The Most High · al-A'la · سورة الأعلى · 19 ayahs

القرآن الكريمAfrica Academy

بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።

سَبِّحِ اسْمَ رَبِّكَ الْأَعْلَى

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የዚያን ከሁሉ በላይ የሆነውን ጌታህን ስም አጥራ (አሞግስ)።

الَّذِي خَلَقَ فَسَوَّىٰ

ያ ሁሉን ነገር የፈጠረውንና ያስተካከለውን፤

وَالَّذِي قَدَّرَ فَهَدَىٰ

ያን የወሰነውን ነገርንም ሁሉ ለተፈጠረለት የመራውን፤

وَالَّذِي أَخْرَجَ الْمَرْعَىٰ

ያም ግጦሽን ለምለም አድርጎ ያወጣውን፤

فَجَعَلَهُ غُثَاءً أَحْوَىٰ

(ከዚያ) ደረቅ ጥቁር ያደረገውንም (አምላክ ስም አሞግስ)።

سَنُقْرِئُكَ فَلَا تَنْسَىٰ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቁርኣንን በእርግጥ እናስነብብሃለን፤ አትረሳምም፤

إِلَّا مَا شَاءَ اللَّهُ ۚ إِنَّهُ يَعْلَمُ الْجَهْرَ وَمَا يَخْفَىٰ

አላህ ከፈለገው ነገር በስተቀር፤ እናም እርሱ ግልጹንም የሚሸሽገውንም ሁሉ ያውቃልና፤

وَنُيَسِّرُكَ لِلْيُسْرَىٰ

ለገሪቱም (ሕይወት እስላምን ትከተል ዘንድ) እናገራሃለን።

فَذَكِّرْ إِنْ نَفَعَتِ الذِّكْرَىٰ

(ሰዎችንም) ገስፅ፤ ግሳፄይቱ ብትጠቅም።

سَيَذَّكَّرُ مَنْ يَخْشَىٰ

(አላህን) የሚፈራ በእርግጥ ይገሰፃል።

وَيَتَجَنَّبُهَا الْأَشْقَى

መናጢዉም ይርቃታል።

الَّذِي يَصْلَى النَّارَ الْكُبْرَىٰ

ያ! ታላቂቱን እሳት የሚገባው፤

ثُمَّ لَا يَمُوتُ فِيهَا وَلَا يَحْيَىٰ

ከዚያም በእርሷ ውስጥ የማይሞትና ህያዉም የማይሆነው።

قَدْ أَفْلَحَ مَنْ تَزَكَّىٰ

(አላህን ከማመፅ) የተጥራራ ሰው በእርግጥ ዳነ፤

وَذَكَرَ اسْمَ رَبِّهِ فَصَلَّىٰ

የጌታውንም ስም ያወሳና የሰገደ።

بَلْ تُؤْثِرُونَ الْحَيَاةَ الدُّنْيَا

ይልቁንም ቅርቢቱን ሕይወት ታስቀድማላችሁ፤

وَالْآخِرَةُ خَيْرٌ وَأَبْقَىٰ

(ሰዎች ሆይ!) መጨረሻይቱ ሕይወት በላጭና፤ ዘወታሪ ሆና ሳለ።

إِنَّ هَٰذَا لَفِي الصُّحُفِ الْأُولَىٰ

ይህ በቀደምቶቹም መጻሕፍት ውስጥ ያለ ነው።

صُحُفِ إِبْرَاهِيمَ وَمُوسَىٰ

በኢብራሂምና በሙሳ መጽሐፍት ውስጥ የሰፈረ እውነታ ነው።