Ar-Ra'd 13:17

Compare 2 Amharic translations

أَنْزَلَ مِنَ السَّمَاءِ مَاءً فَسَالَتْ أَوْدِيَةٌ بِقَدَرِهَا فَاحْتَمَلَ السَّيْلُ زَبَدًا رَابِيًا ۚ وَمِمَّا يُوقِدُونَ عَلَيْهِ فِي النَّارِ ابْتِغَاءَ حِلْيَةٍ أَوْ مَتَاعٍ زَبَدٌ مِثْلُهُ ۚ كَذَٰلِكَ يَضْرِبُ اللَّهُ الْحَقَّ وَالْبَاطِلَ ۚ فَأَمَّا الزَّبَدُ فَيَذْهَبُ جُفَاءً ۖ وَأَمَّا مَا يَنْفَعُ النَّاسَ فَيَمْكُثُ فِي الْأَرْضِ ۚ كَذَٰلِكَ يَضْرِبُ اللَّهُ الْأَمْثَالَ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

ከሰማይ ውሃን አወረደ፡፡ ሸለቆዎቹም በመጠናቸው ፈሰሱ፡፡ ጎርፉም አሰፋፊውን ኮረፋት ተሸከመ፡፡ ለጌጥ ወይም ለዕቃ ፍላጎት በእርሱ ላይ እሳት የሚያነዱበትም (ማዕድን) ብጤው የኾነ ኮረፋት አልለው፡፡ እንደዚሁ አላህ ለእውነትና ለውሸት ምሳሌን ያደርጋል፡፡ ኮረፋቱማ ግብስብስ ኾኖ ይጠፋል፡፡ ለሰዎች የሚጠቅመውማ በምድር ላይ ይቆያል፡፡ እንደዚሁ አላህ ምሳሌዎችን ይገልፃል፡፡

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

ከሰማይ ውሃን አወረደ። ሸለቆዎቹም በየመጠናቸው ፈሰሱ። ጎርፉም አስፋሪውን የውሃ አረፋ ተሸከመ። ለጌጥ ወይም ለዕቃ ፍላጎት በእርሱ ላይ እሳት የሚያነዱበትም ማዕድን ብጤው የሆነ ኮረፋት አለው። ልክ እንደዚሁ አላህ ለእውነትና ለውሸት ምሳሌን ያደርጋል። የውሃ አረፋዉም ግብስብስ ሆኖ ይጠፋል። ለሰዎች የሚጠቅመውማ በምድር ላይ ይቆያል። ልክ እንደዚሁ አላህ ምሳሌዎችን ይገልጻል።

Africa Academy