ከእስራኤል ልጆች ከሙሳ በኋላ ወደ ነበሩት ጭፍሮች ለነቢያቸው (ለሳሙኤል)፡- «ለእኛ ንጉሥን አስነሳልን በአላህ መንገድ እንዋጋለን፤» ባሉ ጊዜ አላየህምን? (አላወቅህምን?)፡-«መዋጋት ቢጻፍባችሁ አትዋጉም ይኾናል» አላቸው፡፡ «ከሀገሮቻችንና ከልጆቻችን የተባረርን ስንኾን በአላህ መንገድ የማንዋጋ ለእኛ ምን አለን?» አሉ፡፡ በእነርሱ ላይ መዋጋት በተጻፈባቸውም ጊዜ ከእነርሱ ጥቂቶች ሲቀሩ አፈገፈጉ፡፡ አላህም በዳዮቹን ዐዋቂ ነው፡፡
Al-Baqarah 2:246
Compare 2 Amharic translations
أَلَمْ تَرَ إِلَى الْمَلَإِ مِنْ بَنِي إِسْرَائِيلَ مِنْ بَعْدِ مُوسَىٰ إِذْ قَالُوا لِنَبِيٍّ لَهُمُ ابْعَثْ لَنَا مَلِكًا نُقَاتِلْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ ۖ قَالَ هَلْ عَسَيْتُمْ إِنْ كُتِبَ عَلَيْكُمُ الْقِتَالُ أَلَّا تُقَاتِلُوا ۖ قَالُوا وَمَا لَنَا أَلَّا نُقَاتِلَ فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَقَدْ أُخْرِجْنَا مِنْ دِيَارِنَا وَأَبْنَائِنَا ۖ فَلَمَّا كُتِبَ عَلَيْهِمُ الْقِتَالُ تَوَلَّوْا إِلَّا قَلِيلًا مِنْهُمْ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ بِالظَّالِمِينَ
DragHold to move · × to hide
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከኢስራኢል ልጆች ከሙሳ ዘመን በኋላ ወደ ነበሩት የኢስራኢል ልጆች ታላላቆች (መሪዎች) ተልኮላቸው ለነበረው ለነብያቸው «ለእኛ ንጉስን ሹምልን እና በአላህ መንገድ እንዋጋ።» ባሉ ጊዜ የሆነውን አላየህምን? እሱም «መዋጋት ቢፃፍባችሁ አትዋጉ ይሆናል።» አላቸው። እነርሱም «ከአገሮቻችንና ከልጆቻችን ተባረን ሳለ በአላህ መንገድ የማንዋጋበት ምን ምክንያት አለን?» አሉ። በእነርሱ ላይ መዋጋት በተፃፈባቸው ጊዜ ግን ከእነርሱ ጥቂቶች ሲቀሩ ከመዋጋት አፈገፈጉ። አላህ አጥፊዎችን ሁሉ በሚገባ ያውቃቸዋል።