Noah · Nuh · سورة نوح · 28 ayahs

القرآن الكريمAfrica Academy

بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።

إِنَّا أَرْسَلْنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوْمِهِ أَنْ أَنْذِرْ قَوْمَكَ مِنْ قَبْلِ أَنْ يَأْتِيَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ

እኛ ኑህን ህዝቦችህን አሳማሚ ቅጣት ሳይመጣባቸው በፊት አስጠንቅቅ በማለት ወደ ወገኖቹ ላክነው።

قَالَ يَا قَوْمِ إِنِّي لَكُمْ نَذِيرٌ مُبِينٌ

እርሱም አለ፡- «ህዝቦቼ ሆይ! እኔ ለእናንተ (የቸገራችሁን) (መልዕክቴን) ገላጭ የሆንኩ ግልጽ አስጠንቃቂ ነኝ።

أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ وَاتَّقُوهُ وَأَطِيعُونِ

«አላህን ተገዙት፤ ፍሩትም፤ እኔንም ታዘዙኝ በማለት አስጠንቃቂ ነኝ።

يَغْفِرْ لَكُمْ مِنْ ذُنُوبِكُمْ وَيُؤَخِّرْكُمْ إِلَىٰ أَجَلٍ مُسَمًّى ۚ إِنَّ أَجَلَ اللَّهِ إِذَا جَاءَ لَا يُؤَخَّرُ ۖ لَوْ كُنْتُمْ تَعْلَمُونَ

«ለእናንተ ኃጢአታችሁን ይምራል እስከ ተወሰነ ጊዜም ያቆያችኋል። አላህ የወሰነው ጊዜ በመጣ ወቅት ግን ለአፍታም አይዘገይም። በትክክል የምታውቁት ብትሆኑ ኖሮ (በታዘዛችሁ ነበር።)»

قَالَ رَبِّ إِنِّي دَعَوْتُ قَوْمِي لَيْلًا وَنَهَارًا

(ህዝቦቹ ስለተቃወሙትም) «ጌታየ ሆይ! እኔ በሌሊትም ሆነ በቀን ህዝቦቼን ጠራሁ።

فَلَمْ يَزِدْهُمْ دُعَائِي إِلَّا فِرَارًا

«ጥሪየም ይበልጥ መሸሽን እንጂ ሌላ አልጨመረላቸዉም።

وَإِنِّي كُلَّمَا دَعَوْتُهُمْ لِتَغْفِرَ لَهُمْ جَعَلُوا أَصَابِعَهُمْ فِي آذَانِهِمْ وَاسْتَغْشَوْا ثِيَابَهُمْ وَأَصَرُّوا وَاسْتَكْبَرُوا اسْتِكْبَارًا

«እኔም ለእነርሱ ትምራቸው ዘንድ ወደ እምነት በጠራኋቸው ቁጥር ጣቶቻቸውን በጆሮዎቻቸው ውስጥ አደረጉ። ልብሶቻቸውንም ተከናነቡ። በመጥፎ ስራቸው ላይ ዘወተሩም። ያለ ልክ መኩራትንም ኮሩ።

ثُمَّ إِنِّي دَعَوْتُهُمْ جِهَارًا

«ከዚያ እኔ በግልጽ ጠራኋቸው።

ثُمَّ إِنِّي أَعْلَنْتُ لَهُمْ وَأَسْرَرْتُ لَهُمْ إِسْرَارًا

«ከዚያ እኔ ለእነርሱ ጥሪየን ይፋ አደረኩ። ለእነርሱ መመስጠርን መሰጠርኩም» አለ።

فَقُلْتُ اسْتَغْفِرُوا رَبَّكُمْ إِنَّهُ كَانَ غَفَّارًا

«እንዲህም አልኩ: ጌታችሁን ምህረትን ለምኑት። እርሱም በጣም መሀሪ ነውና።

يُرْسِلِ السَّمَاءَ عَلَيْكُمْ مِدْرَارًا

«በእናንተ ላይ ዝናምን ተከታታይ አድርጎ ይልካል።

وَيُمْدِدْكُمْ بِأَمْوَالٍ وَبَنِينَ وَيَجْعَلْ لَكُمْ جَنَّاتٍ وَيَجْعَلْ لَكُمْ أَنْهَارًا

«ገንዘቦችንና ልጆችንም ይለግሳችኋል። ለእናንተም አትክልቶችን ያደርግላችኋል። ለእናንተም ወንዞችን ያደርግላችኋል (አልኳቸው።)»

مَا لَكُمْ لَا تَرْجُونَ لِلَّهِ وَقَارًا

ለአላህ ተገቢውን ልቅና የማትሰጡበት ምክንያት ለእናንተ ምን አላችሁ?

