የእስራኤል ልጆችንም ጥብቅ ኪዳን አላህን እንጂ ሌላን አታምልኩ፤ በወላጆችም በጎን ሥራ (አድርጉ)፤ በዝምድና ባለቤቶችም፣ በየቲሞችም (አባት የሌላቸው ልጆች) በምስኪኖችም (በጎ ዋሉ)፤ ለሰዎችም መልካምን ተናገሩ፤ ሶላትንም ደንቡን ጠብቃችሁ ስገዱ፤ ዘካንም ስጡ በማለት በያዝንባቸው ጊዜ (አስታውሱ)፡፡ ከዚያም ከናንተ ጥቂቶች ሲቀሩ ሸሻችሁ እናንተም (ኪዳንን) የምትተዉ ናችሁ፡፡
Al-Baqarah 2:83
Compare 2 Amharic translations
وَإِذْ أَخَذْنَا مِيثَاقَ بَنِي إِسْرَائِيلَ لَا تَعْبُدُونَ إِلَّا اللَّهَ وَبِالْوَالِدَيْنِ إِحْسَانًا وَذِي الْقُرْبَىٰ وَالْيَتَامَىٰ وَالْمَسَاكِينِ وَقُولُوا لِلنَّاسِ حُسْنًا وَأَقِيمُوا الصَّلَاةَ وَآتُوا الزَّكَاةَ ثُمَّ تَوَلَّيْتُمْ إِلَّا قَلِيلًا مِنْكُمْ وَأَنْتُمْ مُعْرِضُونَ
DragHold to move · × to hide
(የኢስራኢል-ልጆችን) “አላህን እንጂ ሌላን አታምልኩ። ለወላጆችም በጎን ስራ ስሩ። ለዝምድና ባለቤቶች፤ ለየቲሞችና ለሚስኪኖችም በጎን ዋሉ። ለሰዎችም ሁሉ መልካምን ብቻ ተናገሩ ። ሶላትን ደንቡን ጠብቃችሁ ስገዱ። ዘካን ለተገቢው ስጡ” በማለት ጥብቅ ቃልኪዳን በያዝንባቸው ጊዜ (የሆነውን አስታውሱ)። ከዚያም ከእናንተ ጥቂቶቹ ሲቀሩ ሸሻችሁ። እናንተ (ቃልኪዳንንም) የምትተው ናችሁ።