وَالسَّمَاءِ ذَاتِ الْبُرُوجِ
የህብረ ከዋክብት ባለቤት በሆነችው ሰማይ፤
القرآن الكريمAfrica Academy
بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።
وَالسَّمَاءِ ذَاتِ الْبُرُوجِ
የህብረ ከዋክብት ባለቤት በሆነችው ሰማይ፤
وَالْيَوْمِ الْمَوْعُودِ
በተቀጠረዉም ቀን፤
وَشَاهِدٍ وَمَشْهُودٍ
በመስካሪና በሚመሰከርበትም እምላለሁ።
قُتِلَ أَصْحَابُ الْأُخْدُودِ
የጉድቡ ባለቤቶች ተረገሙ።
النَّارِ ذَاتِ الْوَقُودِ
የባለማገዶዋ እሳት ባለቤቶች።
إِذْ هُمْ عَلَيْهَا قُعُودٌ
እነርሱ በርሷ (አፋፍ) ላይ ተቀማጮች በሆኑ ጊዜ (ተረገሙ)።
وَهُمْ عَلَىٰ مَا يَفْعَلُونَ بِالْمُؤْمِنِينَ شُهُودٌ
እነርሱም በምዕመኖች ላይ ለሚሰሩት (ማሰቃየት) መስካሪዎች ናቸው።
وَمَا نَقَمُوا مِنْهُمْ إِلَّا أَنْ يُؤْمِنُوا بِاللَّهِ الْعَزِيزِ الْحَمِيدِ
ከእነርሱም በአሸናፊውና በምስጉኑ አላህ ማመናቸውን እንጂ ሌላን ምንንም አልጠሉም።
الَّذِي لَهُ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ شَهِيدٌ
ያ የሰማያትና የምድር ንግስና ለእርሱ ብቻ የሆነውን (ነው ያመኑበት)። አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ መስካሪ ነው (አዋቂ ነው)።
إِنَّ الَّذِينَ فَتَنُوا الْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ ثُمَّ لَمْ يَتُوبُوا فَلَهُمْ عَذَابُ جَهَنَّمَ وَلَهُمْ عَذَابُ الْحَرِيقِ
እነዚያ አማኞችና ምዕመናትን ያሰቃዩና ከዚያ ያልተጸጸቱ ሁሉ ለእነርሱ የገሀነም ቅጣት አለላቸው። ለእነርሱም የመቃጠሉ ስቃይ አላቸው።
إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ لَهُمْ جَنَّاتٌ تَجْرِي مِنْ تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ ۚ ذَٰلِكَ الْفَوْزُ الْكَبِيرُ
እነዚያ በአላህ አምነው መልካም ስራዎችን የሰሩ ሁሉ ለእነርሱ ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች አሏቸው። ይህ ታላቅ ስኬት ነው።
إِنَّ بَطْشَ رَبِّكَ لَشَدِيدٌ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጌታህ በኃይል መያዝ ብርቱ ነው።
إِنَّهُ هُوَ يُبْدِئُ وَيُعِيدُ
እነሆ እርሱ መፍጠርን ይጀምራል፤ ይመልሳልም።
وَهُوَ الْغَفُورُ الْوَدُودُ
እርሱም ምህረቱ የበዛ ወዳድ ነው።
ذُو الْعَرْشِ الْمَجِيدُ
የላቀው የዙፋኑ ባለቤት ነው።
فَعَّالٌ لِمَا يُرِيدُ
የሚሻውን ሁሉ ሰሪ (ፈፃሚ) ነው።
هَلْ أَتَاكَ حَدِيثُ الْجُنُودِ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! የእነዚያ ነብያትን ያስተባበሉ) ሰራዊቶች ወሬ መጣልህን?
فِرْعَوْنَ وَثَمُودَ
የፊርዓውንና የሰሙድ (ወሬ ደርሶሃልን)?
بَلِ الَّذِينَ كَفَرُوا فِي تَكْذِيبٍ
ይልቁንም እነዚያ (በአላህ) የካዱት (ሰዎች ሁሉ) እውነትን በማስተባበል ውስጥ ናቸው።
وَاللَّهُ مِنْ وَرَائِهِمْ مُحِيطٌ
አላህም በዙሪያቸው (በዕውቀቱ) ከባቢ ነው።
بَلْ هُوَ قُرْآنٌ مَجِيدٌ
ይልቁንም እርሱ የተከበረ ቁርኣን ነው።
فِي لَوْحٍ مَحْفُوظٍ
የተጠበቀ በሆነ ሰሌዳ (ሎህ) ውስጥ ነው።