(በአላህ) አጋሪ የሆኑ ሴቶች እስከሚያምኑ ድረስ አታግቡዋቸው፡፡ ከአጋሪይቱ ምንም ብትደንቃችሁም እንኳ ያመነችው ባሪያ በእርግጥ በላጭ ናት፡፡ ለአጋሪዎቹም እስከሚያምኑ ድረስ አትዳሩላቸው፡፡ ከአጋሪው (ጌታ) ምንም ቢደንቃችሁ ምእምኑ ባሪያ በላጭ ነው፡፡ እነዚያ (አጋሪዎች) ወደ እሳት ይጣራሉ፡፡ አላህም በፈቃዱ ወደ ገነትና ወደ ምሕረት ይጠራል፡፡ ሕግጋቱንም ለሰዎች ይገልጻል እነርሱ ሊገሰጹ ይከጀላልና፡፡
Al-Baqarah 2:221
Compare 2 Amharic translations
وَلَا تَنْكِحُوا الْمُشْرِكَاتِ حَتَّىٰ يُؤْمِنَّ ۚ وَلَأَمَةٌ مُؤْمِنَةٌ خَيْرٌ مِنْ مُشْرِكَةٍ وَلَوْ أَعْجَبَتْكُمْ ۗ وَلَا تُنْكِحُوا الْمُشْرِكِينَ حَتَّىٰ يُؤْمِنُوا ۚ وَلَعَبْدٌ مُؤْمِنٌ خَيْرٌ مِنْ مُشْرِكٍ وَلَوْ أَعْجَبَكُمْ ۗ أُولَٰئِكَ يَدْعُونَ إِلَى النَّارِ ۖ وَاللَّهُ يَدْعُو إِلَى الْجَنَّةِ وَالْمَغْفِرَةِ بِإِذْنِهِ ۖ وَيُبَيِّنُ آيَاتِهِ لِلنَّاسِ لَعَلَّهُمْ يَتَذَكَّرُونَ
DragHold to move · × to hide
(ሙስሊሞች ሆይ!) አጋሪዎችን ሴቶችን በአላህ እስከሚያምኑ ድረስ አታግቧቸው። አጋሪይቱ ነፃ ሴት ምንም ብትስባችሁ እንኳ ያመነችው ባሪያ ሴት በእርግጥ ለእናንተ በላጭ ናት። ለአጋሪዎቹ እስከሚያምኑ ድረስ አትዳሩላቸው። ከአጋሪ ወንድ ምንም ቢስባችሁ አማኝ ባሪያ ወንድ ለእናንተ በላጭ ነው። እነዚያ አጋሪዎች ወደ እሳት ይጠራሉ። አላህ ደግሞ በፈቃዱ ወደ ገነትና ወደ ምህረት ይጠራል። ህግጋቱንም ለሰዎች ሊገሰጹ ዘንድ ይገልፅላቸዋል።