Prohibition · at-Tahrim · سورة التحريم · 12 ayahs

القرآن الكريمAfrica Academy

بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።

يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ لِمَ تُحَرِّمُ مَا أَحَلَّ اللَّهُ لَكَ ۖ تَبْتَغِي مَرْضَاتَ أَزْوَاجِكَ ۚ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَحِيمٌ

አንተ ነብይ ሆይ! አላህ ላንተ የፈቀደልህን ነገር ሚስቶችህን ማስወደድን የምትፈልግ ስትሆን (ባንተ ላይ) ለምን እርም ታደርጋለህ? አላህ እጅግ መሀሪና አዛኝ ነው።

قَدْ فَرَضَ اللَّهُ لَكُمْ تَحِلَّةَ أَيْمَانِكُمْ ۚ وَاللَّهُ مَوْلَاكُمْ ۖ وَهُوَ الْعَلِيمُ الْحَكِيمُ

አላህ ለእናንተ የመሐሎቻችሁን መፍቻ ደነገገላችሁ፤ አላህ ረዳታችሁ ነው። እርሱም ሁሉን አዋቂና እጅግ ጥበበኛ ነው።

وَإِذْ أَسَرَّ النَّبِيُّ إِلَىٰ بَعْضِ أَزْوَاجِهِ حَدِيثًا فَلَمَّا نَبَّأَتْ بِهِ وَأَظْهَرَهُ اللَّهُ عَلَيْهِ عَرَّفَ بَعْضَهُ وَأَعْرَضَ عَنْ بَعْضٍ ۖ فَلَمَّا نَبَّأَهَا بِهِ قَالَتْ مَنْ أَنْبَأَكَ هَٰذَا ۖ قَالَ نَبَّأَنِيَ الْعَلِيمُ الْخَبِيرُ

ነብዩ ከሚስቶቹ ወደ አንዷ ወሬን በመሰጠረ ጊዜ (አስታውስ)። እርሱንም በነገረችና አላህ እርሱን ማውራቷን ባሳወቀው ጊዜ ከፊሉን አሳወቀ፤ ከፊሉንም ተወ፤ በእርሱም ባወራት ጊዜ «ይህን ማን ነገረህ?» አለች፤ «ሁሉን አዋቂው እና ውስጠ አዋቂው ነገረኝ» አላት።

إِنْ تَتُوبَا إِلَى اللَّهِ فَقَدْ صَغَتْ قُلُوبُكُمَا ۖ وَإِنْ تَظَاهَرَا عَلَيْهِ فَإِنَّ اللَّهَ هُوَ مَوْلَاهُ وَجِبْرِيلُ وَصَالِحُ الْمُؤْمِنِينَ ۖ وَالْمَلَائِكَةُ بَعْدَ ذَٰلِكَ ظَهِيرٌ

(ሁለታችሁም) ወደ አላህ ብትመለሱ ልቦቻችሁ በእርግጥ ተዘንብለዋልና (ትስማማላችሁ)። በእርሱ (ጥቃት) ላይ ብትረዳዱ ግን ረዳቱ አላህ ነው። ጂብሪልም ከምእምናንም መልካሙ ከዚህም በኋላ መላእክቱ ረዳቶቹ ናቸው።

عَسَىٰ رَبُّهُ إِنْ طَلَّقَكُنَّ أَنْ يُبْدِلَهُ أَزْوَاجًا خَيْرًا مِنْكُنَّ مُسْلِمَاتٍ مُؤْمِنَاتٍ قَانِتَاتٍ تَائِبَاتٍ عَابِدَاتٍ سَائِحَاتٍ ثَيِّبَاتٍ وَأَبْكَارًا

ሁላችሁንም ቢፈታችሁ ከናንተ የበለጡ ሚስቶች ሙስሊሞች፤ ትክክለኛ አማኞች፤ ታዛዦች፤ ተጸፃቾች፤ ለአላህ ተገዢዎች፤ ጿሚዎች፤ ፈቶችም ደናግልም የሆኑትን ጌታው ሊለውጥለት ይከጀላል።

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا قُوا أَنْفُسَكُمْ وَأَهْلِيكُمْ نَارًا وَقُودُهَا النَّاسُ وَالْحِجَارَةُ عَلَيْهَا مَلَائِكَةٌ غِلَاظٌ شِدَادٌ لَا يَعْصُونَ اللَّهَ مَا أَمَرَهُمْ وَيَفْعَلُونَ مَا يُؤْمَرُونَ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! መቀጣጠያዋ ሰዎችና ድንጋዮች ከሆነች እሳት ነፍሶቻችሁንም ቤተሰቦቻችሁንም ጠብቁ፤ በእርሷ ላይ ጨካኝና ኃይለኛ የሆኑ መላዕክት አሉ። አላህን ያዘዛቸውን ነገር በመጣስ አያምጹም፤ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሰራሉ።

