Al-Baqarah 2:232

Compare 2 Amharic translations

وَإِذَا طَلَّقْتُمُ النِّسَاءَ فَبَلَغْنَ أَجَلَهُنَّ فَلَا تَعْضُلُوهُنَّ أَنْ يَنْكِحْنَ أَزْوَاجَهُنَّ إِذَا تَرَاضَوْا بَيْنَهُمْ بِالْمَعْرُوفِ ۗ ذَٰلِكَ يُوعَظُ بِهِ مَنْ كَانَ مِنْكُمْ يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ ۗ ذَٰلِكُمْ أَزْكَىٰ لَكُمْ وَأَطْهَرُ ۗ وَاللَّهُ يَعْلَمُ وَأَنْتُمْ لَا تَعْلَمُونَ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

ሴቶችንም በፈታችሁና ጊዜያቸውን በደረሱ ጊዜ በመካከላቸው በሕግ በተዋደዱ ጊዜ ባሎቻቸውን ከማግባት አታስተጓጉሏቸው፡፡ ይህ (መከልከል) ከእናንተ በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን ሰው በርሱ ይገሰጽበታል፡፡ ይህ ሁኔታችሁ ለእናንተ በላጭ ነው፤ (ከመጠርጠር) አጥሪም ነው፡፡ አላህም ያውቃል፤ እናንተ ግን አታውቁም፡፡

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

ሚስቶቻችሁን በፈታችሁ እና የኢዳ ጊዜያቸውን በጨረሱ ጊዜ ጥንዶቹ በመካከላቸው ሕጋዊና ፍትሀዊ የጋራ ስምምነት ላይ ከደረሱ ባሎቻቸውን ከማግባት አታስተጓጉሏቸው። ይህ ከናንተ መካከል በአላህና በመጨረሻ ቀን የሚያምን ሁሉ ይገሰጽበታል። ይህ ለእናንተ በላጭና አጥሪ ነው። አላህ ያውቃል። እናንተ ግን አታውቁም።

Africa Academy