Al-Baqarah 2:258

Compare 2 Amharic translations

أَلَمْ تَرَ إِلَى الَّذِي حَاجَّ إِبْرَاهِيمَ فِي رَبِّهِ أَنْ آتَاهُ اللَّهُ الْمُلْكَ إِذْ قَالَ إِبْرَاهِيمُ رَبِّيَ الَّذِي يُحْيِي وَيُمِيتُ قَالَ أَنَا أُحْيِي وَأُمِيتُ ۖ قَالَ إِبْرَاهِيمُ فَإِنَّ اللَّهَ يَأْتِي بِالشَّمْسِ مِنَ الْمَشْرِقِ فَأْتِ بِهَا مِنَ الْمَغْرِبِ فَبُهِتَ الَّذِي كَفَرَ ۗ وَاللَّهُ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الظَّالِمِينَ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

ወደዚያ አላህ ንግሥናን ስለሰጠው ኢብራሂምን በጌታው ነገር ወደ ተከራከረው ሰው አላየህምን ኢብራሂም «ጌታዬ ያ ሕያው የሚያደርግና የሚገድል ነው» ባለ ጊዜ «እኔ ሕያው አደርጋለሁ እገድላለሁም» አለ፡፡ ኢብራሂም፡- «አላህ ፀሐይን ከምሥራቅ በኩል ያመጣል (አንተ) ከምዕራብ በኩል አምጣት» አለው፡፡ ያም የካደው ሰው ዋለለ፤ (መልስ አጣ) አላህ በዳዮች ሕዝቦችን አይመራም፡፡

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያንን አላህ ንግስናን ስለ ሰጠውና በጌታው ጉዳይ በኢብራሂም ላይ ክርክር ስለ ከፈተው ሰው (ታሪክ) መረጃ አላየህምን? ኢብራሂም፡-‹‹ጌታዬ ያ የፈለገውን ሕያው የሚያደርግና የፈለገውን የሚገድል ነው›› ሲለው «እኔም የፈለኩትን ህያው አደርጋለሁ፤ የፈለኩትን እገድላለሁ» አለ። ኢብራሂምም፡- «አላህ ጸሐይን በምስራቅ በኩል ያወጣል። እስኪ አንተ ከምዕራብ በኩል አምጣት» አለው። ያም የካደ ሰው ዋለለ (መልስ አጣ)። አላህ ግፈኛ ሕዝቦችን ሁሉ አይመራምና።

Africa Academy