إِذَا السَّمَاءُ انْشَقَّتْ
ሰማይ በተቀደደች (በተሰነጠቀች) ጊዜ፤
القرآن الكريمAfrica Academy
بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።
إِذَا السَّمَاءُ انْشَقَّتْ
ሰማይ በተቀደደች (በተሰነጠቀች) ጊዜ፤
وَأَذِنَتْ لِرَبِّهَا وَحُقَّتْ
የጌታዋንም ትዕዛዝ በሰማች ጊዜ፤ (ልትሰማ) ተገባትም፤
وَإِذَا الْأَرْضُ مُدَّتْ
ምድርም በተለጠጠች ጊዜ፤
وَأَلْقَتْ مَا فِيهَا وَتَخَلَّتْ
በውስጧ ያለውንም ሁሉ በጣለችና ባዶ በሆነች ጊዜ፤
وَأَذِنَتْ لِرَبِّهَا وَحُقَّتْ
የጌታዋንም ትዕዛዝ በሰማች ጊዜ፤ (ልትሰማ) ተገባትም፤
يَا أَيُّهَا الْإِنْسَانُ إِنَّكَ كَادِحٌ إِلَىٰ رَبِّكَ كَدْحًا فَمُلَاقِيهِ
አንተ ሰው ሆይ! አንተ ጌታህን (በሞት) እስከምትገናኝ ድረስ ልፋትን ለፊ ነህ። ተገናኚዉም ነህ።
فَأَمَّا مَنْ أُوتِيَ كِتَابَهُ بِيَمِينِهِ
ያ! መጽሐፉን በቀኝ እጁ የተሰጠውማ
فَسَوْفَ يُحَاسَبُ حِسَابًا يَسِيرًا
በእርግጥ ቀላልን ምርመራ ይመረመራል።
وَيَنْقَلِبُ إِلَىٰ أَهْلِهِ مَسْرُورًا
ወደ ቤተሰቦቹም ተደሳች ሆኖ (በደስታ) ይመለሳል።
وَأَمَّا مَنْ أُوتِيَ كِتَابَهُ وَرَاءَ ظَهْرِهِ
ያ ! መጽሐፉን በጀርባው በኩል የተሰጠው ግን
فَسَوْفَ يَدْعُو ثُبُورًا
(ዋ! ጥፋቴ በማለት) ጥፋትን በእርግጥ ይጠራል።
وَيَصْلَىٰ سَعِيرًا
የተጋጋመች እሳትንም ይገባል።
إِنَّهُ كَانَ فِي أَهْلِهِ مَسْرُورًا
እርሱ በቤተሰቡ ውስጥ ተደሳች ነበርና፤
إِنَّهُ ظَنَّ أَنْ لَنْ يَحُورَ
እርሱም (ወደ አላህ) ፈጽሞ እንደማይመለስ አሰበ።
بَلَىٰ إِنَّ رَبَّهُ كَانَ بِهِ بَصِيرًا
አይደለም (ይመለሳል)፤ ጌታው በእርሱ (ሥራ) ተመልካች ነው።
فَلَا أُقْسِمُ بِالشَّفَقِ
ስለሆነም በወጋገኑ እምላለሁ።
وَاللَّيْلِ وَمَا وَسَقَ
በሌሊቱና በሰበሰበዉም ሁሉ፤
وَالْقَمَرِ إِذَا اتَّسَقَ
በጨረቃውም በሞላ ጊዜ (እምላለሁ)።
لَتَرْكَبُنَّ طَبَقًا عَنْ طَبَقٍ
ከአንድ እርከን ወደ ሌላ እርከን በእርግጥ ትሸጋገራላችሁ።
فَمَا لَهُمْ لَا يُؤْمِنُونَ
የማያምኑት ለእነርሱ ምን አላቸው ( ምን ሆነው ነው)?
وَإِذَا قُرِئَ عَلَيْهِمُ الْقُرْآنُ لَا يَسْجُدُونَ ۩
በእነርሱ ላይ ቁርኣን በተነበበ ጊዜ የማይሰግዱትስ ለእነርሱ ምን አላቸውና ነው?
بَلِ الَّذِينَ كَفَرُوا يُكَذِّبُونَ
ይልቁንም እነዚያ የካዱት ያስተባብላሉ።
وَاللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا يُوعُونَ
አላህ በልቦቻቸው የሚቋጥሩትን ሁሉ አዋቂ ነው።
فَبَشِّرْهُمْ بِعَذَابٍ أَلِيمٍ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአሳማሚ ቅጣት አብስራቸው።
إِلَّا الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ لَهُمْ أَجْرٌ غَيْرُ مَمْنُونٍ
እነዚያ በአላህ አምነው መልካም ተግባራትን የሰሩት ሲቀሩ፤ ለእነርሱማ የማይቋረጥ ምንዳ አላቸው።