Clot · al-'Alaq · سورة العلق · 19 ayahs

القرآن الكريمAfrica Academy

بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።

اقْرَأْ بِاسْمِ رَبِّكَ الَّذِي خَلَقَ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በዚያ (ሁሉንም ነገር) በፈጠረ ጌታህ ስም (ጀምርና) አንብብ!

خَلَقَ الْإِنْسَانَ مِنْ عَلَقٍ

ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)።

اقْرَأْ وَرَبُّكَ الْأَكْرَمُ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንብብ! ጌታህም በጣም ቸር ነው።

الَّذِي عَلَّمَ بِالْقَلَمِ

ያ በብዕር ያስተማረ (ጌታ)፤

عَلَّمَ الْإِنْسَانَ مَا لَمْ يَعْلَمْ

የሰውን ልጅ ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ (ጌታ)።

كَلَّا إِنَّ الْإِنْسَانَ لَيَطْغَىٰ

በእውነቱ የሰው ልጅ ወሰንን ያልፋል።

أَنْ رَآهُ اسْتَغْنَىٰ

ራሱን የተብቃቃ ሆኖ በማየቱ ምክንያት

إِنَّ إِلَىٰ رَبِّكَ الرُّجْعَىٰ

መመለሻው ወደ ጌታህ ብቻ ነው።

أَرَأَيْتَ الَّذِي يَنْهَىٰ

ያንን የሚከለክለውን አየህን?

عَبْدًا إِذَا صَلَّىٰ

ባሪያን በሰገደ ጊዜ (የሚከለክለውን):

أَرَأَيْتَ إِنْ كَانَ عَلَى الْهُدَىٰ

እስቲ ንገረኝ (ተከልካዩ ባሪያየ) በትክክል መንገድ ላይ ቢሆን፤

أَوْ أَمَرَ بِالتَّقْوَىٰ

ወይም (ፈጣሪውን) በመፍራት ቢያዝ ምን እንደሚሆን አየህን?

أَرَأَيْتَ إِنْ كَذَّبَ وَتَوَلَّىٰ

እስቲ ንገረኝ (ከልካዩ) ቢያስተባብልና ከእምነት ቢሸሽ፤

أَلَمْ يَعْلَمْ بِأَنَّ اللَّهَ يَرَىٰ

አላህ የሚያይ መሆኑን አያውቅምን?

كَلَّا لَئِنْ لَمْ يَنْتَهِ لَنَسْفَعًا بِالنَّاصِيَةِ

ይታቀብ፤ የማይከለከል ከሆነ በእርግጥ አናቱን ይዘን እንጎትተዋለን።

نَاصِيَةٍ كَاذِبَةٍ خَاطِئَةٍ

ያቺን ውሸታምና ስህተተኛ የሆነችውን አናቱን።

فَلْيَدْعُ نَادِيَهُ

ሸንጎውንም ይጥራ፤

سَنَدْعُ الزَّبَانِيَةَ

እኛም ዘበኞቻችንን እንጠራለን።

كَلَّا لَا تُطِعْهُ وَاسْجُدْ وَاقْتَرِبْ ۩

በጭራሽ፤ (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህን ለሚል ከሓዲ አትታዘዘው፤ ስገድ፤ ወደ አላህም ተቃረብ።