١ يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ إِذَا طَلَّقْتُمُ النِّسَاءَ فَطَلِّقُوهُنَّ لِعِدَّتِهِنَّ وَأَحْصُوا الْعِدَّةَ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ رَبَّكُمْ ۖ لَا تُخْرِجُوهُنَّ مِنْ بُيُوتِهِنَّ وَلَا يَخْرُجْنَ إِلَّا أَنْ يَأْتِينَ بِفَاحِشَةٍ مُبَيِّنَةٍ ۚ وَتِلْكَ حُدُودُ اللَّهِ ۚ وَمَنْ يَتَعَدَّ حُدُودَ اللَّهِ فَقَدْ ظَلَمَ نَفْسَهُ ۚ لَا تَدْرِي لَعَلَّ اللَّهَ يُحْدِثُ بَعْدَ ذَٰلِكَ أَمْرًا
1 አንተ ነብይ ሆይ! ሴቶችን መፍታት ባሰባችሁ ጊዜ፤ ለዒዳቸው ፍቷቸው፤ ዒዳንም ቁጠሩ፤ ጌታችሁን አላህን ፍሩ፤ ግልጽ የሆነችን ጠያፍ ካልሰሩ በስተቀር ከቤቶቻቸው አታውጧቸው። አይውጡም፤ ይህችም የአላህ ህግጋት ናት። የአላህንም ህግጋት የተላለፈ ሰው በእርግጥ ነፍሱን በደለ፤ ከዚህ (ፍች) በኋላ አላህ (የመመለስ) ነገርን ምናልባት ያመጣ እንደኾነ አታውቅም።
٢ فَإِذَا بَلَغْنَ أَجَلَهُنَّ فَأَمْسِكُوهُنَّ بِمَعْرُوفٍ أَوْ فَارِقُوهُنَّ بِمَعْرُوفٍ وَأَشْهِدُوا ذَوَيْ عَدْلٍ مِنْكُمْ وَأَقِيمُوا الشَّهَادَةَ لِلَّهِ ۚ ذَٰلِكُمْ يُوعَظُ بِهِ مَنْ كَانَ يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ ۚ وَمَنْ يَتَّقِ اللَّهَ يَجْعَلْ لَهُ مَخْرَجًا
2 ጊዜያቸውንም ለመዳረስ በተቃረቡ ጊዜ በመልካም ያዟቸው፤ ወይም በመልካም ተለያዩዋቸው፤ ከናንተም ውስጥ ሁለት የትክክለኛነት ባለቤቶችን አስመስክሩ፤ ምስክርነትንም ለአላህ አስተካክሉ፤ ይሃችሁ በአላህና በመጨረሻ ቀን የሚያምን የሆነ ሰው ሁሉ በእርሱ ይገሰጽበታል፤ አላህንም የሚፈራ ሰው ለእርሱ መውጫን ያደርግለታል።
٣ وَيَرْزُقْهُ مِنْ حَيْثُ لَا يَحْتَسِبُ ۚ وَمَنْ يَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ فَهُوَ حَسْبُهُ ۚ إِنَّ اللَّهَ بَالِغُ أَمْرِهِ ۚ قَدْ جَعَلَ اللَّهُ لِكُلِّ شَيْءٍ قَدْرًا
3 ከማያስበዉም በኩል ሲሳይን ይሰጠዋል፤ በአላህም ላይ የሚጠጋ ሰው እርሱ በቂው ነው። አላህ ፈቃዱን አድራሽ ነው። አላህ ለነገሩ ሁሉ የተወሰነ ጊዜን በእርግጥ አድርጓል።
٤ وَاللَّائِي يَئِسْنَ مِنَ الْمَحِيضِ مِنْ نِسَائِكُمْ إِنِ ارْتَبْتُمْ فَعِدَّتُهُنَّ ثَلَاثَةُ أَشْهُرٍ وَاللَّائِي لَمْ يَحِضْنَ ۚ وَأُولَاتُ الْأَحْمَالِ أَجَلُهُنَّ أَنْ يَضَعْنَ حَمْلَهُنَّ ۚ وَمَنْ يَتَّقِ اللَّهَ يَجْعَلْ لَهُ مِنْ أَمْرِهِ يُسْرًا
4 እነዚያም ከሴቶቻችሁ ከአደፍ (ከወር አበባ) ያቋረጡት በዒዳቸው ህግ ብትጠራጠሩ ዒዳቸው ሶስት ወር ነው። እነዚያም ገና አደፍን ያላዩ ሴቶችም ዒዳቸው እንደዚሁ ነው። የእርግዝና ባለቤቶችም ጊዜያቸው እርጉዛቸውን መውለድ ነው፤ አላህንም የሚፈራ ሰው ከነገሩ ሁሉ ለእርሱ መግራትን ያደርግለታል።
٥ ذَٰلِكَ أَمْرُ اللَّهِ أَنْزَلَهُ إِلَيْكُمْ ۚ وَمَنْ يَتَّقِ اللَّهَ يُكَفِّرْ عَنْهُ سَيِّئَاتِهِ وَيُعْظِمْ لَهُ أَجْرًا
5 ይህ የአላህ ፍርድ ነው። ወደ እናንተ አወረደው፤ አላህንም የሚፈራ ሰው ሁሉ ኃጢአቶችን ከርሱ ይሰርዝለታል። ምንዳንም ለእርሱ ያተልቅለታል።
٦ أَسْكِنُوهُنَّ مِنْ حَيْثُ سَكَنْتُمْ مِنْ وُجْدِكُمْ وَلَا تُضَارُّوهُنَّ لِتُضَيِّقُوا عَلَيْهِنَّ ۚ وَإِنْ كُنَّ أُولَاتِ حَمْلٍ فَأَنْفِقُوا عَلَيْهِنَّ حَتَّىٰ يَضَعْنَ حَمْلَهُنَّ ۚ فَإِنْ أَرْضَعْنَ لَكُمْ فَآتُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ ۖ وَأْتَمِرُوا بَيْنَكُمْ بِمَعْرُوفٍ ۖ وَإِنْ تَعَاسَرْتُمْ فَسَتُرْضِعُ لَهُ أُخْرَىٰ