وَقَدْ خَلَقَكُمْ أَطْوَارًا

በልዩ ልዩ (በተለያዩ) እርከኖች (ሁኔታዎች) በእርግጥ የፈጠራችሁ ሲሆን።

أَلَمْ تَرَوْا كَيْفَ خَلَقَ اللَّهُ سَبْعَ سَمَاوَاتٍ طِبَاقًا

አላህ ሰባት ሰማያትን አንዱ በአንዱ ላይ የተነባበረ ሲሆን እንዴት እንደፈጠረ አታዩምን?

وَجَعَلَ الْقَمَرَ فِيهِنَّ نُورًا وَجَعَلَ الشَّمْسَ سِرَاجًا

በውስጣቸዉም ጨረቃን አብሪ አደረገ። ጸሐይንም አንጸባራቂ (መብራት) አደረገ።

وَاللَّهُ أَنْبَتَكُمْ مِنَ الْأَرْضِ نَبَاتًا

አላህም ከምድር ማብቀልን አበቀላችሁ።

ثُمَّ يُعِيدُكُمْ فِيهَا وَيُخْرِجُكُمْ إِخْرَاجًا

ከዚያም በውስጧ ይመልሳችኋል። ማውጣትንም ያወጣችኋል።

وَاللَّهُ جَعَلَ لَكُمُ الْأَرْضَ بِسَاطًا

አላህም ምድርን ለእናንተ ምንጣፍ አደረጋት።

لِتَسْلُكُوا مِنْهَا سُبُلًا فِجَاجًا

ከእርሷ ሰፋፊ መንገዶችን ትሄዱ ዘንድ።

قَالَ نُوحٌ رَبِّ إِنَّهُمْ عَصَوْنِي وَاتَّبَعُوا مَنْ لَمْ يَزِدْهُ مَالُهُ وَوَلَدُهُ إِلَّا خَسَارًا

ኑሕም አለ፡- «ጌታየ ሆይ! እነርሱም አመጹብኝ ገንዘቡና ልጁም ከጥፋት በስተቀር ያልጨመረለትን ሰው ተከተሉ።

وَمَكَرُوا مَكْرًا كُبَّارًا

«ከባድንም ተንኮል ያሴሩትን ሰዎች ተከተሉ።

وَقَالُوا لَا تَذَرُنَّ آلِهَتَكُمْ وَلَا تَذَرُنَّ وَدًّا وَلَا سُوَاعًا وَلَا يَغُوثَ وَيَعُوقَ وَنَسْرًا

(መሪዎችም) አሉ፡-«አማልክቶቻችሁን፤ ወድንም፤ ሰዋዕንም፤ የጉስንም፤ የዑቅንና ነስርንም አትተው።»

وَقَدْ أَضَلُّوا كَثِيرًا ۖ وَلَا تَزِدِ الظَّالِمِينَ إِلَّا ضَلَالًا

«በእርግጥ (እነዚህ መሪዎች ወይም ጣኦቶች) ብዙዎችን ሰዎች አሳሳቱ። ከሓዲያንንም ጥመትን እንጂ ሌላን አትጨምርላቸው» አለ።

مِمَّا خَطِيئَاتِهِمْ أُغْرِقُوا فَأُدْخِلُوا نَارًا فَلَمْ يَجِدُوا لَهُمْ مِنْ دُونِ اللَّهِ أَنْصَارًا

በኃጢአቶቻቸው ምክንያት ተሰመጡ። እሳትንም እንዲገቡ ተደረጉ። ለእነርሱም ከአላህ ሌላ የሆኑ ረዳቶችን አላገኙም።

وَقَالَ نُوحٌ رَبِّ لَا تَذَرْ عَلَى الْأَرْضِ مِنَ الْكَافِرِينَ دَيَّارًا

ኑህም አለ፡- «ጌታየ ሆይ! ከከሓዲያን በምድር ላይ (በዓለም ላይ) የሚኖርን አንድንም አትተው።

إِنَّكَ إِنْ تَذَرْهُمْ يُضِلُّوا عِبَادَكَ وَلَا يَلِدُوا إِلَّا فَاجِرًا كَفَّارًا

«አንተ ብትተዋቸው ባሮችህን ያሳስታሉና። ኃጢአተኛ ከሓዲንም እንጂ ሌላን አይወልዱም።

رَبِّ اغْفِرْ لِي وَلِوَالِدَيَّ وَلِمَنْ دَخَلَ بَيْتِيَ مُؤْمِنًا وَلِلْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ وَلَا تَزِدِ الظَّالِمِينَ إِلَّا تَبَارًا

«ጌታየ ሆይ! ለእኔም ለወላጆቼም ትክክለኛ አማኝ ሆኖ በቤቴ ለገባ ሁሉ ለአማኞችና ለምዕመናትም ምህረት አድርግ። ከሓዲያንንም ከጥፋት በስተቀር አትጨምርላቸው።» አለ።