Al-Baqarah 2:257

Compare 2 Amharic translations

اللَّهُ وَلِيُّ الَّذِينَ آمَنُوا يُخْرِجُهُمْ مِنَ الظُّلُمَاتِ إِلَى النُّورِ ۖ وَالَّذِينَ كَفَرُوا أَوْلِيَاؤُهُمُ الطَّاغُوتُ يُخْرِجُونَهُمْ مِنَ النُّورِ إِلَى الظُّلُمَاتِ ۗ أُولَٰئِكَ أَصْحَابُ النَّارِ ۖ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

አላህ የእነዚያ ያመኑት ሰዎች ረዳት ነው፡፡ ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ያወጣቸዋል፡፡ እነዚያ የካዱት ረዳቶቻቸው ጣዖታት ናቸው፡፡ ከብርሃን ወደ ጨለማዎች ያወጧቸዋል፡፡ እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው፤ እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

አላህ የአማኞች ወዳጅ ነው። ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ብርሃን ያወጣቸዋል። እነዚያ አላህን የካዱት ግን ረዳቶቻቸው ጣኦታት ናቸው። ከብርሃን ወደ ጨለማ ይመሯቸዋል። እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው። እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው።

Africa Academy