The Sun · ash-Shams · سورة الشمس · 15 ayahs

القرآن الكريمAfrica Academy

بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።

وَالشَّمْسِ وَضُحَاهَا

በጸሐይና በብርሀኗ፤ (እምላለሁ)

وَالْقَمَرِ إِذَا تَلَاهَا

በጨረቃም ጸሐይን በተከተላት ጊዜ፤

وَالنَّهَارِ إِذَا جَلَّاهَا

በቀንም ጸሐይን በገለፃት ጊዜ፤

وَاللَّيْلِ إِذَا يَغْشَاهَا

በሌሊቱም ጸሐይን በሸፈናት ጊዜ፤

وَالسَّمَاءِ وَمَا بَنَاهَا

በሰማይ እና በገነባትም፤

وَالْأَرْضِ وَمَا طَحَاهَا

በምድር እና በዘረጋትም፤

وَنَفْسٍ وَمَا سَوَّاهَا

በነፍስም ባስተካከላትም

فَأَلْهَمَهَا فُجُورَهَا وَتَقْوَاهَا

አመጽዋንና ፍርሃቷንም ባሳወቃት (አምላክም እምላለሁ)።

قَدْ أَفْلَحَ مَنْ زَكَّاهَا

(ነፍስን) ከኃጢአት ያጠራ ሰው ሁሉ በእርግጥ ተሳካለት።

وَقَدْ خَابَ مَنْ دَسَّاهَا

በኃጢአትም የሸፈናት ሰው ሁሉ በእውነት አፈረ (ከሰረ)።

كَذَّبَتْ ثَمُودُ بِطَغْوَاهَا

ሰሙድ ወሰን በማለፍዋ ምክንያት አስተባበለች፤

إِذِ انْبَعَثَ أَشْقَاهَا

እጅግ መናጢዋ በተነሳ ጊዜ።

فَقَالَ لَهُمْ رَسُولُ اللَّهِ نَاقَةَ اللَّهِ وَسُقْيَاهَا

ለእነርሱም የአላህ መልዕክተኛ (ሷሊህ)፡-የአላህን ግመልና የመጠጥ ተራዋን (ጠብቁላት) አላቸው።

فَكَذَّبُوهُ فَعَقَرُوهَا فَدَمْدَمَ عَلَيْهِمْ رَبُّهُمْ بِذَنْبِهِمْ فَسَوَّاهَا

እነርሱ አስተባበሉትም፤ ከዚያ ወጓት፤ በኃጢአታቸዉም ምክንያት ጌታቸው (ቅጣትን) በእነርሱ ላይ ደመደመባቸው (ደመሰሳቸው)፤ አስተካከላትም።

وَلَا يَخَافُ عُقْبَاهَا

ፍፃሜዋንም አይፈራም። (አላህም የዚህን ቅጣት ፍፃሜ አይፈራም።)