም በመቃወም አትሾካሾኩ ግን በበጎ ስራና አላህን በመፍራት ተወያዩ። ያንንም ወደ እርሱ የምትሰበሰቡበትን አላህን ፍሩ።

إِنَّمَا النَّجْوَىٰ مِنَ الشَّيْطَانِ لِيَحْزُنَ الَّذِينَ آمَنُوا وَلَيْسَ بِضَارِّهِمْ شَيْئًا إِلَّا بِإِذْنِ اللَّهِ ۚ وَعَلَى اللَّهِ فَلْيَتَوَكَّلِ الْمُؤْمِنُونَ

በመጥፎ መመሳጠር ከሰይጣን ማስዋብና ማሳመር የሚመጣ ብቻ ነው። እነዚያ ያመኑ ሙስሊሞች ያዝኑ ዘንድ ይቀሰቅሰዋል። ከአላህ ፈቃድ ካልሆነ በስተቀር የሰይጣንም መመሳጠር በምንም ነገር አይጎዳቸዉም። እናም ትክክለኛ አማኞች በአላህ ብቻ ይመኩ።

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا قِيلَ لَكُمْ تَفَسَّحُوا فِي الْمَجَالِسِ فَافْسَحُوا يَفْسَحِ اللَّهُ لَكُمْ ۖ وَإِذَا قِيلَ انْشُزُوا فَانْشُزُوا يَرْفَعِ اللَّهُ الَّذِينَ آمَنُوا مِنْكُمْ وَالَّذِينَ أُوتُوا الْعِلْمَ دَرَجَاتٍ ۚ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرٌ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለእናንተ በመቀመጫዎች ስፍራ ተስፋፉ በተባላችሁ ጊዜ ስፍራን አስፉ። አላህ (በገነት) ያሰፋላችኃልና። ተነሱ በተባለም ጊዜ ተነሱ። አላህ ከናንተ መካከል እነዚያን በትክክል ያመኑትንና እነዚያንም እውቀትን የተሰጡትን በደረጃዎች (በዚች ዓለምም ሆነ በአኼራ) ከፍ ያደርጋል። አላህ በምትሰሩት ነገር ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነውና።

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا نَاجَيْتُمُ الرَّسُولَ فَقَدِّمُوا بَيْنَ يَدَيْ نَجْوَاكُمْ صَدَقَةً ۚ ذَٰلِكَ خَيْرٌ لَكُمْ وَأَطْهَرُ ۚ فَإِنْ لَمْ تَجِدُوا فَإِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَحِيمٌ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከመልዕክተኛው ጋር በተወያያችሁ ጊዜ ከመወያየታችሁ በፊት ምጽዋትን አስቀድሙ። (ሰደቃ ስጡ)። ይህ (ምጸዋትን አስቀድሞ መስጠት) ለእናንተ መልካምና አጥሪ ነው። ባታገኙም ምንንም (ሳትከፈሉ) ሳትሰጡ ብትወያዩ ችግር የለባችሁም። አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና።

أَأَشْفَقْتُمْ أَنْ تُقَدِّمُوا بَيْنَ يَدَيْ نَجْوَاكُمْ صَدَقَاتٍ ۚ فَإِذْ لَمْ تَفْعَلُوا وَتَابَ اللَّهُ عَلَيْكُمْ فَأَقِيمُوا الصَّلَاةَ وَآتُوا الزَّكَاةَ وَأَطِيعُوا اللَّهَ وَرَسُولَهُ ۚ وَاللَّهُ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ

ከውይይታችሁ በፊት ምጽዋቶችን በማስቀደም ድህነትን ፈራችሁን? የታዘዛችሁትን ባልሰራችሁ ጊዜ አላህ ከናንተ ጸጸትን የተቀበለ ሲሆን ሶላትን ስገዱ፤ ዘካንም ስጡ፤ አላህንና መልዕክተኛውንም ታዘዙ። አላህ በምትሰሩት ነገር ውስጠ አዋቂ ነውና።

أَلَمْ تَرَ إِلَى الَّذِينَ تَوَلَّوْا قَوْمًا غَضِبَ اللَّهُ عَلَيْهِمْ مَا هُمْ مِنْكُمْ وَلَا مِنْهُمْ وَيَحْلِفُونَ عَلَى الْكَذِبِ وَهُمْ يَعْلَمُونَ

ወደ እነዚያ አላህ በእነርሱ ላይ የተቆጣባቸውን ህዝቦች (አይሁዶች) ወደ ተወዳጁት አስመሳዮች አላየህምን? እነርሱ ከናንተ አይደሉም። ከእነርሱም አይደሉም። እያወቁ በውሸት ይምላሉ።

أَعَدَّ اللَّهُ لَهُمْ عَذَابًا شَدِيدًا ۖ إِنَّهُمْ سَاءَ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ

አላህ ለእነርሱ (በዚህ መወዳጃና የሀሰት መሀላ) ብርቱ ቅጣትን አዘጋጀ። እነርሱ ይሰሩት የነበሩት መጥፎ ስራ ምንኛ ከፋ!

