Column · as-Saff · سورة الصف · 14 ayahs

القرآن الكريمAfrica Academy

بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።

سَبَّحَ لِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۖ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ

በሰማያትና በምድር ውስጥ ያሉ ሁሉ አላህን አጠሩ። እርሱ አሸናፊና ጥበበኛው ነው።

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لِمَ تَقُولُونَ مَا لَا تَفْعَلُونَ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የማትሰሩትን ነገር ለምን ታወራላችሁ?

كَبُرَ مَقْتًا عِنْدَ اللَّهِ أَنْ تَقُولُوا مَا لَا تَفْعَلُونَ

የማትሰሩትን ነገር መናገራችሁ በአላህ ዘንድ በመጠላት እጅግ ከበደ።

إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الَّذِينَ يُقَاتِلُونَ فِي سَبِيلِهِ صَفًّا كَأَنَّهُمْ بُنْيَانٌ مَرْصُوصٌ

አላህ እነዚያን ልክ እንደተለሰነ ግንብ የተሰለፉ ሆነው በሃይማኖቱ የሚፋለሙትን ይወዳል።

وَإِذْ قَالَ مُوسَىٰ لِقَوْمِهِ يَا قَوْمِ لِمَ تُؤْذُونَنِي وَقَدْ تَعْلَمُونَ أَنِّي رَسُولُ اللَّهِ إِلَيْكُمْ ۖ فَلَمَّا زَاغُوا أَزَاغَ اللَّهُ قُلُوبَهُمْ ۚ وَاللَّهُ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الْفَاسِقِينَ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሙሳም ለህዝቦቹ፡- «ህዝቦቼ ሆይ! እኔ ወደ እናንተ የአላህ መልዕክተኛ መሆኔን እያወቃችሁ ለምን ታሰቃዩኛላችሁ?» ባለ ጊዜ የሆነውን አስታውስ። ከእውነት በዘነበሉ ጊዜ አላህም ልቦቻቸውን አዘነበለባቸው። አላህ አመጸኞችን ህዝቦች አያቀናምና።

وَإِذْ قَالَ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ يَا بَنِي إِسْرَائِيلَ إِنِّي رَسُولُ اللَّهِ إِلَيْكُمْ مُصَدِّقًا لِمَا بَيْنَ يَدَيَّ مِنَ التَّوْرَاةِ وَمُبَشِّرًا بِرَسُولٍ يَأْتِي مِنْ بَعْدِي اسْمُهُ أَحْمَدُ ۖ فَلَمَّا جَاءَهُمْ بِالْبَيِّنَاتِ قَالُوا هَٰذَا سِحْرٌ مُبِينٌ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የመርየም ልጅ ዒሳም፡- «የኢስራኢል ልጆች ሆይ! እኔ ከእኔ በፊት ያለውን ተውራት የማረጋግጥና ከእኔ በኋላ በሚመጣው መልዕክተኛ ስሙ አህመድ በሆነውም የማበስር ስሆን ወደ እናንተ የተላኩ የአላህ መልዕክተኛ ነኝ» ባለ ጊዜ የሆነውን አስታውስ። ግልጽ ታዐምራቶችን ባመጣላቸው ጊዜ «ይህ ግልጽ ድግምት ነው» አሉ።

وَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّنِ افْتَرَىٰ عَلَى اللَّهِ الْكَذِبَ وَهُوَ يُدْعَىٰ إِلَى الْإِسْلَامِ ۚ وَاللَّهُ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الظَّالِمِينَ

እርሱ ወደ ኢስላም የሚጠራ ሲሆን በአላህ ላይ ውሸትን ከቀጣጠፈ ይበልጥ በደለኛ ማን ነው? አላህ በዳዮችን ህዝቦች አይመራም።

يُرِيدُونَ لِيُطْفِئُوا نُورَ اللَّهِ بِأَفْوَاهِهِمْ وَاللَّهُ مُتِمُّ نُورِهِ وَلَوْ كَرِهَ الْكَافِرُونَ

የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ሊያጠፉ ይሻሉ። ከሓዲያን ቢጠሉም እንኳ አላህ ብርሀኑን ሙሉ አድራጊ ነው።

هُوَ الَّذِي أَرْسَلَ رَسُولَهُ بِالْهُدَىٰ وَدِينِ الْحَقِّ لِيُظْهِرَهُ عَلَى الدِّينِ كُلِّهِ وَلَوْ كَرِهَ الْمُشْرِكُونَ

አላህ ያ አጋሪዎቹ ቢጠሉም መልዕክተኛውን በመምሪያ መጽሐፍና በእውነተኛ ሃይማኖት (በኢስላም) ከሃይማኖት ሁሉ በላይ ይፋ ሊያደርገው የላከ ነው።

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا هَلْ أَدُلُّكُمْ عَلَىٰ تِجَارَةٍ تُنْجِيكُمْ مِنْ عَذَابٍ أَلِيمٍ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከአሳማሚ ቅጣት የሚያድናችሁን ትርፋማ ንግድ ላመላክታችሁን?

تُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ وَتُجَاهِدُونَ فِي سَبِيلِ اللَّهِ بِأَمْوَالِكُمْ وَأَنْفُسِكُمْ ۚ ذَٰلِكُمْ خَيْرٌ لَكُمْ إِنْ كُنْتُمْ تَعْلَمُونَ

እርሱም በአላህና በመልዕክተኛው ታምናላችሁ። በአላህ መንገድ በገንዘቦቻችሁና በነፍሶቻችሁ ትታገላለችሁ። ይህ ተግባር የምታውቁ ከሆናችሁ ለእናንተ የተሻለ ነው።

يَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْ وَيُدْخِلْكُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِنْ تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ وَمَسَاكِنَ طَيِّبَةً فِي جَنَّاتِ عَدْنٍ ۚ ذَٰلِكَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ

ኃጢአቶቻችሁን ይምራል። ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸዉም ገነቶችን ያስገባችኋል። በመኖሪያ ገነቶችም በሚያምሩ ቤቶች ውስጥ ያስቀምጣችኋል። ይህ ታላቅ እድል ነው።

وَأُخْرَىٰ تُحِبُّونَهَا ۖ نَصْرٌ مِنَ اللَّهِ وَفَتْحٌ قَرِيبٌ ۗ وَبَشِّرِ الْمُؤْمِنِينَ

ሌላይቱንም የምትወዷትን ጸጋ ይሰጣችኋል። እርሷም ከአላህ የሆነ እርዳታና ቅርብ የሆነ አገር መክፈት ነው። አማኞችንም አብስር።

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا أَنْصَارَ اللَّهِ كَمَا قَالَ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ لِلْحَوَارِيِّينَ مَنْ أَنْصَارِي إِلَى اللَّهِ ۖ قَالَ الْحَوَارِيُّونَ نَحْنُ أَنْصَارُ اللَّهِ ۖ فَآمَنَتْ طَائِفَةٌ مِنْ بَنِي إِسْرَائِيلَ وَكَفَرَتْ طَائِفَةٌ ۖ فَأَيَّدْنَا الَّذِينَ آمَنُوا عَلَىٰ عَدُوِّهِمْ فَأَصْبَحُوا ظَاهِرِينَ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የመርየም ልጅ ዒሳ ለሐዋሪያቱ፡- «ወደ አላህ ረዳቴ ማን ነው» እንዳለና ሐዋርያቶቹም፡- «እኛ የአላህ ረዳቶች ነን» እንዳሉት ሁሉ እናንተም የአላህ ረዳቶች ሁኑ፤ ከኢስራኢል ልጆችም አንደኛዋ ቡድን አመነች። ሌላይቱም ቡድን ካደች። እነዚያን ያመኑትንም በጠላታቸው ላይ አበረታናቸው። ከዚያ እነርሱም አሸናፊዎች ሆኑ።