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ كَفَرُوا لَا تَعْتَذِرُوا الْيَوْمَ ۖ إِنَّمَا تُجْزَوْنَ مَا كُنْتُمْ تَعْمَلُونَ

እናንተ በአላህ የካዳችሁ ሰዎች ሆይ! ዛሬ አታመካኙ፤ የምትመነዱት ያንን ትሰሩት የነበራችሁትን ብቻ ነው (ይባላሉ)።

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا تُوبُوا إِلَى اللَّهِ تَوْبَةً نَصُوحًا عَسَىٰ رَبُّكُمْ أَنْ يُكَفِّرَ عَنْكُمْ سَيِّئَاتِكُمْ وَيُدْخِلَكُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِنْ تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ يَوْمَ لَا يُخْزِي اللَّهُ النَّبِيَّ وَالَّذِينَ آمَنُوا مَعَهُ ۖ نُورُهُمْ يَسْعَىٰ بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَبِأَيْمَانِهِمْ يَقُولُونَ رَبَّنَا أَتْمِمْ لَنَا نُورَنَا وَاغْفِرْ لَنَا ۖ إِنَّكَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህ ነብዩን እነዚያንም ከእርሱ ጋር ያመኑትን በማያሳፍርበት፤ ብርሃናቸው በፊቶቻቸውና በቀኞቻቸው የሚሮጥ ሲሆን፡- «ጌታችን ሆይ! ብርሃናችንን ሙላልን፤ ለእኛ ምህረትንም አድርግልን፤ አንተ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነህና» በሚሉበት ቀን ጌታችሁ ከናንተ ኃጢአቶቻችሁን ሊሰርዝላችሁ፤ ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶችም ሊያስገባችሁ ይከጅላልና ንጹህ የሆነችን ጸጸት በመጸጸት ወደ አላህ ተመለሱ።

يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ جَاهِدِ الْكُفَّارَ وَالْمُنَافِقِينَ وَاغْلُظْ عَلَيْهِمْ ۚ وَمَأْوَاهُمْ جَهَنَّمُ ۖ وَبِئْسَ الْمَصِيرُ

አንተ ነብይ ሆይ! ከሓዲያን እና አስመሳዮችን ታገል፤ በእነርሱም ላይ በርታ፤ መኖሪያቸዉም ገሀነም ናት። ምን ትከፋም መመለሻ!

ضَرَبَ اللَّهُ مَثَلًا لِلَّذِينَ كَفَرُوا امْرَأَتَ نُوحٍ وَامْرَأَتَ لُوطٍ ۖ كَانَتَا تَحْتَ عَبْدَيْنِ مِنْ عِبَادِنَا صَالِحَيْنِ فَخَانَتَاهُمَا فَلَمْ يُغْنِيَا عَنْهُمَا مِنَ اللَّهِ شَيْئًا وَقِيلَ ادْخُلَا النَّارَ مَعَ الدَّاخِلِينَ

አላህ ለእነዚያ ለካዱት ሰዎች የኑህን ሚስት እና የሉጥን ሚስት ምሳሌ አደረገ፤ ባሮቻችን ከሆኑ ሁለት መልካም ባሪያዎች ስር ነበሩ ከዷቸዉም፤ ኑሕም ሉጥም ከሚስቶቻቸው ምንም የአላህን ቅጣት አልገፈተሩላቸዉም፤ «ከገቢዎችም ጋር እሳትን ግቡ» ተባሉ።

وَضَرَبَ اللَّهُ مَثَلًا لِلَّذِينَ آمَنُوا امْرَأَتَ فِرْعَوْنَ إِذْ قَالَتْ رَبِّ ابْنِ لِي عِنْدَكَ بَيْتًا فِي الْجَنَّةِ وَنَجِّنِي مِنْ فِرْعَوْنَ وَعَمَلِهِ وَنَجِّنِي مِنَ الْقَوْمِ الظَّالِمِينَ

ለእነዚያ ለአመኑትም አላህ የፈርዖንን ሚስት ምሳሌ አደረገ። «ጌታየ ሆይ! አንተ ዘንድ በገነት ውስጥ ለእኔ ቤት ገንባልኝ፤ ከፈርዖንና ከስራዉም አድነኝ፤ ከበደለኞች ህዝቦችም አድነኝ» ባለች ጊዜ።

وَمَرْيَمَ ابْنَتَ عِمْرَانَ الَّتِي أَحْصَنَتْ فَرْجَهَا فَنَفَخْنَا فِيهِ مِنْ رُوحِنَا وَصَدَّقَتْ بِكَلِمَاتِ رَبِّهَا وَكُتُبِهِ وَكَانَتْ مِنَ الْقَانِتِينَ

የዒምራን ልጅ መርየምንም ያችን ብልቷን የጠበቀችውን ምሳሌ አደረገ። በእርሷም ውስጥ ከመንፈሳችን ነፋን። በጌታዋ ቃላትና በመጽሐፍቱም አረጋገጠች፤ ከታዛዦችም ነበረች።