Al-Baqarah 2:158

Compare 2 Amharic translations

إِنَّ الصَّفَا وَالْمَرْوَةَ مِنْ شَعَائِرِ اللَّهِ ۖ فَمَنْ حَجَّ الْبَيْتَ أَوِ اعْتَمَرَ فَلَا جُنَاحَ عَلَيْهِ أَنْ يَطَّوَّفَ بِهِمَا ۚ وَمَنْ تَطَوَّعَ خَيْرًا فَإِنَّ اللَّهَ شَاكِرٌ عَلِيمٌ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

ሶፋና መርዋ ከአላህ (ትዕዛዝ መፈጸሚያ) ምልክቶች ናቸው፡፡ ቤቱን (ካዕባን) በሐጅ ወይም በዑምራህ ሥራ የጎበኘ ሰው በሁለቱ (መካከል) በመመላለሱ በርሱ ላይ ኃጢአት የለበትም፡፡ መልካምንም ሥራ በፈቃደኛነት የሠራ ሰው (አላህ ይመነዳዋል)፤ አላህ አመስጋኝ ዐዋቂ ነውና፡፡

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

የሶፋና የመርዋ (ጋራዎች) የአላህን ትዕዛዝ ከመፈጸሚያ ጉልህ ቦታዎች (ምልክቶች) ናቸው። (ካዕባን) በሐጅ ወይም በዑምራ ስራ ምክኒያት የጎበኘ በሁለቱ ጋራዎች መካከል በመመላለሱ ምንም ኃጢአት የለበትም። መልካምንም ስራ በፈቃደኝነት የሰራ (አላህ ይመነዳዋል)። አላህ አመስጋኝና ሁሉን አዋቂ ነውና።

Africa Academy