١ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا عَدُوِّي وَعَدُوَّكُمْ أَوْلِيَاءَ تُلْقُونَ إِلَيْهِمْ بِالْمَوَدَّةِ وَقَدْ كَفَرُوا بِمَا جَاءَكُمْ مِنَ الْحَقِّ يُخْرِجُونَ الرَّسُولَ وَإِيَّاكُمْ ۙ أَنْ تُؤْمِنُوا بِاللَّهِ رَبِّكُمْ إِنْ كُنْتُمْ خَرَجْتُمْ جِهَادًا فِي سَبِيلِي وَابْتِغَاءَ مَرْضَاتِي ۚ تُسِرُّونَ إِلَيْهِمْ بِالْمَوَدَّةِ وَأَنَا أَعْلَمُ بِمَا أَخْفَيْتُمْ وَمَا أَعْلَنْتُمْ ۚ وَمَنْ يَفْعَلْهُ مِنْكُمْ فَقَدْ ضَلَّ سَوَاءَ السَّبِيلِ
1 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ጠላቶቼንና ጠላቶቻችሁን ወዳጆች አድርጋችሁ አትያዙ። የመጣላችሁን ትክክለኛ ሃይማኖት የካዱ ሲሆኑ ውዴታን ለእነርሱ ታደርጋላችሁ። እነርሱ መልዕክተኛውንና እናንተን በጌታችሁ በአላህ ስላመናችሁ ብቻ ከሀገራችሁ አስወጧችሁ። በመንገዴ ለመታገልና ውዴታየን ለመፈለግ የወጣችሁ እንደሆናችሁ እነርሱን ወዳጆች አድርጋችሁ አትያዟቸው። እኔ የምትደብቁትንና የምትገልጹትን የማውቅ ስሆን ከእነርሱ ጋር ፍቅር ትመሳጠራላችሁ። ከናንተ መካከልም ይህንን የሚፈጽም ሰው ቀጥተኛውን መንገድ በእርግጥ ስቷል።
٢ إِنْ يَثْقَفُوكُمْ يَكُونُوا لَكُمْ أَعْدَاءً وَيَبْسُطُوا إِلَيْكُمْ أَيْدِيَهُمْ وَأَلْسِنَتَهُمْ بِالسُّوءِ وَوَدُّوا لَوْ تَكْفُرُونَ
2 ቢያሸንፏችሁ (ቢያገኟችሁ) ለእናንተ ጠላቶች ይሆናሉ። እጆቻቸውና ምላሶቻቸውንም ወደ እናንተ በክፉ ይዘረጋሉ። ብትክዱም ተመኙ።
٣ لَنْ تَنْفَعَكُمْ أَرْحَامُكُمْ وَلَا أَوْلَادُكُمْ ۚ يَوْمَ الْقِيَامَةِ يَفْصِلُ بَيْنَكُمْ ۚ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ
3 ዘመዶቻችሁም ሆኑ ልጆቻችሁ በትንሳኤ ቀን አይጠቅሟችሁም። (አላህ) በትንሳኤ ቀን በመካከላችሁ (ብይን በመስጠት) ይለያል። አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና።
٤ قَدْ كَانَتْ لَكُمْ أُسْوَةٌ حَسَنَةٌ فِي إِبْرَاهِيمَ وَالَّذِينَ مَعَهُ إِذْ قَالُوا لِقَوْمِهِمْ إِنَّا بُرَآءُ مِنْكُمْ وَمِمَّا تَعْبُدُونَ مِنْ دُونِ اللَّهِ كَفَرْنَا بِكُمْ وَبَدَا بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمُ الْعَدَاوَةُ وَالْبَغْضَاءُ أَبَدًا حَتَّىٰ تُؤْمِنُوا بِاللَّهِ وَحْدَهُ إِلَّا قَوْلَ إِبْرَاهِيمَ لِأَبِيهِ لَأَسْتَغْفِرَنَّ لَكَ وَمَا أَمْلِكُ لَكَ مِنَ اللَّهِ مِنْ شَيْءٍ ۖ رَبَّنَا عَلَيْكَ تَوَكَّلْنَا وَإِلَيْكَ أَنَبْنَا وَإِلَيْكَ الْمَصِيرُ
4 ኢብራሂምና እነዚያ ከእርሱ ጋር አብረው የነበሩት አማኞች ለእናንተ መልካም አርአያ ናቸው። ይኸዉም ለህዝቦቻቸው «እኛ ከናንተና ከዚያ ከአላህ ሌላ ከምትገዙት ጣዖታት ሁሉ ንጹሆች ነን። በእናንተም ካድን። በአላህ አንድነት እስከምታምኑ ድረስ በእኛና በእናንተ መካከል ጠብና ጥላቻ ዘወትር ተገለጸ።» ባሉ ጊዜ ኢብራሂም ለአባቱ፡- «ላንተ ከአላህ ቅጣት ምንም የማልጠቅምህ (የማላድንህ) ስሆን ላንተ በእርግጥ ምህረትን እለምንልሃለሁ።» ማለቱ ብቻ ሲቀር «ጌታችን ሆይ ባንተ ላይ ተመካን ወደ አንተም ተመለስን መመለሻም ወደ አንተ ብቻ ነው።» (ባለው ተከተሉ።)
٥ رَبَّنَا لَا تَجْعَلْنَا فِتْنَةً لِلَّذِينَ كَفَرُوا وَاغْفِرْ لَنَا رَبَّنَا ۖ إِنَّكَ أَنْتَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ
5 ጌታችን ሆይ! ለእነዚያ ለካዱት ሰዎች መሞከሪያ አታድርገን። ለእኛ ምህረት አድርግልን። ጌታችን ሆይ! አንተ አሸናፊና ጥበበኛው ነህ።
٦ لَقَدْ كَانَ لَكُمْ فِيهِمْ أُسْوَةٌ حَسَنَةٌ لِمَنْ كَانَ يَرْجُو اللَّهَ وَالْيَوْمَ الْآخِرَ ۚ وَمَنْ يَتَوَلَّ فَإِنَّ اللَّهَ هُوَ الْغَنِيُّ الْحَمِيدُ
6 ከናንተ መካከል አላህንና የመጨረሻውን ቀን ተስፋ ለሚያደርግ ሰው ሁሉ በእነርሱ ውስጥ ለእናንተ በእርግጥ መልካም አርአያ አላችሁ። ፊቱን የሚያዞር ሰው (ራሱን ብቻ ይጎዳል።) አላህ ብቸኛ፤ ተብቃቂና ምስጉን ነውና።
٧ عَسَى اللَّهُ أَنْ يَجْعَلَ بَيْنَكُمْ وَبَيْنَ الَّذِينَ عَادَيْتُمْ مِنْهُمْ مَوَدَّةً ۚ وَاللَّهُ قَدِيرٌ ۚ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَحِيمٌ
7 አላህ በእናንተና በእነዚያ ከእነርሱ ጋር በተጣላችሁት ሰዎች መካከል መፋቀርን ሊያደርግ ይከጀላል። አላህ ሁሉን ማድረግ ቻይ ነው። አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና።
٨ لَا يَنْهَاكُمُ اللَّهُ عَنِ الَّذِينَ لَمْ يُقَاتِلُوكُمْ فِي الدِّينِ وَلَمْ يُخْرِجُوكُمْ مِنْ دِيَارِكُمْ أَنْ تَبَرُّوهُمْ وَتُقْسِطُوا إِلَيْهِمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُقْسِطِينَ
8 ለእነዚያ በሃይማኖት ላልተዋጓችሁ ከአገሮቻችሁም ላላስወጧችሁ ከሓዲያን መልካም ብትውሉላቸውና ወደ እነርሱ ፍትህ ልትውሉላቸው አላህ አይከለክላችሁም። አላህ ትክክለኞችን (ፍትሃዊያን ትክክለኛ አማኞች) ይወዳልና።
٩ إِنَّمَا يَنْهَاكُمُ اللَّهُ عَنِ الَّذِينَ قَاتَلُوكُمْ فِي الدِّينِ وَأَخْرَجُوكُمْ مِنْ دِيَارِكُمْ وَظَاهَرُوا عَلَىٰ إِخْرَاجِكُمْ أَنْ تَوَلَّوْهُمْ ۚ وَمَنْ يَتَوَلَّهُمْ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الظَّالِمُونَ
9 አላህ የሚከለክላችሁማ ከእነዚያ በሃይማኖት ሰበብ ከተዋጓችሁና ከቤቶቻችሁም ያስወጧችሁ እናንተንም ከሀገር በማስወጣት ላይ የረዱትን እንዳትወዳጇቸው ብቻ ነው። እነርሱን ወዳጅ የሚያደርጓቸው ሰዎች ሁሉ እነዚያ እነርሱ (ራሳቸዉን) በዳዩች ናቸው።
١٠ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا جَاءَكُمُ الْمُؤْمِنَاتُ مُهَاجِرَاتٍ فَامْتَحِنُوهُنَّ ۖ اللَّهُ أَعْلَمُ بِإِيمَانِهِنَّ ۖ فَإِنْ عَلِمْتُمُوهُنَّ مُؤْمِنَاتٍ فَلَا تَرْجِعُوهُنَّ إِلَى الْكُفَّارِ ۖ لَا هُنَّ حِلٌّ لَهُمْ وَلَا هُمْ يَحِلُّونَ لَهُنَّ ۖ وَآتُوهُمْ مَا أَنْفَقُوا ۚ وَلَا جُنَاحَ عَلَيْكُمْ أَنْ تَنْكِحُوهُنَّ إِذَا آتَيْتُمُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ ۚ وَلَا تُمْسِكُوا بِعِصَمِ الْكَوَافِرِ وَاسْأَلُوا مَا أَنْفَقْتُمْ وَلْيَسْأَلُوا مَا أَنْفَقُوا ۚ ذَٰلِكُمْ حُكْمُ اللَّهِ ۖ يَحْكُمُ بَيْنَكُمْ ۚ وَاللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ
