Al-Baqarah 2:214

Compare 2 Amharic translations

أَمْ حَسِبْتُمْ أَنْ تَدْخُلُوا الْجَنَّةَ وَلَمَّا يَأْتِكُمْ مَثَلُ الَّذِينَ خَلَوْا مِنْ قَبْلِكُمْ ۖ مَسَّتْهُمُ الْبَأْسَاءُ وَالضَّرَّاءُ وَزُلْزِلُوا حَتَّىٰ يَقُولَ الرَّسُولُ وَالَّذِينَ آمَنُوا مَعَهُ مَتَىٰ نَصْرُ اللَّهِ ۗ أَلَا إِنَّ نَصْرَ اللَّهِ قَرِيبٌ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

በእውነቱ የእነዚያ ከበፊታችሁ ያለፉት (ምእምናን መከራ) ብጤ ሳይመጣችሁ ገነትን ልትገቡ ታስባላችሁን? መልክተኛውና እነዚያ ከርሱ ጋር ያመኑት «የአላህ እርዳታ መቼ ነው?» እስከሚሉ ድረስ መከራና ጉዳት ነካቻቸው፤ ተርበደበዱም፡፡ ንቁ! የአላህ እርዳታ በእርግጥ ቅርብ ነው (ተባሉም)፡፡

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

(እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) በእውነቱ የእነዚያ ከበፊታችሁ ያለፉት (አማኞችን) ያጋጠመ መከራ የመሰለ ሳይመጣባችሁ ገነትን ልትገቡ ታስባላችሁን? መልዕክተኛውና እነዚያ ከእርሱ ጋር ያመኑት «የአላህ እርዳታ መቼ ነው?» እስከሚሉ ድረስ መከራና ጉዳት ደረሰባቸው። ተርበደበዱም።(ለእነርሱም) «አስተውሉ! የአላህ እርዳታ በእርግጥ ቅርብ ነው» (ተባሉ)።

Africa Academy