በቅርቢቱ ዓለምና በመጨረሻይቱ ታስተነትኑ ዘንድ (ይገለጽላችኋል)፡፡ ከየቲሞችም ይጠይቁሃል፡፡ «ለእነርሱ (ገንዘባቸውን በማራባት) ማሳመር በላጭ ነው፡፡ ብትቀላቀሏቸውም ወንድሞቻችሁ ናቸው፡፡ አላህም የሚያጠፋውን ከሚያበጀው (ለይቶ) ያውቃል፡፡ አላህም በሻ ኖሮ ባስቸገራችሁ ነበር፤ አላህ አሸናፊ ጥበበኛ ነውና» በላቸው፡፡
Al-Baqarah 2:220
Compare 2 Amharic translations
فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ ۗ وَيَسْأَلُونَكَ عَنِ الْيَتَامَىٰ ۖ قُلْ إِصْلَاحٌ لَهُمْ خَيْرٌ ۖ وَإِنْ تُخَالِطُوهُمْ فَإِخْوَانُكُمْ ۚ وَاللَّهُ يَعْلَمُ الْمُفْسِدَ مِنَ الْمُصْلِحِ ۚ وَلَوْ شَاءَ اللَّهُ لَأَعْنَتَكُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٌ
DragHold to move · × to hide
በዱኒያም በአኼራም (ታስተነትኑ ዘንድ ይገልፅላችኋል)። (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ስለየቲሞችም ይጠይቁሀል። «የእነርሱን ሁኔታ ማሻሻል በላጭ ነው። (ጉዳያቸውን) ከናንተ ጋር ብትቀላቅሉም ወንድሞቻችሁ ናቸው። አላህም አጥፊውን ከአልሚው ለይቶ ያውቃል። አላህም በፈለገ ኖሮ መፈናፈኛ ያሳጣችሁ (ባስቸገራችሁ) ነበር። አላህ አሸናፊና ጥበበኛ ነው።» በላቸው።