6 ከችሎታችሁ ከተቀመጣችሁበት ስፍራ አስቀምጧቸው። በእነርሱም ላይ ልታጣብቡ አትጉዷቸው። የእርግዝና ባለቤቶችም ቢሆኑ እርጉዛቸውን እስኪወልዱ ድረስ በእነርሱ ላይ ቀልቡ። ለእናንተም ልጆቻችሁን ቢያጠቡላችሁ የልፋት ዋጋቸውን ስጧቸው። በመካከላችሁም በመልካም ነገር ተመካከሩ፤ ብትቸጋገሩም ለእርሱ ሌላ (ሴት) ታጠባለታለች።
٧ لِيُنْفِقْ ذُو سَعَةٍ مِنْ سَعَتِهِ ۖ وَمَنْ قُدِرَ عَلَيْهِ رِزْقُهُ فَلْيُنْفِقْ مِمَّا آتَاهُ اللَّهُ ۚ لَا يُكَلِّفُ اللَّهُ نَفْسًا إِلَّا مَا آتَاهَا ۚ سَيَجْعَلُ اللَّهُ بَعْدَ عُسْرٍ يُسْرًا
7 የችሎታ ባለቤት በችሎታው ልክ ይቀልብ፤ በእርሱም ላይ ሲሳዩ የተጠበበበት ሰው አላህ ከሰጠው ይስጥ። አላህ ነፍስን የሰጣትን ያህል እንጂ አያስገድድም። አላህ ከችግር በኋላ ምቾትን በእርግጥ ያደርጋል።
٨ وَكَأَيِّنْ مِنْ قَرْيَةٍ عَتَتْ عَنْ أَمْرِ رَبِّهَا وَرُسُلِهِ فَحَاسَبْنَاهَا حِسَابًا شَدِيدًا وَعَذَّبْنَاهَا عَذَابًا نُكْرًا
8 ከከተማም መካከል ከጌታቸው እና ከመልዕክተኞች ትዕዛዝ ያመጹ በመሆናቸው፤ ብርቱን ምርመራ የተሳሰብናቸዉና መጥፎንም ቅጣት የቀጣናቸው ብዙ ናቸው።
٩ فَذَاقَتْ وَبَالَ أَمْرِهَا وَكَانَ عَاقِبَةُ أَمْرِهَا خُسْرًا
9 የነገራቸዉንም ቅጣት ቀመሱ። የነገራቸዉም መጨረሻ ኪሳራ ሆነ።
١٠ أَعَدَّ اللَّهُ لَهُمْ عَذَابًا شَدِيدًا ۖ فَاتَّقُوا اللَّهَ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ الَّذِينَ آمَنُوا ۚ قَدْ أَنْزَلَ اللَّهُ إِلَيْكُمْ ذِكْرًا
10 አላህ ለእነርሱ ብርቱ ቅጣትን አዘጋጀ። እናንተም በአላህ ያመናችሁ የአእምሮ ባለ ቤቶች ሆይ! አላህን ፍሩ፤ አላህ ወደ እናንተ ግሳጼን በእርግጥ አወረደ፤
١١ رَسُولًا يَتْلُو عَلَيْكُمْ آيَاتِ اللَّهِ مُبَيِّنَاتٍ لِيُخْرِجَ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ مِنَ الظُّلُمَاتِ إِلَى النُّورِ ۚ وَمَنْ يُؤْمِنْ بِاللَّهِ وَيَعْمَلْ صَالِحًا يُدْخِلْهُ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِنْ تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا ۖ قَدْ أَحْسَنَ اللَّهُ لَهُ رِزْقًا
11 እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችን የሰሩትን ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ያወጣ ዘንድ የአላህን አንቀጾች ገላጮች ሲኾኑ በእናንተ ላይ የሚያነብላችሁን መልዕክተኛን ላከ። በአላህም የሚያምን መልካምን ስራ የሚሰራም ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ዘውታሪዎች ሲሆኑ ያገባዋል። አላህ ለርሱ ሲሳይን በእርግጥ አሳመረ።
١٢ اللَّهُ الَّذِي خَلَقَ سَبْعَ سَمَاوَاتٍ وَمِنَ الْأَرْضِ مِثْلَهُنَّ يَتَنَزَّلُ الْأَمْرُ بَيْنَهُنَّ لِتَعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ وَأَنَّ اللَّهَ قَدْ أَحَاطَ بِكُلِّ شَيْءٍ عِلْمًا
12 አላህ ያ ሰባትን ሰማያት የፈጠረ ነው። ከምድርም መሰላቸውን (ፈጥሮአል)፤ በመካከላቸዉም ትዕዛዙ ይወርዳል። አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ መሆኑን አላህም በነገሩ ሁሉ በእውቀት ያካበበ መሆኑን ታውቁ ዘንድ (ይህንን አሳወቃችሁ)።