Ways of Ascent · al-Ma'arij · سورة المعارج · 44 ayahs

القرآن الكريمAfrica Academy

بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።

سَأَلَ سَائِلٌ بِعَذَابٍ وَاقِعٍ

ወዳቂ (ተከሳቺ) የሆነውን ቅጣት ጠያቂ ጠየቀ።

لِلْكَافِرِينَ لَيْسَ لَهُ دَافِعٌ

ከሓዲያን ላይ (የሚወርድ ነው)፤ ለእርሱ መላሽ የለዉም።

مِنَ اللَّهِ ذِي الْمَعَارِجِ

የ(ሰማያት) መሰላሎች ባለቤት ከሆነው አላህ (መላሽ የለዉም)።

تَعْرُجُ الْمَلَائِكَةُ وَالرُّوحُ إِلَيْهِ فِي يَوْمٍ كَانَ مِقْدَارُهُ خَمْسِينَ أَلْفَ سَنَةٍ

መላዕክትና መንፈሱም (ጂብሪል) ልኩ ሀምሳ ሺህ ዓመት በሆነ ቀን ውስጥ ወደ እርሱ ይወጣሉ።

فَاصْبِرْ صَبْرًا جَمِيلًا

መልካምን ትዕግስት ታገስ።

إِنَّهُمْ يَرَوْنَهُ بَعِيدًا

እነርሱ ያንን ቀን ሩቅ አድርገው ያዩታል።

وَنَرَاهُ قَرِيبًا

እኛም ቅርብ ሆኖ እናየዋለን።

يَوْمَ تَكُونُ السَّمَاءُ كَالْمُهْلِ

ሰማይ እንደ ዘይት አተላ በምትሆንበት ቀን፤

وَتَكُونُ الْجِبَالُ كَالْعِهْنِ

ጋራዎችም (በተለያዩ ቀለማት) እንደ ተነከረ (የተበተነ) ሱፍ በሚሆኑበት ቀን፤

وَلَا يَسْأَلُ حَمِيمٌ حَمِيمًا

ዘመድም ዘመድን በማይጠይቅበት ቀን (መላሽ የለዉም)።

يُبَصَّرُونَهُمْ ۚ يَوَدُّ الْمُجْرِمُ لَوْ يَفْتَدِي مِنْ عَذَابِ يَوْمِئِذٍ بِبَنِيهِ

