Al-Baqarah 2:247

Compare 2 Amharic translations

وَقَالَ لَهُمْ نَبِيُّهُمْ إِنَّ اللَّهَ قَدْ بَعَثَ لَكُمْ طَالُوتَ مَلِكًا ۚ قَالُوا أَنَّىٰ يَكُونُ لَهُ الْمُلْكُ عَلَيْنَا وَنَحْنُ أَحَقُّ بِالْمُلْكِ مِنْهُ وَلَمْ يُؤْتَ سَعَةً مِنَ الْمَالِ ۚ قَالَ إِنَّ اللَّهَ اصْطَفَاهُ عَلَيْكُمْ وَزَادَهُ بَسْطَةً فِي الْعِلْمِ وَالْجِسْمِ ۖ وَاللَّهُ يُؤْتِي مُلْكَهُ مَنْ يَشَاءُ ۚ وَاللَّهُ وَاسِعٌ عَلِيمٌ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

ነቢያቸውም ለእነርሱ፡- «አላህ ጧሉትን (ሳኦልን) ንጉሥ አድርጎ በእርግጥ ላከላችሁ» አላቸው፡፡ (እነርሱም)፡- «እኛ ከእርሱ ይልቅ በንግሥና ተገቢዎች ስንኾን ከሀብትም ስፋትን ያልተሰጠ ሲኾን ለእርሱ በኛ ላይ እንዴት ንግሥና ይኖረዋል?» አሉ፡፡ (ነቢያቸውም)፡-«አላህ በእናንተ ላይ መረጠው፡፡ በዕውቀትና በአካልም ስፋትን ጨመረለት፡፡ አላህም ንግሥናውን ለሚሻው ሰው ይሰጣል፡፡ አላህም ችሮታው ሰፊ ዐዋቂ ነው» አላቸው፡፡

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

ነብያቸው ‹‹አላህ ጧሉትን ንጉስ አድርጎ በእርግጥ ላከላችሁ›› አላቸው። እነርሱም፡- «ሰፊ ሀብትም ያልተሰጠ እኛም ከእርሱ ይልቅ ለንግስና ተገቢዎች ስንሆን እርሱ በእኛ ላይ እንዴት ይነግሣል?» አሉ። ነብያቸዉም፡- «አላህ በእናንተ ላይ መረጠው እውቀትና የሰውነት ጥንካሬም አጎናጽፎታል። አላህ ንግስናውን ለሚሻለት ሰው ይሰጣል። አላህ ችሮታው ሰፊና አዋቂ ነው።» አላቸው።

Africa Academy