The Rolling · at-Takwir · سورة التكوير · 29 ayahs

القرآن الكريمAfrica Academy

بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።

إِذَا الشَّمْسُ كُوِّرَتْ

ጸሐይ በተጠቀለለች ጊዜ፤

وَإِذَا النُّجُومُ انْكَدَرَتْ

ከዋክብትም በረገፉ ጊዜ፤

وَإِذَا الْجِبَالُ سُيِّرَتْ

ተራራዎች ከቦታቸው በተነዱ ጊዜ፤

وَإِذَا الْعِشَارُ عُطِّلَتْ

የአስር ወር እርጉዝ ግመሎች ያለጠባቂ በተተው ጊዜ፤

وَإِذَا الْوُحُوشُ حُشِرَتْ

አራዊቶችም በተሰበሰቡ ጊዜ፤

وَإِذَا الْبِحَارُ سُجِّرَتْ

ባህሮችም በተቀጣጠሉ ጊዜ፤

وَإِذَا النُّفُوسُ زُوِّجَتْ

ነፍሶች በተቆራኙ ጊዜ፤

وَإِذَا الْمَوْءُودَةُ سُئِلَتْ

ከነሕይወቷ የተቀበረችው ሴት ልጅም በተጠየቀች ጊዜ፤

بِأَيِّ ذَنْبٍ قُتِلَتْ

በምን ወንጀል እንደተገደለች፤ በተጠየቀች ጊዜ፤

وَإِذَا الصُّحُفُ نُشِرَتْ

ጹሑፎችም በተዘረጉ ጊዜ፤

وَإِذَا السَّمَاءُ كُشِطَتْ

ሰማይም በተገሸለጠች ጊዜ፤

وَإِذَا الْجَحِيمُ سُعِّرَتْ

ገሀነምም በተነደደች ጊዜ፤

وَإِذَا الْجَنَّةُ أُزْلِفَتْ

ገነትም በተቀረበች ጊዜ፤

عَلِمَتْ نَفْسٌ مَا أَحْضَرَتْ

ነፍስ (ሁሉ ከስራ) ያቀረበችውን ታውቃለች፤

فَلَا أُقْسِمُ بِالْخُنَّسِ

(ሁኔታው ከሓዲያን እንደሚሉት አይደለም)። ተመላሾች በሆኑት (ከዋክብት) እምላለሁ።

الْجَوَارِ الْكُنَّسِ

አንዳንድ ጊዜ ሂያጆች በሌላ ጊዜ ገቢዎች በሆኑት

وَاللَّيْلِ إِذَا عَسْعَسَ

በሌሊቱም (ጨለማውን) በጠነሰሰ ጊዜ፤

وَالصُّبْحِ إِذَا تَنَفَّسَ

በንጋትም (በብርሃን) በተነፈሰ ጊዜ እምላለሁ።

إِنَّهُ لَقَوْلُ رَسُولٍ كَرِيمٍ

እርሱ (ቁርኣን) የተከበረው መልዕክተኛ (ጅብሪል) ቃል ነው።

ذِي قُوَّةٍ عِنْدَ ذِي الْعَرْشِ مَكِينٍ

የኃይል ባለቤት የሆነ፤ ከዐርሹ ባለቤት ዘንድም ባለሟል የሆነ፤

مُطَاعٍ ثَمَّ أَمِينٍ

በዚያ ስፍራ ትዕዛዙ ተሰሚ፤ ታማኝም የሆነው (መልዕክተኛ ቃል ነው)።

وَمَا صَاحِبُكُمْ بِمَجْنُونٍ

ባልደረባችሁም (ሙሐመድ) እብድ አይደለም።

وَلَقَدْ رَآهُ بِالْأُفُقِ الْمُبِينِ

(ጅብሪልን) በግልጹ አድማስ ላይ በእርግጥ አይቶታል።

وَمَا هُوَ عَلَى الْغَيْبِ بِضَنِينٍ

እርሱም በሩቁ ወሬ ላይ ሰሳች (ንፉግ) አይደለም።

وَمَا هُوَ بِقَوْلِ شَيْطَانٍ رَجِيمٍ

(ቁርኣን) የርጉም ሰይጣን ቃልም አይደለም።

فَأَيْنَ تَذْهَبُونَ

ታዲያ (ይህንን በተመለከተ) ወዴት ትሄዳላችሁ?

إِنْ هُوَ إِلَّا ذِكْرٌ لِلْعَالَمِينَ

እርሱ የዓለማት መገሰጫ እንጂ ሌላ አይደለም።

لِمَنْ شَاءَ مِنْكُمْ أَنْ يَسْتَقِيمَ

ከናንተ መካከል ቀጥተኛ መሆንን ለፈለገ (ሁሉ መገሰጫ) ነው።

وَمَا تَشَاءُونَ إِلَّا أَنْ يَشَاءَ اللَّهُ رَبُّ الْعَالَمِينَ

(ሰዎች ሆይ!) የዓለማት ጌታ የሆነው አላህ ካልሻ በስተቀር እናንተ አንድም ነገር አትሹም።