ሙሳንም መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው፡፡ ከበኋላውም መልክትኞችን አስከታተልን፡፡ የመርየምን ልጅ ዒሳንም ግልጽ ታምራቶችን ሰጠነው፡፡ በቅዱሱ መንፈስም አበረታነው፡፡ ነፍሶቻችሁ በማትወደው ነገር መልክተኛ በመጣላችሁ ቁጥር (ከመከተል) ትኮራላችሁን? ከፊሉን አስተባበላችሁ፤ ከፊሉንም ትገድላላችሁ፡፡
Al-Baqarah 2:87
Compare 2 Amharic translations
وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَى الْكِتَابَ وَقَفَّيْنَا مِنْ بَعْدِهِ بِالرُّسُلِ ۖ وَآتَيْنَا عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ الْبَيِّنَاتِ وَأَيَّدْنَاهُ بِرُوحِ الْقُدُسِ ۗ أَفَكُلَّمَا جَاءَكُمْ رَسُولٌ بِمَا لَا تَهْوَىٰ أَنْفُسُكُمُ اسْتَكْبَرْتُمْ فَفَرِيقًا كَذَّبْتُمْ وَفَرِيقًا تَقْتُلُونَ
DragHold to move · × to hide
ለሙሳ መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው። ከርሱ በኋላም ሌሎች መልዕክተኞችን ልከናል። የመርየምን ልጅ ዒሳንም ግልጽ ተዐምራትን ሰጠነው። ቅዱስ መንፈስ (ጅብሪል) በሚባለው መልአክ አበረታነው። ነፍሶቻችሁ በማትወደው ነገር መልዕክተኛው በመጣላችሁ ቁጥር እነርሱን ከመከተል ይልቅ በትዕቢት ከፊሉን አስተባበላችሁ። ከፊሉን ደግሞ ትገድላላችሁን?