እርሱ በነፍስ ሁሉ ላይ በሠራቸው ሥራ ተጠባባቂ የኾነው (አላህ እንደዚህ እንዳልኾነው ጣዖት ብጤ ነውን?) (አይደለም)። ለአላህም ተጋሪዎችን አደረጉ፡፡ ጥሯቸው «አላህን በምድር ውስጥ የማያውቀው ኖሮ ትነግሩታላችሁን? ወይስ ከቃል በግልጽ (ፍቺ በሌለው ከንቱ ቃል ተጋሪዎች በማለት ትጠሩዋቸዋላችሁን?)» በላቸው፡፡ በእውነቱ ለእነዚያ ለካዱት ተንኮላቸው ተሸለመላቸው፡፡ ከእውነቱ መንገድም ታገዱ፡፡ አላህም ያጠመመው ሰው ለእርሱ ምንም አቅኚ የለውም፡፡
Ar-Ra'd 13:33
Compare 2 Amharic translations
أَفَمَنْ هُوَ قَائِمٌ عَلَىٰ كُلِّ نَفْسٍ بِمَا كَسَبَتْ ۗ وَجَعَلُوا لِلَّهِ شُرَكَاءَ قُلْ سَمُّوهُمْ ۚ أَمْ تُنَبِّئُونَهُ بِمَا لَا يَعْلَمُ فِي الْأَرْضِ أَمْ بِظَاهِرٍ مِنَ الْقَوْلِ ۗ بَلْ زُيِّنَ لِلَّذِينَ كَفَرُوا مَكْرُهُمْ وَصُدُّوا عَنِ السَّبِيلِ ۗ وَمَنْ يُضْلِلِ اللَّهُ فَمَا لَهُ مِنْ هَادٍ
DragHold to move · × to hide
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ነፍስ ሁሉ በሰራችው ሥራ ላይ ተጠባባቂ የሆነው አላህም እንደዚህ እንዳልሆነው ጣዖት ብጤ ነውን? ለአላህ ተጋሪዎችን አደረጉ። «ጥሯቸው። አላህን በምድር ውስጥ የማያውቀው ነገር ኖሮ ትነግሩታላችሁን? ወይስ ከቃል በቀጥታ ፍቺ በሌለው ከንቱ ቃል ተጋሪዎቹ በማለት ትጠሯቸዋላችሁን?» በላቸው። በእውነቱ ለእነዚያ ለካዱት ተንኮላቸው ተሸለመላቸው። ከእውነቱ መንገድም ታገዱ። አላህ ያጠመመውንም ምንም አቅኚ የለዉም።