ፍች ሁለት ጊዜ ነው፤ (ከዚህ በኋላ) በመልካም መያዝ ወይም በበጎ አኳኋን ማሰናበት ነው፡፡ የአላህንም ሕግጋት አለመጠበቃቸውን ካላወቁ በስተቀር ከሰጣችኃቸው ነገር ምንንም ልትወስዱ ለእናንተ (ለባሎች) አይፈቀድላችሁም፡፡ የአላህንም ሕግጋት አለመጠበቃቸውን ብታውቁ በእርሱ (ነፍሷን) በተበዠችበት ነገር በሁለቱም ላይ ኃጢኣት የለም፡፡ ይህች የአላህ ሕግጋት ናት፤ አትተላለፏትም፡፡ የአላህንም ሕግጋት የሚተላለፉ እነዚያ እነርሱ በዳዮች ናቸው፡፡
Al-Baqarah 2:229
Compare 2 Amharic translations
الطَّلَاقُ مَرَّتَانِ ۖ فَإِمْسَاكٌ بِمَعْرُوفٍ أَوْ تَسْرِيحٌ بِإِحْسَانٍ ۗ وَلَا يَحِلُّ لَكُمْ أَنْ تَأْخُذُوا مِمَّا آتَيْتُمُوهُنَّ شَيْئًا إِلَّا أَنْ يَخَافَا أَلَّا يُقِيمَا حُدُودَ اللَّهِ ۖ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا يُقِيمَا حُدُودَ اللَّهِ فَلَا جُنَاحَ عَلَيْهِمَا فِيمَا افْتَدَتْ بِهِ ۗ تِلْكَ حُدُودُ اللَّهِ فَلَا تَعْتَدُوهَا ۚ وَمَنْ يَتَعَدَّ حُدُودَ اللَّهِ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الظَّالِمُونَ
DragHold to move · × to hide
(የመመለስ እድል የሚሰጠው) ፍቺ ሁለት ጊዜ ብቻ ነው። ከዚያም በመልካም መያዝ ወይም በበጎ አኳኋን ማሰናበት ነው። (ባሎች ሆይ!) የአላህን ህግጋት ያለማክበር ስጋት ካልኖረባቸው በስተቀር ከሰጣችኋቸው ነገር ምንንም ልትወስዱ ለእናንተ አይፈቀድላችሁም። የአላህን ሕግጋት አለመጠበቃቸውን ብትፈሩ ራሷን ነፃ ለማውጣት በምትሰጠው ነገር በሁለቱም ላይ ኃጢአት የለባቸዉም። እኒህ የአላህ ሕግጋት ናቸው። አትተላለፏቸው። እነዚያ እነርሱ የአላህን ሕግጋት የሚተላለፉ ሁሉ (በደለኞች) አጥፊዎች ናቸው።