The Dawn · al-Fajr · سورة الفجر · 30 ayahs

القرآن الكريمAfrica Academy

بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።

وَالْفَجْرِ

በጎህ፤ እምላለሁ

وَلَيَالٍ عَشْرٍ

በአስሩ ሌሊቶችም፤

وَالشَّفْعِ وَالْوَتْرِ

በጥንዱም በነጠላዉም፤

وَاللَّيْلِ إِذَا يَسْرِ

በሌሊቱም በሚጓዝበት ጊዜ እምላለሁ።

هَلْ فِي ذَٰلِكَ قَسَمٌ لِذِي حِجْرٍ

በዚህ መሀላ ለባለ አእምሮ ታላቅ መሀላ የለበትምን?

أَلَمْ تَرَ كَيْفَ فَعَلَ رَبُّكَ بِعَادٍ

ጌታህ በዓድ ህዝቦች ላይ እንዴት እንደሰራ አላወክምን?

إِرَمَ ذَاتِ الْعِمَادِ

በባለ ረዣዥሚቱ አዕማድ ኢረም ላይም፤

الَّتِي لَمْ يُخْلَقْ مِثْلُهَا فِي الْبِلَادِ

በዚያች ብጤዋ በአገሮች ውስጥ ያልተፈጠረ በሆነችው፤

وَثَمُودَ الَّذِينَ جَابُوا الصَّخْرَ بِالْوَادِ

በእነዚያ (በሸለቆዎች) ቋጥኝን የቦረቦሩ በሆኑት ሰሙድም፤

وَفِرْعَوْنَ ذِي الْأَوْتَادِ

ባለ ችካሎች በሆነው ፈርዖንም፤

الَّذِينَ طَغَوْا فِي الْبِلَادِ

በእነዚያ በአገሮች ላይ ግፍ የሰሩ (በሆኑትም ላይ)፤

فَأَكْثَرُوا فِيهَا الْفَسَادَ

በእርሷም ውስጥ ጥፋትን ያበዙ በሆኑት (እንዴት እንደሰራ አታውቅምን?)

فَصَبَّ عَلَيْهِمْ رَبُّكَ سَوْطَ عَذَابٍ

በእነርሱ ላይም ጌታህ የቅጣትን አለንጋ አወረደባቸው።

إِنَّ رَبَّكَ لَبِالْمِرْصَادِ

ጌታህ በእርግጥ በመጠባበቂያ ላይ ነውና።

فَأَمَّا الْإِنْسَانُ إِذَا مَا ابْتَلَاهُ رَبُّهُ فَأَكْرَمَهُ وَنَعَّمَهُ فَيَقُولُ رَبِّي أَكْرَمَنِ

የሰው ልጅ ጌታው በሞከረው ጊዜ ባከበረውና ባንደላቀቀው ጊዜ ጌታየ አከበረኝ (አበለጠኝ) ይላል።

وَأَمَّا إِذَا مَا ابْتَلَاهُ فَقَدَرَ عَلَيْهِ رِزْقَهُ فَيَقُولُ رَبِّي أَهَانَنِ

በሞከረውና በእርሱ ላይ ሲሳዩን ባጠበበበት (ጊዜ) እንዲሁ ጌታየ አሳነሰኝ ይላል።

كَلَّا ۖ بَلْ لَا تُكْرِمُونَ الْيَتِيمَ

በፍፁም! ይልቁንም የቲምን አታከብሩም፤

وَلَا تَحَاضُّونَ عَلَىٰ طَعَامِ الْمِسْكِينِ

ድሃንም በማብላት ላይ አታነሳሱም፤

وَتَأْكُلُونَ التُّرَاثَ أَكْلًا لَمًّا

የውርስንም ገንዘብ የመሰብሰብን አበላል (ያለአግባብ) ትበላላችሁ፤

وَتُحِبُّونَ الْمَالَ حُبًّا جَمًّا

ገንዘብንም አብዝታችሁ (አለቅጥ) ትወዳላችሁ፤

كَلَّا إِذَا دُكَّتِ الْأَرْضُ دَكًّا دَكًّا

(ሰዎች ሆይ! ተዉ)። ታቀቡ። ምድር ደጋግማ በተንኮታኮተች ጊዜ፤

وَجَاءَ رَبُّكَ وَالْمَلَكُ صَفًّا صَفًّا

ጌታህ በመጣና መላዕክትም በሰልፍ በሰልፍ ሆነው በመጡ ጊዜ፤

وَجِيءَ يَوْمَئِذٍ بِجَهَنَّمَ ۚ يَوْمَئِذٍ يَتَذَكَّرُ الْإِنْسَانُ وَأَنَّىٰ لَهُ الذِّكْرَىٰ

ገሀነምም በዚያ ቀን በተመጣች ጊዜ በዚያ ቀን ሰው ሁሉ (ጥፋቱን) በትክክል ይገነዘባል። መገንዘቡ በየት በኩል (ይጥቀመው)?

يَقُولُ يَا لَيْتَنِي قَدَّمْتُ لِحَيَاتِي

"ወይ እኔ! ምነው በሕይወቴ (መልካምን ስራ) ባስቀደምኩ ኖሮ" ይላል።

فَيَوْمَئِذٍ لَا يُعَذِّبُ عَذَابَهُ أَحَدٌ

በዚያ ቀንም የእርሱን አቀጣጥ የመሰለ አንድም አካል አይቀጣም።

وَلَا يُوثِقُ وَثَاقَهُ أَحَدٌ

የእርሱንም አስተሳሰር አንድም አያስርም።

يَا أَيَّتُهَا النَّفْسُ الْمُطْمَئِنَّةُ

(ለአመነች ነፍስም እንዲህ ትባላለች)፡- አንቺ (በአላህ) የተረጋጋሽው ነፍስ ሆይ!

ارْجِعِي إِلَىٰ رَبِّكِ رَاضِيَةً مَرْضِيَّةً

(ከእርሱም) የወደድሽ፤ (እርሱ ዘንድም) የተወደደሽ ሆነሽ ወደ ጌታሽ ተመለሺ።

فَادْخُلِي فِي عِبَادِي

ከዉድ ባሮቼም ጋር ተቀላቀይ።

وَادْخُلِي جَنَّتِي

ወደ ገነቴም ግቢ ትባላለች።