إِذَا السَّمَاءُ انْفَطَرَتْ
ሰማይ በተሰነጠቀች ጊዜ፤
القرآن الكريمAfrica Academy
بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።
إِذَا السَّمَاءُ انْفَطَرَتْ
ሰማይ በተሰነጠቀች ጊዜ፤
وَإِذَا الْكَوَاكِبُ انْتَثَرَتْ
ከዋክብትም ተበታትነው በወደቁ ጊዜ፤
وَإِذَا الْبِحَارُ فُجِّرَتْ
ባህሮችም በተከፈቱና በተደባለቁ ጊዜ፤
وَإِذَا الْقُبُورُ بُعْثِرَتْ
መቃብሮችም በተገለባበጡና ሙታን በተነሱ ጊዜ፤
عَلِمَتْ نَفْسٌ مَا قَدَّمَتْ وَأَخَّرَتْ
(ያኔ) ማንኛይቱም ነፍስ ያስቀደመችውንና ያዘገየችውን ታውቃለች።
يَا أَيُّهَا الْإِنْسَانُ مَا غَرَّكَ بِرَبِّكَ الْكَرِيمِ
አንተ ሰው ሆይ! በቸሩ ጌታህ ምን አታለለህ?
الَّذِي خَلَقَكَ فَسَوَّاكَ فَعَدَلَكَ
በዚያ በፈጠረህ፤ አካለ ሙሉም ባደረገህ፤ ባስተካከለህም፤
فِي أَيِّ صُورَةٍ مَا شَاءَ رَكَّبَكَ
በማንኛውም (እርሱ) በፈለገው ቅርጽ በገጣጠመህ ጌታህ ምን አታለለህ?
كَلَّا بَلْ تُكَذِّبُونَ بِالدِّينِ
(ሰዎች ሆይ!) ተከልከሉ፤ ይልቁንም በፍርዱ ቀን ታስተባብላላችሁ።
وَإِنَّ عَلَيْكُمْ لَحَافِظِينَ
በእናንተ ላይ ጠባቂዎች ያሉባችሁ ስትሆኑ፤
كِرَامًا كَاتِبِينَ
የተከበሩ ጸሐፊዎች የሆኑ (ተጠባባቂዎች)፤
يَعْلَمُونَ مَا تَفْعَلُونَ
የምትሰሩትን (ሁሉ) ያውቃሉ፤
إِنَّ الْأَبْرَارَ لَفِي نَعِيمٍ
(እውነተኞቹ) ደጋጎች በእርግጥም በገነት ውስጥ ናቸው።
وَإِنَّ الْفُجَّارَ لَفِي جَحِيمٍ
ከሓዲያንም በእርግጥ በገሀነም ውስጥ ናቸው።
يَصْلَوْنَهَا يَوْمَ الدِّينِ
በፍርዱ ቀን ይገቧታል።
وَمَا هُمْ عَنْهَا بِغَائِبِينَ
እነርሱም (ምን ጊዜም) ከእርሷ ራቂዎች አይደሉም።
وَمَا أَدْرَاكَ مَا يَوْمُ الدِّينِ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የፍርዱ ቀን ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ?
ثُمَّ مَا أَدْرَاكَ مَا يَوْمُ الدِّينِ
ከዚያም የፍርዱ ቀን ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ?
يَوْمَ لَا تَمْلِكُ نَفْسٌ لِنَفْسٍ شَيْئًا ۖ وَالْأَمْرُ يَوْمَئِذٍ لِلَّهِ
(እርሱ) ማንኛይቱም ነፍስ ለሌላይቱ ነፍስ ምንም ማድረግ የማትችልበት ቀን ነው። ነገሩም ሁሉ በዚያ ቀን ለአላህ ብቻ ነው።