(ምርመራውን) ከወንድሙም ዕቃ በፊት በዕቃዎቻቸው ጀመረ፡፡ ከዚያም (ዋንጫይቱን) ከወንድሙ ዕቃ ውስጥ አወጣት፡፡ እንደዚሁ ለዩሱፍ ብልሃትን አስተማርነው፡፡ አላህ ባልሻ ኖሮ በንጉሡ ሕግ ወንድሙን ሊይዝ አይገባውም ነበር፡፡ የምንሻውን ሰው በደረጃዎች ከፍ እናደርጋለን፡፡ ከዕውቀት ባለቤቶች ሁሉ በላይም ዐዋቂ አልለ፡፡
Yusuf 12:76
Compare 2 Amharic translations
فَبَدَأَ بِأَوْعِيَتِهِمْ قَبْلَ وِعَاءِ أَخِيهِ ثُمَّ اسْتَخْرَجَهَا مِنْ وِعَاءِ أَخِيهِ ۚ كَذَٰلِكَ كِدْنَا لِيُوسُفَ ۖ مَا كَانَ لِيَأْخُذَ أَخَاهُ فِي دِينِ الْمَلِكِ إِلَّا أَنْ يَشَاءَ اللَّهُ ۚ نَرْفَعُ دَرَجَاتٍ مَنْ نَشَاءُ ۗ وَفَوْقَ كُلِّ ذِي عِلْمٍ عَلِيمٌ
DragHold to move · × to hide
ምርመራውን ከወንድሙ እቃ በፊትም በእቃዎቻቸው ጀመረ። ከዚያ ዋንጫይቱን ከወንድሙ እቃ ውስጥ አወጣት። ልክ እንደዚሁ ለዩሱፍ ዘዴ ዘየድንለት። አላህ ባይሻ ኖሮ በንጉሱ ሕግ ወንድሙን ሊይዝ አይገባዉም ነበር። የምንሻውን ሰው በደረጃዎች ከፍ እናደርጋለን። ከእውቀት ባለቤቶች ሁሉ በላይም አዋቂ አለ።