The Land · al-Balad · سورة البلد · 20 ayahs

القرآن الكريمAfrica Academy

بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።

لَا أُقْسِمُ بِهَٰذَا الْبَلَدِ

በዚህ ሀገር (በመካ) እምላለሁ

وَأَنْتَ حِلٌّ بِهَٰذَا الْبَلَدِ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ በዚህ አገር (መዋጋት) የተፈቀደልህ ስትሆን።

وَوَالِدٍ وَمَا وَلَدَ

በወላጂና በወለዳቸውም (በአደምና በዘሮቹ) ሁሉ (እምላለሁ)።

لَقَدْ خَلَقْنَا الْإِنْسَانَ فِي كَبَدٍ

ሰውን ሁሉ በእርግጥ በልፋት ውስጥ ሆኖ ፈጠርነው።

أَيَحْسَبُ أَنْ لَنْ يَقْدِرَ عَلَيْهِ أَحَدٌ

በእርሱ ላይ አንድም አካል የማይችል መሆኑን ያስባልን?

يَقُولُ أَهْلَكْتُ مَالًا لُبَدًا

"ብዙን ገንዘብ አጠፋሁ" ይላል፤

أَيَحْسَبُ أَنْ لَمْ يَرَهُ أَحَدٌ

አንድም ያላየው መሆኑን ያስባልን?

أَلَمْ نَجْعَلْ لَهُ عَيْنَيْنِ

ለእርሱ ሁለት አይኖችን አላደረግንለትንምን?

وَلِسَانًا وَشَفَتَيْنِ

አንድ ምላስንና ሁለት ከንፈሮችንም፤

وَهَدَيْنَاهُ النَّجْدَيْنِ

ሁለትን መንገዶችስ አልመራነዉምን?

فَلَا اقْتَحَمَ الْعَقَبَةَ

ዐቀበቱን አልወጣም።

وَمَا أَدْرَاكَ مَا الْعَقَبَةُ

ዐቀበቱን መውጣት ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ?

فَكُّ رَقَبَةٍ

ያ ጫንቃን መልቀቅ ነው።

أَوْ إِطْعَامٌ فِي يَوْمٍ ذِي مَسْغَبَةٍ

ወይም የረሀብ ባለቤት በሆነ ቀን (ረሀብተኛን) ማብላት፤

يَتِيمًا ذَا مَقْرَبَةٍ

የዝምድና ባለቤት የሆነን የቲም፤

أَوْ مِسْكِينًا ذَا مَتْرَبَةٍ

ወይም የአፈር ባለቤት የሆነን (ችግረኛ) ማብላት ነው።

ثُمَّ كَانَ مِنَ الَّذِينَ آمَنُوا وَتَوَاصَوْا بِالصَّبْرِ وَتَوَاصَوْا بِالْمَرْحَمَةِ

ከዚያም ከእነዚያ በአላህ ካመኑትና በመታገስና በመተዛዘንም ላይ አደራ ከተባባሉት ሰዎች ጋር መሆን ነው።

أُولَٰئِكَ أَصْحَابُ الْمَيْمَنَةِ

እነዚያ (ይህንን የፈጸሙ) የቀኝ ጓዶች ናቸው።

وَالَّذِينَ كَفَرُوا بِآيَاتِنَا هُمْ أَصْحَابُ الْمَشْأَمَةِ

እነዚያ በአናቅጻችን የካዱ ሁሉ እነርሱ የግራ ጓዶች ናቸው።

عَلَيْهِمْ نَارٌ مُؤْصَدَةٌ

ለእነርሱ የምትዘጋባቸው እሳትም አለች።