10 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሴት ምዕመናት ስደተኞች ሆነው ወደ እናንተ በሚመጡበት ጊዜ (ለሀይማኖት ሲሉ መሰደዳቸውን) ፈትኗቸው። አላህ በእምነታቸው ከናንተ ይልቅ አዋቂ ነው። ትክክለኛ አማኞችም መሆናቸውን ብታውቁ ወደ ከሓዲያን ባሎቻቸው አትመልሷቸው። እነርሱ ሙስሊም ሴቶች ለከሓዲ ወንዶች አይፈቀዱምና። ከሓዲያን ወንዶችም ለአማኝ ሴቶች የተፈቀዱ አይደሉምና። ያወጡትንም ገንዘብ መህሩን ስጧቸው። መህራቸውንም ከሰጣችኋቸው ብታገቧቸው ኃጢአት የለባችሁም ። የከሓዲያት ሚስቶቻችሁንም የጋብቻ ቃል ኪዳኖች አትያዙ። ሆኖም እናንተ ያወጣችሁትን ገንዘብ ጠይቁ ። እነርሱም ያወጡትን ይጠይቁ። ይህ የአላህ ፍርድ ነውና። በመካከላችሁም ይፈርዳል። አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው።
١١ وَإِنْ فَاتَكُمْ شَيْءٌ مِنْ أَزْوَاجِكُمْ إِلَى الْكُفَّارِ فَعَاقَبْتُمْ فَآتُوا الَّذِينَ ذَهَبَتْ أَزْوَاجُهُمْ مِثْلَ مَا أَنْفَقُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ الَّذِي أَنْتُمْ بِهِ مُؤْمِنُونَ
11 ከሚስቶቻችሁም አንዳቸው ወደ ከሓዲያን ቢያመልጧችሁ ቀጥሎም ብትዘምቱባቸው ለእነዚያ ሚስቶቻቸው ለሄዱባቸው ሰዎች ያወጡትን ወጪ ያክል ስጧቸው። ያንንም እናንተ በእርሱ ያመናችሁበትን አላህን ፍሩት።
١٢ يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ إِذَا جَاءَكَ الْمُؤْمِنَاتُ يُبَايِعْنَكَ عَلَىٰ أَنْ لَا يُشْرِكْنَ بِاللَّهِ شَيْئًا وَلَا يَسْرِقْنَ وَلَا يَزْنِينَ وَلَا يَقْتُلْنَ أَوْلَادَهُنَّ وَلَا يَأْتِينَ بِبُهْتَانٍ يَفْتَرِينَهُ بَيْنَ أَيْدِيهِنَّ وَأَرْجُلِهِنَّ وَلَا يَعْصِينَكَ فِي مَعْرُوفٍ ۙ فَبَايِعْهُنَّ وَاسْتَغْفِرْ لَهُنَّ اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَحِيمٌ
12 አንተ ነብይ ሆይ! ምዕመናቶቹ በአላህ ምንም ላያጋሩ፤ ላይሰርቁ፤ ላያመነዝሩ፤ ልጆቻቸውን ላይገድሉ፤ በእጆቻቸውና በእግሮቻቸው መካከል የሚቀጣጥፉትን ቅጥፈት (ከባሎቻቸው ያልሆነን ልጅ ማስጠጋትን) ላያመጡ (ላይሰሩ)፤ በበጎም ስራም ትዕዛዝን ላይጥሱ ቃል ኪዳን ሊገቡልህ ወደ አንተ በመጡ ጊዜ ቃል ኪዳን ተጋባቸው። ለእነርሱም አላህን ምህረት ለምንላቸው። አላህ በጣም መሀሪና እጅግ በጣም አዛኝ ነውና።
١٣ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَوَلَّوْا قَوْمًا غَضِبَ اللَّهُ عَلَيْهِمْ قَدْ يَئِسُوا مِنَ الْآخِرَةِ كَمَا يَئِسَ الْكُفَّارُ مِنْ أَصْحَابِ الْقُبُورِ
13 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህ በእነርሱ ላይ የተቆጣባቸውን ህዝቦች አትወዳጁ። ከሓዲያን ከመቃብር ሰዎች ተስፋ እንደቆረጡ ሁሉ በመጨረሻይቱም ዓለም (ምንዳ መኖር) በእርግጥ ተስፋ ቆርጠዋል።