(ዘመዶቻቸውን) ያዩዋቸዋል፤ አመጸኛው ከዚያ ቀን ስቃይ (ነፍሱን) በልጆቹ ቤዛ ሊያደርግ ይመኛል።

وَصَاحِبَتِهِ وَأَخِيهِ

በሚስቱም በወንድሙም፤

وَفَصِيلَتِهِ الَّتِي تُؤْوِيهِ

በዚያች በምታስጠጋው ጎሳውም፤

وَمَنْ فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا ثُمَّ يُنْجِيهِ

በምድርም ላይ ባለው ሁሉ (ሊበዥ) ከዚያ ሊያድነው (ይመኛል)።

كَلَّا ۖ إِنَّهَا لَظَىٰ

ይከልከል፤ እርሷ (እሳቲቱ) ነዲድ እሳት ናት።

نَزَّاعَةً لِلشَّوَىٰ

የራስን ቅል ቆዳ የምትሞሽልቅ ስትሆን፤

تَدْعُو مَنْ أَدْبَرَ وَتَوَلَّىٰ

(ከእምነት) የዞረንና የሸሸን ሰው (ወደ እርሷ) ትጠራለች።

وَجَمَعَ فَأَوْعَىٰ

ገንዘብን የሰበሰበንና (ዘካውን ሳይሰጥ) ያከማቸንም (ትጠራለች)።

إِنَّ الْإِنْسَانَ خُلِقَ هَلُوعًا

ሰው ቅጠ ቢስ ሆኖ ተፈጠረ።

إِذَا مَسَّهُ الشَّرُّ جَزُوعًا

ክፉ ነገር ባገኘው ጊዜ ብስጭተኛ፤

وَإِذَا مَسَّهُ الْخَيْرُ مَنُوعًا

መልካምም ነገር (ድሎት) ባገኘው ጊዜ ከልካይ ሆኖ ተፈጠረ።

إِلَّا الْمُصَلِّينَ

ሰጋጆች ብቻ ሲቀሩ።

الَّذِينَ هُمْ عَلَىٰ صَلَاتِهِمْ دَائِمُونَ

እነዚያ እነርሱ በሶላታቸው ላይ ዘወታሪዎች የሆኑት።

وَالَّذِينَ فِي أَمْوَالِهِمْ حَقٌّ مَعْلُومٌ

እነዚያም በገንዘቦቻቸው ላይ የታወቀ መብት ያለባቸው የሆኑት፤

لِلسَّائِلِ وَالْمَحْرُومِ

ለለማኝ እና ከልመና ለሚቆጠብም መብት (ያለባቸው የሆኑ)፤

وَالَّذِينَ يُصَدِّقُونَ بِيَوْمِ الدِّينِ

እነዚያም በፍርዱ ቀን እውነት የሚሉት።

وَالَّذِينَ هُمْ مِنْ عَذَابِ رَبِّهِمْ مُشْفِقُونَ

እነዚያም እነርሱ ከጌታቸው ቅጣት ፈሪዎች የሆኑት።

إِنَّ عَذَابَ رَبِّهِمْ غَيْرُ مَأْمُونٍ

የጌታቸው ቅጣት የማያስተማምን ነውና።

وَالَّذِينَ هُمْ لِفُرُوجِهِمْ حَافِظُونَ

እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የሆኑት፤

إِلَّا عَلَىٰ أَزْوَاجِهِمْ أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُهُمْ فَإِنَّهُمْ غَيْرُ مَلُومِينَ

በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዙዋቸው ባሮች ላይ ሲቀር። እነርሱ በነዚህ የማይወቀሱ ናቸውና።

فَمَنِ ابْتَغَىٰ وَرَاءَ ذَٰلِكَ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الْعَادُونَ

ከዚያ ወዲያ የፈለገ እነዚያ እነርሱ ድንበር አላፊዎች ናቸው።

وَالَّذِينَ هُمْ لِأَمَانَاتِهِمْ وَعَهْدِهِمْ رَاعُونَ

እነዚያም እነርሱ አደራዎቻቸውና ቃል ኪዳናቸውን ጠባቂዎች የሆኑት።

وَالَّذِينَ هُمْ بِشَهَادَاتِهِمْ قَائِمُونَ

እነዚያም እነርሱ በምስክርነቶቻቸው ላይ ቀጥ ያሉት።

وَالَّذِينَ هُمْ عَلَىٰ صَلَاتِهِمْ يُحَافِظُونَ

እነዚያም እነርሱ በሶላቶቻቸው ላይ የሚጠባበቁት።

أُولَٰئِكَ فِي جَنَّاتٍ مُكْرَمُونَ

እነዚያ (ከዚህ በላይ የተወሱት ሁሉ) በገነቶች ውስጥ የሚከበሩ ናቸው።

فَمَالِ الَّذِينَ كَفَرُوا قِبَلَكَ مُهْطِعِينَ

እነዚያ (በአላህ) የካዱት ወደ አንተ በኩል አንገቶቻቸውን መዘው የሚያተኩሩት ምን አላቸው?

عَنِ الْيَمِينِ وَعَنِ الشِّمَالِ عِزِينَ

ከቀኝና ከግራ ክፍልፍል ቡድኖች ሲሆኑ፤

أَيَطْمَعُ كُلُّ امْرِئٍ مِنْهُمْ أَنْ يُدْخَلَ جَنَّةَ نَعِيمٍ

ከእነርሱ እያንዳንዱ ሰው የጸጋይቱን ገነት መግባትን ይከጅላልን?

كَلَّا ۖ إِنَّا خَلَقْنَاهُمْ مِمَّا يَعْلَمُونَ

ይከልከል፤ በፍጹም እኛ ከሚያውቁት ነገር (ከፍትወት ጠብታ) ፈጠርናቸው።

فَلَا أُقْسِمُ بِرَبِّ الْمَشَارِقِ وَالْمَغَارِبِ إِنَّا لَقَادِرُونَ

(እናም ጉዳዩ ከሓዲያን እንደሚሉት አይደለም)። በምስራቆችና በምዕራቦች ጌታ እምላለሁ፤ እኛ በእርግጥ ቻዮች ነን።

عَلَىٰ أَنْ نُبَدِّلَ خَيْرًا مِنْهُمْ وَمَا نَحْنُ بِمَسْبُوقِينَ

ከእነርሱ የተሻለን በመለወጥ ላይ እኛም ተሸናፊዎች አይደለንም።

فَذَرْهُمْ يَخُوضُوا وَيَلْعَبُوا حَتَّىٰ يُلَاقُوا يَوْمَهُمُ الَّذِي يُوعَدُونَ

ያንንም የሚስፈራሩበትን ቀናቸውን እስከሚያገኙ ድረስ ተዋቸው፤ በአሉባልታዎችም ዉስጥ ይዋኙ፤ ይጫወቱም።

يَوْمَ يَخْرُجُونَ مِنَ الْأَجْدَاثِ سِرَاعًا كَأَنَّهُمْ إِلَىٰ نُصُبٍ يُوفِضُونَ

ያ ቀን ወደ ጣዖት እንደሚሽቀዳደሙ ሆነው ከመቃብሮቻቸው ፈጥነው የሚወጡበት ቀን ነው።

خَاشِعَةً أَبْصَارُهُمْ تَرْهَقُهُمْ ذِلَّةٌ ۚ ذَٰلِكَ الْيَوْمُ الَّذِي كَانُوا يُوعَدُونَ

ዓይኖቻቸው ያፈሩ ሆነው፤ ውርደት ትሸፍናቸዋለች። ይህ ቀን ያ ይስፈራሩበት የነበሩት ቀን ነው።