Al-Baqarah 2:114

Compare 2 Amharic translations

وَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّنْ مَنَعَ مَسَاجِدَ اللَّهِ أَنْ يُذْكَرَ فِيهَا اسْمُهُ وَسَعَىٰ فِي خَرَابِهَا ۚ أُولَٰئِكَ مَا كَانَ لَهُمْ أَنْ يَدْخُلُوهَا إِلَّا خَائِفِينَ ۚ لَهُمْ فِي الدُّنْيَا خِزْيٌ وَلَهُمْ فِي الْآخِرَةِ عَذَابٌ عَظِيمٌ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

የአላህንም መስጊዶች በውስጣቸው ስሙ እንዳይወሳ ከከለከለና እርሷንም በማበላሸት ከሮጠ ሰው ይበልጥ በዳይ ማነው? እነዚያ ፈሪዎች ኾነው እንጂ እርሷን መግባት አይገባቸውም። ለእነርሱ በቅርቢቱ ዓለም ውርደት አላቸው፡፡ ለነርሱም በመጨረሻይቱ አገር ታላቅ ቅጣት አላቸው፡፡

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

የአላህን መስጊዶች በውስጣቸው ስሙ እንዳይወሳበት ከከለከለና እርሷን (መስጊዶችን) ለማበላሸት ከጣረ ይበልጥ ድንበር አላፊ (አጥፊ) ማን ነው? እነዚያ በፍርሃት ተውጠው እንጂ ወደ መስጊዶች ሊገቡ አይገባቸዉም። ለነርሱም በቅርቢቱ ዓለም ውርደት አለባቸው። በመጨረሻይቱ ሀገርም ታላቅ ቅጣት አለባቸው።

Africa Academy