اتَّخَذُوا أَيْمَانَهُمْ جُنَّةً فَصَدُّوا عَنْ سَبِيلِ اللَّهِ فَلَهُمْ عَذَابٌ مُهِينٌ

መሓሎቻቸውን ጋሻ አድርገው ያዙ። ሰዎችንም ከአላህ መንገድ አገዱ። ስለዚህ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አለባቸው።

لَنْ تُغْنِيَ عَنْهُمْ أَمْوَالُهُمْ وَلَا أَوْلَادُهُمْ مِنَ اللَّهِ شَيْئًا ۚ أُولَٰئِكَ أَصْحَابُ النَّارِ ۖ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ

ገንዘቦቻቸውና ልጆቻቸውም ከአላህ (ቅጣት) ምንም አያድኗቸዉም። እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው። እነርሱ በእርሷ ውስጥ ዘወታሪዎች ናቸው።

يَوْمَ يَبْعَثُهُمُ اللَّهُ جَمِيعًا فَيَحْلِفُونَ لَهُ كَمَا يَحْلِفُونَ لَكُمْ ۖ وَيَحْسَبُونَ أَنَّهُمْ عَلَىٰ شَيْءٍ ۚ أَلَا إِنَّهُمْ هُمُ الْكَاذِبُونَ

አላህ የተሰበሰቡ ሆነው በሚያስነሳቸውም ቂያማ ቀን ለእናንተ እንደ ሚምሉላችሁ በሚጠቅም ነገር ላይ መሆናቸውን የሚያስቡ ሆነው ለእርሱም (ለአላህም) ይምላሉ። (ሙስሊሞች ሆይ) ንቁ! ውሸታሞች እነርሱ ብቻ ናቸው።

اسْتَحْوَذَ عَلَيْهِمُ الشَّيْطَانُ فَأَنْسَاهُمْ ذِكْرَ اللَّهِ ۚ أُولَٰئِكَ حِزْبُ الشَّيْطَانِ ۚ أَلَا إِنَّ حِزْبَ الشَّيْطَانِ هُمُ الْخَاسِرُونَ

በእነርሱም ላይ ሰይጣን ተቆጣጠራቸው (ተመቻቸባቸው) እናም አላህን ማስታወስን አስረሳቸው (ትዕዛዛቱንም ተዉ)። እነዚያ የሰይጣን ቡድኖች ( ሰራዊቶች) ናቸው። ሙስሊሞች አስተዉሉ። የሰይጣን ቡድኖች ከሳሪዎች እነርሱ ብቻ ናቸው።

إِنَّ الَّذِينَ يُحَادُّونَ اللَّهَ وَرَسُولَهُ أُولَٰئِكَ فِي الْأَذَلِّينَ

እነዚያ አላህንና መልዕክተኛውን የሚቃረኑ እነዚያ በዱንያም ሆነ በአኺራ በጣም ከተዋረዱ ወገኖች ውስጥ ናቸው።

كَتَبَ اللَّهُ لَأَغْلِبَنَّ أَنَا وَرُسُلِي ۚ إِنَّ اللَّهَ قَوِيٌّ عَزِيزٌ

አላህ እኔ አሸንፋለሁ መልዕክተኞቼም እንዲሁ ያሸንፋሉ ሲል ድሮውኑ ጽፏል። አላህ ብርቱና አሸናፊ ነውና።

لَا تَجِدُ قَوْمًا يُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ يُوَادُّونَ مَنْ حَادَّ اللَّهَ وَرَسُولَهُ وَلَوْ كَانُوا آبَاءَهُمْ أَوْ أَبْنَاءَهُمْ أَوْ إِخْوَانَهُمْ أَوْ عَشِيرَتَهُمْ ۚ أُولَٰئِكَ كَتَبَ فِي قُلُوبِهِمُ الْإِيمَانَ وَأَيَّدَهُمْ بِرُوحٍ مِنْهُ ۖ وَيُدْخِلُهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِنْ تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا ۚ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا عَنْهُ ۚ أُولَٰئِكَ حِزْبُ اللَّهِ ۚ أَلَا إِنَّ حِزْبَ اللَّهِ هُمُ الْمُفْلِحُونَ

በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑትን ህዝቦች አላህንና መልዕክተኛውን የሚቃረኑ ሰዎች አባቶቻቸው ወይም ልጆቻቸው ወይም ወንድሞቻቸው ወይም ዘመዶቻቸው ቢሆኑም እንኳ የሚወዳጁ ሆነው አታገኛቸዉም። እነዚያ አላህ በልቦቻቸው ውስጥ እምነትን ጽፏል። ከእርሱም በሆነ መንፈስ ደግፏቸዋል። ከስሮቻቸዉም ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች በውስጣቸው ዘወታሪዎች ሲሆኑ ያስገባቸዋል። አላህ ከእነርሱ ወደደ። እነርሱም ከእርሱ ወደዱ። እነዚያ የአላህ ወገኖች ናቸው። ንቁ! የአላህ ወገኖች ምኞታቸውን የሚያገኙ እነርሱ ናቸው።