Al-Baqarah 2:233

Compare 2 Amharic translations

وَالْوَالِدَاتُ يُرْضِعْنَ أَوْلَادَهُنَّ حَوْلَيْنِ كَامِلَيْنِ ۖ لِمَنْ أَرَادَ أَنْ يُتِمَّ الرَّضَاعَةَ ۚ وَعَلَى الْمَوْلُودِ لَهُ رِزْقُهُنَّ وَكِسْوَتُهُنَّ بِالْمَعْرُوفِ ۚ لَا تُكَلَّفُ نَفْسٌ إِلَّا وُسْعَهَا ۚ لَا تُضَارَّ وَالِدَةٌ بِوَلَدِهَا وَلَا مَوْلُودٌ لَهُ بِوَلَدِهِ ۚ وَعَلَى الْوَارِثِ مِثْلُ ذَٰلِكَ ۗ فَإِنْ أَرَادَا فِصَالًا عَنْ تَرَاضٍ مِنْهُمَا وَتَشَاوُرٍ فَلَا جُنَاحَ عَلَيْهِمَا ۗ وَإِنْ أَرَدْتُمْ أَنْ تَسْتَرْضِعُوا أَوْلَادَكُمْ فَلَا جُنَاحَ عَلَيْكُمْ إِذَا سَلَّمْتُمْ مَا آتَيْتُمْ بِالْمَعْرُوفِ ۗ وَاتَّقُوا اللَّهَ وَاعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

እናቶችም ልጆቻቸውን ሙሉ የኾኑን ሁለት ዓመታት ያጥቡ፡፡ (ይህም) ማጥባትን መሙላት ለሻ ሰው ነው፡፡ ለእርሱም በተወለደለት (አባት) ላይ ምግባቸውና ልብሳቸው በችሎታው ልክ አለበት፡፡ ነፍስ ችሎታዋን እንጂ አትገደድም፡፡ ወላጂት (እናት) በልጅዋ ምክንያት ለርሱ የተወለደለትም (አባት) በልጁ ምክንያት አይጎዳዱ፡፡ በወራሽም ላይ እንደዚሁ ብጤ አለበት፡፡ (ወላጆቹ) ከሁለቱም በኾነ መዋደድና መመካከር (ልጁን ከጡት) መነጠልን ቢፈልጉ በሁለቱም ላይ ኃጢኣት የለባቸውም፡፡ ልጆቻችሁንም ለሌሎች አጥቢዎች ማስጠባትን ብትፈልጉ ልትሰጡ የሻችሁትን በመልካም ኹኔታ በሰጣችሁ ጊዜ (በማስጠባታችሁ) በእናንተ ላይ ኃጢኣት የለባችሁም፡፡ አላህንም ፍሩ፤ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች መኾኑን ዕወቁ፡፡

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

እናቶች ልጆቻቸውን ሁለት ሙሉ ዓመታትን ያጠባሉ። ይህም ማጥባትን የተሟላ ለማድረግ ለፈለገ ሰው ነው። በአባት ላይ ምግባቸውንና ልብሳቸውን በአግባቡ የማቅረብ ግዴታ አለበት። ማንም ነፍስ ከችሎታዋ በላይ አትገደድምና። እናት በልጇ ምክኒያት ጉዳት እንዲደርስባት አይደረግም። አባትም በልጁ ምክንያት እንዲንገላታ መሆን የለበትም። በወራሽም ላይ የዚሁ ተመሳሳይ ሀላፊነት አለበት። ወላጆቹ በመልካም ፈቃድ ልጁን ከጡት መነጠል (ማስጣል) ቢፈልጉ በሁለቱም መማከር በሁለቱም ላይ ኃጢአት የለባቸዉም። ለልጆቻችሁ አጥቢዎችን ብትቀጥሩ ተስፋ የሰጣችሁትን ክፍያ በአግባቡ እስከሰጣችሁ ድረስ በማስጠባታችሁ በእናንተ ላይ ምንም ኃጢአት የለባችሁም። አላህን ፍሩ። አላህ የምትሰሩትን ነገር ሁሉ ተመልካች መሆኑን እወቁ።

Africa Academy