Decree · al-Qadr · سورة القدر · 5 ayahs

القرآن الكريمAfrica Academy

بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።

إِنَّا أَنْزَلْنَاهُ فِي لَيْلَةِ الْقَدْرِ

እኛ (ቁርኣንን) በመወሰኛይቱ ሌሊት ውስጥ አወረድነው።

وَمَا أَدْرَاكَ مَا لَيْلَةُ الْقَدْرِ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የመወሰኛይቱ ሌሊት ምን እንደሆነች ምን አሳወቀህ?

لَيْلَةُ الْقَدْرِ خَيْرٌ مِنْ أَلْفِ شَهْرٍ

የመወሰኛይቱ ሌሊት ከሺህ ወር የምትበልጥ ነች።

تَنَزَّلُ الْمَلَائِكَةُ وَالرُّوحُ فِيهَا بِإِذْنِ رَبِّهِمْ مِنْ كُلِّ أَمْرٍ

በእርሷ ውስጥ መላዕክትና ሩሕም (ጂብሪል) በጌታቸው ፈቃድ በሁሉም ጉዳዮች ይዘው ይወርዳሉ።

سَلَامٌ هِيَ حَتَّىٰ مَطْلَعِ الْفَجْرِ

እርሷም ጎህ እስኪወጣ ድረስ ሰላም ነች።