Al-Baqarah 2:74

Compare 2 Amharic translations

ثُمَّ قَسَتْ قُلُوبُكُمْ مِنْ بَعْدِ ذَٰلِكَ فَهِيَ كَالْحِجَارَةِ أَوْ أَشَدُّ قَسْوَةً ۚ وَإِنَّ مِنَ الْحِجَارَةِ لَمَا يَتَفَجَّرُ مِنْهُ الْأَنْهَارُ ۚ وَإِنَّ مِنْهَا لَمَا يَشَّقَّقُ فَيَخْرُجُ مِنْهُ الْمَاءُ ۚ وَإِنَّ مِنْهَا لَمَا يَهْبِطُ مِنْ خَشْيَةِ اللَّهِ ۗ وَمَا اللَّهُ بِغَافِلٍ عَمَّا تَعْمَلُونَ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

ከዚያም ከዚህ በኋላ ልቦቻችሁ ደረቁ፤ እርሷም እንደ ድንጋዮች ወይም በድርቅና ይበልጥ የበረታች ናት፡፡ ከድንጋዮችም ከርሱ ጂረቶች የሚፈሱለት አልለ፡፡ ከነርሱም በእርግጥ የሚሰነጠቅና ከርሱ ውሃ (ምንጭ) የሚወጣው አልለ፡፡ ከነርሱም አላህን ከመፍራት የተነሳ ወደ ታች የሚወርድ አልለ፡፡ አላህም ከምትሠሩት ነገር ዘንጊ አይደለም፡፡

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

ከዚያም ልቦቻችሁ ከዚህ (ትዕይንት) በኋላ ደረቁ። እርሷም በድርቅና እንደ አለት ድንጋዮች ወይም ከእርሱ ይበልጥ የበረቱ ናቸው። ምክንያቱም ከድንጋዮች መካከል ጅረቶች (ወንዞች) የሚፈሱበት፤ ከእነርሱም የሚሰነጥቅና ከእርሱ ውሃ ምንጭ የሚወጣው፤ ከእነርሱም አላህን ከመፍራቱ የተነሳ ወደ ታች የሚወርድ አለና። አላህ ከምትሰሩት ነገር ሁሉ ከአንዱም ዘንጊ አይደለም።

Africa Academy