ሰዎቹ ሁሉ አንድ ሕዝብ ነበሩ፤ (ተለያዩ)፡፡ አላህም ነቢያትን አብሳሪዎችና አስፈራሪዎች አድርጎ ላከ፡፡ ከእነርሱም ጋር መጻሕፍትን በሰዎቹ መካከል በዚያ በርሱ በተለያዩበት ነገር ይፈርድ ዘንድ በእውነት አወረደ፡፡ በእርሱም (በሃይማኖት) ግልጽ አስረጂዎች ከመጡላቸው በኋላ በመካከላቸው ለኾነው ምቀኝነት እነዚያው የተሰጡት እንጂ አልተለያዩበትም፡፡ አላህም እነዚያን ያመኑትን ሰዎች ለእዚያ ከእውነት በርሱ ለተለያዩበት በፍቃዱ መራቸው፡፡ አላህም የሚሻውን ሰው ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመራል፡፡
Al-Baqarah 2:213
Compare 2 Amharic translations
كَانَ النَّاسُ أُمَّةً وَاحِدَةً فَبَعَثَ اللَّهُ النَّبِيِّينَ مُبَشِّرِينَ وَمُنْذِرِينَ وَأَنْزَلَ مَعَهُمُ الْكِتَابَ بِالْحَقِّ لِيَحْكُمَ بَيْنَ النَّاسِ فِيمَا اخْتَلَفُوا فِيهِ ۚ وَمَا اخْتَلَفَ فِيهِ إِلَّا الَّذِينَ أُوتُوهُ مِنْ بَعْدِ مَا جَاءَتْهُمُ الْبَيِّنَاتُ بَغْيًا بَيْنَهُمْ ۖ فَهَدَى اللَّهُ الَّذِينَ آمَنُوا لِمَا اخْتَلَفُوا فِيهِ مِنَ الْحَقِّ بِإِذْنِهِ ۗ وَاللَّهُ يَهْدِي مَنْ يَشَاءُ إِلَىٰ صِرَاطٍ مُسْتَقِيمٍ
DragHold to move · × to hide
ሰዎች ሁሉ (አላህን አንድ በማድረግ) አንድ ሕዝብ ነበሩ። (ከዚያም ተለያዩ)። ከዚያም አላህ ነብያትን ለመልካም ሰዎች በገነት አብሳሪዎችና ለመጥፎ ሰዎች ደግሞ ከእሳት አስጠንቃቂዎች አድርጎ ላከ። ከነሱ ጋርም ከሰዎቹ መካከል በዚያ እነርሱ በተለያዩበት ነገር ይፈርድ ዘንድ መጽሐፍትን በእውነት አወረደ። በእርሱ ግልጽ አስረጂዎች ከመጡላቸው በኋላ በመካከላቸው በተፈጠረው ምቀኝነት ሰበብ እነዚያው መጽሐፍትን የተሰጡት ሰዎች እንጂ አልተለያዩበትም። አላህ እነዚያን በአላህ ያመኑትን ሰዎች በእነርሱ የተለያዩበትን እውነታ ይገነዘቡ ዘንድ በፈቃዱ መራቸው። አላህ የሚሻውን ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመራል።